#ኡቡንቱ #አርባምንጭ #ቲክቫህ #ፒስሞዴል
በዛሬው የውይይት ዝግጅት ላይ በስፋት ከተነሱት ሀሳቦች መካከል ሰው በሰውነቱ፡ብቻ ሊከበር እንደሚገባውና ሰላምን የሚያስቀድም ትውልድ ለመገንባት ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ እንደሚገባ ተገልጿል፡፡ በውይይቱ የተሳተፉ ወጣቶች ደግሞ የጋሞ አባቶች ሰላም ወዳድነት ከአንድም ሁለት ጊዜ በተግባር የተገለጠ መሆኑን ጠቅሰው እንዲህ በአንድ መድረክ ስለ ሰላም አብረው መምከራቸው ትልቅ ትምህርት እንደሚሰጣቸው አንስተዋል፡፡ በአጠቃላይ ከውይይቱ በኀላ ሁሉም እጅ ለእጅ ተያይዘው ስለ ሁሉም ሰው ልጆች ክብር የድርሻቸውን ለመወጣትና ይህን ለማድረግ እድሜ እንደማይገድበው በማመን የሚጠበቅባቸውን ሀላፊነት ሁሉ ለመወጣት ቃል ገብተዋል፡፡
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

በዛሬው መርኃ ግብራችን ላይ ታዳጊ ህጻናት እንዲህ በማለት መልዕክታቸውን አቅርበዋል፡-
"እኛ ህጻናት የእናንተው ልጆች ነን ለሀገራችንም ተምረን ተስፋ የምንሆናት ትውልዶች እኛ ነን፡፡ በፍቅር አድገን ወላጆቻችንንና ሀገራችንን ማገዝ እንመኛለን፡፡"
"እኛ ህጻናት ፍቅር ያስፈልገናል፡፡ የወደፊት የሀገራችን ተስፋዎች እኛ ነንና ታላላቆቻችን ፍቅር ልታስተምሩን ይገባል"
"መልካምነትን የምንማረው ከታላላቆቻችን ነውና እባካችሁ መልካምነትን በተግባር አስተምሩን"
"አባቶቻችን ትላንት እርጥብ ሳር ይዘው ለሰው ልጅ እንዴት ክብር መስጠት እንዳለብን አስተምረውናልና እኛ ህጻናት ከልባችን እናመሰግናቸዋለን"
ይህንን መልዕክት በኮልታፋ አንደበታቸው ካቀረቡ በኀላ በትህትና ዝቅ ብለው የአባቶችን ጉልበት ስመዋል አባቶችም ህጻናቱን መርቀው የሰላም ምልክት የሆነውን ነጭ ባንዲራ አበርክተውላቸው ልጆቻቸው በሰላም እንዲኖሩ በሙሉ አቅማቸው ለሰው ልጅ ክብርና ለሰላም እንደሚተጉ ቃል ገብተውላቸዋል፡፡
#ጋሞዞን #አርባምንጭ #ቲክቫህ #ፒስሞዴል #ሃይሌሪዞርት
@tikvahethiopia @tsegabwolde

#እናመሰግናለን!
ጥሪያችንን አክብራችሁ የተገኛችሁ የሃይማኖት አባቶች፣ የጋሞ አባቶች፣ የአርባ ምንጭ ከተማ ነዋሪዎች እና የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በሙሉ ላቅ ያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን።
ለዚህ መርኃግብር መሳካት የድርሻችሁን ለተወጣችሁ ለመልካሙ ሀሳብ መልካምነታችሁን ለገለጻችሁ በሙሉ የዚህ ዝግጅት መሳካት ክብሩ የእናንተ ነውና ክብር ይገባችኀል፡፡
በተለይ ባስፈላጊው ነገር ሁሉ ላልተለየው ድጋፋቸው የጋሞ ዞን አስተዳደርን ከልብ እናመሰግናለን፡፡ ለዚህ ስራ ብዙ ድጋፍ ያደረጉ አካላትንም ሳናመሰግን አናልፍም፡፡ በተለይም ኃይሌ ሪዞርት፣ ኦሞቲክ ጀነራል ትሬዲንግና ዊዝደም አካዳሚ ከልብ እናመሰግናለን፡፡
ዲዛይነሮቻችን፦
•ፌቨን ደረጀ
•በረከት መንግስቱ
•ሂሩት ታዬ
•ሄርሜላ ተሾመ
•ቅዱስ ዮሐንስ
ሳውንድ ሲስተምና ዲኮር፦
•ሙሉቀን መሉ የሳውንድ ሲስተምና ዲኮር ስራ
#ኡቡንቱ #አርባምንጭ #ቲክቫህኢትዮጵያ #ፒስሞዴል
በቀጣይ በሌሎች የሀገራችን ከተሞች ከሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች (ከወጣቶች፣ ከሃይማኖት አባቶች፣ ከሃገር ሽማግሌዎች፣ ከአባ ገዳዎች ጋር ተመሳሳይ መድረኮችን እያዘጋጀን የምንመክር ይሆናል። እንዲሁም በዩኒቨርሲቲዎች፣ አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች ጋር ተመሳሳይ ዝግጅቶችን ይኖሩናል።
"በምክንያት የሚያምን ሚዛናዊ በሆነ ትውልድ መካከል የሚፈጠር የሃሳብ ልዩነት የጥንካሬ ምንጭ እንጂ የጠብ መነሻ አይሆንም!"
"እኛ ወንድምና እህት ነን፤ እዚህ ምድር ላይ አብረን እንጓዛለን!"
ቲክቫህ ቤተሰቦች!
@tsegabwolde @tikvahethiopia

"አብሮነት ከጋሞ እስከ ጎንደር" የተሰኘ የጉዞ ፕሮግራምን በተመለከተ እና " የኢትዮጵያ የሀገር ሸማግሌዎች ሕብረት" ምስረታን በተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ በአርባ ምንጭ ተሰጠ!
የግንዛቤ ማስጨበጫውን ያዘጋጀው ሕብረመንጎል ቲቪ መልቲ ሚዲያ የተባለ የግል ድርጅት ሲሆን እስካሁን በመንግስትም ሆነ በሌሎች አካላቶች እየተሰሩ ያሉትን የሠላም እና የእርቅ ሥራዎችን ለማገዝ እና የበኩሉን አስተዋፅኦ ትውልዱ ላይ ለማሳረፍ ፣እንዲሁም ሃላፊነቱን ለመወጣት ይቅርታ፣ ፍቅርን ፣ መቻቻልን እና መከባበርን ፣ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትና አንድነትን ለማጠናከር ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ተገልጿል።
More👇
https://telegra.ph/eth-12-08-3
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot

የጉበት በሽታ በኢትዮጵያ!
የኢትዮጵያ ጉበት ጤና በጎ አድራጎት ድርጅት ምስረታ ጉባኤ በአዲስ አበባ አካሂዷል። ድርጅቱ በጉበት በሽታ ሐኪሞች፣ የህመሙ ተጠቂዎችና ሌሎች ጉዳዩ በሚመለከታቸው በጎ ፈቃደኞች እነደተመሰረተ ተገልጿል። በወቅቱ እንደተገለጸው በኢትዮጵያ የጉበት በሽታ ወይም ሄፓታይተስ በሽታ ተጠቂዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱ ተገልጿል።
በዚህም ምክንያት የበሽታውን ተጎጂዎች ለመደገፍ እና በበሽታው መካለከል ዙሪያ ስራዎችን ለመስራት የኢትዮጵያ ጉበት ጤና በጎ አድራጎት ድርጅት ተመስርቷል።
በዓለማችን ከ325 ሚሊዮን ዜጎች በጉበት በሽታ የተጠቁ ሲሆን በኢትዮጵያ ደግሞ ከ1 ነጥብ 7 ሚሊዮን በላይ ዜጎች በጉበት በሽታ መጠቃታቸው ተገልጿል። የጉበት በሽታ በተለይም ንጽህናውን ባልጠበቀ ምግብና ውሃ የሚተላለፍ ገዳይ በሽታ ሲሆን ከሄፓታይተስ ቢ ውጪ ሌሎቹ የጉበት በሽታዎች በወቅቱ ህክምና ካገኙ መዳን ይቻላል።
የሕክምና ባለሙያዎች አራት አይነት የጉበት በሽታዎች ያሉ ሲሆን ሄፓ ታይተስ A,B,C,D,E በሚል ያስቀምጧቸዋል። በጤና ላይ ከሚያደርሱት ጉዳት አንጻር ደግሞ ሄፓታይተስ A እና E የጉበት በሽታ ተጠቂዎች በወቅቱ ህክምና ካገኙ በቀላሉ ከበሽታው መዳን የሚቻል ሲሆን ሄፓታይተስ ቢ እና ሲ የበሽታው ምልክቶች ሳይታዩ ከ20 አስከ 30 ዓመት ተደብቀው ሊቆዩ ይችላሉ።
በኢትዮጵያ ካሉ ከ1 ነጥብ 7 ሚሊዮን የበሽታው ተጠቂዎች ውስጥ የሄፓታይተስ ሲ የጉበት በሽታ ተጠቂዎች ቁጥር እስከ 230 ሺህ የሚደርስ ሲሆን እስከ 110 ሺህ የሚሆኑት ደግሞ የሄፓታይተስ ቢ ጉበት በሽታ ተጠቂዎች ናቸው ተብሏል።
https://telegra.ph/ETH-12-08-4
(ETHIO FM 107.8)

‹‹የፀረ ሽብር ህጉ ሠለባዎች›› ጥያቄያቸውን በዝርዝር ለመንግስት አቀረቡ!
•በአንድነት ፓርክ ውስጥ የመታሰቢያ ሃውልት እንዲቆምላቸውም ጠይቀዋል!
ከሁለት መቶ በላይ የሚሆኑት በፖለቲካ እስር ምክንያት የፀረ ሽብር ህጉ ሠለባዎች የነበሩ ግለሰቦች ከመንግስት የሚፈልጉትን በዝርዝር ያቀረቡ ሲሆን፤ መንግስት አፋጣኝ ምላሽ ይሰጣቸው ዘንድ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ተቋማት ጫና እንዲያደርጉ ጠይቀዋል፡፡
ባለፈው አመት ጥር ወር ከአዲስ አበባ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ጋር ስለደረሰባቸው ጉዳትና መንግስት ሊያደርግላቸው ስላቀደው ድጋፍ የተነጋገሩ ቢሆንም እስከዛሬ አለመፈፀሙን የጠቆሙት የፀረ ሽብር ህጉ ሠለባዎች፤ መንግስት አሁንም አፋጣኝ ምላሽ የማይሰጣቸው ከሆነ ኢትዮጵያ የፈረመቻቸውን የሰብአዊ መብት ጥበቃ ድንጋጌዎችን መነሻ በማድረግ፤ በአለማቀፍ ህግ መንግስትን ለመክሰስ መዘጋጀታቸውንም አስታውቀዋል፡፡
ባለፉት አመታት በፀረ ሽብር ህጉ ምርመራ ሲደረግባቸው በሃይልና በአስገዳጅነት የሠጡት ቃል፣ አሻራና የመሳሰሉት ሰነዶች በይፋ እንዲሠረዙላቸው፤ መንግስት ይቅርታ በጠየቀው መሠረት ለተፈፀመባቸው ግፍ በግልጽና በሠነድ እውቅና እንዲሰጣቸውና ያለፉት ማህደሮች መምከናቸውን እንዲያረጋግጥላቸውም ጠይቀዋል፡፡
በተጨማሪም በወቅቱ ንብረት ሃብታቸውን አጥተው ቤተሰባቸው ተበትኖ ለከፍተኛ ችግርና እንግልት ተዳርገው እንደነበር በማመልከትም መጠለያ እንዲሠጣቸውም ጠይቀዋል፡፡
More👇
https://telegra.ph/ETH-12-08-2
(Addis Admas)

"አስተዳደሩ ምንም አይነት አዲስ የከተማ አደረጃጀትም ሆነ ማስተርፕላን የመተግበር ሀሳብ የለውም!" - ከንቲባ ፅ/ቤት
"የአዲሰ አበባ ከተማ አሰተዳደር የከተማዋን ማስተርፕላን ሊያሻሽል ነው፤ በከተማዋ ያሉት የክፍለ ከተማዎች ቁጥርም ወደ 13 ከፍ ሊል ነው" በሚል በማህበራዊ ድረ ገጾች እየተዘዋወረ ያለው መረጃ የተሳሳተ መሆኑን የከተማ መስተዳድሩ አሳውቋል። የከተማ አስተዳደሩ ምንም አይነት አዲስ የከተማ አደረጃጀትም ሆነ ማስተርፕላን የመተግበር ሀሳብ የሌለው መሆኑን ገልጿል።
(Mayor Office Of AA)
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
"የአዲሰ አበባ ከተማ አሰተዳደር የከተማዋን ማስተርፕላን ሊያሻሽል ነው፤ በከተማዋ ያሉት የክፍለ ከተማዎች ቁጥርም ወደ 13 ከፍ ሊል ነው" በሚል በማህበራዊ ድረ ገጾች እየተዘዋወረ ያለው መረጃ የተሳሳተ መሆኑን የከተማ መስተዳድሩ አሳውቋል። የከተማ አስተዳደሩ ምንም አይነት አዲስ የከተማ አደረጃጀትም ሆነ ማስተርፕላን የመተግበር ሀሳብ የሌለው መሆኑን ገልጿል።
(Mayor Office Of AA)
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ...
"እንኳን የኢትዮጵያዊነት ቀን ለሆነው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በዓል አደረሳችሁ፡፡ ይህን በዓል ስናከብር ወደ ቀደመው አሐዳዊነትም ሆነ ወደ እጅ አዙር አሐዳዊነት ዳግም እንደማንመለስ እያረጋገጥን ነው፡፡ ከፊታችን ያለው ዘመን መንፈሳዊ፣ አእምሯዊና ቁሳዊ ብልጽግናችን የሚረጋገጥበት ዘመን ይሆናል፡፡ ባህሎቻችን፣ ቋንቋዎቻችን፣ ዕሴቶቻችን፣ የሚበለጽጉበት ዘመን ይሆናል፡፡ አንድነታችን፣ አብሮነታችን፣ ወንድማማችነታችን የሚበለጽግበት ዘመን ይሆናል፤ በዕውቀትና በሀብት የምንበለጽግበት ዘመን ይሆናል፡፡ በፍትሕ፣ በሰላም፣ በጋራ ደኅንነት፣ የምንበለጽግበት ዘመን ይሆናል፡፡ ካሳለፍናቸው ዘመናት ይልቅ ወደፊት የምናሳልፋቸው ዘመናት ብዙ ናቸው፡፡"

አሁንም የሚሰማን አካል ካለ ድምፃችንን እናሰማለን!
በአንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እየታዩ ያሉ ምልክቶች ሀገሪቱን የማትወጣው አዘቅት ውስጥ ሊከታት የሚችል ስለሆን መንግስት ሰምቶ እንዳልሰማ፤ አይቶ እንዳላይ ከማለፍ ሳይውል ሳያድር መፍትሄ ቢፈልግ መልካም ነው። እከሌ መማር ትችላለህ፤ እከሌ መማር አትችልም ውጣልኝ፣ ሂድ ከዚህ የሚሉ መልዕክቶችን በግቢ ውስጥ የሚያሰራጩ አካላትን መለየት እና መፍትሄ መፈለግ እንዴት እንዳልተቻለ ግራ አጋብቶናል።
በርካታ ተማሪዎች ስጋት አድሮባቸው፣ ማስፈራሪያ ደርሷቸው ወደቤተሰባቸው መመለሳቸውን አረጋግጠናል፤ የግቢ በር ተዘግቶባቸው ከግቢ መውጣት ያልቻሉ እንዳሉም እናውቃለን፣ በሚደርስባቸው ማስፈራሪያን ወደመማሪያ ክፍል የማይገቡም እንዳሉ እናውቃለን፣ ሌላው ሲማር አንዳንድ ተማሪዎች ተለይተው እንዳይማሩ ጫና እየተደረገባቸው እንዳሉ እናውቃለን።
አሁንም ወደ ቤተሰቦቻቸው እየሄዱ ያሉ ተማሪዎች እንዳሉ እናውቃለን፤ ያለምንም ትምህርት ከሳምንታት በላይ የተቀመጡ ተማሪዎችም እንዳሉ እናውቃለን፣ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ወጥተው በአዲስ አበባ ዙሪያ የተቀመጡ፤ በሰዎች እገዛ ያሉም እንዳሉ እናውቃለ፤ ይህ ሁሉ ነገር እንዳለ የሀገሪቱ መንግስት አያውቅም ማለት ቀልድ ነው።
የሚመለከታቸው አካላት አሁን ያሉትን ችግሮች በዘላቂነት ከመፍታት ይልቅ ምንም እንዳልተፈጠረ አድርገው ለሚዲያ የሚሰጧቸው መረጃዎች የተማሪዎችን ስሜት በእጅጉ እየጎዳው ወጣቱ በሀገሩና በመንግስት ላይ እምነቱን እንዲያጣ እያደረገው እንደሆነ እየተመለከትን ነው። የተማሪ ቤተሰቦችም የህግ የበላይነት ጥያቄ ውስጥ በመውደቁ በመንግስት ላይ እምነት እያጡ እንደሆነ ነግረውናል።
እየታዩ ያሉት ምልክቶች እጅግ አደገኛ፣ለሀገርም ህልውና አስጊ በመሆናቸው መፍትሄ ይፈለግላቸው!
@TikvahethiopiaBot

"የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ትግል ሁሉም እኩል የሆኑባትን ኢትዮጵያን መፍጠር ነው" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የብሔር ብሔረሰቦችን ቀን ለማክበር በተዘጋጀ ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ትግል ሁሉም እኩል የሆኑባትን ኢትዮጵያን ለመፍጠር ያለመ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
"ዴሞክራሲን ማስፈን ቀላል ተግባር አይደለም፤ የጅማሮው ሥራ የቱንም ያህል አስቸጋሪ ቢሆን፣ ጉዞን ወደዚያ ማድረግ ለፍሬ የሚያበቃ ነው" ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡
ወደ ብልጽግና በምናደርገው ጉዞ ራሳችንን በመከባበር፣ በመቻቻል እና በትዕግስት መልህቅ ካጠነከርን እነዚህኑ ፍሬዎች እናጭዳለን ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፡፡
ምንጭ፡- የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት

#መከላከያሰራዊት
"የመተዳደሪያ ህገ ደንቡ መሻሻል የሰራዊቱን #ኑሮ በመለወጥ ተቋሙ ጠንካራ ሆኖ እንዲቀጥል ይረዳዋል!" - ምክትል ኢታማዦር ሹም ጀነራል ብርሀኑ ጁላ
.
.
የኢፌደሪ መከላከያ ሰራዊት ምክትል ኢታማዦር ሹም ጀነራል ብርሀኑ ጁላ በቅርቡ የፀደቀውን የመከላከያ ሰራዊት መተዳደሪያ ደንብ በመተግበር የሰራዊቱን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ተናገሩ፡፡
ምክትል ኢታማዦር ሹም ጀነራል ብርሃኑ ይህን ያሉት በተሻሻለው የመከላከያ ሰራዊት መተዳደሪያ ደንብ እንዲሁም በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ለሰራዊቱ ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ማጠናቀቂያ መርሀ ግብር ላይ ተገኝተው ነው፡፡
ጀነራል ብርሀኑ በዚሁ ወቅት የሰራዊቱ መተዳደሪያ ደንብ መሻሻል ከነባራዊና ወቅታዊ ሁኔታ ጋር የሚራመድ ገለልተኛ መከላከያ ሰራዊት ለመገንባት ታስቦ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በሌላ በኩል የመተዳደሪያ ህገ ደንቡ መሻሻል የሰራዊቱን ኑሮ በመለወጥ ተቋሙ ጠንካራ ሆኖ እንዲቀጥል እንደሚረዳውም ምክትል ኢታማዦር ሹም ጀነራል ብርሀኑ ጁላ ተናግረዋል፡፡
መከላከያ ሰራዊቱ ገለልተኛ እና ስራዎቹን እውቀትን መሰረት በማድረግ የሚሰራ የመከላከያ ሰራዊት መለዮውን እየቀየረ ነው ያሉት ጀነራል ብርሀኑ ከዚህ በኋላ የመከላከያ መለዮ ከተቋሙ አባል ውጪ ሊለበስ እንደማይችል እና በምንም ምክንያት ወደ ውጪ እንደማይወጣ ተናግረዋል፡፡
(የመከላከያ ሚኒስቴር የኢንፎርሜሽን ዳይሬክተር )