TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
ጎንደር ከተማ የተያዘው ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ከሱዳን በመተማ በኩል አደርጎ የገባ እንደሆነ የጎንደር ከተማ አስተዳደር ኮሚኒኬሽ ገልጿል።

የተያዘው ህገ ወጥ መሳሪያ፦

•ከ2000 በላይ ሽጉጥና
•ከ70 በላይ ክላሽ ጠበንጃ ነው።

ህገወጥ ከጦር መሳሪያው በነዳጅ ውስጥ ተይዞ ሲጓዝ በነበረ ቦቲ መኪና ውስጥ ነው ጎንደር ከተማ ላይ በተደረገ ፍተሻ የተያዘው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#DOHA

1,500 ሜትር የሴቶች ዉድድር ተጀምሯል!!

መልካም ዕድል!!!

@tikvahethsport
እንኳን ደስ አለን!

በ1,500 ሜትር ሴቶች ኢትዮጵያ በጉዳፍ ጸጋዬ የነሀስ ሜዳልያን ማግኘት ችለናል።

@tikvahethsport
#Irreechaa2019 ሆራ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል!!

TIKVAH ETHIOPIA FAMILIES

PHOTO: HANI, FUAD & DIGO

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሴቶች 5000 ሜትር የፍፃሜ ውድድር በቀጥታ በዋልታ ቴሌቪዥን ተከታተሉ! #DOHA

መልካም ዕድል ለሀገራችን ልጆች!

Join @tikvahethsport

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኬንያዊያን 1 እኛ 2 ፧ ጀርመናዊ አትሌት 3ኛ ጨርሰዋል። ኢትዮጵያዊያኑ አትሌቶችቻን ፋንቱ ወርቁ :ጸሃይ ገመቹ : ሃዊ ፈይሳ ከ4ኛ አስከ 10ኛ ደረጃ ጨርሰዋል።

Via Ethio Kickoff
@tsegabwolde @tikvahethioia
የኢትዮጵያ መንግስት በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የውሃ አሞላል እና አለቃቀቅ ዙሪያ የተጀመረውን የሶስትዮሽ ቴክኒካዊ ምክክር ለማስቀጠል ቁርጠኛ ነው!

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-05-4
#EGYPT

የግብፅ ፕረዜደንት ቢሮ በካርቱም ሲካሄድ የነበረው የኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብፅ የውሀ ሚኒስትሮች ውይይት ካለ ውጤት መጠናቀቁን ተከትሎ መግለጫ አውጥቶ ነበር፤ ባወጣው መግለጫም አሜሪካ በህዳሴ ግድብ ዙርያ የማደራደር ሚና እንድትጫወት እንደሚፈልግ ገልጿል።

Via Elias Meseret
@tsegabwolde @tikvahethioia
"የግብጽ መንግስት ሶስተኛ ወገን በጉዳዩ ጣልቃ እንዲገባ እያቀረበ ያለው ሃሳብ በሶስቱ አገራት የትብብር መድረክ የታየውን አበረታች ሂደት የሚያጣጥል እና ሶስቱም አገራት በመጋቢት 2007 ዓ.ም. የፈረሙትን የመርሆዎች መግለጫ ስምምነት የሚጥስ ተግባር ነው፡፡ የሶስተኛ ወገን ጣልቃ-ገብነት ኢትዮጵያ እና ሱዳን የማይቀበሉት እና ተገቢ ያልሆነ፤ በአገራቱ መካከል ያለውን ዘላቂ ትብብር የሚጎዳ፤ ለውይይት ያለውን በቂ እድል ወደጎን የሚያደርግ እና ገንቢ የሆነውን የውይይት መንፈስ የሚያደፈርስ ነው፡፡" የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#PMOEthiopia

The Government of the Federal Democratic Republic of Ethiopia commends the Water Affairs Ministers of Ethiopia, Sudan, and Egypt for convening in Khartoum to continue with the trilateral dialogue on the filling and operation of Great Ethiopian Renaissance Dam.

Ethiopia reiterates rights of all the 11 basin countries of the Nile to utilize Nile waters based on principles of equitable utilization & causing of no significant harm, which underlines the right of Ethiopia to develop its water resources to meet dev’t needs of its people.

The Government of Ethiopia will reinforce its effort to make the ongoing trilateral dialogue a success. It also expects a similar commitment from the two downstream countries, Egypt and Sudan. Ethiopia stands ready to resolve any differences and outstanding concerns by consultation among the three countries.

#PMOEthiopia

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#EliasMelka

የሙዚቃ ሰው ኤልያስ መልካ የቀብር ስነ ስርዓት ሰኞ፣ መስከረም 26 ቀን 2012 ዓ/ም ከቀኑ 9:00 ሰዓት በጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤተ ክርስቲያን ወዳጅ ዘመድና አድናቂዎቹ በተገኙበት ይፈፀማል።

ዛሬ ከሰዓት በፋና ኤፍ ኤም 98.1 የከሀ እስከ ፐ ፕሮግራም ላይ በቀጥታ ቆይታ ያደረጉት ሙዚቀኛ ዳዊት ይፍሩ እና ሰርፀ ፍሬስብሃት እንዳስታወቁት፣ ከቀብር ስነ-ስርዓቱ አስቀድሞ ሙዚቃን በተማረበት ያሬድ የሙዚቃ ት/ቤት አሊያም በሚሊንየም አዳራሽ አሸኛኘት ይደረግለታል። ይህን የሚያስፈጽም ኮሚቴ ተዋቅሮም በስራ ላይ ይገኛል።

ምንጭ፦ ከሀ እስከ ፐ የሬድዮ ፕሮግራም
@tsegabwolde @tikvahethiopia