TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የአቶ በረከት ስምኦን እና የአቶ ታደሰ ካሣን የመከላከያ ምስክሮች አዳምጧል። ችሎቱ በትላትና ውሎው ሁለቱ ተከሳሾች በጥረት ኮርፖሬት ሀብት ምዝበራ ጋር ተያይዞ ለተመሠረተባቸው ክስ የመከላከያ ቃላቸውን ለፍርድ ቤቱ አሰምተዋል። ተከሳሾቹ ጥረት ኮርፖሬትን ውጤታማ የሚያደርጉ ሥራዎችን እንጂ የድርጅቱን ጥቅም የሚጎዱ ተግባራትን አለመፈጸማቸውን ለፍርድ ቤቱ…
#UPDATE

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በእነ አቶ በረከት ስምኦን የክስ መዝገብ በቀረቡ ማስረጃዎች ላይ የአቃቤ ሕግን አስተያየት ለመስማት ለየካቲት 10/2012 ቀጠሮ ሰጠ።

ፍርድ ቤቱ ከማክሰኞ ጀምሮ አንደኛ ተከሳሽ አቶ በረከት ስምኦን እና ሁለተኛ ተከሳሽ አቶ ታደሰ ካሣ አሉን ያሏቸውን የመከላከያ ምስክሮች ሰምቷል። ሁለቱም ተከሳሾች የቀረበባቸውን የሰነድና የሰው ማስረጃ በመቃወም ቃላቸውን ለፍርድ ቤቱ ሰጥተዋል፡፡

ተከሳሾች በቀረቡባቸው አራት ክሶች ለመከላከያ ምስክርነት አሉን ካሏቸው ምስክሮች መካከል የተወሰኑት ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ቀርተዋል።

የተከሳሽ ጠበቃ መጥሪያ ለምክትል ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ደመቀ መኮንን እና ለውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው መሰጠቱን ገልጸው የቀድሞው ጠቀላይ ሚንስትር አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝን ማግኘት ባለመቻላቸው መጠሪያ መስጠት አለመቻላቸውን ለፍርድ ቤቱ ገልጸው ነበር።

በፋክስ በደረሰው መረጃ መሠረት አቶ ደመቀ እና አቶ ገዱ በሥራ ምክንያት አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ደግሞ በግል ጉዳይ መቅረብ እንደማይችሉ መግለጻቸውን ፍርድ ቤቱ አስታውቋል። የተከሳሾች ጠበቃ በመከላከያ ምስክርነት የቀረቡት ምስክሮች በቂ መሆናቸውን በመግለጽ ሦስቱ ግለሰቦች አይቅረቡ ሲሉ ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል።

ከጠየቋቸው ሰነድ ማስረጃዎች መካከል ሦስቱ እንዲላክላቸው ትዕዛዝ ይሰጥልን ሲሉ ጠይቀዋል። ጉዳዩን የተከታተለው ፍርድ ቤትም ማስረጃዎቹ እንዲላኩ ትዕዛዝ ሰጥቶ በቀረቡት ማስረጃዎች ላይ የአቃቤ ሕግን አስተያየትን ለመስማት ለየካቲት 10/2012 ቀጠሮ ሰጥቷል።

https://telegra.ph/BBC-01-16

#BBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
‘ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሟን አሳልፎ የሚሰጥ ውይይት ፈጽሞ አላደረገችም፣ ወደፊትም አታደርግም’

በትናንትናው እለት የኢትዮጵያ፣ የግብጽ እና የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፣ የውሃ ሃብት ሚኒስትሮች እና የልዑካን ቡድኖቻቸው በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ እኤአ ከጃንዋሪ 13 እስከ 15 ቀን 2020 በዋሽንግተን ዲሲ ሲያካሂዱት የነበረው ውይይት በጥሩ ውጤት መጠናቀቁ ይታወሳል።

የውይይቱን ውጤት እና የኢትዮጵያን አቋም አስመልክቶ ክቡር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው እና የውሃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ስለሺ በቀለ ዛሬ በዋሽንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም የተነሱ ዋና ዋና ሃሳቦች እንደሚከተለው ቀርበዋል፦

• ኢትዮጵያ ከህዳሴ ግድቡ ጋር በተያያዘ ትናንት በተደረገው የመግባቢያ ነጥብ ብሔራዊ ጥቅሟን አሳልፎ የሚሰጥ አንዳችም ውይይት ፈጽሞ አላደረገችም፣ ይሄ ወደፊትም የኢትዮጵያ ቀዳሚው መርህ ሆኖ ይቀጥላል።

• ከግድቡ ጋር የሚደረጉ ድርድሮች እና ውይይቶች ኢትዮጵያ ሌሎች ግድቦችን የመገንባት መብቷን የማይጋፋ ነው። 

• ከዚህ ቀደም ለውይይቱ መጓተት እንደምክንያት ሲነሳ የነበረውን የህዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌት ከታችኛው ተፋሰስ አገራት ግድቦች የማያያዝ ውኔታ እንደቀር ማድረግ ተችሏል። 

• የግድቡ ግንባታ በአሁኑ ወቅት በተጠናከተረ ሆኔታ ቀጥሏል፣ ግድቡ በፍጥነት እንዲጠናቀቅ በመንግስት በኩል ከፍተኛ ፖለቲካዊ ቁርጠኝነት እየተደገፈ ነው።

More https://telegra.ph/GERD-01-16-2

(የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ከዱ ቬንቸርስ... ኩዱ ቬንቸርስ በሁለት ኢትዮጵያዊያን ስራ ጀማሪዎች ላይ የሁለት ሚሊዮን ብር ኢንቨስትመንት ማድረጉን ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል፡፡ ኢንቨስትመንቱ የተሰጣቸው ወጣቶች ስራቸው በጤናና ትምህርት ላይ ያተኮረ እንደሆነ ተገልጿል፡፡ ይህን እድል ካገኙት ወጣቶች መካከል የጥቁር አንበሳ የአምስተኛ አመት የጤና ህክምና ተማሪ የሆነችው ቤቴል ሳምሶን ስትሆን ይዛ የቀረበችው እቴጌ የተሰኘ…
ኩዱ ቬንቸር ማነው?

ኩዱ ቬንቸር በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የቬንቸር ካፒታል ኩባንያ ሲሆን የማህበረሰቡን ችግር የሚቀርፉ ጅምር (ስታርት አፕ) ድርጅቶች እንዲሁም ሃሳቦች ላይ ኢንቨስት ያደርጋል፡፡

በዘንድሮ አመት ኩዱ ቬንቸርስ ለወጣት ሥራ ፈጣሪዎች ወደ መቶ ሚሊዮን ብር መመደቡን የኩዱ ቬንቸር መስራች ወጣት ኖኤል ዳንኤል ገልጿል፡፡ እስካሁን ወደ 7,000,000 ብር ኢንቨስት የተደረገ ሲሆን ከዚህም ውስጥ 5,000,000 ብሩን ለ #SolveIt መርኃግብር የዋለ እንደሆነ ወጣት ቤቴልሔም ደሴ ተናግራለች፡፡ ቀሪው 2 ሚሊዮን ብር ትላንት ለእቴጌና አስኳል ድርጅቶች ተሰጥቷል፡፡

በዚህ አመት የተያዘው 100,000,000 ብር ለጀማሪ ወጣት ስራ ፈጣሪዎች እንደመነሻ ካፒታል የሚሰጥ ይሆናል ተብሏል፡፡ ይህንን አቅም በአግባቡ ለመጠቀም ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር እንዲሁም ከወጣት ሥራ ፈጣሪዎች ጋር በቅርበት እንደሚሰሩም ነው ወጣት ቤቴልሔም የገለጸችው፡፡

ቲክቫህ ኢትዮጵያም በቀጣይ ከኩዱ ቬንቸር ጋር በቅርበት በመስራት ችግር ፈቺ የሆኑ የወጣቶች የስራ ሃሳቦችን ወደ ተግባር እንዲቀየሩ ለማድረግ እንደምንሰራ ቃል እንገባለን ቀጣይ እንቅስቃሴዎችንም በቅርበት ተከታትለን የምናሳውቅ ይሆናል፡፡

Via @tikvahethmagazie
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ወደ ጎንደር 19 ተጨማሪ በረራዎች ተዘጋጅተዋል...

የጥምቀት በዓልን ምክንያት በማድረግ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ - ጎንደር ተጨማሪ የበረራ መርሃ ግብሮችን ማዘጋጀቱን አስታውቋል፡፡ እስካሁን ድረስ ጥር 8/2012 ድረስ በአጠቃላይ ወደ ጎንደር የሚደረጉ 19 ተጨማሪ በረራዎች መዘጋጀታቸውን ነው አየር መንገዱ የገለፀው። ለጥምቀት በዓልና ተያያዥ ጉዳዮች በቀጥታ ወደ ጎንደር የሚያመሩ 2 ሺህ 500 የሚደርሱ መንገደኞች መመዝገባቸውም ተመላክቷል፡፡

#AMMA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ስለኩዱ ቬንቸር ከወጣት ቤተልሄም...

- ኩዱ ቬንቸርስ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የቬንቸር ካፒታል ኩባንየ ነው። ዘንድሮ ለወጣት ሥራ ፈጣሪዎች ወደ 100,000,000 ብር መድቧል።

- እስካሁን ወደ 7,000,000 ብር ኢንቨስት የተደረገ ሲሆን ከዚህም ውስጥ 5 ሚሊዮን ብሩን ለSolve it መርኃግብር ውሏል። ቀሪው 2 ሚሊዮን ብር ትላንት ለእቴጌና አስኳል ድርጅቶች ተሰጥቷል፡፡

- በዚህ አመት የተያዘው 100,000,000 ብር ለጀማሪ ወጣት ስራ ፈጣሪዎች እንደመነሻ ካፒታል የሚሰጥ ይሆናል።

- ኩዱ ቬንቸርስ አቅሙን በአግባቡ ለመጠቀም ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር እንዲሁም ከወጣት ሥራ ፈጣሪዎች ጋር በቅርበት ይሰራል።

(ወጣት ቤተልሄም ደሴ ለቲክቫህ ከተናገረችው)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የታገቱት ተማሪዎች ጉዳይ...

ከታገቱት ተማሪዎች መካከል ከወምበርማ ወረዳ ለትምህርት የሄዱ ተማሪዎች እንደሚገኙበት የወረዳው ኮሚኒኬሽን ቢሮ በፌስቡክ ገፁ ዛሬ አሳውቋል። መንግስት ተማሪዋቹን ለማስለቀቅ ኃላፊነቱን እንዲወጣም ተጠይቋል። የነገዋን ሀገር የሚረከቡ ተማሪዎችን ማገት የተወገዘ ተግባር እንደሆነም ነው የወምበርማ ወረዳ ያስታወቀው። መላው የወምበርማ ወረዳ ህዝብም ይህንን ድርጊት በጽኑ ያወግዘዋል ሲል ገልጿል።

ከወረዳው ለትምህርት ሂደው ከታገቱት ተማሪዎች መካከል የሚከተሉት እንደሚገኙበትም በይፋ አሳውቋል፦

1, ተማሪ አሳቤ አያል = ቀንጠፍን ቀበሌ
2, ተማሪ ሳምራዊት ቀሬ= ጭራር ጋለቤድ ቀበሌ
3, ተማሪ ሞነሞን በላይ = ጭራር ጋለቤድ ቀበሌ

(Womberma Woreda Communications)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የአዲስ አበባ ፖሊስ ድንገተኛ አሰሳ...

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ልዩ ቦታው ጋዝ ተራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በአዲስ ከተማ ፖሊስ ጥር 6 ቀን 2012 ዓ.ም. በአካባቢው ላይ በተደረገ ድንገተኛ አሰሳ በርካታ የስልክ ገመዶች በሸራ ተሸፍኖ መገኘቱን አስታወቀ።

በተመሳሳይ ጥር 05 ቀን 2012 ዓ/ም በዚሁ አካባቢ በርካታ የስልክ ገመዶችን አከማችተው የተገኙ 2 ተጠርጣሪዎች ከነንብረቱ በቁጥጥር ስር መዋላቸውም ይታወሳል ሲል የአዲስ አበባ ፓሊስ አስታውቋል።

(Addis Abeba Police Commission)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሪፎርም...

የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በዘርፉ ያለውን የህግ የበላይነት ለማስጠበቅና ፍትሃዊ አገልግሎት ለህዝቡ ለማድረስ የሪፎርም ስራዎች ማከናወኑን አስታወቀ። የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በክልሉ ከሚገኙ ከተለያዩ የፍትህ አካላት ጋር በሪፎርም ስራው ውይይት እያደረገ ይገኛል።

በአዳማ እየተካሄደ ባለው ውይይት በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የተሰሩ ስራዎችን ማሳወቅና በዘርፉ የሚገኙ ባለሙያዎች ምርጫን ታሳቢ በማድረግ ስራዎች እንዴት መከናወን አለባቸው በሚሉ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው ተብሏል፡፡

#OBN
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#NewsAlert

ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ 3 ምክትል ፕሬዝዳንቶቹን ከስራ አገደ። ዩኒቨርሲቲ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ተፈራ አስናቀ እንዳረጋገጡት ሶስቱ ምክትል ፕሬዝዳንቶች የታገዱት በዩኒቨርሲቲው ሴኔት ውሳኔ መሰረት ነው።

ምክትል ፕሬዝዳንቶች የታገዱት ቀደም ሲል ያጋጠሙ ግጭቶችን ተከትሎ የደረሰውን ጉዳት ለመቆጠርና እና ኃላፊነታቸውን ለመወጣት ጥረት ስላላደረጉ በሚል በመገምገሙ እንደሆነ ከዩኒቨርስቲው የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

(ኢዜአ)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የትንንሽ ልቦች ዘመቻ...

ሻርጃህ ቻሪቲ ኢንተርናሽናል (SCI) የተሰኘ የተባበሩት አረብ ኢሜሬቶች ዓለም አቀፍ ግብረሰናይ ድርጅት በኢትዮጵያ ከሚገኘው የሀገሪቱ ኤምባሲ ጋር በመተባበር ካለፈው ረቡዕ ጀምሮ በኢትዮጵያ የትንንሽ ልቦች ዘመቻ "SMALL HEARTS CAMPAIGN" ጀምሯል። በዚህም መረሰት ድርጅቱ ንብ ማዕከል ለ4 ቀናት የሚቆይ ነፃ የህፃናት የልብ ህክምና በማድረግ ላይ ነው።

(አል-ዓይን)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#CARD

በመብቶች ዴሞክራሲ ብልፅግና ማዕከል (CARD) አማካኝነት ሶሻል ሚዲያ ላይ ንቁ ተሳታፊ ከሆኑና መረጃዎችን እንዲሁም ኃሳቦችን በማቅረብ ከሚሳተፉ ሚዲያዎችና ግለሰቦች ጋር በምርጫ ህጉ ዙሪያ በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ለማስቻል ያለመ የግንዛቤ ማስጨበጫ ዛሬ ተካሂዷል፡፡

የCARD ፕሮግራም ዳይሬክተር አቶ አጥናፉ ብርሃኔ እንደገለጹት ሌሎች ሚዲያዎች የራሳቸውን ሰው የማሰልጠን አቅሙ ይኖራቸዋል ነገር ግን ሶሻል ሚዲያው ላይ ላሉ አዘጋጆች ታስቦ የሚዘጋጅ ባለመኖሩ ማዕከሉ ይህንን መሰረት አድርጎ ዝግጅቱን እንዳዘጋጀ ገልጸዋል፡፡

ለተሳታፊዎቹ ስለአጠቃላይ ህጉ መግለጫ የሰጡትና ለተነሱ ጥያቄዎችም መልስ የሰጡት የምርጫ ቦርድ የኮሚውኒኬሽን አማካሪ ወይዘሪት ሶልያና ሽመልስ ሲሆኑ ከዚህ በፊት የነበረውን አዋጅ ጨምሮ በአዲሱ የተቀየሩ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ከተሳታፊዎችም ወቅታዊ እና በምርጫ ጊዜ ሊከሰቱ ይችላሉ የተባሉ አንኳር ነጥቦች ከሕጉ አንጻር ተነስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡ በቀጣይም ተመሳሳይ ውይይቶች እንደሚካሄዱ ማዕከሉ ገልጿል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

ረቂቁ የኤክሳይዝ ታክስ ከ1300 ሲሲ በታች ላሉ አዳዲስ ተሽከርካሪዎች የሚጣለውን የታክስ መጠን ከ30% ወደ 5% አወረደ። ይህም የአዳዲስ ቤት መኪኖችን ዋጋ እስከ 83% ይቀንሰዋል ተብሏል።

ምንጭ፦ ካፒታል ጋዜጣ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
አንድም የአሜሪካ ወታደር ጉዳት አልደረሰበትም... የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶላንድ ትራንፕ ኢራን በኢራቅ በሚገኙ የአሜሪካ የጦር ሰፈሮች ላይ ባደረሰችው ጥቃት አንድም የአሜሪካ ወታደር ጉዳት አልደረሰበትም ብለዋል፡፡ በጥቃቱ በጦር ሰፈሮቹ ላይ መጠነኛ ጉዳት ከመድረሱ ባለፈ በስፍራው የሚገኝ የአሜሪካ ወታደር ላይ ምንም አይነት ጉዳት አለመድረሱን በመግለፅም ለአሜሪካውያን እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡ ፕሬዝዳንት…
ኢራን የአሜሪካ ወታደሮችን አቁስላለች...

አሜሪካ በወሰደችው የአየር ጥቃት የኢራኑን ጦር ጀነራል መግደሏን ተከትሎ የኢራን ሰራዊት በኢራቅ በሚገኝ የአሜሪካ ጦር ሰፈር ላይ የሚሳዬል ድብደባ ማድረጉ ይታወሳል፡፡

በዚህም ጥቃት የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕን ጨምሮ የአገሪቱ መከላከያ መስሪያ ቤት/ፔንታጎን/ በጦር ሰፈሩ ወታደሮች ላይ ጉዳት እንዳልደረሰባቸው አስታውቀው እንደነበር አይዘነጋም፡፡

ሆኖም ኢራን በጦር ሰፈሩ ላይ ባስወነጨፈችው 16 ሚሳዬሎች በርካታ የአሜሪካ ወታደሮች የመቁሰል አደጋ እንደደረሰባቸው አንድ የአሜሪካ የጦር መኮንን ዋቢ በማድረግ ሲኤንኤን አስነብቧል፡፡

በወቅቱም በሚሳዬል ጥቃቱ የተጎዱ ወታደሮች ለህክምና ክትትል ጀርመን እንዲሄዱ መደረጉንና ህክምናቸውንም አጠናቀው ወደ ጦር ሰፈሩ መመለሳቸው ተነግሯል፡፡

(ሲ.ኤን.ኤን፣ ኢቢሲ)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

በሰኔ 15ቱ የጦር ጄነራሎች እና የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ግድያ በተያያዘ በእነ አስር አለቃ መሳፍንት ጥጋቡ መዝገብ ክስ የተመሰረተባቸው ተጠርጣሪዎች ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡

በችሎቱ ቤተሰቦቻቸው በተገቢው ሁኔታ እንዲታደሙ ባለመደረጉ ከማረሚያ ቤት ከመጡበት መኪና አንወርድም ሲሉ ተቃውሞ አሰምተዋል፡፡

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት በበኩሉ የፀረ-ሽብር እና ህገመንግስታዊ ሥርዓት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን በተመለከተ ችሎቱን የሚታደሙ ቤተሰቦች እንዲቀነሱ ትእዛዝ የሰጠሁት ህግን ባለ ማክበር የችሎት ሥራ እየታወከ በመሆኑ ነው ብለሏል፡፡

ተከሳሾች ችሎቱን ለመታደም ፍቃደኛ ባለመሆናቸው ከዚህ በኋላ በማረሚያ ቤት ሆነው በፕላዝማ እንዲከታተሉ ሲል ችሎቱ አዟል፡፡ የአዲስ አበባ ፖሊስ የፕላዝማ ችሎቱን እንዲያመቻች በማዘዝ ለየካቲት 18፣ 2012 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

በአንደኛ ተከሳሽ አስር አለቃ መሳፍት ጥጋቡ ላይ የተሻሻለው ክስ አቃቤ ህግ በማረሚያ ቤት በኩል ለተከሳሾች እንዲደርስ በችሎቱ ትዕዛዝ ተላልፏል፡፡ የተከሳሽ ጠበቆች ተከሳሾች በሌሉበት ችሎት አንቀርብም በማለት ፍርድ ቤቱ እንዲያሰናብታቸው ጠይቀዋል፡፡

(waltainfo. com)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የተሻሻለው የኤክሳይዝ ታክስ...

- በተሻሻለው ረቂቅ ከ1 ሺህ 300 ሲሲ በታች ባሉ አዳዲስ ተሽከርካሪዎች ላይ የሚጣለው የታክስ መጠን ከ30 በመቶ ወደ 5 በመቶ ወርዷል። ይህም የተሽከርካሪዎችን ዋጋ እስከ 83 በመቶ ይቀንሰዋል ተብሏል።

- በሲጋራ ላይ ተጥሎ የነበረው የ35 በመቶ ታክስ ወደ 36 በመቶ ከፍ እንዲል በማሻሻያው ቀርቧል።

- በታሸጉ የውሃ ምርቶች ላይ ሊጣል የነበረው የ15 በመቶ ታክስ 10 በመቶ ሆኖ ቀርቧል። አምራቾች የውሃ ፕላስቲኮችን የመሰብሰብና አካባቢን እንዳይበክሉ የማድረግ ስራ እየሰራን ነው ማለታቸው ለማሻሻያው ምክንያት መሆኑን ተገልጿል።

- የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትም የቀረበውን ረቂቅ ማሻሻያ ተመልክቶ በቅርቡ ያጸድቀዋል ተብሎ ይጠበቃል።

- ይህን መሰረት በማድረግ በመሰረታዊ የፍጆታ ሸቀጦች ላይ ታክስ የተጣለ በማስመሰል የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ እስከመውሰድ የደረሰ እንቅስቃሴ እየተደረገ ይገኛል።

(የገንዘብ ሚኒስቴር፣ ኤፍ ቢ ሲ)
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
የተቃውሞ ሰልፎች በከምባታ ጠምባሮ ዞን...

ዛሬ በደቡብ ክልል ከንባታ ጠምባሮ ዞን የተቃውሞ ሰልፎች ሲደረጉ ውለዋል። ተቃውሞ ትናንት ዳምቦያ በተባለች ከተማ የተቀሰቀሰ ሲሆን የተቃውሞው ገፊ ምክንያት የሀላባ፣ ከምባታና ሃዲያ ዞኖችን የሚያገናኝ የሃላባ-ዳምቦያ ማዞሪያ መንገድ ይሰራልን የሚል ነው።

ዛሬ ተቃውሞ በተለያዩ አካባቢዎች የተካሄደ ሲሆን፣ ከሆሳዕና-ሃላባ-ሻሸመኔ የሚወስደው መንገድ ተዘግቶ ውሏል። የተቃዋሚዎች ጥያቄም ከመንገድ ይሰራልን ወደ ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍልና ወደ ክልልነት ጥያቄዎች ከፍ ብሏል።

"መንግስት ነገሮች ሳይካረሩ ሕዝብን ፊት ለፊት አግኝቶት የልቡን ትርታ እንዲያዳምጥና ተገቢውን ምላሽ እንዲሰጥ በተደጋጋሚ ያሰማነው ጥሪ ምላሽ አላገኘም" ብለዋል ኢንጅነር ጌታሁን ሄራሞ።

ኢንጂነር ጌታሁን አክለውም "ከብዙ ጊዜ በፊት የታቀዱ የመንገድ ፕሮጀክቶች በከምባታና ሌሎች ዞኖች ተሰርዘው አዳዲስ የቢሊዮን ብር ፕሮጀክቶች በአዳዲሶቹ ገዢዎች ዞኖች እንዲገነቡ ፕሮጀክቶች ፀድቀዋል" ሲሉ ገልፀዋል።

(ELU,Eng.Getahun Heramo,Elias Meseret)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በትግራይ የወረዳነት ጥያቄ...

ከመቀሌ ከተማ ወደ ሳምረ የሚወስደው መንገድ "ወረዳችን ይመለስልን" በሚሉ የሕንጣሎ ነዋሪዎች ደንጎላት በሚባል አካባቢ ከትናንት በስቲያ ጀምሮ እንደተዘጋ ቢቢሲ ዘግቧል።

'ሕንጣሎ ወጀራት' ተብሎ ይጠራ የነበረው ወረዳ ለሁለት ተከፍሎ፤ ወጀራት እራሱን የቻለ ወረዳ ሲሆን ሕንጣሎ ደግሞ ሒዋነ ከምትባል ሌላ ወረዳ ጋር እንዲካተት ተደርጓል።

ሒዋነ ከምትባለው ወረዳ ጋር እንዲቀላቀሉ የተደረጉት የሕንጣሎ ነዋሪች፤ እራሳችንን የቻለ ሕንጣሎ የተባለ ወረዳ ሊኖረን ይገባል እንጂ ከሒዋነ ወረዳ ጋር መቀላቀል የለብንም የሚል ቅሬታ ነው የሚያነሱት።

ቢቢሲ ነዋሪዎቹን ጠቅሶ እንደዘገበው አሁን በተጀመረው አዲስ የአስተዳደር መዋቅር፤ ወጀራት ከ1-9 ጣቢያዎች ያሉት ሲሆን ሕንጣሎ ግን ሒዋነ ወደሚባል ወረዳ እንዲቀላቀል ተደርጓል። ታዲያ ነዋሪዎቹ የራሳችን ወረዳ ይኑረን ሲሉ ነው እየጠየቁ ያሉት።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በትግራይ የወረዳነት ጥያቄ...

የአካባቢው ነዋሪዎች ኮሚቴ ወኪል አቶ ደሱ ፀጋየ፦

- ጥያቄያችን ወረዳችን ይመለስልን የሚል ነው፤ ህንጣሎ ውጀራት ወረዳ ነበረች። ወጀራት ተመለሰች ነገር ግን ህንጣሎ ተሰጠች።

- ይህንን ጥያቄያችንን ማቅረብ ከጀመርን ስድስት ወራት ተቆጥረዋል። ቅሬታችንን ለማቅረብ ያልሄድንበት ፤ ያልደረስንበት ቦታ የለም። በወረዳ እና በዞን የሚገኙ የፍትሕም ሆነ የፀጥታ አካላትን አዳርሰናል። ነገር ግን ያገኘነው ምላሽ የለም።

- እኛ መንግሥት በደነገገው ሕግ መሠረት ሁሉንም አሟልተናል። አንደኛ ከ115 ሺህ ሕዝብ በላይ ነን። ሁለተኛ መንግሥት 'ከ20 ኪሎ ሜትር በላይ ተጉዞ የወረዳ አገልግሎት ማግኘት የለበትም' ነው የሚለው እኛ ግን ከ30 በላይ ኪሎ ሜትር በላይ ሄደን ነው ይህንን አገልግሎት የምናገኘው፤ ስለዚህ የልማት ጥያቄያችን እንዲመለስልን ነው የምንፈልገው።

- ይህንን ጥያቄ ማንሳት ከጀመርን የቆየን ቢሆንም፤ የፖለቲካ አስተዳዳሪዎችን መልስ እንዲሰጡን ቢንጠይቅም ጆሮ የሰጠን የለም። በተቃራኒው በዞንና በወረዳ ፖሊስ አማካኝነት ያስፈራሩን ገቡ፤ ወደ ገበያ የሚሄዱ ከብቶች ሳይቀሩ መንገድ ላይ ነው የዋሉት፤ መንገድ ዝግ ነው፤ ይሄው እንዲህ ከሆነ ሦስት ቀን ሆኖታል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የደህንነት ካሜራ በዩኒቨርሲቲዎች... መንግስት በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን በደህንነት ካሜራዎችና በር ላይ በሚደረግ ጥብቅ ቁጥጥርና ፍተሸ እንዲታጀብ እንደሚያደርግ በዛሬው ዕለት አሳውቋል፡፡ @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የደህንነት ካሜራዎች በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት...

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚንስቴር ሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የደኅንነት ካሜራ በመግቢያ እና መውጫ በራቸው ላይ እንዲገጥሙ ማዘዙን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘግቧል፡፡ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፣ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፣ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ፣ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ እና ዋቻሞ ዩኒቨርስቲ ቀደም ሲል በራሳቸው ተነሳሽነት ካሜራውን ተክለዋል፡፡

(The Ethiopian Herald,WazemaRadio)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Audio
ከእገታ የተለቀቁት ተማሪዎች...

🎤የኦሮሚያ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ ከጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጋር ደረጉት ቃለ ምልልስ!

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#UPDATE

ከእገታ የተለቀቁት ተማሪዎች...

ከደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ወደ ቤተሰቦቻቸው ሲሄዱ ከታገቱ በኋላ መንግስት መለቀቃቸውን ያስታወቀው ሃያ አንድ ተማሪዎች ወደ ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ መመለሳቸውን የኦሮሚያ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ ከጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ ተናገሩ። 

ተማሪዎቹ ከእገታ ከተለቀቁ በኋላ ከወላጆቻቸው ጋር ያልተገናኙት በአካባቢው የስልክ ግንኙነት አገልግሎት ባለመኖሩ የተነሳ መሆኑንም አቶ ጌታቸው ባልቻ ዛሬ ተናግረዋል። የታገቱ ቀሪ ስድስት ተማሪዎችን ለማስለቀቅም ጥረት እየተደረገ መሆኑንም አመልክተዋል።

የጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ  ተማሪዎቹ ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ መኖራቸውን ለማጣራት ወደ ዩኒቨርስቲው ስልክ ቢደውልም ስልክ ባለመስራቱ እንዳልተሳካለት ገልጿል።

(የጀርመን ድምፅ ሬድዮ)
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot