TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#GONDAR

በወቅታዊ ችግሮች ምክንያት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የ2012 የትምህርት ዘመን ተማሪዎች መግቢያ ቀን ተራዝሟል ሲል ዩኒቨርሲቲው አስታውቋል። በዚህም የነባር ተማሪዎች መግቢያ ቀናት ወደ መስከረም 29 እና 30 / 2012 ዓ.ም የተራዘመ ሲሆን የአዲስ ገቢ ተማሪዎች መግቢያ ቀን ደግሞ ወደ ጥቅምት 6 እና 7 ቀን 2012 ዓ.ም እንደተራዘመ ዩኒቨርሲቲው በፌስቡክ ገፁ ይፋ አድርጓል።

#ሼር #share

@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ፕሬዘዳንት ሳህለወርቅ⬆️ በሚሊኒየም አዳራሽ እየተካሄደ በሚገኘው 28ኛው ሀገር አቀፍ የአረጋዊያን ቀን የኢፌዴሪ ፕሬዘዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ተገኝተዋል። PHOTO : TIKVAH-ETHIOPIA @tsegabwolde @tikvahethiopia
"የቃልኪዳን የልጆች ጤና እንክብካቤ በጎ አድራጎት ማህበር መስራቾችና አባላት ዛሬ በሚሊኒየም አዳራሽ በመገኘት ከአረጋዊያን አባቶቻችንና እናቶቻችን ምርቃት ተቀብለናል፡፡ ህጻናት ምግብና መጠለያ ብቻ ሳይሆን ጤናማ ኑሮም ያስፈልጋቸዋል ብለን ስለምናምን በሞያችን በጎ ፈቃድ አገልግሎት እየሰጠን እንገኛለን፡፡"

#TIKVAH_ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሰራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ የአረጋውያንን እግር ዝቅ ብለው በማጠብ ክብር ሰጥተዋል፡፡

PHOTO : EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የቤተ መንግስት እድሳት ሀሙስ መስከረም 29 2012 ዓ.ም ተጠናቆ ለጎብኚዎች ክፍት ይደረጋል!

የቤተ መንግስት እድሳት በቀጣይ ሳምንት ማለትም ሀሙስ መስከረም 29 2012 ዓ.ም ተጠናቆ ለጎብኚዎች ክፍት እንደሚደረገ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ገለፁ።

አርብ መስከረም 30 2012 ዓ.ም የመከላከያ ሰራዊት እና የፌዴራል ፖሊስ አባላት ቤተ መንግስቱን እንደሚጎበኙ ዶ/ር አብይ አስታውቀዋል።

ቅዳሜ እና እሁድ ደግሞ በእድሜ ታላላቅ ዜጎች እና የጎዳና ተዳዳሪዎች ቤተ መንግስቱን እንደሚጎበኙ ገልፀዋል። ከሰኞ ማለትም ከጥቅምት 3 2012 ጅምሮ ማንኛውም ዜጋ 200 ብር በመክፈል ቤተ መንግስቱን መጎብኘት እንደሚችልም ነው ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ የገለፁት።

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Mayor Office of Addis Abeba

ከዩኒፎርም ስርጭት ጋር በተያያዘ መጠነኛ ቅሬታዎች እየቀረቡልን ይገኛሉ። የከተማ አስተዳደሩ ዋነኛ አላማው ተማሪዎች በተለያዩ ችግሮች ምክንያት ትምህርታቸውን እንዳያቋርጡ ማድረግና እንዲሁም ወላጆችን ከጭንቀት ለማዳን ነው።የከተማ አስተዳደሩ የየትኛውንም ሀይማኖት አስተምህሮትም ይሁን ስርአት ያከብራል።ለተማሪዎች በነጻ የዩኒፎርም ስናዘጋጅም ይህን ባገናዘበ መልኩ ነው።

ነገር ግን አሁን እየተነሱ ያሉ ጥያቄዎች በስርጭት ወቅት የተፈጠሩ በመሆናቸው መስተካከል ይችላሉ። ከዩኒፎርም አቅራቢ ድርጅቶች ጋር ስምምነት ያለን በመሆኑ ለተማሪዎች በታደሉ ዩኒፎርሞች ላይ ቅሬታ ያለው ማንኛውም ግለሰብ እንዲያሳውቅና አፋጣኝ ማስተካከያ የምንወስድ መሆኑን እናስታውቃለን።

Mayor Office of Addis Abeba

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#SHEGER

በቻይና መንግሥት ድጋፍ የሚገነባው የአዲስ አበባ የወንዝ ዳርቻ አረንጓዴ ልማት ፕሮጀክት ዛሬ በይፋ ተጀምሯል። በፕሮጀክቱ ማስጀመሪያ ስነ ስርዓት ላይም የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እና የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች እና የቻይና መንግስት ተወካዮች ተገኝተው ነበር።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በመስቀል ደመራ በዓል አከባበር 55 ሰዎች መታሰራቸውን የአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት አስታወቀ! በዛሬው የመስቀል ደመራ በአል አከባበር ላይ 55 የበዓሉ ታዳሚዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት ህዝብ ግንኙነት እና ጉዳይ አስፈፃሚ መላከ ሕይወት አባ ወልደየሱስ ሰይፉ ለቢቢሲ ገለፁ። መላከ ህይወት አባ ወልደየሱስ እንደገለፁት 33ቱ ምእመናን…
የደመራ ዕለት ከታሰሩ 55 ግለሰቦች ውስጥ የተወሰኑት ተለቀቁ!

የደመራ ዕለት በአዲስ አበባ ከታሰሩት 55 ግለሰቦች መካከል መልዕክት ያለበት ቲሸርት በመልበሳቸው የታሰሩት መፈታታቸው ተገለፀ፡፡ ከታሰሩት ውስጥ የተወሰኑት ‹‹በቤተክርስቲን ላይ የሚደርሰው ጥቃት ይቁም›› የሚል ፅሑፍ ያለበት ቲሸርት በመልበሳቸው የታሰሩ እንደነበሩና እነዚህም እንዲፈቱ ማስደረጉን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስቲያን የአዲስ አበባ አገረ ስብከት ለአሐዱ ቴሌቪዥን ገልጿል፡፡ ይሁን እንጂ ቁጥራቸውን በግልፅ ይህ ነው አላለም፡፡ በአንጻሩ ‹‹ስለት መሳሪያ ይዛችኋል›› በሚል የተያዙ መኖራቸውን በመጠቆም ጉዳዩ በፖሊስ መያዙንና አለመፈታታቸውን አገረ ስብከቱ አክሏል፡፡

ምንጭ፦ አሃዱ ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ📸የኢትዮጵያ ሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ 11ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን እያካሄደ ነው። #ETHIOPIA #FBC

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኤካ ኮተቤ አጠቃላይ ሆስፒታል እና የአእምሮ ጤና ኢንስቲትዩት ህንጻ ተመረቀ።የምርምር ኢንስቲትዩት ተመረቀ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የኤካ ኮተቤ አጠቃላይ ሆስፒታል እና የኢትዮጵያ የአእምሮ ጤና ምርመር ኢንስቲትዩት ህንፃን በይፋ መርቀው ከፍተዋል።

ምንጭ- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀዋሳ ከተማ በመጪው ጥቅምት ወር የባለኮከብ ሆቴሎች መድረክን ታስተናግዳለች!

የሀዋሳ ከተማ ሙሉ ለሙሉ ወደቀደመው ሰላምና መረጋጋቷ መመለሷንና በአሁኑ ወቅት ያለምንም ስጋት የሚሰሩባትና የሚንቀሳቀሱባት ከተማ መሆኗን አዲሱ የከተማዋ ምክትል ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ ገለፁ። በመጪው ጥቅምት መጀመሪያ ከ700 በላይ ባለድርሻ አካላት የሚሳተፉበት የባለ ኮከብ ሆቴሎች መድረክን እንደምታስተናግድም ገልፀዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-01-2

@tsegabwolde @tikvahethiopia
‹‹ሀዋሳ ከተማ አሁን ያለምንም #ስጋት የሚሰሩባትና የሚንቀሳቀሱባት ከተማ ሆናለች። ቱሪስቶችም ሆኑ ለተለያዩ ስራዎች ወደ ከተማዋ መምጣት የሚፈልጉ ሁሉ ያለምንም ስጋት ወደ ከተማዋ መምጣት ይችላሉ። በተለይ ኢንቨስት ለማድረግ የሚመጡ አካላትን ከተማ አስተዳደሩ ከመቼውም ጊዜ በተሻለ ለማገልገል ዝግጁ ነው።›› የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ጥራቱ በየነ #HAWASSA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#GONDAR በአሁን ሰዓት በጎንደር ከተማ ተደጋጋሚ የተኩስ ድምፅ እየሰሙ እንደሚገኙ ነገር ግን ምክንያቱ ምን እንደሆነ እንደማያውቁ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባል የሆኑ የጎንደር ነዋሪዎች እና የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የጤና ተማሪዎች ጠቁመዋል።

በከተማይቱ ያለውን እና የተፈጠረውን ጉዳይ አጣርተን እናሳውቃለን!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#CPJ

በግብጽ በቅርቡ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ 6 ጋዜጠኞች ለእስር መዳረጋቸውን ሲፒጄ አስታውቋል፡፡ ጋዜጠኞች የታሰሩት በግብጽ የተለያዩ ከተሞች የአብዱል ፋታህ አል ሲሲን መንግሥት በመቃወም በርካታ ግብጻውያን አደባባይ መውጣታቸውን የሚያሳይ ዘገባ አሰራጭተዋል በሚል ነው፡፡

ሲፒጂ የግብጽ ባለስልጣናት ጋዜጠኛ አላ አብዱልፈታህ ፣ናሰር አብደልሃፌዝ ፣ኢንጊ አብደልወሃብ እና ሌሎች ሶስት ጋዜጠኞች በአስቸኳይ ከእስር እንዲለቀቁ ጠይቋል፡፡ ግብጽ መገናኛ ብዙሃንን እና ጋዜጠኞችን ከማፈን እና ከማሰር ልትቆጠብ ይገባል ሲልም አሳስቧል ሲፒጄ፡፡ መሐመድ አሊ የተባለ ግለሰብ ፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲ ለሚስታቸው እና ለጄኔራሎቻቸው እጅግ ቅንጡ ቪላ ቤቶችን መግዛታቸውን የሚሳይ ቪዲዮ ማሰራጨቱን ተከትሎ ሥልጣናቸውን እንዲለቁ ግብፃውያን እየጠየቁ ነው፡፡

Via አልጀዚራ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢፌዴሪ ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ከዲፕሎማሲ ማህበረሰብ አባላትና ከልማት አጋር ድርጅቶች ጋር በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ዙሪያ እየመከረ ነው። በምክክር መድረኩ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ፣የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደማሪያም እና የተለያዩ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ታድመዋል። ከዚህ ባለፈም የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችና የልማት አጋር ድርጅቶች ተወካዮች በምክክር መድረኩ ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ።

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የወልድያ-ቆቦ መንገድ በደለል ምክንያት መዘጋቱ ተገለፀ!

ከወልዲያ ቆቦ የሚወስደው ዋና የአስፓልት መንገድ በጎርፍ ምክንያት በተደጋጋሚ የሚዘጋ ነው። ዛሬም በጣለው ዝናብ ከቀላል እስከ ከባድ ተሽከርካሪዎች መንቀሳቀስ አልቻሉም።

መንገዱ የተዘጋው ከተራራማ ቦታዎች የሚወርድ ደለልን መከላከል የሚያስችል ደጋፊ የግንብ አጥር ባለመኖሩ ነው። በኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የኮምቦልቻ መንገድ ዝርጋታ ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ተስፋዬ ‹‹ችግር በተፈጠረባቸው አካባቢዎች የመንገድ ጠረጋ እየተከናወነ ነው፤ በዘላቂነት ችግሩን ለመፍታት ደግሞ ከሰባት ሚሊዮን ብር በላይ በጀት በመመደብ የጎርፍ መከላከያ ደጋፊ ግንብ ይሠራል›› ብለዋል፡፡

የጎርፍ መከላከያ ደጋፊ ግንቡ ከደሴ ዋጃ ያለውን መንገድም ተመሳሳይ ችግር እንዳይገጥመው ታሳቢ ያደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የወልድያ ቆቦ መንገድ ከአዲስ አበባ በደሴ-ወልድያ-ቆቦ-መቀሌ የሚገባ ነው፡፡ መንገዱ ክልል ከክልል የሚያገናኝና በኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የሚተዳደር ነው፡፡

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ERA

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን አዲስ አበባን ከክልል ከተሞች ጋር የሚያገናኙ አራት ፈጣን መንገዶችን ለመገንባት በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ ገለፀ። ፈጣን መንገዶቹ አዲስ አበባን መዳረሻ በማድረግ ደብረ ማርቆስ፣ ጅማ፣ ነቀምት እና ኮምቦልቻ የሚገነቡ ሲሆን አዲስ አበባ አዳማ ፈጣን መንገድን ጨምሮ በከተማዋ እና በፈጣን መንገዶች መገናኛ ቦታዎች ላይ የማሻሻያ ሥራዎችን የሚጨምር ነው።

Via Addis Maleda
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#AddisAbeba

የአዲስ አበባ አስተዳደር በከባድ ጭነት ተሸከርካሪዎች በከተማዋ እንዳይንቀሳቀሱ ጥሎት የነበረውን ማሻሻሉን ካፒታል አስነብቧል፡፡ ማንኛውም የጭነት መጠን ያለው የጭነት ተሸከርካሪዎች ቅዳሜ ቅዳሜ በቀን ብቻ እንዲንቀሳቀሱ ተፈቅዶላቸዋል፡፡ የትራፊክ ፍሰትን ለመቀነስ ሲባል አስተዳደሩ እገዳውን የጣለው በሐምሌ ነበር፡፡

ምንጭ፦ ካፒታል ጋዜጣ/ዋዜማ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢሬቻን በዩኔስኮ ለማስመዝገብ ዝግጅት መጠናቀቁ ተገለፀ!

የኢሬቻ በዓልን ከገዳ ስርዓት ማሳያነት ባለፈ ራሱን ችሎ በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ ሳይንስና ባሕል ድርጅት ለማስመዝገብ ዝግጅት መጠናቀቁን የኦሮሚያ ክልል ባሕልና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ፡፡

ዩኒስኮ በአሉን ለማስመዝገብ የሚያስቀምጣቸውን መስፈርቶች ለሟሟላት የሚያስችሉ ጥናቶች እየተደረጉ መሆኑም ተነግሯል፡፡ በተለይም ባሕሉን በዓለም ዐቀፍ ደረጃ የማስተዋወቅ ስራ ትልቁ ትኩረት የተሰጠው ጉዳይ ነው ተብሏል፡፡

በ2009 ዓ.ም በበዓሉ አከባበር ወቅት የተፈጠረው ግርግርና የሰዎች ሞት በዓሉን በማስተዋወቅ ጥረት ላይ መጥፎ አሻራ አሳርፎ ስለማለፉ ተጠቁሟል፡፡ በዚህ ዓመት በአዲስ አበባ በሚደረገው የበአሉ አከባበር ላይ ከአምስት ሚሊዮን በላይ ታዳሚ እንደሚጠበቅ የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ለአሐዱ ቴሌቪዥን ገልጿል፡፡

ምንጭ፦ አሃዱ ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert

በኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ። በፊርማ ስነ ስርዓቱ ላይ የኢህአዴግና የኦዲፒ ሊቀ መንበር እና የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ፣ የኦዲፒ ምክትል ሊቀ መንበርና የመከላከያ ሚኒስትር አቶ ለማ መገርሳ፣ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ፣ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ሊቀ መንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና፣ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ሊቀ መንበር አቶ ሌንጮ ለታን ጨምሮ በርካታ በኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ተሳትፈዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-01-3

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በሲዳማ ዞን ተከስቶ በነበረው ግጭት ሳቢያ በአለታ ወንዶ ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች ለማቋቋም የተከናወኑ ስራዎች ተጎበኙ!

ባለፈው በጀት ዓመት በደቡብ ክልሉ በነበረው ግጭት ሳቢያ በሲዳማ ዞን አለታ ወንዶ ከተማ ጉዳት የደረሰባቸው አካላትን መልሶ ለማቋቋም የተሰራውን ስራ የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ርስቱ ይርዳው ጎብኝተዋል፡፡

ከተማዋን ወደ ቀድሞ ሰላሟ መመለስ ቢቻልም ተጎጂዎችን መልሶ የማቋቋም ሂደት በተፈለገው መልክ አልተሰራም ብለዋል፡፡ ተጎጅዎችን ለማቋቋም ከተዋቀረው ኮሚቴ ጋርም መክረዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-01-4

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በዛሬው ዕለት የፖሊስ ኃይል በከፈተው ተኩስ አንድ ሰው መገደሉ ተሰምቷል!

ቻይና ዛሬ በኮሙኒስት ፓርቲ ሥር ያለውን ሥርዓትዋን 70ኛ ዓመት ሰፊ ወታደራዊ ትዕይንት አድርጋ ኃይሏን በማሳየት አክብራ ውላለች። በሆንግ ኮንግ ግን በዲሞክራሲ ደጋፊ ሰልፈኞችና በፀጥታ ኃይሎች መካከል ግጭት ተነስቷል።

ቻይና የራስ ገዝ አስተዳደር ከተማ ላይ ቁጥጥር ለማጥበቅ የምታደርገውን ጥረት ሆንግ ኮንግ ያሉት ተቃዋሚዎች እየተገዳደሩ ነው። ሆንግ ኮንግ ከተማ ውስጥ ጃንጥላ የያዙ የተቃውሞ ሰልፈኞች ቤት የተሰሩ የቤንዚን ቦምቦች በፖሊሶች ላይ ወርውረዋል። በከተማይቱ ዋና ዋና አካባቢዎች እሳት አጋይተዋል። ፖሊሶቹ በበኩላቸው ዕምባ አስመጪ ጋዝ ተኩሰውባቸዋል፤ የውሀ ግፊትም ተጠቅመዋል። አንድ ሰው ፖሊስ በከፈተው ተኩስ መገደሉ ተዘግቧል።

ምንጭ፦ ቪኦኤ
@tsegabwolde @tikvahethiopia