TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
Audio
AudioLab
ያዳምጡ⬆️

ልዩ መረጃ ከኤልያስ ጋር
በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8


ፌስቡክ በአፍሪካ ሀገራት ስለጀመረው የሦስተኛ ወገን መረጃ ማጥሪያ ስርዓቱን ሊጀምር ነው፡፡ በተያያዘ ዜናም በቅርቡ ተካሂዶ በነበረው የጣና ፎረም ላይ ይህንን ጉዳይ አስመልክቶ ስለተካሄደው ፎረም ተዳሷል፡፡ ያዳምጡ!

ልዩ መረጃ ከኤልያስ ጋር
በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8


@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
AudioLab
ያዳምጡ⬆️

ልዩ መረጃ ከኤልያስ ጋር
በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8

#የፌደራል_ጠቅላይ_አቃቤ_ህግ የኮምኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ዝናቡ ቱሉ እንዳረጋገጡት ህገውጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎችን እስከሞት የሚያስቀጣ ህግ እየተረቀቀ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ልዩ መረጃ ከኤልያስ ጋር
በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8


@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
AudioLab
ያዳምጡ⬆️

ልዩ መረጃ ከኤልያስ ጋር
በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8


ፌስቡክ በአፍሪካ ሀገራት ስለጀመረው የሦስተኛ ወገን መረጃ ማጥሪያ ስርዓቱን ሊጀምር ነው፡፡ በተያያዘ ዜናም በቅርቡ ተካሂዶ በነበረው የጣና ፎረም ላይ ይህንን ጉዳይ አስመልክቶ ስለተካሄደው ፎረም ተዳሷል፡፡ ያዳምጡ!

ልዩ መረጃ ከኤልያስ ጋር
በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8


@tsegabwolde @tikvahethiopia
#AddisAbeba

የዓድዋ ማዕከል ግንባታ የማስመጀር ስነ ስርዓት በዛሬው እለት በይፋ ተካሂዷል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ የዓድዋ ማዕከል ግንባታን በይፋ ማስጀመራቸውን የከንቲባ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

የዓድዋ ማዕከል ግንባታ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ከሚድሮክ ተመላሽ በተደረገው ቦታ ላይ የሚገነባ መሆኑንም ጽህፈት ቤቱ ገልጿል።
የዓድዋ ማዕከል በውስጡም ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች በጥቂቱ ፦

• የአድዋ ሙዚየም
• ከ2 ሺህ ሰው በላይ የሚይዝ የዓድዋ አዳራሽ
• እያንዳንዳቸው 400 ሰው የመያዝ አቅም ያላቸው ሶስት(3) አዳራሾች
• የሲኒማ አዳራሽ
• ቤተ-መፅሐፍ
• የስፖርት ማዘውተርያዎች እና ጂሞች
• የህፃናት መጫወቻ እና የማቆያ ስፍራ
• የጌጣጌጥ መደብሮች
• የቤተ-ስዕል ማዕከላት
• ዘመናዊ የባስ እና የታክሲ ማቆሚያ
• ከ600 መቶ መኪና በላይ የመያዝ አቅም ያለው ዘመናዊ የመኪና ማቆሚያ
• ካፌዎች እና የምግብ አገልግሎት መስጫ ተቋማት
• ለንባብ አገልግሎት የሚሆኑ የአረንጓዴ ስፍራ እና የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡

ማዕከሉ የውስጥም ሆነ የውጪ ይዞታው ለመዝናኛ የተመቸ ሲሆን፥ በውስጡም "ሁሉም ከዚህ ይጀምራል!" የሚል የአዲስ አበባ ከተማ 'ዜሮ ኪሎ ሜትር' በአንድ ኪ.ግ ወርቅ ምልክት ይቀመጥበታል፡፡ በፕሮጀክት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ ኢንጂነር ታከለ ኡማ፥ የትውልድ አሻራ፣ የአንድነትና የአሸናፊነት ተምሳሌት የሆነውን የዓደዋ ማዕከልን ማስገንባት የሚያኮራውና ለፍፃሜውም የከተማ አስተዳደሩ ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል ብለዋል።

Via FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
PHOTO: በዛሬው ዕለት የኢፌዴሪ አየር ኃይል አካዳሚ በበረራና በቴክኒሺያንነት ያሰለጠናቸውን 166 ሰልጣኞችን አስመርቋል። ከተመራቂዎቹ መካከል 17ቱ አብራሪዎች ሲሆኑ 149 የሚሆኑት ደግሞ የበረራ ቴክኒሺያን ናቸው፡፡

Via EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢ/ር ታከለ ከስልጣናቸው ሊነሱ ነው...

አዲስ አበባ ከተማን በምክትል ከንቲባነት እየመሩ የሚገኙት ኢንጂነር ታከለ ኡማ ከስልጣናቸው ሊነሱ እንደሆነ ተሰማ። ስለ ጉዳዩ እውነትነት ያረጋገጡት ምንጮች በስራቸው ላይ ለመቆየት ፍላጎት ቢኖራቸውም ኢንጂነሩ በአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባነት ሊቆዩ የሚችሉት ቢበዛ አንድ ሳምንት እንደሆነ ተናግረዋል። ኢንጂነር ታከለ ኡማ ሊነሱ የተፈለገበት ግልፅ ምክንያት የለም ቢባልም ምናልባት የፓርቲያቸው ውሳኔ ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል። በሌላ በኩል ኢንጂነር ታከልን የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ሊተኳቸው እንደሚችሉ ጭምጭምታዎች ተሰምተዋል።

Via Elias Meseret/Associated Press/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የፕሬዘዳንት ቅጥር ማስታወቂያ!

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ስራ አመራር ቦርድ በመንግስት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የስራ አመራርና ኃላፊዎች ምርጫና ሹመት ምደባ ለመደንገግ በወጣ መመሪያ ቁጥር 002/2011 መሰረት የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንት አወዳድሮ ለመመደብ ይፈልጋል።

የመወዳደሪያ መስፈርቶች👇
http://www.wku.edu.et/index.php/en/2013-11-08-03-53-43/321-2019-10-15-08-20-39

Via Yohannes G./TIKVAH ETH FAMILY/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Awlo Media?

አውሎ ሚዲያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በማህበራዊ ሚዲያው ላይ ከፍተኛ የሆነ እንቅስቃሴ እያደረገ የሚገኝ መረጃዎችን ለህዝብ እያደረሰ የሚገኝ በጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው የሚመራ ሚዲያ ነው።

ጋዜጠኛ በቃሉ በሚሰራቸው ስራዎች ገለልተኛ ነው፤ ለየትኛውም አካል ወገንተኛ ባለመሆን እውነተኛ መረጃዎችን እያጣራ በማቅረብ በተለይም በዩትዩብ እና ፌስቡክ ላይ በስፋት ይንቀሳቀሳል። እስካሁን ጋዜጠኛ በቃሉ በAwlo Media ላይ፦

•የቀድሞ የህውሓት ታጋይ አቦይ ስብሃት ነጋ
•አትሌት ኃይሌ ገ/ስላሴ
•የአብን ሊቀመንበር ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ
•ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ
•የሳልሳይ ወያነ ትግራይ መስራች አባል ወልደግዮርጊስ ገ/ህይወት
•ዓባይ ትግራይ ባይቶና ፓርቲ መስራች ኪዳነ አመነ
•አክቲቪስት ዳንኤል ብርሃነ
•አርክቴክት እና ደራሲ ሚካኤል ሽፈራውን ቃለመጠይቅ አድርጓል።

የምታስታውሱ ከሆነም ጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው ከዚህ ቀደም የመጀመሪያ የአቦይ ስብሃት ነጋ ቃለመጠይቅን እናተ የቤተሰቦቻችን አባላት እንድትመለከቱት ጋብዟችሁ ነበር።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Awlo Media

ከሳምንት በፊት በኢ/ር ታከለ ኡማ እና ኢ/ር እንዳወቅ አብጤ ከኃላፊነታቸው መነሳት ዙሪያ አውሎ ሚዲያ ታማኝ ምንጮቹን ጠቅሶ በሰበር ዜና ለህዝብ ይፋ አድርጎ ነበር። እንደ አውሎ ሚዲያ ከሆነ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ብቻ ሳይሆኑ ኢንጂነር እንዳወቅ አብጤም ከኃላፊነታቸው ይነሳሉ። ምክትል ከንቲባ ኢ/ር ታከለ እና ኢ/ር እንዳወቅ ለትምህርት ወደ ቻይና ሊላኩ እንደሆነ ነው አውሎ ሚዲያ ከሳምንት በፊት ምጮቹን ጠቅሶ የዘገበው።

Via Awlo Media/ጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው/

TIKVAH-ETHIOPIA: በከተማ አስተዳደሩ ውስጥ ከሚሰሩ ቤተሰቦቹ ስለሚሰራጩት መረጃዎች ማረጋገጫዎች ከተላኩልን እንዲሁም በዚህ ጉዳይ ከተማ አስተዳደሩ የሚሰጠው ምላሽ ካለ ተከታትለን እናጋራለን!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Ida'amuu,
Gurmuudhaan Gara Badhaadhinaatti!
መደመር፣ በህብር ወደ ብልጽግና!
Onkoloolessa 8/2012 Godinaalee Oromiyaa 20 fi Magaalota gurguddoo 19tti ni eebbeifama!
ጥቅምት 8/2012 በኦሮሚያ 20 ዞኖች እና 19 ከተሞች ይመረቃል!

Via Addisu Arega

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#WMO | የዓለም የሜቲዮሮሎጂ ድርጅት(WMO) የአፍሪካ ጽህፈት ቤቱን በአዲስ አበባ ሊከፍት መሆኑን ተገለጸ። ይህ የተገለጸው የትራንስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ህይወት ሞሲሳ ሴክረተሪ ጀነራል ፒተሪ ታላሰን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት ነው።

Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
በምስራቅ ጉጂ ስድስት ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ገለፁ!

#TIKVAH_ETHIOPIA
#ETHIOPIA

ባለፈው ቅዳሜ በቦረናና በምስራቅ ጉጂ ስድስት ሰዎች በኦሮሞ ነፃነት ግንባር ተዋጊዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ራድዮ ጣቢያ ተናገሩ። ከመካከላቸው የፀጥታ ጠባቂ ሚሊሺያዎችና ነዋሪዎች እንዳሉባቸው የአካባቢው አስተዳደር ገልጿል።

Via VOA AMHARIC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በድጋሚ የወጣ የህዝበ ውሳኔ አስፈጻሚዎች ምልመላ ማስታወቂያ!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በመጪው ህዳር 2012 ዓ.ም ለሚያካሂደው የሲዳማ የክልልነት የመደራጀት ጥያቄ ህዝበ ውሳኔ 5500 ( አምስት ሺህ አምስት መቶ) የሚሆኑ የህዝበ ውሳኔ አስፈጻሚዎችን በበጎ ፍቃድ አበል ክፍያ ከአንድ ወር ላልበለጠ ጊዜ ለማሰራት ማስታወቂያ ማውጣቱ ይታወሳል፡፡ነገር ግን በቂ የሆኑ አመልካቾች ስላልተገኙ ይህንን ማስታወቂያ በድጋሚ ለማውጣት ተገዷል፡፡

•የስራው ሁኔታ- የህዝበ ውሳኔ አስፈጻሚ
የሚፈለገው ሰው ብዛት - 5500 (አምስት ሺህ አምስት መቶ)

•የማመልከቻ ጊዜ- ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ተፈላጊው ቁጥር እስከሚሟላ ድረስ

•የማመልከቻ ቦታ- ንፋስ ስልክ ቡና ቦርድ ፊትለፊት በሚገኘው የምርጫ ቦርድ ማሰልጠኛ ማእከል

አመልካቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች፦

• የማንኛውም የፓለቲካ ፓርቲ አባል ያልሆነ/ያልሆነች
• በትምህርት ዝግጅታቸው በማንኛውም የትምህርት መስክ የመጀመሪያ ዲግሪ ያላት/ ያለው
• እድሜ ከ20- 45 አመት የሆነች/የሆነ
• በገጠር ቀበሌዎች ተንቀሳቅሰው መስራት የሚችሉ
• የስራ ልምድ አይጠይቅም- ሆኖም በምርጫ አፈጻጸም ዙሪያ ወይም በተለያየ ማህበራዊ አገልግሎቶች የተሳተፉ አመልካቶች ቅድሚያ ይሰጣቸዋል፡፡

ቦርዱ በስራ የሚሳልፉትን ጊዜ የቀን አበል የሚከፍል እና ስልጠና የሚሰጥ ሲሆን በተጨማሪም በህዝበ ውሳኔው ላይ በበጎ ፈቃደኝነት ለተሳተፉ አስፈጻሚዎች የተሳትፎና የእውቅና ምስክር ወረቀት ይሰጣል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
ቡርጂ ልዩ ወረዳ በተከሰተ ግጭት ቢያንስ 20 ሰዎች መገደላቸውን የአከባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል!

#TIKVAH_ETHIOPIA
ቡርጂ ልዩ ወረዳ በተከሰተ ግጭት ቢያንስ 20 ሰዎች ተገደሉ!

ከፈረሰው የሰገን አከባቢ ሕዝቦች ዞንና ከመዋቅር ጥያቄ ጋር በተገናኘ በደቡብ ክልል ቡርጂ ልዩ ወረዳ በተከሰተ ግጭት ቢያንስ 20 ሰዎች መገደላቸውን የአከባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ። ግጭቱ የተፈጠረው በወረዳ በነያ በተሰኘ ቀበሌ ገበሬ ማኅበር ሲሆን መንስኤው የመዋቅር ጥያቄ መሆኑን ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ ተናግረዋል።

Via ቪኦኤ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ችሎት

በኢሉአባቦር ዞን ሁሩሙ ወረዳ ህገ-ወጥ የጦር መሳርያ ሲያዘዋውር የተገኘ ግለሰብ ፍርድ ቤት ቀርቦ በእስራትና በገንዘብ ተቀጣ። የወረዳው አቃቢ ህግ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ብዙአየሁ ምትኩ እንዳሉት ሰይድ አደም የተባለው ግለሰብ ላይ ቅጣቱ የተወሰደው የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ ሶስት 00610 አዲስ አበባ በሆነ መለስተኛ አውቶብስ ከመቱ ወደ አዲስ አበባ የጦር መሳሪያዎችን ደብቆ ለማሳለፍ ሲሞክር በመያዙ ነው።

በትላንትናው እለት በሁሩሙ ኬላ በተደረገው ፍተሻ ከበርበሬ ጋር በጆንያ ተደብቀው የተገኙት የጦር መሳሪያዎች ስምንት የተለያዩ ጠመንጃዎችና 82 የሽጉጥና የጠመንጃ ጥይቶች መሆናቸውን ገልጸው ግለሰቡም ወዲያውኑ ለፍርድ እንዲቀርብ መደረጉን አስረድተዋል። ጉዳዩን የተመለከተው የወረዳው ፍርድ ቤትም የክስ መዝገቡን መርምሮ በሁለት አመት ከስድስት ወር እስራትና በ3ሺህ ብር እንዲቀጣ መወሰኑን ገልጸዋል።

Via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#AAiT #NOKIA #AASTU

#NOKIA | ኖኪያ የ4G እና 5G የቴሌ ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት በኢትዮጵያ ለመዘርጋት መዘጋጀቱን ገለፀ። ኩባንያው ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና የአዲስ አበባ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ጋር የዲጂታል ክህሎትንና የፈጠራ አቅምን ማጎልበት ዙሪያ በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራርሟል።

ፊርማውን የአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ደረጀ እንግዳ እና የአዲስ አበባ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ኢኒስቲትዩትን በመወከል ዶክተር ኢንጂነር ኢሳያስ ገብረዮሀንሰ እንዲሁም በመካከለኛው ምስራቅና ምዕራብ አፍሪካ የኖኪያ ተጠሪ ዳንኤል ጃገር ፈርመውታል።

ስምምነቱ ኩባንያው ለሁለቱ ዩኒቨርሲቲዎች በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መስክ አለም የደረሰበትን አሰራር እና የቴክኖሎጂ ገበያውን ፍላጎት መሰረት ያደረገ ዘመናዊ የትምህርት እና ስልጠና ፕሮግራሞችንና የልምድ ልውውጦችን ማዘጋጀትን እንደሚያካትት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታውቋል።

Via FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#WolaitaSodo #Dessie

በወላይታ ሶዶና በደሴ ከተማ የታየው የመጠጥ ውሃ ጥራት በሌሎችም ከተሞች ሊታይ እንደሚገባ የውሃ ልማት ኮሚሽን አስታወቀ። የወላይታ ሶዶ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ለህብረተሰቡ የሚያሰራጨውን ውሃ በኢትዮጵያ ተስማሚነትና ምዘና ድርጅት ተመርምሮ የኢትዮጵያ የመጠጥ ውሃ የተቀመጠለት መስፈርት በማሟላቱ የ ሲኢኤስ - 58 አይሶ ፡ 2019 (CES-58 ISO :2019) ጥራት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት አገኘ። የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ዶክተር በሻህ ሞገሴ የሰርተፍኬት ማግኘቱን ምክንያት በማድረግ ትናንትና በብሉ ስካይ ሆቴል የዕውቅና አሰጣጥ ፕሮግራም ላይ እንደገለፁት በሀገራችን በሁለቱ ከተሞች የታየው የውሃ ጥራት በኢትዮጵያ ተስማሚነትና ምዘና ድርጅት ተመርምሮ አልፏል፤ ይህ ተሞክሮ ሌሎች የሀገራችን ከተሞች ሊተገብሩት ይገባል ብለዋል።

Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢትዮ-ቴሌኮም 47 ድርጅቶች ላይ እርምጃ ወሰደ!

ከሞባይል ተጠቃሚው ፈቃድና ፍላጎት ውጪ አጭር የጽሑፍ መልዕክትን በመላክ ሲያማርሩ ነበር የተባሉ 47 ድርጅቶች ላይ እርምጃ መውሰዱን ኢትዮ-ቴሌኮም አስታወቀ፡፡

ኩባንያው የአጭር መልዕክት አገልግሎት ላይ ደንበኞች ለረጅም ጊዜ ቅሬታ ሲያቀርቡ እንደነበር ገልጿል፡፡ ''አጭር ቁጥር በመጠቀም የሚሰጡ የመልዕክት አገልግሎቶች በህብረተሰቡ ፈቃድ ላይ ብቻ የተመሰረቱ መሆን አለባቸው'' ያለው ኢትዮ ቴሌኮም ያለፈቃድ ይልኩ የነበሩትን ድርጅቶች መዝጋቱን አክሏል፡፡

በዐጭር የፅሑፍ አገልግሎት ጠቃሚ መልዕክቶች እንደሚተላፉም እረዳለሁ ያለው መንግሥታዊው ተቋም አገልግሎቶቹን በህብረተሰቡ ፈቃድ ላይ ብቻ ተመስርተው እንዲሰጡ ቁጥጥር እያደረግሁ ነው ብሏል፡፡

በአሁኑ ወቅት 310 ድርጅቶች ከኢትዮ-ቴሌኮም ጋር በመተባበር በአጭር ቁጥር የጽሁፍ መልዕክት አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙ የኢዜአ ዘገባ ያስረዳል፡፡

ምንጭ፦ አሃዱ ሬድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የሶማሊያ ጦር #በሬይዳብ መንደር ባደረገው ኦፕሬሽን በአልሸባብ ስር የነበሩ 300 ፍየሎችን፣ በጎችን እና የጦር መሳሪያዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የጦሩ የሬዲዮ ጣቢያ አስታውቋል። አልሸባብ እንስሳቱን ከአካባቢው ነዋሪዎች በኃይል አስገድዶ የወሰዳቸው እንደነበሩም ተነግሯል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia