TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Awlo Media

ከሳምንት በፊት በኢ/ር ታከለ ኡማ እና ኢ/ር እንዳወቅ አብጤ ከኃላፊነታቸው መነሳት ዙሪያ አውሎ ሚዲያ ታማኝ ምንጮቹን ጠቅሶ በሰበር ዜና ለህዝብ ይፋ አድርጎ ነበር። እንደ አውሎ ሚዲያ ከሆነ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ብቻ ሳይሆኑ ኢንጂነር እንዳወቅ አብጤም ከኃላፊነታቸው ይነሳሉ። ምክትል ከንቲባ ኢ/ር ታከለ እና ኢ/ር እንዳወቅ ለትምህርት ወደ ቻይና ሊላኩ እንደሆነ ነው አውሎ ሚዲያ ከሳምንት በፊት ምጮቹን ጠቅሶ የዘገበው።

Via Awlo Media/ጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው/

TIKVAH-ETHIOPIA: በከተማ አስተዳደሩ ውስጥ ከሚሰሩ ቤተሰቦቹ ስለሚሰራጩት መረጃዎች ማረጋገጫዎች ከተላኩልን እንዲሁም በዚህ ጉዳይ ከተማ አስተዳደሩ የሚሰጠው ምላሽ ካለ ተከታትለን እናጋራለን!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Ida'amuu,
Gurmuudhaan Gara Badhaadhinaatti!
መደመር፣ በህብር ወደ ብልጽግና!
Onkoloolessa 8/2012 Godinaalee Oromiyaa 20 fi Magaalota gurguddoo 19tti ni eebbeifama!
ጥቅምት 8/2012 በኦሮሚያ 20 ዞኖች እና 19 ከተሞች ይመረቃል!

Via Addisu Arega

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#WMO | የዓለም የሜቲዮሮሎጂ ድርጅት(WMO) የአፍሪካ ጽህፈት ቤቱን በአዲስ አበባ ሊከፍት መሆኑን ተገለጸ። ይህ የተገለጸው የትራንስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ህይወት ሞሲሳ ሴክረተሪ ጀነራል ፒተሪ ታላሰን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት ነው።

Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
በምስራቅ ጉጂ ስድስት ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ገለፁ!

#TIKVAH_ETHIOPIA
#ETHIOPIA

ባለፈው ቅዳሜ በቦረናና በምስራቅ ጉጂ ስድስት ሰዎች በኦሮሞ ነፃነት ግንባር ተዋጊዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ራድዮ ጣቢያ ተናገሩ። ከመካከላቸው የፀጥታ ጠባቂ ሚሊሺያዎችና ነዋሪዎች እንዳሉባቸው የአካባቢው አስተዳደር ገልጿል።

Via VOA AMHARIC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በድጋሚ የወጣ የህዝበ ውሳኔ አስፈጻሚዎች ምልመላ ማስታወቂያ!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በመጪው ህዳር 2012 ዓ.ም ለሚያካሂደው የሲዳማ የክልልነት የመደራጀት ጥያቄ ህዝበ ውሳኔ 5500 ( አምስት ሺህ አምስት መቶ) የሚሆኑ የህዝበ ውሳኔ አስፈጻሚዎችን በበጎ ፍቃድ አበል ክፍያ ከአንድ ወር ላልበለጠ ጊዜ ለማሰራት ማስታወቂያ ማውጣቱ ይታወሳል፡፡ነገር ግን በቂ የሆኑ አመልካቾች ስላልተገኙ ይህንን ማስታወቂያ በድጋሚ ለማውጣት ተገዷል፡፡

•የስራው ሁኔታ- የህዝበ ውሳኔ አስፈጻሚ
የሚፈለገው ሰው ብዛት - 5500 (አምስት ሺህ አምስት መቶ)

•የማመልከቻ ጊዜ- ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ተፈላጊው ቁጥር እስከሚሟላ ድረስ

•የማመልከቻ ቦታ- ንፋስ ስልክ ቡና ቦርድ ፊትለፊት በሚገኘው የምርጫ ቦርድ ማሰልጠኛ ማእከል

አመልካቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች፦

• የማንኛውም የፓለቲካ ፓርቲ አባል ያልሆነ/ያልሆነች
• በትምህርት ዝግጅታቸው በማንኛውም የትምህርት መስክ የመጀመሪያ ዲግሪ ያላት/ ያለው
• እድሜ ከ20- 45 አመት የሆነች/የሆነ
• በገጠር ቀበሌዎች ተንቀሳቅሰው መስራት የሚችሉ
• የስራ ልምድ አይጠይቅም- ሆኖም በምርጫ አፈጻጸም ዙሪያ ወይም በተለያየ ማህበራዊ አገልግሎቶች የተሳተፉ አመልካቶች ቅድሚያ ይሰጣቸዋል፡፡

ቦርዱ በስራ የሚሳልፉትን ጊዜ የቀን አበል የሚከፍል እና ስልጠና የሚሰጥ ሲሆን በተጨማሪም በህዝበ ውሳኔው ላይ በበጎ ፈቃደኝነት ለተሳተፉ አስፈጻሚዎች የተሳትፎና የእውቅና ምስክር ወረቀት ይሰጣል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
ቡርጂ ልዩ ወረዳ በተከሰተ ግጭት ቢያንስ 20 ሰዎች መገደላቸውን የአከባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል!

#TIKVAH_ETHIOPIA
ቡርጂ ልዩ ወረዳ በተከሰተ ግጭት ቢያንስ 20 ሰዎች ተገደሉ!

ከፈረሰው የሰገን አከባቢ ሕዝቦች ዞንና ከመዋቅር ጥያቄ ጋር በተገናኘ በደቡብ ክልል ቡርጂ ልዩ ወረዳ በተከሰተ ግጭት ቢያንስ 20 ሰዎች መገደላቸውን የአከባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ። ግጭቱ የተፈጠረው በወረዳ በነያ በተሰኘ ቀበሌ ገበሬ ማኅበር ሲሆን መንስኤው የመዋቅር ጥያቄ መሆኑን ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ ተናግረዋል።

Via ቪኦኤ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ችሎት

በኢሉአባቦር ዞን ሁሩሙ ወረዳ ህገ-ወጥ የጦር መሳርያ ሲያዘዋውር የተገኘ ግለሰብ ፍርድ ቤት ቀርቦ በእስራትና በገንዘብ ተቀጣ። የወረዳው አቃቢ ህግ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ብዙአየሁ ምትኩ እንዳሉት ሰይድ አደም የተባለው ግለሰብ ላይ ቅጣቱ የተወሰደው የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ ሶስት 00610 አዲስ አበባ በሆነ መለስተኛ አውቶብስ ከመቱ ወደ አዲስ አበባ የጦር መሳሪያዎችን ደብቆ ለማሳለፍ ሲሞክር በመያዙ ነው።

በትላንትናው እለት በሁሩሙ ኬላ በተደረገው ፍተሻ ከበርበሬ ጋር በጆንያ ተደብቀው የተገኙት የጦር መሳሪያዎች ስምንት የተለያዩ ጠመንጃዎችና 82 የሽጉጥና የጠመንጃ ጥይቶች መሆናቸውን ገልጸው ግለሰቡም ወዲያውኑ ለፍርድ እንዲቀርብ መደረጉን አስረድተዋል። ጉዳዩን የተመለከተው የወረዳው ፍርድ ቤትም የክስ መዝገቡን መርምሮ በሁለት አመት ከስድስት ወር እስራትና በ3ሺህ ብር እንዲቀጣ መወሰኑን ገልጸዋል።

Via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#AAiT #NOKIA #AASTU

#NOKIA | ኖኪያ የ4G እና 5G የቴሌ ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት በኢትዮጵያ ለመዘርጋት መዘጋጀቱን ገለፀ። ኩባንያው ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና የአዲስ አበባ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ጋር የዲጂታል ክህሎትንና የፈጠራ አቅምን ማጎልበት ዙሪያ በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራርሟል።

ፊርማውን የአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ደረጀ እንግዳ እና የአዲስ አበባ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ኢኒስቲትዩትን በመወከል ዶክተር ኢንጂነር ኢሳያስ ገብረዮሀንሰ እንዲሁም በመካከለኛው ምስራቅና ምዕራብ አፍሪካ የኖኪያ ተጠሪ ዳንኤል ጃገር ፈርመውታል።

ስምምነቱ ኩባንያው ለሁለቱ ዩኒቨርሲቲዎች በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መስክ አለም የደረሰበትን አሰራር እና የቴክኖሎጂ ገበያውን ፍላጎት መሰረት ያደረገ ዘመናዊ የትምህርት እና ስልጠና ፕሮግራሞችንና የልምድ ልውውጦችን ማዘጋጀትን እንደሚያካትት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታውቋል።

Via FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#WolaitaSodo #Dessie

በወላይታ ሶዶና በደሴ ከተማ የታየው የመጠጥ ውሃ ጥራት በሌሎችም ከተሞች ሊታይ እንደሚገባ የውሃ ልማት ኮሚሽን አስታወቀ። የወላይታ ሶዶ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ለህብረተሰቡ የሚያሰራጨውን ውሃ በኢትዮጵያ ተስማሚነትና ምዘና ድርጅት ተመርምሮ የኢትዮጵያ የመጠጥ ውሃ የተቀመጠለት መስፈርት በማሟላቱ የ ሲኢኤስ - 58 አይሶ ፡ 2019 (CES-58 ISO :2019) ጥራት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት አገኘ። የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ዶክተር በሻህ ሞገሴ የሰርተፍኬት ማግኘቱን ምክንያት በማድረግ ትናንትና በብሉ ስካይ ሆቴል የዕውቅና አሰጣጥ ፕሮግራም ላይ እንደገለፁት በሀገራችን በሁለቱ ከተሞች የታየው የውሃ ጥራት በኢትዮጵያ ተስማሚነትና ምዘና ድርጅት ተመርምሮ አልፏል፤ ይህ ተሞክሮ ሌሎች የሀገራችን ከተሞች ሊተገብሩት ይገባል ብለዋል።

Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢትዮ-ቴሌኮም 47 ድርጅቶች ላይ እርምጃ ወሰደ!

ከሞባይል ተጠቃሚው ፈቃድና ፍላጎት ውጪ አጭር የጽሑፍ መልዕክትን በመላክ ሲያማርሩ ነበር የተባሉ 47 ድርጅቶች ላይ እርምጃ መውሰዱን ኢትዮ-ቴሌኮም አስታወቀ፡፡

ኩባንያው የአጭር መልዕክት አገልግሎት ላይ ደንበኞች ለረጅም ጊዜ ቅሬታ ሲያቀርቡ እንደነበር ገልጿል፡፡ ''አጭር ቁጥር በመጠቀም የሚሰጡ የመልዕክት አገልግሎቶች በህብረተሰቡ ፈቃድ ላይ ብቻ የተመሰረቱ መሆን አለባቸው'' ያለው ኢትዮ ቴሌኮም ያለፈቃድ ይልኩ የነበሩትን ድርጅቶች መዝጋቱን አክሏል፡፡

በዐጭር የፅሑፍ አገልግሎት ጠቃሚ መልዕክቶች እንደሚተላፉም እረዳለሁ ያለው መንግሥታዊው ተቋም አገልግሎቶቹን በህብረተሰቡ ፈቃድ ላይ ብቻ ተመስርተው እንዲሰጡ ቁጥጥር እያደረግሁ ነው ብሏል፡፡

በአሁኑ ወቅት 310 ድርጅቶች ከኢትዮ-ቴሌኮም ጋር በመተባበር በአጭር ቁጥር የጽሁፍ መልዕክት አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙ የኢዜአ ዘገባ ያስረዳል፡፡

ምንጭ፦ አሃዱ ሬድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የሶማሊያ ጦር #በሬይዳብ መንደር ባደረገው ኦፕሬሽን በአልሸባብ ስር የነበሩ 300 ፍየሎችን፣ በጎችን እና የጦር መሳሪያዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የጦሩ የሬዲዮ ጣቢያ አስታውቋል። አልሸባብ እንስሳቱን ከአካባቢው ነዋሪዎች በኃይል አስገድዶ የወሰዳቸው እንደነበሩም ተነግሯል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዛሬም ሰልፍ እየተደረገ ይገኛል!

የመከላከያ ሰራዊት የሰጠው ምላሽ ተገቢ አይደለም ያሉ፤ እንዲሁም በንፁሃን ዜጎች ላይ እየደረሰ ያለውን ጥቃት #በመቃወም የአፋር ክልል የተለያዩ ወረዳዎች የሚኖሩ ነዋሪዎች በተለያዩ ከተሞች የተቃውሞ ሰልፎች እየተደረጉ ይገኛሉ።

Via Abu Jaefar Dalol
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ETHIOPIA

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #ዐቢይ_አህመድ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ኢትዮጵያን እንዲጉበኙ ጋበዟቸው፡፡ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የኖቤል የሰላም ተሸላሚ በመሆናቸው የደስታ መግለጫ ማስተላለፋቸውን ከእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

Via EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"የመገናኛ ብዙሃን ሚዛናዊ ዘገባ እያቀረቡ አይደለም!" አቶ ዑመር አብዲ

የሶማሌ ክልል መንግሥት ከአፋር ክልል በሚነሱ ታጣቂዎች ጥቃት ካለፈው ታኅሣሥ ጀምሮ ከ270 በላይ ንጹሀን ዜጎች ተገድለዋል አለ። ባለፈው ቅዳሜ ተከስቶ በነበረው ግጭትም ከ30 በላይ የሶማሌ ክልል ተወላጆች በሦሥት ቦታዎች መገደላቸውን ገልጿል። የሲቲ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ዑመር አብዲ የመገናኛ ብዙሃን ሚዛናዊ ዘገባ እያቀረቡ አይደለም ሲሉ ወቅሰዋል።

Via VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ምርጫ2012

በ2012 ሀገራዊ ምርጫ የሴቶች ፖለቲካዊ ተሳትፎ ዙሪያ የሚመክር የአንድ ቀን ጉባኤ ነገ በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ ሴቶች ማህበራት ቅንጅት አስታወቀ።

Dimo-Finland ከተባለ አለምአቀፍ ተቋም ጋር በመተባበር የተዘጋጀው ይህ ጉባኤ ሴቶች በተመራጭነት እንዲወዳደሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሴቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ እያደረጉ ያሉትን ጥረት እና በቀጣይም መሠራት ያለባቸውን ስራዎች ያመላክታል ተብሏል።

Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሳዛኝ ዜና!

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የመጨረሻ አመት የህክምና ተማሪ ከፎቅ ላይ ወድቆ ህይወቱ ማለፉን ዩኒቨርሲቲው አስታወቀ። ተማሪ አሌክሳንደር ተስፋዬ የqualification ፈተና ለመፈተን በዝግጅት ላይ በነበረበት ወቅት ነው፤ በቀን 02/02/2012 ዓ.ም ምሽት ላይ ከፎቅ ላይ ወድቆ ህይወቱ እንዳለፈ የተገለፀው።

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሀዘን መግለጫ፦

የሀዘን መግለጫ!

ተማሪ አሌክሳንደር ተስፋዬ በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ከ 2004 ዓ.ም ጀምሮ ተማሪ ሲሆን፤ በአሁኑ ወቅት የመጨረሻ ዓመት የህክምና ተማሪ ሆኖ የqualification ፈተና ለመፈተን በዝግጅት ላይ በነበረበት ወቅት፤ ማለትም በቀን 02/02/2012 ዓ.ም ምሽት ላይ በደረሰበት ከፎቅ ላይ የመውደቅ ድንገተኛ አደጋ ወደ ሆስፒታል ተወስዶ ሕይወቱን ለማትረፍ ከፍተኛ ርብርብ ቢደረግም ሳይሳካ ቀርቶ በቀን 03/02/2012 ዓ.ም ላይ ሕይወቱ ሊያልፍ ችሏል፡፡ ሃዋሳ ዩኒቨርሲቲም በተማሪ አሌክሳንደር ተስፋየ ድንገተኛ ሞት ምክንያት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን እየገለፀ ለቤተሰቦቹና ዘመድ ወዳጆቹ መጽናናትን ይመኛል።

ሀዋሳ ዩንቨርስቲ

@tsegabwolde @tikvahethiopia