TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
የ10ኛ ክፍል ውጤት ይፋ ተፋደርጓል! መልካም ዕድል!

TIKVAH-MAGAZINE በመቀላቀል ውጤታችሁ እንዲታይላችሁ ማድረግ ትችላላችሁ👇
https://yangx.top/joinchat/AAAAAEcez-UrldBjOpa-qQ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አርዓያ ገብረእግዚአብሄር፦

•ከተፈታኞቹ መካከልም ከ10 ሺህ በላይ ተማሪዎች አራት ነጥብ አምጥተዋል።

•75 ነጥብ 5 በመቶ ያህል ተፈታኞች ሁለት እና ከዚያ በላይ ነጥብ ያመጡ ናቸው።

•ሁለት ነጥብ እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡት ተማሪዎች ቁጥር ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር ብልጫ አለው።

•ከተፈታኞቹ መካከል ወንዶች 682 ሺህ 572 ሲሆኑ 572 ሺህ 997 ሴቶች ናቸው፡፡ ከእነዚህ መካከል 894 ሺህ 318 በመደበኛ፣ 354 ሺህ 782 በግል እና 6 ሺህ 469 ደግሞ በማታው ክፈለ ጊዜ ተፈታኞች ነበሩ።

በዘንድሮው የ10ኛ ክፍል ፈተና ከ1 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ ተማሪዎች ለፈተና መቀመጣቸውን የኤጀንሲ መረጃ ያመላክታል። ባለፈው አመት ሁለት እና ከዚያ በላይ ነጥብ ያስመዘገቡት ተፈታኞች 71 በመቶ መሆናቸው የሚታወስ ነው። ተማሪዎች ውጤታቸውን በኤጀንሲው ድረ ገጽ http://
app.neaea.gov.et ወይም www.neaea.gov.et እንዲሁም በአጭር የጽሁፍ መልዕክት 8181 ላይ ID- ብለው የአድሚሽን ቁጥራቸውን በማስገባት መመልከት ይችላሉ።

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የመስከረም 4ቱ ሰልፍ ተራዝሟል!

በኢትዮጵያ ኦርቶዳክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ላይ ጥቃት እየደረሰ ነው በሚል መስከረም 4 ቀን ሊካሄድ ታስቦ የነበረው ሰላማዊ ሰልፍ መራዘሙ ተገልጿል። የሰልፉ አስተባባሪዎች ጋዜጣዊ መግለጫ በመስጠት ላይ ናቸው። ሰልፉም ወደ ጥቅምት 30 ቀን 2012 ዓ.ም መዘዋወሩን አዘጋጅ ኮሚቴው አስታውቋል።

ምንጭ፦ ኢትዮ ኤፍ ኤም
ፎቶ: ፋይል
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ADDISABEBA

በአዲስ አበባ በተለምዶ አፍንጮ በር በሚባለው አካባቢ ዛሬ እኩለ ቀን ላይ ግንብ ተደርምሶ በመኖሪያ ቤቶች ላይ ጉዳት አደረሰ። አደጋዉ ሁለት መኖሪያ ቤቶችን ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ዉጭ ያደረገ ሲሆን ሌሎች 6 የሚሆኑትን ደግሞ በከፊል እንደጎዳ ነዋሪዎች ለኢዜአ ተናግረዋል። በወረዳው 88 ቤቶች ለአደጋ ተጋላጭ መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡

በአደጋው  ቤታቸውና ንብረታቸው ሙሉ በሙሉ መውደሙን ወይዘሮ አዜብ ሞገስ  የተባሉ ነዋሪ ገልፀዋል። አደጋ ከመድረሱ በፊት በአካባቢው የአደጋ ስጋት መኖሩን ከወረዳ እስከ ክፍለ ከተማ በተደጋጋሚ አቤቱታ በማቅረብ ከቦታው ተነስተው ተለዋጭ ቤት እንዲሰጣቸው ጠይቀው እንደነበርም ተናግረዋል። አክለውም መንግስት የደረሰባቸውን ችግር በመረዳት ቤተሰባቸውን የሚያኖሩበት ቤት እንዲሰጣቸዉና ለእለት ፍጆታ የሚሆን  የምግብ እርዳታ እንደያደርግላቸውም ጠይቀዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-13-4

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለ10ኛ ክፍል ተማሪዎች፦

የ2011 ዓ/ም የ10ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት የወጣ ሲሆን ተማሪዎች ወይም ወላጆች ውጤታቸውን ቀጥሎ በተመለከተው የድህረ ገፅ አድራሻ መሠረተ ማወቅ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

www.app.neaea.gov.et ቀጥሎ student result የሚለውን ይጫኑ ቀጥሎ Click here for Grade 10 result የሚለውን ይጫኑ!

1ኛ. የተማሪዉ/ዋ/ን መለያ ኮድ ወይም አድሚሽን ቁጥር ማስገባት

ማሳሰቢያ

የተማሪዉ/ዋ/ን ውጤት ለማወቅ የሚያስፈልጉ መረጃዎች፦

A ማለት 4 ነጥብ ነው
B ማለት 3 ነጥብ ነው
C ማለት 2 ነጥብ ነው
D ማለት 1 ነጥብ ነው
F ማለት 0 ነጥብ ነው

2ኛ. ከተዘረዘሩት የትምህርት አይነቶች ውስጥ የግድ መያዝ ያለባቸውን፦ #የmaths , #english & #civics ውጤቶችን በመመዝገብ እና ተጨማሪ 4 የተሻሉ የትምህርት አይነት ውጤቶችን መመዝገብ በአጠቃላይ 7 የትምህርት አይነት ይሆናሉ ማለት ነው።

3ኛ. ከላይ በተዘረዘረው የነጥብ አሰጣጥ መሰረት የ7ቱን የትምህርት አይነቶች አጠቃላይ ድምር ማግኘት አና ለ7 ማካፈል ነው።

#TIKVAH_ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NewsAlert ከቡራዩ ጥቃት ጋር ተያይዞ 22 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ። ከቡራዩ ጥቃት ጋር ተያይዞ የኦነግ- ሸኔ አባላትና ሌሎች ከእነሱ ጋር ትስስር ያላቸው 22 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን EBC የኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃን ጠቅሶ ዘግቧል። @tsegabwolde @tikvahethiopia
አቶ ዳውድ ኢብሳ...

"እነማን እንደተያዙ አናውቅም። መረጃውን እንደሁሉም ሰው ከሚድያ ነው የሰማሁት። እርግጥ ነው በየግዜው ተያዙ እየተባለ ይወራል፣ እኛም ለመለየት አስቸጋሪ ሆኖብናል። ስለዚህ ስለተባለው ነገር አላውቅም።"

ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት/AP/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከህንድ የተላከ...

"ትላንት እና ከትላንት በስትያ ከሀገር ውጪ በህንድ የምንገኝ ኢትዮጵያዊያን በማርዋዲ ዩኒቨርስቲ ተሰባስበን እንዲ በደማቅ ሁኔታ በአሉን ከህንዳውያን፣ ኢንዶኔዥያ፣ ኔፓል፣ ባንግላዴሽ፣ ስሪያ፣ አፍጋኒስታን እና ሌሎች አፍሪካን ሀገራት ጋር በሕብረት አክብረናል። መልካም አዲስ አመት!" #BINI

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በኢንፎርሜሽ መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ ከዚህ ቀደም ሹመት የነበረው የመካከለኛ ደረጃ ኃላፊነት ምደባ በውድድር እንዲሆን ማድረጉን ኤጀንሲው አስታውቋል። ሰራተኞች በፈለጉበት ቦታ መስራት የሚችሉበትንም አሰራር መፍጠሩን ያለፈውን ዓመት ኤጀንሲው ያከናወናቸውን ተግባራት በገመገመበት ወቅት ገልጿል።

ምንጭ፦ አዲስ ማለዳ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መስከረም 2 ቀን 1967⬆️

"ደርግ ንጉሱን ለማውረድ ከሰኔ 21፣ 1966 እስከ መስከረም 1፣ 1967 ድረስ 56 ቀናት ያህል ወስዶበታል።" ሌ/ኮሎኔል ፍስሐ ደስታ/አብዮቱና ትዝታዬ/

በወቅቱ የነበራችሁ የቤተስባችን አባላት ምን ትዝ ይላችኃል?? ሁኔታውን እንዴት ታስታውሱታላችሁ?? @tsegabwolde
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከዛሬ መስከረም 2 ቀን 1967 ዓ/ም ጀምሮ ቀዳማዊ ኃይለስላሴ ከስልጣናቸው ወርደዋል። #ETHIOPIA

አዋጅ ቁጥር 1/1967

1ኛ. ይህ አዋጅ የኢትዮጵያ ጊዜያዊ ወታደራዊ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1/1967 ዓ/ም ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል።
.
.
ይህ አዋጅ እስከፀናበት ድረስ "ኢትዮጵያ ትቅደም" የሚለውን አላማ የመቃወም አድማ የሚያደርግ፤ ስራ የሚያቆም፤ ያለ ፍቃድ ሰላማዊ ሰልፍ እና ስብሰባ የማድረግ በጠቅላላው የህዝቡን ፀጥታና ሰላም የሚነሳ ተግባር መፈፀም ክልክል ነው።

#TIKVAH_ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#US_EMBASSY

አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ በጋምቤላ ክልል ሁለት የግብረ-ሰናይ ድርጅት ሰራተኞች የገደሉ ታጣቂዎችን መንግሥት በአፋጣኝ በቁጥጥር ሥር አውሎ ለሕግ እንዲያቀርብ ጠየቀ። አክሽን አጌይንስት ኸንገር የተባለው ዓለም አቀፍ የግብረ-ሰናይ ድርጅት ሰራተኞች ጥቃት የተፈጸመባቸው በጋምቤላ ክልል ደቡብ ሱዳናውያን ስደተኞች ከሚኖሩበት ኙንዬል ከተባለ የመጠለያ ጣቢያ (Nguenyyiel Refugee Camp) ሥራቸውን አጠናቀው በመጓዝ ላይ ሳሉ እንደነበር ድርጅቱ አስታውቋል። በጥቃቱ የመስክ ሰራተኛ እና አሽከርካሪ ሕይወታቸውን አጥተዋል። የአሜሪካ ኤምባሲ በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ የግብረ-ሰናይ ሰራተኞች መሆኑን የሚጠቁም ምልክት በነበረው ተሽከርካሪ ላይ ባለፈው ሳምንት የተፈጸመውን ጥቃት አውግዟል።

Via #EsheteBekele
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
mwfellows.info/apply

በመጪው የአውሮፓ ዓመት ለሚካሄደው የ2020 የማንዴላ የወጣት አፍሪካዊያን መሪዎች ዋሽንግተን ፌሎውሽፕ መርሐ ግብር ምዝገባ ተጀመረ።

‘የማንዴላ ዋሽንግተን ፌሎውሽፕ’ የተባለው መርሃ ግብር ወጣት አፍሪካዊያንን በመመልመል በአሜሪካን አገር በሚገኙ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለ6 ሳምንት የሚዘልቅ የአመራርነት ስልጠና የሚሰጥበት ነጻ የትምህርት እድል ነው።

በኢትዮጵያ የአሜሪካን ኤምባሲ ዛሬ በሰጠው ማብራሪያ በአውሮፓዊያን ቀመር በመጪው ዓመት ለሚሰጠው መርሐ ግብር ምዝገባው ትናንት ተጀምሯል። ምዝገባም እንደ አውሮፓ አቆጣጠር አስከ ጥቅምት 9 ቀን 2019 ይቆያል ተብሏል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-13-5
#FAKE የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቅያ ወይም የመሰናዶ መግቢያ #መቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ እየተባለ በማህበራዊ ሚዲያ ሚሰራጨው። በዛሬው ዕለት ይፋ የተደረገው ተማሪዎች ውጤት ብቻ ነው። የመቁረጫ ነጥብ ይፋ አልተደረገም። በሚሰራጩ ሀሰተኛ መረጀዎች እንዳትታለሉ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ከዕገታው ጀርባ የእስራኤል የስለላ ድርጅት ሞሳድ እንደሚኖር ጥርጣሬያቸውን ገልፀዋል!"

ሐሰን ጃበር የተባሉ ሊባኖሳዊ የንግድ ሰው በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀናት ትራንዚት በሚያደርጉበት አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ታግተው እንደተወሰዱ እና የደረሱበት እንዳልታወቀ ቤተሰቦቻቸው አስታውቀዋል።

በዕለቱ ከአፍሪካዊቷ አገር ጋቦን በመነሳት በአዲስ አበባ አድርገው ወደ ሊባኖስ ቤሩት በማምራት ላይ የነበሩት ሐሰን አዲስ አበባ ደርሰው ቀጣዩ ጉዟቸውን ለማድረግ በሚሰናዱበት ወቅት ለጊዜው ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ዕገታ እንደተፈፀመባቸው እና ሊሰወሩ እንደቻሉ የተገለፀው። የግለሰቡ ቤተሰቦች ከሊባኖስ ጋዜጣ አል አክበር ጋር ባደረጉት ቆይታ ከዕገታው ጀርባ የእስራኤል የስለላ ድርጅት ሞሳድ እንደሚኖር ጥርጣሬያቸውን ገልፀዋል።

እንደ ጋዜጣው ዘገባ ግለሰቡ ከዓመታት በፊት በፈረንጆች 2017 ከሒዝቦላህ ጋር ግንኙነት አለው በሚል በጋቦን የፀጥታ አካላት ምርመራ የተደረገባቸው መሆኑን አውስቷል። ይሁን እንጂ ሐሰን ከሒዝቦላህ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌላቸው ቤተሰቦቻቸው አስታውቀዋል።

በአሁኑ ሰዓት ሊባኖሳዊው ግለሰብ የት እና በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኙ የሚታወቅ ነገር የለም። ስለጉዳዩ ኢትዮጵያ አየር መንገድ ምንም የሚያውቀው ነገር አለመኖሩን ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

የሊባኖስ የወጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኢትዮጵያ በኩል የሚመለከታቸው የፀጥታ አካላት በጉዳዩ ላይ ግልፅ ምላሽ እስከ መጪው ሰኞ መስከረም 5/2012 ድረስ እንዲሰጥበት አሳስበዋል። ካልሆነ ግን ተመጣጣኝ እርምጃ እንደሚወስድ የሊባኖስ መንግስት አስጠንቅቋል።

Via #AddisMaleda
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በደንብ ተመልከቱ⬆️

እኛ እንዲህ ነን፤ ተያይዞ፣ ተቻችሎ፣ ተዋዶ መኖር ካልቻልን ተያይዞ መጥፋት ነው የሚሆነው፤ አንዱን ጠጠር ብታነሱት ሁሉም ይፈርሳል፤ ለሁሉም መኖር የአንዱ መኖር ወሳኝ ነው።

#እንዋደድ #እንከባበር #እንፋቀር #ሰላም #ፍቅር #ተስፋ

ሀሳቡ ከማህበራዊ ሚዲያ ተወሰደ!


🚪መስከረም 2 ቀን 2012 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ማስታወቂያ!

ለዩኒቨርስቲ ተመዳቢ ተማሪዎች በሙሉ!

በ2012 የትምህርት ዘመን ለሚካሄደው የተማሪዎች/ተፈታኞች ምደባ፦

1. ከተፈጥሮ ሳይንስ ወደ ማህበራዊ ሳይንስ ትምህርት መስክ መቀየር የምትፈልጉ ተማሪዎች/ተፈታኞች እና

2. የዩኒቨርስቲ ምርጫችሁን ማስተተካከል (መቀየር) ለምትፈልጉ ተማሪዎች /ተፈታኞች የዩኒቨርስቲ ምርጫችሁን ማስተካከልም ሆነ የትምህርት መስክ ምርጫ (የመምህርነት መስክ ምርጫ መምረጥ) የሚቻለው በተማራችሁበት ት/ቤት (ፈተና በወሰዳችሁበት የፈተና ጣቢያ) በኩል መሆኑን እያሳወቅን የዩኒቨርስቲ ምርጫ ማስተካከያና የፊልድ መቀየሪያ ቀናት ከመስከረም 5/2012 እስከ መስከረም 12 /2012 ዓ.ም ድረስ ብቻ መሆኑን ኤጀንሲው እየገለፀ የመሰናዶ ት/ቤቶችም የተማሪዎችን ምርጫ ማስተካከልና የፊልድ ቅየራ /ከተፈጥሮ ሳይንስ ወደ ማህበራዊ ሳይንስ/ ጥያቄ በመቀበል እንዲታስተናግዱ ያሳስባል፡፡

ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ

በየዕለቱ የሚወጡ የትምህርት ነክ ጉዳዮችን በTIKVAH-MAGAZINE ማግኘት ትችላላችሁ👇
https://yangx.top/joinchat/AAAAAEcez-UrldBjOpa-qQ
#update ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ወደ ካርቱም ሊያቀኑ ነው። የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ሃላፊ ሌተናል ጀኔራል አብድል ፋታ አል ቡርሃን ባቀረቡላቸው ግብዣ መሰረት በፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የሚመራ የኤርትራ ልኡካን ቡድን ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ ሱዳን ይገባል ተብሏል። ፕትሬዚዳንት ኢሳያስ በቆይታቸው የሀገራቱን የሁለትዮሽ ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች እንዲሁም ባለፉት አመታት የነበረውን መልካም ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል። ፕሬዚዳንቱ ለሁለት ቀናት የስራ ጉብኝት ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትራቸው እና የደህንነት አማካሪያቸው ጋር በዛሬው ዕለት ሱዳን ካርቱም ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል። የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ሃላፊ ሌተናል ጀኔራል አብድል ፋታ አል ቡርሃን በቅርቡ በኤርትራ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳል።

ምንጭ ፦የሱዳን ዜና አገልግሎት/ebc/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጥቆማ በአንዳድ የሀገሪቱ ከተሞች የ10ኛ ክፍል የብሄራዊ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች ውጤታቸውን ለማየት እደተቸገሩ እየገለፁ ይገኛሉ። የሚመለከተው አካል ችግሩን እንዲፈታም ጠይቀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት ውስጥ ዕውቀት እና ሃሳብ ያላቸውን ሰዎች ንድፍ ወደተግባር እንዲቀይሩ በማድረግ ቴክኖሎጂ እና ፈጠራን መሰረት ያደረጉ ሁለት ሺ አነስተኛ ተቋማት ሊያቋቋቁም መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር አስታወቁ።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ጀማል በከር በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደገለጹት፤ በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት ውስጥ ሁለት ሺ አነስተኛ የሳይንስና ፈጠራ ንግድ እና አገልግሎት ተቋማትን በማቋቋም እና ድጋፍ ይደረጋል።

በስራቸውም 20 ሺ ሰዎችን በቀጥታ ተጠቃሚ ለማድረግ ሀገራዊ እንቅስቃሴ በሚኒስቴሩ ተጀምሯል። እንደ አቶ ጀማል ገለጻ፤በተለይ በተንቀሳቃሽ ስልክ እና በኮምፒውተር በመተግበሪያዎች፣ በሮቦት እና ሌሎች ፈጠራ ስራዎች እንዲሁም በማምረቻ እና አገልግሎት ዘርፉ ውስጥ ቴክኖሎጂን ተጠቅመው ችግር ፈቺ ንግድ ለሚጀምሩ ሰዎች የገንዘብ ድጋፍም ይደረጋል።

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዚምቧብዌ የቀድሞ ፕሬዝዳንቷን ሥርዓተ ቀብር ከመፈፀሟ በፊት፤ ሮበርት ሙጋቤን ለመሰናበት የአፍሪካ መሪዎች በዋና ከተማዋ ሐራሬ ይሰባሰባሉ ተብሎ ይጠበቃል። የደቡብ አፍሪካው ሲሪል ራማፎሳን ጨምሮ በርካታ በስልጣን ላዩ ያሉና የቀድሞ የአፍሪካ ርዕሰ ብሄሮችም በስንብቱ ላይ ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

Via #BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መፍትሄ ያልተገኘለት የቴፒ ጉዳይ...

"እንደምታውቀው አመት ያለፈው የቴፒ ውጥረት እስካሁን መፍትሄ አላገኘም። በግጭቱ ሳቢያ ከቀያቸው የተፈናቀሉ ሰዎች ይኸው በአንድ አዳራሽ ውስጥ ተጠልለው ስምንት ወር አለፋቸው። ይህ ሁሉ ሲሆን አንድም የመንግስት አካል ሌላው ቀርቶ ሰብዓዊ እርዳታ እንኳን አላደረገላቸውም። በዚሁ ከቀጠለ የቡና ምርት ወቅት ስለደረሰ ተፈናቃዮቹ ወደቀያቸው ካልተመለሱ ሌላ ቀውስ መፈጠሩ አይቀሬ ነው።...የሚያሳዝነው ነገር ግጭቱ ከጀመረ አንስቶ ከቀን ቀን እየጨመረ የመጣውና እስከ ሰው ህይወት መጥፋት የተደረሰ የዝርፊያ ተግባር ነው። መጠኑ ይለያይ እንጂ አንድም ቀን የተኩስ ድምፅ ሳይሰማ ቀርቶ አያውቅም። ሰው ይሞታል፤ ንብረት ይዘረፋል።...አሁንም ቢሆን መንግስት ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥቶ ነገሮች ካልተስተካከሉ ግጭቱ እንዳዲስ አገርሽቶ ሌላ ጥፋት እንዳያስከትል ስጋቴ ነው።" ከቴፒ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ

@tsegabwolde @tikvahethiopia