አንድ፣ ሁለት ብሎ የጀመረው የቤት ኪራይ ነፃ የማድረግ በጎ ተግባር አሁንም ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው!
አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚገኘው 'የአይመን ንግድ ማዕከል' በህንፃው ተከራይተው ለሚሰሩ ነጋዴዎችና ድርጅቶች በሙሉ የአንድ ወር ኪራይ (የሚያዚያን) ነፃ አድርጓል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

አጫጭር ዓለም አቀፍ መረጃዎች፦
- በዩናይትድ ኪንግደም በ24 ሰዓት 980 ሰዎች መሞታቸው ተሰምቷል። በተጨማሪ 5,195 ሰዎችም በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል። በአጠቃላይ 70, 272 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን 8,958 ሰዎች ሞተዋል።
- በጣልያን በ24 ሰዓት 570 ሰዎች ሞተዋል። ቁጥሩ ትላንት ከተመዘገበው መቀነስ አሳይቷል። 3,951 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል። በሌላ በኩል ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 30,000 ደርሷል።
- በሩሲያ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በፍጥነት እየጨመረ ነው። በአንድ ቀን ብቻ 1,786 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል።
- በሳዑዲ አረቢያ በ24 ሰዓት ውስጥ 364 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል። ቁጥሩ እስካሁን በሀገሪቱ በአንድ ቀን ከተመዘገቡት ከፍተኛው ነው። በተጨማሪ 3 ሰዎች መሞታቸውን ተከትሎ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 47 ደርሷል።
- በስፔን በ24 ሰዓት 605 ሰዎች በኮቪድ-19 ሞተዋል። በ2 ሳምንት ውስጥም የተመዘገበ ዝቅተኛ የሟቾች ቁጥር እንደሆነ ተገልጿል።
- በፈረንሳይ የሟቾች ቁጥር 13,000 ደርሷል። ባለፉት 24 ሰዓት ብቻ 987 ሰዎች በቫይረሱ ሞተዋል።
- በዓለም አቀፍ ደረጃ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ከ1.6 ሚሊዮን በልጧል። ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ከ370,000 በላይ ሆኖ ተመዝግቧል። ከ101,000 በላይ ሰዎች ደግሞ ሞተዋል።

በሱማሊያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች 21 ደረሱ። በአንድ ቀን ብቻ 9 በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ሪፖርት ተደርጓል። ስድስቱ (6) ከዚህ ቀደም ቫይረሱ ካለባቸው ግለሰቦች ጋር ንክኪ ያላቸው ናቸው።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጦርነት ላይ ነን!
ከኮሮና ቫይረስ ጋር በሚደረገው ትግል አንድ ሞቅ፣ አንዴ ቀዝቀዝ፤ አንዴ ደግሞ መርሳት ፣ የሆነ ነገር ሲፈጠር ድንግጥ እያልን የምንቀጥል ከሆነ እጅግ በጣም ከፍተኛ ዋጋ እንከፍላለን።
በተለይ በተለይ ከገጠር እስከ ከተማ ያሉ የጤና ባለሞያዎች ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲደረግላቸው ካልተደረገ የምንከፍለው ዋጋ እጥፍ ይሆናል።
ከሳምንት በፊት ምንም ኬዝ እንደሌለባት የሚነገርላት ጎረቤት ሀገር ሱማሊያ በጥቂት ቀናት አንድ ብላ ሀያ አንድ ላይ ደርሳለች።
በፍጥነት በወሰደችው እርምጃ ስናሞካሻት የነበረችው፣ እሷ ጋር እንኳን አይደርስም የተባለችው ደቡብ ሱዳን 3 ኬዝ አስመዝግባለች። ሌላው ይቅር በጦርነት የምትታመሰው የመን አንድ ብላለች። ሊቢያ ሀያ አራት (24) ገብተዋል።
ዘመናዊ የህክምና ቁሳቁስ ያላቸው፣ የጤና ስርዓታቸው ብርቱ ነው የሚባልላቸው ሀገራት በየዕለቱ በመቶዎች አንዳንዶቹ እንደነ አሜሪካ ደግሞ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎቻቸውን እያጡ ነው። መነሻቸው አንድ እና ሁለት ኬዝ እንደነበር አይረሳም።
ወደ ሀገራችን ስንመጣ ደግሞ በየዕለቱ አዳዲስ ኬዞችን መስማት አስደንጋጭነቱ ቀርቷል። መሽቶ ሲነጋ ስንት ሰው ታያዝ ዛሬ? ብሎ መጠየቅ ተጀምሯል። ጥንቃቄው አንድ ቀን ሞቅ፣ ሌላ ቀን ቀዝቀዝ እያለ ቀጥሏል።
መዘናጋቱና ቸልተኝነቱ ምን ያህል ዋጋ እንደሚያስከፍል የገባን አልመሰለንም። ቫይረሱ በአንድ ጊዜ ከፍተኛ ቁጥር ላይ እንደማይደርስ የጤና ባለሞያዎች እየተናገሩ ነው። ለምሳሌ ቻይና በቫይረሱ ስትታመስ አሜሪካ አስመዝግባው የነበረውን ኬዝ መልስ ብላችሁ ተመልከቱ።
ጥንቃቄ ይበጃል፤ ጦርነት ላይ ነን!

አጫጭር መረጃዎች፦
- በአሜሪካ በ24 ሰዓት ከ2,000 በላይ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መሞታቸው ሪፖርት ተደረገ። ሀገሪቱ ከዓለም በአንድ ቀን ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰው ያጣች ሀገር ሆና ተመዝግባለች። አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር ከ18,700 በላይ የሆነ ሲሆን በጣልያን የተመዘገበውን የሟቾች ቁጥር ሊበልጥ ተቃርቧል። በሌላ በኩል በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ከግማሽ ሚሊዮን በልጠዋል።
- ካናዳ በአንድ ቀን ብቻ 1,383 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። 77 ሰዎችም ሞተዋል።
- በዩጋንዳ ትላንት 439 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ሁሉም ከቫይረሱ ነፃ መሆናቸው ተረጋግጧል። በሀገሪቱ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች አሁንም 53 ናቸው።
- በኤርትራ ትለንት አንድ (1) ተጨማሪ ሰው በቫይረሱ መያዙ ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 34 ደርሰዋል። ቫይረሱ የተገኘባቸው ግለሰብ የ72 ዓመት የኤርትራዊ ሲሆኑ በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያሉ ናቸው። ግለሰቡ በረራ ከመታገዱ በፊት ወደ ኤርትራ መግባታቸው ተነግሯል።
- በዓለም አቀፍ ደረጃ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ከ1.7 ሚሊዮን በልጧል። ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ከ376,000 በላይ ሆኖ ተመዝግቧል። ከ102,000 በላይ ሰዎች ደግሞ ሞተዋል።

#AFAR
ትላንት በአፋር ክልል አርጎባ ልዩ ወረዳ አምሬፍ ኸልዝ አፍሪካ የተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት ከወረዳ መስተዳድር ጋር በመተባበር በኮሮና ቫይረስ ዙሪያ የማህበረሰብ ንቅናቄ ስራ መሰራቱን የአርጎባ ልዩ ወረዳ የኮሙኒኬሽን ጉደዮች ፅህፈት ቤት ገልጿል።
#afargcao

በተለያዩ የሀገራችን ከተሞች የሆቴል ባለቤቶችን የወቅቱን ፈተና አብሮ ለመሻገር ሆቴላቸውን ለለይቶ ማቆያ እየሰጡ እንደሆነ ይታወቃል ፤ አቶ ነስረላ ጠልሃ የተባሉ ባለሀብትም በአዳማ ከተማ የሚገኘውን 'ገልፍ ፍላወር ሆቴል' የኮሮና ቫይረስ ተጠርጣሪዎች ለይቶ ማቆያ ይሆን ዘንድ ባለፈው ሳምንት ማስረከባቸው ተነግሮናል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#HARAR
በሀረር ከተማ የሚገኙ የንግድ ማዕከል ባለቤቶች ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ የንግድ ስራው በመቀዛቀዙ ለተከራዮቻቸውን የወራት ቤት ኪራይ ስረዛ አድርገዋል።
የአውሃኪም የንግድ ማዕከል ባለቤት አቶ አብዱልሃኪም መሀመድ በሀረሪ ክልል የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል በክልሉ የሚገኙ የጎዳና ተዳዳሪዎች፣ አረጋዊያንና አቅመ ደካሞችን የክልሉ መንግስት ድጋፍ እንዲያደርጉ በጠየቃቸው መሰረት 100 ሺ ብር ለግሰዋል።
ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ የንግድ ስራ መቀዛቀዝ በመታየቱና ችግሩን ለመጋራት በማሰብ በንግድ ማዕከላቸው ውስጥ ያከራያኋቸውን 10 ተከራይ ነጋዴዎችን ሁለት ወራት ከኪራይ ነጻ እንዲሰሩ አድርገዋል።
የኦሬንታል ትሬዲንግ የንግድ ማዕከል ባለቤት አቶ ኑሜር አብዱላዚዝ በንግድ ማዕከሉ ውስጥ ለሚሰሩ ለ26 ግለሰቦች የአንድ ወር የቤት ኪራይ ነጻ ሆነው ስራቸውን እንዲያከናውኑ አድርገዋል። በወር አጠቃላይ የማገኘው 480 ሺህ ብር ነው።
ምንጭ፦ የሀረሪ ክልል ኮሚኒኬሽን

አዲስ አበባ ከተማ ጀሞ 1 ደንይሽር የገበያ ማእከል የኑሮ ጫና እንዳይፈጠር የሁለት ወር የቤት ኪራይ ለተከራዮች በሙሉ ነፃ አድርጓል። በተጨማሪ ለተከራይ በሙሉ 20 ኪሎ ዱቄት፣ 5 ሊትር ዘይት እና 5 ኪሎ እሩዝ እና አካባቢው ላይ ያሉ በኑሮ አነስተኛ የሆኑ በሙሉ ዱቄት እሩዝ ዘይት አግዟል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የኑሮ ጫና እንዳይፈጠር የተለያዩ የንግድ ማዕከላት የቤት ኪራይ ነፃ እያደረጉ እንደሆነ ይታወቃል አንዳንዶች የአንድ ወር፣ ሌሎች እስከ ሶስት ወር ድረስ ነፃ እያደረጉ ነው።
በሌላ በኩል ገበያ በተቀዛቀዘበት በዚህ ወቅት በአስቸኳይ የሶስት ወር የቤት ኪራይ እንዲከፍሉ እየተገደዱ ያሉ ዜጎች እንዳሉንም ነግረውናል።
ከዚህ በተጨማሪ የህንፃ ባለቤቶች አንድም የነጋዴዎችን ጫና ለመቀነስ እንዲሁም የህብረተሰብ ኑሮ ላይ ያለው ጫና እንዲቀስ በሚወስዱት እርምጃ እየተመሰገኑ ቢሆንም የቤት ኪራይ ነፃ የተደረገላቸው አንዳንድ ነጋዴዎች ከልክ ያለፈ የዋጋ ጭማሪ ሲያደርጉ መታዘባቸውን የቤተሰባችን አባላት ገልፀውልናል።
ነጋዴዎችም እንተሳሰብ ተብላችኃል!

የቤት ለቤት የኮቪድ-19 ምርመራ ሊጀመር ነው!
በአዲስ አበባ ከተማ የቤት ለቤት የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ሊጀመር ነው። ምክትል ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ እንደገለጹት ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ በአዲስ አበባ ሁሉም ወረዳዎች የኮሮናቫይረስ ምርመራ ይጀመራል።
ምርመራው ተጋላጭ ሊሆኑ ይችላሉ ተብለው ከተለዩ ወረዳዎች የሚጀምር መሆኑን ገልጸው በመዲናዋ 117ቱም ወረዳዎች ይከናወናል ብለዋል።
ለምርመራው ጡረታ ላይ የነበሩና በሞያው ልምድ ያላቸው ከ1 ሺህ 200 በላይ ሃኪሞች የመንግስትን ጥሪ ተቀብለው ካሉት ሃኪሞች ጋር ተጨማሪ ሃይል በመሆን ዝግጁ መሆናቸውንም ከንቲባው ገልጸዋል።
ምንጭ፦ ኢዜአ

#EngTakeleUma
በሚቀጥለው ሳምንት ተማሪዎች በያሉበት ሆነው ትምህርት እንደሚጀምሩና የምገባ መርሃ ግብሩም እንደሚቀጥል የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ አረጋግጠዋል።
በተያዘው መርሃ ግብር መሰረት ከ7ኛ ክፍል በታች የሚማሩ ተማሪዎች ትምህርቱን በሬዲዮ የሚከታታሉ ይሆናል ተብሏል። ከ7ኛ እስከ 12ኛ ክፍል የሚማሩ ተማሪዎች ደግሞ ትምህርታቸውን በፕላዝማ የሚከታተሉ ይሆናል።
በዚህ ሂደት ተማሪዎችና መምህራን የተለያዩ መረጃዎችን የሚለዋወጡበት የአሰራር ስርአትም መሰርጋቱ ተገልጿል።
የተማሪዎች ምገባ መርሃ ግብርም በተለያዩ አካባቢዎች 1 ሺህ 200 ተማሪዎች የሚመገቡባቸው የምግብ ባንኮች ተዘጋጅተዋል፤ ለምግብ አቅርቦቱም 30 ሺህ ወጣቶች ዝግጁ ሆነዋል ተብሏል።

#AddisAbaba
በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የደንበኛ ድርቅ የመታቸው የአዲስ አበባ ሆቴሎች ያጡት ገቢ እየተጠና መሆኑን አሀዱ ቴሌቪዥን ዘግቧል።
የአገልግሎት ዘርፍ የሆነውና ከቱሪዝም ጋር ጥብቅ ቁርኝት እንዳለው የሚታመነው የሆቴል ዘርፍ የኮቪድ-19 መከሰትን ተከትሎ የገቢ ማጣት ጉዳት እየደረሰበት ነው።
የአዲስ አበባ ሆቴል ባለንብረቶች ማኅበር ማኔጂንግ ዳይሬክተር ቢንያም ብስራት እንደተናገሩት በከተማዋ ያሉ ሆቴሎች የደረሰባቸው የጉዳት መጠን በገንዘብ ለማወቅ ጥናት እየተደረገ ነው።
ቫይረሱ ኢትዮጵያ ውስጥ ከተከሰተ በኋላ እንግዶች ወደ ሆቴሎች እየመጡ ባለመሆኑ፤ የሚያጡት ገቢ ከፍተኛ እንደሚሆን መገመት አዳጋች አይደለም ተብሏል።
በማኅበሩ ሥር የሚወከሉ 130 ሆቴሎች ውስጥ የሚሰሩ 15 ሺሕ ሰራተኞች ያሉ ሲሆን ሥራቸውን እንዳያጡ ጥረት እየተደረገ ስለመሆኑም ዳይሬክተሩ ገልፀዋል።
ምንጭ፦ አሐዱ ቴሌቪዥን

ከመጋቢት 27 - ሚያዚያ 2 ኮቪድ-19 በኢትዮጵያ!
በኢትዮጵያ የካሮና ቫይረስ ምርመራ ከዕለት ወደዕለት ከፍ እያለ መጥቷል። በዛው ልክ በየእለቱ ቫይረሱ የሚገኝባቸው ሰዎችም እየጨመረ ነው።
• መጋቢት 27/2012 ዓ/ም የወጣው መግለጫ - 'ባለፉት 24 ሰዓት 59 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ አምስት (5) ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል'
• መጋቢት 28/2012 ዓ/ም የወጣው መግለጫ - 'ባለፉት 24 ሰዓት 164 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ አንድ (1) ሰው በቫይረሱ መያዙ ተረጋግጧል'
• መጋቢት 29/2012 ዓ/ም የወጣው መግለጫ - 'ባለፉት 24 ሰዓት 264 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ስምንት (8) ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል'
• መጋቢት 30/2012 ዓ/ም የወጣው መግለጫ - 'ባለፉት 24 ሰዓት 225 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ሶስት (3) ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል'
• ሚያዚያ 1/2012 ዓ/ም የወጣው መግለጫ - 'ባለፉት 24 ሰዓት 294 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ አንድ (1) ሰው በቫይረሱ መያዙ ተረጋግጧል'
• ሚያዚያ 2/2012 ዓ/ም የወጣው መግለጫ - 'ባለፉት 24 ሰዓት 442 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ዘጠኝ (9) ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል'

በትግራይ ቤት ለቤት ምርመራ ሊጀመር ነው!
በትግራይ ክልል ሁሉም ወረዳዎችና ከተሞች የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ያለመ የቤት ለቤት ዳሰሳ ከሚቀጥለው ሰኞ ሚያዚያ 5 ቀን 2012 ጀምሮ ለተከታታይ አራት ቀናት እንደሚካሄድ የክልሉ ጤና ቢሮ አስታውቋል።
የቢሮው ሀላፊ ዶክተር ሓጎስ ጎደፋይ እንደገለፁት፥ በዳሰሳው 23 ሺህ የጤና ባለሙያዎች ይሳተፋሉ። ህብረተሰቡ ቫይረሱ የሚያስከትለው ጉዳት፣ ለመከላከል የሚያስችል ግንዛቤና በክልሉ የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በሚመለከት ያለው ግንዛቤ በእያንዳንዱ ቤት ይዳሰሳል ነው ያሉት።
በተጨማሪም ከክልሉ ውጭ የመጡ ሰዎች ካሉ እያንዳንዱን ቤት በመፈተሽ ምርመራ ይደረግላቸዋል። ሁሉም ባለሙያ በክልሉ ባሉት 92 ወረዳዎች የተመደበ ሲሆን፥ በዚህም በገጠር በቀን ከ15 እስከ 20 እንዲሁም በከተማ ከ25 እስከ 30 ቤቶች ለማጥናት እቅድ ተይዟል ብለዋል።
ዳሰሳው በመቐለ ከተማ ነገ እንደሚጀመር በመጠቆምም ህብረተሰቡ ለዳሰሳው እገዛ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።
ምንጭ፦ ኤፍ ቢ ሲ

ከኬር አውድ ኢንተርናሽናል ሆቴል የደረሰን መልዕክት ፦
- ሆቴሉ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመግታት በሚደረገው ጥረት ሀገራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ ይገኛል።
- በሀዋሳ ከተማ ሆቴሉ ባለበት ክፍለ ከተማ ለሚገኙ 720 ለሚጠጉ ነዋሪዎች የንፅህና መጠበቂያ ሳኒታይዘር እገዛ አድርጓል።
- የቫይረሱ ወረርሽኝ በሀዋሳ ከተማ ከተከሰተ እና ገፍቶ ከመጣ ደግሞ ሆቴሉ 100 ለሚሆኑ የጤና ባለሞያዎች ለአንድ ወር ነፃ የምሳ አገልግሎት ለመስጠት መዘጋጀቱን አሳውቋል።
- ወረርሽኙን ለመግታት በሚደረገው ጥረት እስከመጨረሻው ድረስ ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ጎን በመቆም ማህበራዊ ግዴታዬን እወጣለሁ ብሏል።
- በተጨማሪ በድርጅቱ ስር በሻሸመኔ ከተማ ሱቆች ተከራይተው ለሚሰሩ ዜጎች በሙሉ የአንድ ወር የቤት ኪራይ ነፃ አድርጓል።

በኢትዮጵያ ተጨማሪ አራት (4) ግለሰቦች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው!
በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት የላቦራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው 345 ግለሰቦች መካከል አራቱ የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው መረጋገጡን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።
የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ እስካሁን ባለው ሂደት በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ለሶስት ሺህ 500 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተከናውኗል።
ዛሬ ቫይረሱ የተገኘባቸው አራቱም ግለሰቦች ኢትዮጵያዊያን መሆናቸውንም ነው የገለጹት።
ሁለቱ ወንድ ሁለቱ ደግሞ ሴቶች ሲሆኑ ሶስቱ የጉዞ ታሪክ ያላቸው ናቸው።
ከእነዚህም መካከል አንድ የ30 ዓመት ሴትና አንድ የ29 ዓመት ወንድ ኢትዮጵያዊያን ከዱባይ መጥተው በለይቶ ማቆያ ክትትል ሲያደርጉ የነበሩ መሆኑን ሚኒስትሯ ገልጸዋል።
አንድ የ33 ዓመት ሴት ኢትዮጵያዊት ደግሞ የአሜሪካ አገር የጉዞ ታሪክ ያላት ናት።
ሌላኛው ግለሰብ የ42 ዓመት እድሜ ያለው ኢትዮጵያዊ ነው ብለዋል። ግለሰቡ የውጭ አገር የጉዞ ታሪክ የሌለው ሲሆን፤ በህመሙ ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ እንዳለውና እንደሌለው እየተጣራ መሆኑን ተናግረዋል።