TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
የኢህአዴግን ውህደት ህወሓት ፍፅሞ እንደማይቀበለው አቶ ጌታቸው ረዳ ተናገሩ!

የገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ ተዋህዶ አንድ ወጥ ሃገራዊ ፓርቲ ይሆናል እየተባለ የሚነገረውን ጉዳይ ህወሓት ፈጽሞ እንደማይቀበለው የህወሓትና የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ ለቢቢሲ ተናገሩ።

ኢህአዴግ አጋር ድርጅቶችን ጨምሮ በመዋሃድ "የኢትዮጵያ የብልጽግና ፓርቲ" ይሆናል እየተባለ የሚነገረውን ጉዳይ በተመለከተ የግንባሩ መስራችና እስከቅርብ ጊዜ ድረስ የድርጅቱ ቁንጮ ሆኖ የቆየው ህወሓት ያሉ ችግሮች መፍትሄ ሳያገኙ እንደማይቀበለው አቶ ጌታቸው ገልጸዋል።

በስፋት እየተነገረ ስላለው የግንባሩ ውህደት ጉዳይን በተመለከተ የህወሓትን አመለካከት ሲገልጹ "እንደዚህ ዓይነት ለስልጣን ተብሎ የሚፈጠር ውህደት ህወሓት ፈጽሞ አይቀበለውም" ብለዋል።

ጨምረውም "ህወሓት እንደ መርህ የሚከተለው ግለሰቦች ስልጣን ላይ እንዴት ይቆዩ የሚል ሳይሆን፤ አንድን ድርጅት፣ ድርጅት የሚያደርገው ሃሳብን ነው ብሎ ነው የሚያምነው።"

ይፋዊ መግለጫ መውጣቱን እንደማያውቁ የሚናገሩት አቶ ጌታቸው፤ "ይሁን እንጂ እንዲህ አይነት ሩጫ እየተካሄደ መሆኑን አውቃለሁ" ሲሉ ይናገራሉ።

አክለውም ባለፈው በተካሄደው የግንባሩ ስብሰባ ወቅት ውህድ ፓርቲ የመፍጠር ጉዳይ ተነስቶ እንደነበር አስታውሰው "የተባለው ውሁድ ፓርቲ ስለተባለ ብቻ መፈጠር የለበትም" ተብሎ፤ የዓላማ አንድነት በአባል ፓርቲዎች መካከል ተፈጥሯል ወይ የሚል ጥያቄ በህወሓት ተነስቶ እንደነበር ገልጸዋል።

#BBC

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-25-6

@tsegabwolde @tikvahethiopia
•መምህራን ለሁለት ዓመት ደሞዝ አልተከፈላቸውም!
•3.7 ሚሊየን ህጻናት ከትምህርት ገበታ ውጭ የመሆን ስጋት ተደቅኖባቸዋል!


#YEMEN

ጦርነት ባልተለያት የመን ውስጥ የሚገኙ ሁለት ሚሊየን ህፃናት ከትምህርት ገበታ ውጭ መሆናቸውን የተባበሩት መንግሥታት የህፃናት መርጃ ድርጅት(ዩኒሴፍ) አስታውቋል። ከእነዚህም ውስጥ አንድ አራተኛ የሚሆኑት ከፈረንጆቹ 2015 መጋቢት 2 ጀምሮ ትምህርታቸውን ያቋረጡ መሆናቸውን ገልጿል። #ዩኒሴፍ ባወጣው መግለጫ መምህራን ለሁለት ዓመታት ደመወዝ አለማግኘታቸውን ተከትሎ ሌሎች 3.7 ሚሊየን ህጻናትም ከትምህርት ገበታ ውጭ የመሆን ስጋት ተደቅኖባቸዋል።

በትምህርት ቤቶች ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶች፣ መፈናቀል እና ግጭቶች ተማሪዎችን ከትምህርት ገበታ እንዲርቁ ያደረጉ ምክንያቶች ናቸው ሲሉ በየመን የዩኒሴፍ ተወካይ ሳራ ቤይሶሎ ኛታኒ ተናግረዋል። የህጻናቱ ከትምህርት ገበታ ውጭ መሆን ልጆች ወደ ጦርነት እንዲገቡ መገደድና ለሌሎች ጫና እየተዳረጉ መሆኑንም ነው የጠቆሙት። እንደ ዩኒሴፍ መረጃ እድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ 1.8 ሚሊየን ህፃናት ለተመጣጠነ ምግብ እጥረት ተጋልጠዋል።

ምንጭ፦ አል ጀዚራ/በENA ይቀረበ/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ትምህርት ሚንስቴር እኛ ለእኛ የበጎ ፍቃደኞች መርኃግብር ላይ ንቁ ተሳትፎ ላደረጉ በጎ ፈቃደኞች ዛሬ 4 ኪሎ በሚገኘው የትምህርት ሚንስቴር መሰብሰቢያ አዳራሽ ወስጥ የግማሽ ቀን ስልጠና እና የምስክር ወረቀት አሰጣጥ እየተከናወነ ይገኛል፡፡

#TIKVAH_ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሳዉላ⬆️

"ለጎፋ ልማት በአንድነት እንሮጣለን" በሚል መርህ ቃል ዛሬ መስከረም 14/2012 ዓ.ም ደማቅ ሩጫ በጎፋ ዞን በሳዉላ ከተማ ተካሂዷል።

Via Gofa Sawla
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጋዜ ማስቃላ!

"አንድ ስንሆን እናምራለን፤ እንበረታለን!" በሚል መርህ የጎፋና ኦይዳ ብሄረሰቦች የዘመን መለወጫ በሳውላ ከተማ እየተከበረ ይገኛል። በአሁን ሰዓት በሳውላ ከተማ ሚሊኒየም አዳራሽ እየተካሄደ በሚገኘው ስነ ስርዓት ላይ ከአዲስ አበባ እና ከሌሎች የኢትዮጵያ አካባቢዎች የተገኙ እንግዶች እና የጎፋ ዞን ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በማዕከላዊ ጎንደር ዞን #በሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ በተለያዩ መስሪያ ቤቶች ተቀጥረው ያለአግባብ ደመወዝ ሲከፈላቸው በነበሩ 95 ግለሰቦች ላይ እርምጃ መውሰዱን የዞኑ ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት አስተዳደር መምሪያ አስታውቋል።

https://telegra.ph/ETH-09-25-7

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#update ለግሸን ደብረ ከርቤ ዓመታዊ ክብረ በዓል ልዩ የበረራ አገልግሎት ማዘጋጀቱን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታውቋል።

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ድል በርን አለፍ ብሎ የመኪና አደጋ ደርሷል፤ አደጋው በሁለት አይሱዙ መኪናዎች መካከል የተፈጠረ ነው። በሰው ላይ ቀላል ጉዳት ደርሷል፤ በንብረት ላይም ጉዳት ደርሷል።

Via Ermi/TIKVAH-ETH/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሽከርካሪዎች ጥንቃቄ እንድታደርጉ!

ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ወደ ሱሉልታ መውጫ ድል በር አከባቢ በደረሰው የመኪና አደጋ መንገድ ተዘግቷል፡፡ ወደዛ መስመር የምትጓዙ አሽከርካሪዎች ጠንቃቄ እድታደርጉ፡፡

Via Ermi/TIKVAH-ETH/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#REFERENDUM

በሀዋሳ ከተማ በ166 የምርጫ ጣቢያዎች እድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ከ190000 (ከመቶ ዘጠና ሺህ) በላይ ሰው ድምፅ ይሰጣል ተብሎ ዕቅድ ተይዟል!

በሲዳማ ብሔር የክልልነት ጥያቄ ማስፈፀሚያ ዕቅድ እና አተገባበር ዙሪያ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ገለፃ አደረገ
በሀገር ደረጃ ለአስተዳደራዊ ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ለመጀመሪያ ጊዜ የሲዳማ ብሔር የክልልነት ጥያቄ ህዝበ ውሳኔ ህዳር 3 ቀን 2012 ዓ.ም እንደሚካሄድ ይታውቋል፡፡

በዚህ መነሻ በተደረገው ገለፃ በከተማ አስተዳደሩ በሁሉም እርከን የሚገኘው አመራር የተሳተፈ ሲሆን የሲዳማ ብሔር ክልል የመሆን ጥያቄ ህዝበ ውሳኔ መላውን ህዝብ ያሳተፈ፣ ፍፁም ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የከተማ አመራሩ እንደሚሰራ ተገልጿል፡፡

የሲዳማን የክልልነት ጥያቄ ህዝበ ውሳኔ ለማካሄድ ከተቋቋሙ 19 የድምፅ መስጫ ክልልሎች አንዷ በሆነችው ሀዋሳ ከተማ በ166 የምርጫ ጣቢያዎች እድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ከ190000 (ከመቶ ዘጠና ሺህ) በላይ ሰው ድምፅ ይሰጣል ተብሎ ዕቅድ ተይዟል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-25-8

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በሐረሪ ክልል የታየውን የኮሌራ /አተት/ በሽታ ለመከላከል እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ጤና ጥበቃ ቢሮ አስታወቀ፡፡ በቢሮው የህብረተሰብ ጤና ላብራቶሪ ምርምርና ድንገተኛ አደጋዎች ቁጥጥር ዳይሬክተር አቶ አሰፋ ቱፋ እንደገለጹት በክልሉ በሽታው ከሐምሌ  ወር 2011  ጀምሮ  ምልክቱ ታይቷል፡፡ በሐምሌና መስከረም ወር ላይ በክልሉ የበሽታው  ምልክት ታይቶባቸው ምርመራ ከተደረገባቸው 27  ሰዎች መካከል በ11 ላይ በሽታው  ሙሉ ለሙሉ ሊገኝ መቻሉን ተናግረዋል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የትምህርት መጀመሪያ ጊዜ መራዘሙ ተሰምቷል!

በአዲስ አበባ የመንግስት ትምህርት ቤቶች ትምህርት የሚጀመረው መስከረም 26 እንደሆነ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ተናግሯል። የትምህርት ቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ #ዘላለም_ሙላቱ የመንግስት ትምህርት ቤቶችን አገልግሎት ለማሻሻል እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ባለመጠናቀቃቸው ትምህርት መጀመሪያ ጊዜው መራዘሙን ለሸገር ራድዮ 102.1 ገልፀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሳዛኝ ዜና!

በምስራቅ ጎጃም ዞን ደብረ ኤልያስ ወረዳ በቤት ዉስጥ የተቀመጠ ቦምብ ፈንድቶ አንድ የሶሰት ዓመት ህጻን ሲገድል በአራት ህጻናት ላይ ደግሞ ከባድ ጉዳት ማድረሱ ተገለጸ።

የምስራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ የህዝብ ግንኙነት አስተባባሪ ዋና ኢንስፔክተር ጎበዜ ይርሳዉ እንዳሉት በደብረ ኤልያስ ወረዳ ጥጃ ጎጠር የጠንጠር ቀበሌ ዛሬ ከቀኑ 8.00 ሰዓት በአቶ ጌታሁን የኋላዉ ቤት ዉስጥ ተቀምጦ የነበረን የጣሊያን ቦንብ ልጆች ሲነካኩ በመፈንዳቱ ምክንያት በልጆች ላይ ጉዳት አድርሷል።

በጉዳቱ የሶስት አመት ህጻን ህይወቷ ወዲያዉኑ ሲያልፋ እድሚያቸዉ ከሶስት ወር እስከ ሃያ አመት የሆኑ አራት የአንድ ቤተሰብ ልጆች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዉ በደብረ ማርቆስ ሪፈራል ሆስፒታል እየተረዱ ነዉ።

ህዝቡ በቤት ዉስጥ ያስቀመጠዉ ቦሞብ ካለ በሰዉ ህይወትና ንብረት ላይ ጉዳት ከማድረሱ በፊት ለመንግስት ገቢ እንዲያደርጉም ዋና ኢንስፔክተር ጎበዜ ይርሳዉ ማሳሰባቸውን የወረዳው የመንግስት ኮሙንኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

Via Machakel Woreda Government Communication/ETHIO-FM/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የመንግስት የስራ ኃላፊዎች የህዳሴ ግድብን እየጎበኙ ይገኛሉ!

የውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በቀለን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ዛሬ (መስከረም 14 ቀን 2012 ዓ.ም) ታላቁ የኢትየጵያ ህዳሴ ግድብን በመጎብኘት ላይ ናቸው።

የአባይን ወንዝ በተመለከተ እ ኤ አ የ1959 ስምምነት ተቀባይነት እንደሌለው ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢንጂነር የታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ከጎበኙ ብኋላ ገልጸዋል።

እንደ ሚኒስትሩ ግድቡ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ በርካታ ተጽዕኖዎችን ለማሳደር የሚደረጉ መሯሯጦች መኖራቸውን አስታውሰው ይሁንና መንግስት ከተፋሰሱ አገራት ጋር በመነጋገር ችግሮችን እየፈታ ነው ብለዋል።

ከግብጽ በኩል ሰሞኑን እየተራገበ ያለው ነገር በምን ምክንያት እንደተነሳ እንደማያውቁ የገለጹት ሚኒስትሩ አዲስ የሰራነው ነገር የለም የውኃ ሙሌቱንም በተመለከተ በምን አኳኋን መካሄድ እንዳለበት ከታችኛው ተፋሰስ አገሮች ጋር ተነጋግረን ተስማምተናል ብለዋል።

ውኃ በብዛት በሚኖርበትና ውኃ በሚቀንስበት ወቅት አሞላሉ ምን መምሰል እንዳለበት ከታችኛው የተፋሰስ አገራቱ ጋር ንግግር መደረጉን የገለጹት ሚኒስትሩ ሙሌቱ በእነርሱ ላይ ተጽዕኖ በማይኖረው መልኩ እንደሚከናወን ግብጽም ሆነች ሱዳን ጠንቅቀው ያውቃሉ ብለዋል።

ሰሞኑን በግብጽ ሚዲያዎች የሚራገቡ ነገሮች መነሻቸው ምን አልባት ከሌሎች ነገሮች ጋር የተያያዙ ሊሆኑ ይችላሉ ሲሉ ሚኒስትሩ ግምታቸውን አስቀምጠዋል።

Via #EPA
Photo: EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ETHIOPIA | ኢንጂነር ስለሺ_በቀለ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ የደረሰበትን ደረጃ ዛሬ በጎበኙበት ወቅት የብረታ ብረት እና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) #አጓትቶት የነበረው የኤሌክትሮ ሜካኒካል እና የብረታ ብረት ሥራ ለአምስት ዓለም አቀፍ ኮንትራክተሮች ከተሰጠ ወዲህ ስራው በጥሩ ሁኔታ እየሄደ መሆኑን ገልፀዋል። በዚህም ምክንያት ሳሊኒ ከዚህ በፊት አቁሞት የነበረው የሲቪል ሥራ(በተለይ በግድቡ የመሃል ክፍል ላይ አርማታ የመሙላት ሥራ)አሁን መጀመሩን ተናግረዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ አሁን ያለበት ሁኔታ፦

• ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ በመጪው ዓመት አጋማሽ በኃላ ወደ ኃይል ማመንጨት ይሸጋገራል፣
• በቅድሚያ ኃይል የሚያመነጩት ዩኒት 9 እና 10 ሲሆኑ አሁን ላይ የሁለቱ ዩኒት አፈጻጸም 50 በመቶ ደርሷል፣
• የዋናው ግድብ የኮንክሪት ግድብ ይወስዳል ተብሎ ከተገመተው 10 ነጥብ 2 ሚሊዮን ሜትሪክ ኪዩብ ውስጥ ከ8 ሚሊዮን በላይ የኮንክሪት ሙሊት ተከናውኗል፤ አፈጻጸሙም ከ80.4 በመቶ ነው፣
• የኮርቻ ቅርፅ ግድቡ ግንባታ አፈጻጸም 96 በመቶ ተጠናቋል፣
• ለቅድመ ማመንጨት ሥራው የሚያስፈልጉ ተርባይኖች የሚገጠሙበት የስፓይራል ኬዝ ተከላ እና የብየዳ ስራ በጥራት በመከናወን ላይ ነው፣
• በግድቡ የግራ ክፍል ግድቡን ከባህር ጠለል በላይ 560 ሜትር ከፍታ ላይ ለማድረስ 26 ሺህ ሜትር ኪዩብ ኮንክሪት ተሞልቷል፣ በቀሪው የግድቡ ክፍል ላይ ደግሞ 50 ሺህ ሜትር ኪዩብ ኮንክሪት የመሙላት ሥራ እየተከናወነ ነው፤
• ለታችኛው የውሃ ማስተንፈሻ (ቦተም አውትሌት) ሥራ የሚያስፈልገውን ማቴሪያል ከውጭ ሃገር በማስገባት በሳይት ላይ የምርት ሥራ ተጀምሯል፣
• በአሁኑ ሰዓት የጎርፍ ማስተንፈሻ 96 በመቶ፣ የኃይል ማመንጫ ክፍል 70 በመቶ እንዲሁም የዋናው ግድብ የኮንክሪት ሙሌት 80 በመቶ ተጠናቋል፣
• ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የግንባታ ሥራው በ2003 ዓ.ም የተጀመረ ሲሆን ዓመታዊ አማካይ የኃይል ምርት አቅሙም 15,670 ጊጋ ዋት ሰዓት ነው፣
• ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ አፈፃፀም አሁን ላይ 68 ነጥብ 3 በመቶ ደረሷል።

ምንጭ፦ ኢፕድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ላይ #ተጽዕኖ ለማሳረፍ የሚደረጉ መሯሯጦች ተቀባይነት የላቸውም"- ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በአዲስ አበባ ከተማ ለሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አብያተ ክርስቲያናት የመሬት የባለቤትነት የይዞታ ማረጋገጫ ሰነዶችን አስረከቡ። ምክትል ከንቲባው ሰነዶቹን ያስረከቡት በፓትርያርክ ፅህፈት ቤት በመገኘት ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ነው። ጥያቄ ከቀረበባቸው 137 አብያተ ክርስቲያናት መካከል 15ቱ ዛሬ የባለቤትነት የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ተሰጥቷቸዋል።

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኬንያና ሶማሊያ ግንኙነታቸውን ወደ ወደ ሰላማዊ ሁኔታው ለመመለስ ተስማሙ፡፡ ኬንያና ሶማልያ በህንድ ውቅያኖስ ጠረፍ ስፍራ ይገባኛል ውጥረት ውስጥ ገብተው ለወራት ዘልቀዋል፤ ጉዳዩንም ዘ ሄግ ለሚገኘው ዓለማቀፍ ፍርድ ቤት አቅርበዋል፡፡ አሁን ላይ ግን ግንኙነታቸውን ለማሻሻል #መግባባት ላይ መድረሳቸው ተሰምቷል፡፡ በግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ አሸማጋይነት በተደረገ ምክክር የሁለቱ ሀገራት መሪዎች ስምምነት ላይ መድረሳቸውን አፍሪካ ኒውስ ዘግቧል፡፡

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#EGYPT vs #ETHIOPIA | ግብጽ በይፋ ዲፕሎማሲያዊ ዘመቻ ጀምራለች። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ #ሳሜሕ_ሽኩሪ በካይሮ የአረብ ሊግ ስብሰባ ላይ በድርድሮቹ ኢትዮጵያ «ግትር» ሆናለች ሲሉ መውቀሳቸውን አል ሞኒተር የተባለው የግብጽ ጋዜጣ ዘግቧል። የግብጽ ውጭ ጉዳይ ረዳት ሚኒስትር ሐምዲ ሎዛ በበኩላቸው መቀመጫቸውን በካይሮ ካደረጉ የአውሮፓ አገራት አምባሳደሮች ጋር በጉዳዩ ላይ ባደረጉት ውይይት ኢትዮጵያ የሌሎች አገሮችን ጥቅም ችላ በማለት የራሷን አተያይ ብቻ ለመጫን ጥረት እያደረገች ነው ሲሉ ወቅሰዋል።

Via #EsheteBekele
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የከምባታ ጠምባሮ ዞን ምክር ቤት 17ኛ መደበኛ ጉባኤውን ከመስከረም 21- 23 ቀን 2012 ዓ/ም ያደርጋል። #ዱራሜ

Via Z/TIKVAH-ETH
@tsegabwolde @tikvahethiopia