TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#GERD

"የአሜሪካ መንግስት ለግብፅ እያደላ ነው" - ዴቪድ ሺን

በኢትዮጵያና በቡርኪና ፋሶ የቀድሞ የአሜሪካ አምባሳደር የነበሩት ዴቪድ ሺን የሕዳሴው ግድብ የውሃ አሞላል ድርድርን አስመልክቶ የአሜሪካ መንግሥት ለግብጽ እያደላ ያለ ይመስላል ማለታቸው ተሰምቷል፡፡

ዴቪድ ሺን ከሕዳሴው ግድብ የውሃ አሞላል ጋር በተያያዘ ኢትዮጵያ፣ግብጽ እና ሱዳን እያካሄዱ ባሉት ድርድር ዙርያ የአሜሪካ ግምጃ ቤት በዶናልድ ትራምፕ ተወክሎ በታዛቢነት መግባቱን እንደሚያውቁ ጠቅሰው፣ ነገር ግን በዚህ ጉዳይ ላይ መግለጫ እስከ መስጠት መድረሱ ግራ እንዳጋባቸው በብሎጋቸው ላይ ጽፈዋል፡፡

የትሬዥሪ መምሪያው ኃላፊ ስቲፈን ምኑቺን ባለፈው አርብ ይፋ ባደረጉት መግለጫ በአሜሪካ አደራዳሪነት ተደረሰበት ያሉትን ስምምነት ግብጽ ለመፈረም ዝግጁ መሆኗን በአድናቆት ማውሳታቸው እንግዳ ነገር ነው ብለዋል ዴቪድ ሺን፡፡

ተደራዳሪዎቹ አካላት ስምምነት ላይ ስለመድረሳቸው አንዳችም በይፋ የሚታወቅ ነገር አለመኖሩን የጠቀሱት አምባሳደር ሺን መግለጫው ድርድሩ በስምምነት ሳይቋጭ የመጨረሻ ሙከራና ግድቡን ውሃ የመሙላት ሥራ መካሄድ የለበትም ሲል ኢትዮጵያን ማስጠንቀቁ አስገራሚ ነው ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ ስምምነቱን ለመቀበል ዝግጁ ስለመሆኗ ምልክት እንኳ እንዳልሰጠች፣ ሌላው ቀርቶ ሱዳንም ስምምነቱን መቀበል አለመቀበሏን እንዳላሳወቀች አምባሳደር ዴቪድ ሺን አስታውሰዋል፡፡

በእንዲህ ዓይነቱ ድርድር ላይ ሚና ሊኖረውና መግለጫ ሊሰጥም የሚገባው የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ ሆኖ ሳለ፣ የግምጃ ቤቱ መምሪያ በኢትዮጵያ ላይ ጫና የሚያሳድር መግለጫ ማውጣቱ አሜሪካ ለግብጽ እያደላች ነው የሚል ጥርጣሬ እንደሚያሳድር ዴቪድ ሺን በብሎጋቸው ጽፈዋል፡፡

#ShegerFM #ዘከርያመሐመድ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በአዊ ብሄ/አስተዳደር በእንጅባራ ከተማ በቦንብ ፍንዳት የሁለት ሰዎች ሂወት አለፈ!

የእንጅባራ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽ/ቤት ሀላፊ ኮማደር አበበ ዘውዴ እንደገለፁት በቀን 24/06/2012 ዓ ም ከጥዋቱ 1:00 ስዓት አከባቢ በእንጅባራ ቅድስት ስላሴ ቤተክርስቲያን በሟች አቶ አለነ አገኝ የህግ ባለቤቱ የነበረችውን ለመግደል በተወረወረው ቦንብ የሁለት ሰው ሂወት አልፏል።

በተወረወረው ቦንብ 8 ሰዎች ላይም ጉዳት ደርሶባቸው በእንጅባራ ጠቅላላ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑን ገልፀዋል። ኮማደር አበበ ዘውዴ አያይዘውም ሟች አቶ አለነ የወረወረው ቦንብ የድሮ ባለቤቱን ለመግደል እንጂ ቤተክርስቲያንን ለማቃጠል እንዳልሆነ ህብረተሰቡ እንዲገነዘብ አሳስበዋል።

ምንጭ፦ Awi Communication
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

በቻይና ዛሬ ማክሰኞ እለት 125 የኮሮና ቫይረስ ኬዞች የተመዘገቡ ሲሆን ይህ ቁጥር ባለፉት ስድስት ሳምንታት ከተመዘገቡ አዳዲስ የለት 'ተለት ስርጭቶች ዝቅተኛ የሚባል ነው ተብሏል።

ቫይረሱ በተቀሰቀሰባት ሁቤይ ግዛት 31 ተጨማሪ ሞቶች ሲመዘገቡ በጥቅሉ በቻይና 2943 ሰዎች በኮሮናቫይስ ሞተዋል።

በሌላ በኩል ኮሮና ቫይረስ ተመልሶ እንዳይመጣ በማሰብ የቻይናዋ ጉዋንዶንግ ግዛት ቫይረሱ ከተቀሰቀሰባቸው አካባቢዎች የሚመጡ ሰዎች ለ14 ቀናት ራሳቸውን አግልለው እንዲቆዩ አስታውቋል።

የግዛቲቱ ባለስልጣናት፤ በዚህ መልኩ ራሳቸውን ማግለል ያለባቸው ከየት አገር የሚሄዱ ሰዎች እንደሆኑ አገራትን ለይተው አላስቀመጡም።

#BBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ItsMyDam #ItsOurDam #GERD

የህግ ባለሞያው ሼክስፒር ፈይሳ ስለግድቡ፦

ግብፆች በታላቁ ህዳሴ ግድብ ላይ አንድ ነው የሆኑት፤ ተማሪውም፣ አዋቂውም፣ ህፃኑም፣ አስተማሪውም፣ ሀብታሙም፣ ድሃውም በአንድ ቃል ነው መንግስታቸውን የሚደግፉት። መንግስታቸው ደግሞ ይሄን ካላደረገ መንግስታቸውን የሚቃወሙትም በአንድ ቃል ነው።

እኛም እንደዛው መሆን አለብን። የግብፆችን ማስጠንቀቂያ አይታችሁ ከሆነ፤ ወይም በፌስቡክ፣ በሶሻል ሚዲያ የነሱ ፀሃፊዎች የሚሉትን ካያችሁ ለምንድነው ጦርነት፣ የኛ ወታደሮች ምንድነው የሚሰሩት በአስቸካይ ኢትዮጵያ እንቢ ብላለች ጦርነት መክፈት አለብን፤ መዋጋት አለብን አልሲሲ ጀነራሉ እሱ ነው ፊት እየሰጣቸው ያለው ነው የሚሉት።

እኛም አንድ መሆን አለብን ብዙ ሰዎች በግድቡ ላይ ይሄ ግድብ መጀመሪያውን አስፈላጊ አይደለም ይላሉ፤ አዎን! ሊሆን ይችላል መጀመሪያ በማን ተጀመረ፣ ለምን ተጀመረ እሱን አለፍን አሁን ላይ ደርሰናል፤ በአሁን ሰዓት ግድቡ 60 እና 70 በመቶ ደርሶ ወደኃላ መመለስ የሚባል ነገር አይሰራም። ብዙ ሀብት የፈሰሰበት፣ ብዙ ስራ የተሰራበት ግድብ ነው። ግድቡ መቀጠል ነው ያለበት። ይሄ ደግሞ ጥቅማችን ነው። አንድ ላይ ሆነን መቀጠል አለብን።

#AtkeltiAsefa
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
3ኛው ዙር የ8100A ገቢ ማሰባሰቢያ ይፋ ሆነ!

የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ገቢ ማሰባሰቢያ 3ኛው ዙር የ8100A ሁለት አዳዲስ ንዑስ ፕሮጀክቶችን ይዞ መቅረቡን የታላቁ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሄራዊ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት አስታውቋል፡፡

የጽሕፈት ቤቱ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ የሪሶርስና ፕሮጀክት ማኔጅመንት ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ተወካይ ሰለሞን ተካ እንደገለጹት ለ6 ወራት የሚቆይ በተንቀሳቃሽ ስልክ በኩል የሚደረግ ድጋፍና ለ3 ወራት የሚቆይ የሊቀናይል የጥያቄና መልስ ውድድር ሁለቱ ንዑስ ፕሮጀክቶች ናቸው፡፡

በመርሃ ግብሩ ዜጎች በዝቅተኛ ገንዘብ ተሳትፈውበት 20 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ገቢ ለማግኘት የታቀደ ቢሆንም ፕሮጀክቱ በዋናነት የህዳሴ ግድቡን አጀንዳ በማድረግ አገራዊ መግባባትና አንድነትን ማጠናከርን ታሳቢ ያደረገ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

#WaltaInfo
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrTedrosAdhanom

በአለም አቀፍ ደረጃ የኮሮና ቫይረስ [#COVID19] ስርጭት ከፍተኛ መሆኑን የአለም የጤና ድርጅት አስታውቋል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ቴድሮስ አድሃኖም ÷ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ብቻ ከቻይና ውጭ ስምንት እጥፍ ያህል አዳዲስ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ሪፖርት መደረጉን  ገልጸዋል፡፡

በደቡብ ኮሪያ፣ጣሊያን፣ኢራንና ጃፓን የተከሰተው ወረርሽኝ ከፍተኛ  መሆኑን የጠቆሙት ዶክተር ቴድሮስ፤ በአሁኑ ጊዜ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት አደጋ በዓለም አቀፍ ደረጃ በጣም  አሳሳቢ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

#ሮይተርስ #ቢቢሲ #ኤፍቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የግል መገልገያ እቃዎችን ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት የሚያስፈልጉ ማስረጃዎች ምን ምን ናቸው?

ተመላሽ ኢትዮጵያዊ፡-

- በውጭ አገር የቆየበትን ጊዜ እና ጠቅሎ ወደ ኢትዮጵያ መመለሱን የሚገልጽ በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የተረጋገጠ (Authenticated) የመሸኛ ደብዳቤ ከነበረበት አገር ካለው ወይም የነበረበትን ሀገር ጭምር ከሚያገለግለው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ወይም ቆንስላ ወይም ሚስዮን ማቅረብ ያስፈልጋል፤

- የኢትዮጵያ ሚስዮን ከሌለበት አገር የሚመጣ ከሆነ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የመኖሪያ ፈቃዱን እና የስራ ውሉን ሳያሰርዝ የመጣ መሆኑን በማጣራት በፓስፖርቱ ላይ በተለጠፈው ስቲከር ላይ ተሰርዟል (Void) የሚል ማህተም በማድረግ የሚሰጠውን የመሸኛ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርበታል፤

More https://telegra.ph/ETH-03-03

#የገቢዎችሚኒስቴር
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

ኬንያ በቻይና ውሃን በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ወደ ሀገር መመለስ ያልቻሉትን ዜጎቿን እንደምትመልስ አስታውቃለች።

የኬንያ መንግሥት ጤና ሚኒስቴር ካቢኔ እንዳስታወቁት መንግሥት ዜጎቹን ለማስወጣት አማራጮችን እያየ ነው ብለዋል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሀገሩ መንግሥት የፈቀደውን ከቻይና ወደ ኬንያ የሚደረገዉን በረራ አግዷል።

#VOA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19 #ETHIOPIA

በኢትዮጵያ እስካሁን ድረስ የኮሮና ቫይረስ አለመከሰቱን የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዛሬ በሰጠው መግለጫ ገልጻል፡፡

የኢንስቲትዩቱ ዳይሬክተር ዶ/ር ኤባ አባተ ዛሬ በሰጡት መግለጫ በሽታው ወደ አገሪቱ እንዳይገባ በመግቢያ በሮች ያሉ የቁጥጥር ስራዎች ተጠናክሮ መቀጠሉን አስታውቀዋል፡፡

አየር መንገዱን ጨምሮ በ29 የየብስ መንገዶች ላይ በሽታውን የመለየት ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉ የተነገረ ሲሆን፣ በቅርቡም በአፋር በኩል የሙቀት መጠን ልየታ ተጀምሯል ተብሏል፡፡

በትላንትናው ዕለት የኮሮና ቫይረስ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገባ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት እንደተደረገ ነው የተገለፀው፡፡ህብረተሰቡም በአሁኑ ሰዓት በተለያዩ ወሬዎች ሽብር ውስጥ እንዳይገባ ዶ/ር ኤባ አሳስበዋል፡፡

#ኢቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኢንተርኔት ሶሳይቲ በኢትዮጵያ ቻፕተር መስርቷል!

በአለም ሀገራት ወደ 114 የሚጠጉ ቻፕተሮች እንዳሉት የተገለጸው ኢንተርኔት ሶሳይቲ የተባለው ለትርፍ ያልተቋቋመ ማህበር በኢትዮጵያም ቻፕተሩን መስርቷል፡፡

ከዚህ ቀደም 35 በሚሆኑ የአፍራካ ሀገራት ቻፕተሩን መመስረቱ ነው የተነገረው፡፡ እስካሁን በነበሩት የህግ ገደቦች ምክንያት በኢትዮጵያ እንዳልተቋቋመና አሁን ላይ ህጉ ላይ ማሻሻያ በመደረጉ ቻፕተሩ ሊመሰረት እንደቻለ ተነግሯል፡፡

የማህበሩ ፕሬዝዳንት ሆነው የተመረጡት አቶ አዱኛ ነቾ ስለ ማህበሩ አላማ እንደነገሩን ከሆነ ማህበሩ በሀገሪቱ የኢንተርኔት አስተዳደር ዙሪያ አውደ ጥናቶችን፣ ስልጠናዎችንና ሴሚናሮችን የሚያዘጋጅ ሲሆን ክፍት፣ ደኅንነቱ የተጠበቀ እና አስተማማኝ የኢንተርኔት ተደራሽነት በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ የሚደረጉ የልማት ማስፋፋት ስራዎችን ይደግፋል ብለዋል፡፡

ማህበሩ ላይ ለመሳተፍ ሙያ እንደማይጠይቅ የተናገሩት የኢንተርኔት ሶሳሳይቲ የአፍሪካ አስተባባሪ ዶክተር ዳዊት በቀለ በትላልቅ ከተሞችም ሆነ በገጠራማ ቦታዎች የኢንተርኔት ተደራሽነትን ለማስፋትና የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማሳደግ የሚደረጉ ጥናቶችን ለመደገፍ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

#TikvahFamily
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

ጠቅላይ ዐቃቢ ህጉ እና የንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አምባሳደር ሆነው ተሹመዋል!

ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ በዛሬው ዕለት የሚከተለውን ሹመት ሰጥተዋል፡፡

በባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደርነት፦

1. አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ
2. ወ/ሮ የአለም ፀጋዬ
3. ወ/ሮ ሂሩት ዘመነ
4. አምባሳደር ማርቆስ ተክሌ
5. አቶ ባጫ ጊኒ
6. አቶ ይበልጣል አዕምሮ
7. አቶ ምህረተአብ ሙሉጌታ
8. አቶ ነብያት ጌታቸው
9. አቶ ተፈሪ መለስ ተሹመዋል፡፡

እንዲሁም፦

1. አቶ አድጐ አምሳያ
2. አቶ ጀማል በከር
3. አቶ አብዱ ያሲን
4. አቶ ለገሠ ገረመው
5. ወ/ሮ እየሩሳሌም አምደማርያም እና
6. አቶ ሽብሩ ማሞ

በአምባሳደርነት ማዕረግ መሾማቸውን የፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡

#ShegerFM
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ኢትዮጵያ በራሷ ንብረት በሌላ ኃይል ተጽዕኖ የምትፈርመው ምንም አይነት ስምምነት አይኖርም!

ኢትዮጵያ በራሷ ንብረት በሌላ ኃይል ተጽዕኖ ተገዳ የምትፈርመው ምንም አይነት ስምምነት እንደማይኖር የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ተደራዳሪ ቡድን አስታወቀ።

ተደራዳሪ ቡድኑ የህዳሴ ግድብን አስመልክቶ ከታችኛው ተፋሰስ አገራት እየተደረገ ስላለው ድርድር ሁኔታ ዛሬ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መግለጫ ሰጥቷል።

ግድቡ ለኢትዮጵያ ህልውና አስፈላጊ መሆኑንና አገሪቷ ከድህነት ለመውጣት የምታደርገውን ጥረት እንደሚያግዝ በመንግስትና በህዝብ ታምኖበት ወደ ስራ መገባቱም ተገልጿል።

ያም ሆኖ የአባይ ወንዝ ድንበር ተሻጋሪ በመሆኑ የታችኛውን ተፋሰስ አገራት በማይጎዳ መልኩ መገንባቱ ታምኖበት ከ2007 ዓ.ም ጀምሮ ከግብጽና ከሱዳን ጋር ውይይት ና ድርድር ሲካሄድ ቆይቷል።

More https://telegra.ph/GERD-03-03-2

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

ቱርክ ዐርብ ዕለት ስደተኞች ወደ አውሮጳ መጓዝ እንደሚችሉ ፍቃደኛነቷን በማሳየቷ በሺህዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች ወደ አውሮጳዊቷ የግሪክ ድንበር ተሰባስበዋል። የቱርኩ ርእሰ-ብሔር ራቺፕ ጣይብ ኤርዶኃን «ሚሊዮን» ፈላሲያንን ወደ አውሮጳ ሊልኩ መዘጋጀታቸውን ሰኞ የካቲት 23 ቀን፣ 2012 ዓ.ም ከዛቱ በኋላ በድንበር አካባቢ የስደተኛው ቊጥር እየጨመረ ነው። በሚቀጥሉት ቀናት የስደተኞች ጎርፍ ከአምስት ዓመት በፊት እንደታየው አውሮጳን ሊያጥለቀልቅ ይችላል የሚል ፍራቻ በኅብረቱ ዘንድ አሳድሯል።

#DW
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ItsMyDam #ItsOurDam #GERD

በመጪው ክረምት በሕዳሴ ግድቡ የውሃ መሙላት እንደሚጀመር እና የግድቡ ግንባታ በተያዘለት ጊዜ መሰረት እንደሚቀጥል የውኃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የውኃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ በግድቡ ሁለት ተርባይኖች የሚጀመረው የቅድመ ሀይል ማመንጨት ስራም በተያዘለት እቅድ መሰረት እንደሚጀመርም አስታውቀዋል፡፡

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ያለበትን ደረጃ እና ሂደት እንዲሁም የድርድር ሁኔታ ላይ በጠቅላይ ሚንስትር ፅ/ቤት መግለጫ ተሰጥቷል፡፡

በመግለጫው ላይ የተገኙት የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በበኩላቸው አሜሪካ የግድቡን ሙሌት በተመለከተ ያወጣችው መግለጫ ፈፅሞ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

አሜሪካ የተፋሰሱ አገራት በራሳቸው ወደ ስምምነት እንዲደርሱ ግፊት በማድረግ በጎ ሚናዋን ብቻ እንድትወጣ ኢትዮጵያ እንደምትፈልግ እና በሌላ ተፅዕኖ የሚሆን ነገር እንደሌለም ሚንስትሩ አረጋግጠዋል።

#ኢቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ኢትዮጵያ የዲጂታል ክፍያ ስርዓት ለመዘርጋት ምን ደረጃ ላይ ትገኛለች?

ይህንን ጥያቄ ያቀረብነው የኢትዮጵያ የበይነመረብ ልማት ኮንፍረንስ መክፈቻ ስነ-ስርዓት ላይ ንግግር ላደረጉት ለኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የአይሲቲ ልማትና አስተዳደር ዘርፍ ዳይሬክተር ጀነራል አብዮት ሲናሞ (ዶ/ር ኢንጂ ) ሲሆን እሳቸውም ተከታዩን ምላሽ ሰጥተዋል፦

E-Transaction proclamation ( የዲጂታል ዝውውር አዋጅ ) በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጸድቆ ጠቅላይ አቃቤ ህግ አዋጁ ላይ ግብዓት ከሰጠ በኃላ አሁን ላይ የሚኒስትሮች ምክር ቤት እንዲያጸድቀው እየተጠበቀ ነው ያሉ ሲሆን መታሰብ ያለበት ግን ዲጂታል ግብይት ዝውውሩን መክፈት ብቻ ሳይሆን data protection proclamation እንዲሁም ሌሎች አዋጆች እንደሚያስፈልጉና ይህም በዝግጅት ላይ እንዳለ ገልጸዋል፡፡

እንደ ዶ/ር አብዮት ገለጻ ለዘርፉ ትልቅ ተግዳሮት የሆነው የኢንተርኔት ስርጭት ( internet connectivity ) ዝቅተኛ መሆንን ለመቅረፍም አሁን ላይ ወረዳ ኔት የተሰኘ የተለያዩ መስሪያ ቤቶችን በማገናኘት ከወረዳ ወደ ማዕከል መረጃዎችን ለማሰባሰብ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡ ይህንን ሥራም ኢንተርኔት ለማስፋፋት ከሚሰሩ አካላት ጋር አብሮ ለመስራት ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነም ነው የተገለጸው፡፡

More https://telegra.ph/TIKVAH-03-03

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE ዓለም አቀፍ መረጃ፦ - የሟቾች ቁጥር 3,086 ከፍ ብሏል - በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 90,294 ዛሬ ባገኘነው ሪፖርት በኮሮና ቫይረስ [#COVID19] የሞቱ ሰዎች ቁጥር 3,086 የደረሰ ሲሆን 90,294 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተጠቅተዋል። ከበሽታው አገግመው ከሆስፒታል የወጡ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 45,705 ደርሰዋል። @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

ዓለም አቀፍ መረጃ፦

- የሟቾች ቁጥር 3,164 ከፍ ብሏል
- በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 92,823

ዛሬ ባገኘነው ሪፖርት በኮሮና ቫይረስ [#COVID19] የሞቱ ሰዎች ቁጥር 3,164 የደረሰ ሲሆን 92,823 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተጠቅተዋል። ከበሽታው አገግመው ከሆስፒታል የወጡ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 48,469 ደርሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በነጋራችን ላይ ዛሬ አርጀንቲና በኮሮና ቫይረስ የተያዘ ግለሰብ በሀገሯ መገኘቱን ዛሬ አረጋግጣለች፤ ስፔን ደግሞ በዛሬው ዕለት በሀገሯ በቫይረሱ የሞተ አንድ ሰው እንዳለ ሪፖርት አድርጋለች።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
መከላከያ ሰራዊት የሰጠው ማሳሰቢያ፦

በሱማሌ ፣ በለሃዋ በሚባል ቦታ የካቲት 23/2012 ዓ/ም በመንግሥት ሠራዊት እና በመንግሥት ተቃዋሚ ታጣቂ ሃይሎቾ መካከል ግጭት መከሰቱን ና የተኩሰ ልውውጥ እንደነበረ ከስፍራው ከነበረው የመረጃ ምንጮች ደርሶናል።

ይህ በእንዲህ አንዳለ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በወቅቱ በደሎ፣ በሉቅ እና በለፍቱ በሚባሉ ኣካባቢዎች በግዳጅ ላይ የነበረ ሲሆን በወቅቱ በአከባቢው ሆኖ የተኩሰ ድምፅ መስማቱን እና ከዚህ ጋር ተያይዞ ባለበት ቦታ ሇኖ አከባቢው ከመጠበቅ ውጪ ሌላ ምንም ዓይነት በግዳጅም ሇነ አዲስ ስምሪት ላይ ኣልነበረም።

ይሁን እንጂ ኣንድአንድ የመረጃ ቋቶች የኢትዮጲያ መከላከያ ሃይል የመንግስት ወታደሮችን ደግፎ ውግያው ላይ እንደተሳተፈ የሚገልጽ ፍፁም የተሳሳተ መረጃ ለሕብረተሰቡ እያስተላለፉ ይገኛሉ።

ይህ መረጃ ፍፁም የተሳሳተ እና ሠራዊታችን ከተሰማራበት አካባቢ ውጪ የተፈፀመ በመሆኑ ለዚህም ከተቋሙ እውቅና ውጪ የሆነ መረጃ መሆኑን ለማስገንዘብ እንወዳለን።

[የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት]

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከግብር ከፋዮች ከአምስት ቢሊዮን ብር በላይ ውዝፍ ዕዳ ይጠበቃል!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በከተማዋ ከ13 ሺ በላይ ግብር ከፋዮች ከአምስት ቢሊዮን ብር በላይ ውዝፍ ዕዳ እንዳለባቸው አስታወቀ።

በቢሮው የእቅድና በጀት ዝግጅት ፣ ክትትልና ግምገማ ዳይሬክተር አቶ ጥላሁን ግርማ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ ባለፉት ሰባት ወራት 4ሺ940 ግብር ከፋዮች 778 ሚሊዮን 295 ሺ 900 ብር ያለባቸውን ውዝፍ ዕዳ ሲከፍሉ በአንጻሩ 13ሺ 45 ግብር ከፋዮች ያለባቸውን አምስት ቢሊዮን 067ሚሊዮን 358 ሺ 343 ብር ውዝፍ ዕዳ አልከፈሉም ብሏል።

ዳይሬክተሩ እንዳብራሩት፤ በከተማዋ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ግብር ከፋይ ውዝፍ ዕዳ ያለበት በመሆኑ፤ በተያዘው በጀት ዓመት ችግሩን በመቅረፍ የከተማ አስተዳደሩን ገቢ ለማሳደግ በአስተዳደሩ ካቢኔ ውሳኔ መሰረት ውዝፍ እዳ ያለባቸው ግብር ከፋዮች ወለድና ቅጣቱ ቀርቶ ከጥቅምት ወር 2012 ዓ.ም አስከ ሰኔ 30 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ፍሬ ግብሩን ብቻ እንዲከፍሉ የዕዳ ማጽጃ ስርዓት መዘርጋቱን ተናግረዋል።

ምንጭ፦ አዲስ ዘመን ጋዜጣ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

የ83 አመቱ የሮማው ካቶሊክ ሊቀ ጳጳስ ፖፕ ፍራንሲስ ሰሞኑ ሳልና ብርድ ስለተያባቸው በኮሮኖ ቫይረስ ተጠቅተዋል በሚል ስጋት የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ዛሬ ማክሰኞ የካቲት 24 እንዳደረጉና ከበሽታውም ነፃ እነደሆኑ የጣሊያኑ ኢል ማሳጂሮ ጋዜጣ አስነብቧል።

እንደ ጋዜጣው ዘገባ ፖፕ ፍራንሲስ የፋሲካን ፃም አስመልክቶ ንስሀ ስለመግባት ፣ይቅር ስለማለት ፣ስለ አለም ሰላምና ስለ እራስ ሰለ መፀለይ በየአመቱ በሚደረገውና ባለፈው እሁድ ተጀምሮ ለስድስት ሳምንት በሚቆየው ፕሮግራም ላይ ተገኘተው ተደጋጋሚ ሳል የተያባቸው ሲሆን ጳጳሱ አሟቸው ቀሪውን ፓሮግራም በደቡብ ሮም በሚገኘው ቤታቸው ውስጥ ሆነው ነው የተከታተሉት።

ምንጭ፦ fidelPost.com
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

በጄነራል ሰዓረ መኮንንና በሜጀር ጄነራል ገዛኢ አበራ ግድያ ተጠርጥሮ በእስር ላይ ያለው አስር አለቃ መሳፍንት ጥጋቡ "ድርጊቱን አለመፈጸሙንና ወንጀለኛም እንዳልሆነ" ለፍርድ ቤት ተናገረ። መሳፍንት የእምነት ክህደት ቃሉን የሰጠው የካቲት 18 ነው።

በቀድሞው የጠቅላይ ኤታማዦር ሹም እና ጓደኛቸው ላይ የተፈጸሙ ግድያዎችን አስመልክቶ የቀረበውን የወንጀል ክስ እየመረመረ የሚገኘው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት፤ የአቃቤ ህግ ምስክሮችን ለመስማት ከግንቦት 26 እስከ ሰኔ 2 ቀጠሮ ሰጥቷል።

#ሪፖርተር #ተስፋለምወልደየስ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia