TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#attention

#ሱሉልታ ከተማ ዛሬም አለመረጋጋት ይታያል። መንገዶች ተዘግተዋል። በየአስፓልቱ የሚቃጠል ጎማዎችም ይታያሉ። መንግስት ለከተማይቱ ትኩረት እንዲሰጥ የቲክቫህ ሱሉልታ ቤተሰቦች አሳስበዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Bishoftu

ሀገር መከላከያ ሰራዊት በከተማይቱ ከትላንት ጀምሮ የተፈጠረውን አለመረጋጋት ለመቆጣጠር ጥረት እያደረገ ይገኛል። በሌላ በኩል በዛሬው ዕለት በቢሾፍቱ ከተማ የሰው ህይወት ላይ ጉዳት ደርሷል። ዝርዝር መረጃዎችን ስናገኝ የምን ቅርብ ይሆናል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ከዶይቼ ቬለ (DW) ቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ #የደህንነት ባለስልጣኖቻቸው በቂ መረጃ ይሰጧቸው እንዳልነበር ተናግረዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አቶ ኃይለማርያም በስልጣን ዘመናቸው የደህንነት ባለስልጣኖቻቸው በቂ መረጃ ይሰጧቸው እንዳልነበር ተናገሩ!

የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በዶይቼ ቬለ (DW) ቴሌቪዥን ጣቢያ ከሚተላለፈው “ኮንፍሊክት ዞን” ከተባለ ፕሮግራም ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ “አምባገነን ተብዬ ልጠራ አይገባኝም” አሉ።የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር በእርሳቸው የስልጣን ዘመን ስለተፈጸሙ ግድያዎች፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እና የሙስና ወንጀሎች ተጠይቀው ምላሽ ሰጥተዋል።

እነዚህን ጉዳዮች በተመለከተ የደህንነት ባለስልጣኖቻቸው በወቅቱ በቂ መረጃ ይሰጧቸው እንዳልነበር ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ አሁን ያለው ለውጥ እንዲመጣ የራሴን ድርሻ ተወጥቻለሁ” ያሉት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር፤ “እኔን አምባገነን አድርጎ መሳል ትክክል አይደለም” ብለዋል።

Via DW/ኢፕድ/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በኦሮሚያ ክልል በምትገኘው የባሌ ሮቤ ከተማ ለጀዋር መሐመድ ድጋፍ ከተደረገ ሰልፍ በኋላ በተቀሰቀሰ ግጭት ቁጥራቸው በወል ያልታወቀ ሰዎች መሞታቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ። የባሌ ሮቤ ነዋሪዎች የሐይማኖት መልክ ይዟል ባሉት ግጭት ሆቴሎች፣ ምግብ ቤቶች እና ሻይ ቤቶች መቃጠላቸውን የዐይን እማኞች ለጀርመን ራድዮ ተናግረዋል።

የጀርመን ሬድዮ ያነጋገራቸው ሶስት የከተማዋ ነዋሪዎች ከትናንት አመሻሽ ጀምሮ ባሌ ሮቤን ከሌሎች አካባቢዎች የሚያገናኙ መንገዶች፣ የግብይት መደብሮች፣ የመንግሥት እና ማኅበራዊ ተቋማት መዘጋታቸውን አስረድተዋል። ጀዋር መሐመድ በማኅበራዊ ድረ-ገፆች ካሰራጨው መልዕክት በኋላ ትናንት ጠዋት በአብዛኛው ወጣቶች የተሳተፉበት ሰልፍ መካሔዱን የገለጹት ነዋሪዎች በሒደት መልኩን እየቀየረ ወደ ግጭት እና ጥቃት መቀየሩን ተናግረዋል።

https://telegra.ph/ETH-10-24-3

Via DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#SHASHEMENE

በሻሸመኔ ከተማ ተዘግተው የነበሩ መንገዶች በመክፈት ላይ ይገኛሉ። የትራንስፖርት እንቅስቃሴም አልፎ አልፎ ይታያል። ንግድ ቤቶችም መከፈት ጀምረዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከትላንት ጀምሮ ተዘግተው የነበሩት የሻሸመኔ መንገዶች እየተከፈቱ ነው። ተሽከርካሪዎችም እየተንቀሳቀሱ ይገኛል። የወትሮዋና ደማቋ ሻሸመኔ ባትመስልም ነገሮች እየተረጋጉ እና እየረገቡ ነው።

ከየከተሞቹ ያሉ ሁኔታዎችን ቤተሰቦቻችን ማሳወቅ ትችላላችሁ፤ እንደሁል ጊዜው በፎቶ ማስደገፍ እንዳትረሱ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ሻሸመኔ | የትራንስፖርት እንቅስቃሴው ተጀምሯል። መንገድ ላይ የነበሩ ድንጋዮችም እየተነሱ ነው። የንግድ ሰዎችም ወደ ስራቸው እንዲመለሱ መልዕክት እየተላለፈላቸው ይገኛል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አወዳይ ከተማ መንገድ እየተከፈተ ይገኛል። በየአስፓልቱ የተጣሉ ድንጋዮችም እየተነሱ ይገኛሉ። አስፓልቱ በከተማው ነዋሪዎች እየፀዳ ነው።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሱሉልታ ከተማ ላይ ተዘግቶ የነበረው መንገድ አሁን ክፍት ሆኗል። ተሽከርካሪዎችም እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ። #ETH

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#SEBETA የሰበታ ከተማ ነዋሪ ቲክቫህ ቤተሰቦች የሰበታን እንቅስቃሴ አሳውቀውናል፤ መንገዶች ተከፍተዋል። የትራንስፖርት እንቅስቃሴም እየተጀመረ እንደሆነ ገልፀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#HARAR

ሀረር ከተማ አሁን ረገብ ብላለች። ጠዋት የከተማው ውሥጥ ከፍተኛ ውጥረት ነበር። ሱቆች ግን ዝግ ናቸው። መንገዶች ግን እንዲከፈቱ እየተደረገ ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#attention | አሁንም ቢሆን በድሬዳዋ ከተማ ስጋቶች እንዳሉ የቤተሳብችን አባላት እየገለፁ ናቸው። መንግስት አስፈላጊውን ትኩረት እንዲሰጥ አሳስበዋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሰላምና በፍቅር እንዲሁም በህዝቦች አብሮነት የምትታወቀው ድሬዳዋ ከተማ በተደጋጋሚ የፀጥታ መደፍረስ እያጋጠማት ይገኛል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#SULULTA | የሱሉልታ መንገድ ላይ የነበሩ ድንጋዮች ተነስተዋል። ትራንስፖርት እንቅስቃሴውም ተጀምሯል። የንግድ ሰዎችም ወደ ስራቸው እየተመለሱ ይገኛሉ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኦነግ መግለጫ፦

በሺሕዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሕይወት አልፎበት የተገኘው ለውጥ በአግባቡ እየተስተናገደ አይደለም ሲል የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) መንግሥት ወቀሰ፡፡

ለለውጡ እውን መሆን በግለሰብም ይሁን በቡድን ደረጃ ከፍተኛ ሚና የነበራቸው ‹‹የሕብረተሰብ ክፍሎች ተገቢዉን መብት፣ ክብርም ሆነ እዉቅና ተነፍጓቸዋል›› ሲልም በመግለጫው ከሷል፡፡

ይልቁንም ስልጣን በያዘው አካል እንደ ለውጥ አደናቃፊና ጠላት እየተፈረጁ ነው ሲልም አክሏል፡፡ ሆኖም እንማናቸው የሚለውን በዝርዝር አልገለጸም፡፡

ኦነግ የኢሕአዴግ የ27 ዓመታት አፈና እንዲገታም እንደኦሮሞ ሕዝብ መስዋዕትነት የከፈለ የለም የሚል እምነት እንዳለው በመግለጫው ጠቅሷል፡፡

የኦሮሞን የመብት ጥያቄ እያንሸራሸሩ ነው ያላቸው ጃዋር መሐመድና በስራ አስኪያጅነት የሚመሩት ኦኤምኤን የተሰኘ የቴሌቪዥን ጣቢያ ላይ ያነጣጠረ የጥቃት ዛቻና ማስፈራሪያ አለ በማለትም ከምን የመነጨ እንደሆነ ‹‹ከሕዝባችን የተሰወረ ኣይደለም›› ሲል መንግሥትን ተጠያቂ አድርጓል፡፡

ምንጭ፦ አሃዱ ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#AMBO | የአምቦ ከተማ የፀጥታ ሁኔታ ወደነበረበት አልተመለሰም(ውጥረቱ አሁንም አልረገበም) ተደጋጋሚ የተኩስ ድምፅ እንደሚሰማ የገለፁት የአምቦ ቲክቫህ ቤተሰቦች ለከተማይቱ ትኩረት እንዲሰጥ አሳስበዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#BATU

በተመሳሳይ የባቱ ከተማ (ዝዋይ) የፀጥታ ሁኔታ ወደነበረበት አልተመለሰም ስጋቶች አሁንም አሉ። ከተማው ልዩ ትኩረት እንዲሰጠው የባቱ ቲክቫህ ቤተሰቦች አሳስበዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#AddisAbeba

በኦሮሚያ ተጽዕኖ ፈጣሪ የሆኑ የሃገር ሽማግሌዎች እና ፖለቲከኞች ዛሬ ከሰዓት በሰጡት የጋራ መግለጫ ወጣቶች ከሰሞኑ ከተከሰተው ግጭት እራሳቸውን እዲቆጥቡ ጥሪ አስተላልፈዋል።

ከትናንት በስቲያ በጀዋር ሞሐመድ መኖሪያ ቤት ከተፈጠረው ክስተት በኋላ በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች የተቃውሞ ሰልፎች ተካሂደው ነበር። ከዚህ ጋር ተያይዞ በተፈጠረ በግጭት ቢያንስ 12 ሰዎች ሕይወታቸውን ማጣታቸው ታውቋል። ዛሬ ከሰዓት መግለጫ የሰጡት ፖለቲከኞች ወጣቶች እንዲረጋጉ እና ሠላማዊ ትግል እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

በጀዋር መሐመድ መኖሪያ ቤት በተሰጠው መግለጫ ላይ፤ ጀዋር ሞሐመድን ጨምሮ የኦነግ ሊቀመንበር ዳውድ ኢብሳ፣ ሌንጮ ባቲ፣ ከማል ገልቹ እና ሌሎች የፖለቲካ ሰዎች ተካፋይ ነበሩ።

ጀዋር መሐመድ፦

በመኖሪያ ቤቱ የተፈጸመውን ክስተት ካወገዘ በኋላ ይህ 'ሸር' የኦሮሞን ህዝብ በጣም 'አስከፍቷል' ብሏል። ጀዋር እሱን በመደገፍ ወጣቶች ያሳዩትን ድጋፍ አድንቆ "ከዚህ በላይ ኩራት ሊሰማኝ አይችልም" ሲል ተደምጧል። "ይህን ህዝብ ለመንካት ለሚያስብ ኃይል መልዕክት ደርሶታል" ያለ ሲሆን፤ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝደንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽነር የሰጡት መግለጫ "ኃላፊነት የተሞላበት ስለሆነ ሊመሰገኑ ይገባል" ብሏል። የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዝድነት አቶ ሽመልስ አብዲሳ በጀዋር መሐመድ መኖሪያ ቤት ላይ የተፈጸመው ክስተት "መሆን ያልነበረበት ትልቅ ስህተት ነው" ማለታቸው ይታወሳል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-24-4

Via BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"አሁን ላይ ሀገሪቱ ባለችበት ሁኔታ ምርጫ ማካሄድ እጅግ አደገኛ ነው ብዬ አስባለሁ። ጠ/ሚሩ እንዲሁም አንዳንድ ምርጫውን እናሸንፋለን ብለው የሚያስቡ ፓርቲዎች ምርጫው እንዲካሄድ እንደሚፈልጉ አውቃለሁ። ምርጫውን ማሸነፍ ይቻላል፣ ሀገር ግን ይጎዳል።" አክቲቪስ ጃዋር መሃመድ

በዛሬው ዕለት የAssociated Press አለም አቀፉ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ከአክቲቪስት ጃዋር መሃመድ ጋር ቃለመጠይቅ አድርጎ ነበር። በቃለመጠይቁ ጃዋር ካነሳቸው ሃሳቦች መካከል፦

•እስካሁን ሊገባኝ ያልቻለው ለምን በለሊት ጥበቃ ማንሳት እንደተፈለገ ነው። ከፌደራል ፖሊስም ሆነ ከደህንነት ተቋማት ጋር የነበረኝ ግንኙነት ጥሩ የሚባል ነበር። 

•የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነሩ ትናንት "ጥበቃዎቹ እንዲነሱ የተፈለገው የፀጥታ ችግር ስለሌለ ነው" ብሎ ነበር። እውነታው ግን ከሁለት ሳምንት በፊት እንቅስቃሴያችንን እንድንቀንስ እና በርካታ ህዝብ ከሚሰበሰብበት ቦታ ከመሄድ እንድንታቀብ ተነግሮን ነበር። እንደውም ተጨማሪ ሀይል ለመጨመር ሀሳብ እንዳላቸው ነግረውን ነበር። ስለዚህ ይህ እየተባለ የፀጥታ አካላቱን ለማንሳት መፈለጋቸው ግር የሚል ነበር። 

•ለምን ይህ እንደተከሰተ ሊናገር የሚፈልግ የለም። ጣት መጠቋቆም ብቻ ነው ያለው፣ ይህም የሰው ህይወት እንዲጠፋ ምክንያት ሆኗል። 

•ከጠ/ሚሩ ጋርም ሆነ ከሌሎች አመራሮች ጋር ቁጭ ብለን ማውራት እንችላለን። እኔ ለዛ ዝግጁ ነኝ። 

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-24-5

Via ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት (Associated Press)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የ16 ሰው ህይወት አልፏል!

አክቲቪስት ጃዋር መሐመድ በኦሮሚያ ለድጋፍና ተቃውሞ የወጡ ዜጎች እንዲረጋጉ መልዕክት ማስተላለፉን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ ዛሬ በመኖሪያ ቤቱ ለተሰባሰቡ ደጋፊዎቹ ባስተላለፈው መልዕክት፣ በከተሞች የተዘጉ መንገዶችን ክፈቱ፣ ከከተሞች መሰናክሎችን አንሱ፣ ከተጣላችኋቸው ጋር ታረቁ ሲል ለወጣቶች ጥሪ አድርጓል፡። በሁከቱ እስካሁን 16 ሰዎች ተገድለዋል ብሏል ዘገባው፡፡

Via ሮይተርስ/wazema radio/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከምርጥ 10 የአፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ ሆነ!

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አፍሪካ ውስጥ ካሉ ምርጥ 10 ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ መሆኑን የዓለም ዩኒቨርሲቲዎች ደረጃ አውጪ ተቋም ጥናት አመልክቷል። ተቋሙ ዓለማችን ላይ ያሉ ምርጥ ዩኒቨርሲቲዎችን በ13 መስፈርቶች አወዳድሮ ደረጃ ያወጣል።

ከመስፈርቶቹም መካከል ዓለም አቀፍ ደረጃን የጠበቀ ጥናት የማድረግ ብቃት፣ የቀጠና ደረጃን የጠበቀ ጥናት የማድረግ ብቃት፣ የማሳተም ብቃት፣ የመጽሐፍ አቅርቦት፣ ኮንፈረንሶችን የማካሄድ እና የዩኒቨርሲቲው ‘ሳይት’ የመደረግ ብቃት ይገኙበታል።

እያንዳንዱ ተቋም የተመዘነው ጥናት በማድረግ ብቃቱ እና በቀጠናው እና በዓለም ዙሪያ ያሉ የአካዳሚክ ማኅበረሰቦች በሰጡት ነጥብ እንደሆነ ተገልጿል።

በደረጃው መሰረት ከ1ኛ እስከ 5ኛ የተቀመጡት የደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርስቲዎች ሲሆኑ የግብፁ ካይሮ ዩኒቨርሲቲ በ6ኛ ደረጃ ላይ ተቀመጧል፡፡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲም ከደቡብ አፍሪካ፣ ግብፅ፣ ሞሮኮና ኡጋንዳ ዩኒቨርሲቲዎች ቀጥሎ በ10ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሀና ዩኒቨርሲቲው ላስመዘገበው ውጤት ለዩኒቨርሲቲው ሰራተኞች የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

Via EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia