አመስግኑልን⬆️
"የበጎ ስራ ለህጻናት ዳይፕር" በሚል ገቢውን ለልዩ ልዩ ውላጅ አልባና አቅም ለሌላቸው ወላጆች የሚበረከት ነው። ለእንቁጣጣሽ አበባዬሽ እያሉ በየ ቤቱ በሀዋሳ 05 አካባቢ ዘመን መለወጫውን በደማቅ ሁኔታ እያከበሩት ነው። እነዚህ ወጣቶች ሊመሰገኑ ይገባል።ህጻናቶች ነገ የዚች ሀገር ተረካቢ ናቸው! አዲሱ አመት ለኢትዬጲያ የሰላም፣ የፍቅር ፣የመቻቻልና፣የእንድነት ጊዜ ይሁንልን!!" Yared Tassew
@tsegabwolde @tikvahethiopia

’’ከክረምት በኋላ የደፈረሱ ወንዞች እንደሚጠሩት ሁሉ፤ መሬቱ እንደሚለመልመው፤ አበቦች በአዲስ ተስፋ ሰጪነት እንደሚያብቡት ሁሉ እኛም ሌላ ክረምት ሳንጠብቅ ራሳችንን ለማጥራት እንጀምር።‘ - ፕሬዚደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
’’2012 ዓ.ም የመጪውን አስር #የብልጽግና አመታት አቅጣጫ ቀይሰን የምንተምበት የቀጣይ መቶ አመታት የሥልጣኔ መንገድ መሰረት የምንጥልበት ወሳኝ እጣ ፈንታችን ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያ ትፈርሳለች ለሚሉ ዳግም ተሻግረን የምናሳይበትና የምናረጋግጥበት አመት ነው።‘ - ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"እንኳን ለ-2012 ዓ.ም በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። በአሮጌው ዓመት ከድህነት የሚመነጩ እና ወደፊት የማያራምዱ እኩይ አስተሳሰቦች አራግፈን መሻገር ይኖርብናል። በዓዲሱ ዘመን በሃገራችን የታላቅነት ጉዞ ብስራት የሚታወጅበት እና የብልጽግና መሰረት በጋራ የምንጥልበት ይሆናል። "ማቅ አውልቀን ~ ግምጃ እንልበስ!" በሚል ቅን እሳቤ ለስኬቱ እጅ ለእጅ ተያይዘን እንድንረባረብ አደራ አላለሁ። ዘመኑ ለሁላችንም የሰላም፥ የስራ፥ የአንድነት፥ የትብብር እና የብልጽግና እንዲሆንልን ከልብ እመኛለሁ።" ደመቀ መኮንን/ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Alert ጅማ ከተማ ዳሸን ባንክ /መርካቶ/ አካባቢ የተለያዩ ሸቀጣ ሸቀጥ ሱቆች በሚገኙበት ቦታ የእሳት አደጋ መድረሱን በቦታው የሚገኙ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ጠቁመዋል። የእሳቱ መነሻ ለጊዜው አልታወቀም። በአካባቢው የእሳት አደጋ ሰራተኞች ደርሰዋል/ብዙ ንብረት ከወደመ በኃላ/፣ በስፍራው የመከላከያ ሠራዊት እና የፌደራል የፖሊስ አባላት እንደሚታዩም የቤተሰባችን አባላት ጠቁመዋል። ፎቶዎች…
የትላንት ምሽቱ የእሳት ቃጠሎ አደጋ የ11 ሚሊየን ብር ንብረት አወደመ!
በጅማ ከተማ ትናንት ማታ በደረሰ የእሳት ቃጠሎ አደጋ ግምቱ 11 ሚሊየን ብር የሚሆን ንብረት መውደሙን ፖሊስ አስታወቀ። የጅማ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አዛዠ ኮማንደር አብዱራዛቅ ነጋ እንደገለጹት አደጋው በትናንትናው እለት ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት ላይ የተከሰተው በከተማው “መርካቶ” እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ነው።
በአደጋውም ግምቱ 11ሚሊየን ብር የሆነ ንብረት መውደሙን ኮማንደር አብዱራዛቅ ተናግረዋል። ኮማንደር አብዱራዛቅ እንዳሉት በአደጋው 12 ሼድ ኮንቴነር የንግድ ሱቆች በውስጣቸው ከያዟቸው ንብረቶች ጋር ሙሉ በሙሉ ወድመዋል።
የጅማ ከተማ እና የአየር መንገድ የድንገተኛና የእሳት መከላከያ ተሽከርካሪዎች ከህብረተሰቡና ከጸጥታ አካላት ጋር ሆነው ባደረጉት ርብርብ እሳቱ ሳይስፋፋ መቆጣጠር እንደተቻለም አንስተዋል። የአደጋውን መንስኤ ፖሊስ በማጣራት ላይ መሆኑን ኮማንደሩ አክለው መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
Via #ENA

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የሁላችንም አባት...ሙፍቲ ሀጂ ኡመር እድሪስ፦
"ሳንሞኛኝ ለአንድነት መዘጋጀት አለብን፤ ሳንታለል ለአንድነት መዘጋጀት አለብን፤ ለሰላም ዝግጁ መሆን አለብን፤ ሀገራዊ አመለካከት ሊኖረን ይገባል። ህዝባዊ አመለካለት ሊኖረን ይገባል። መንግስታዊ አመለካከት ሊኖረን ይገባል። አላህ እኮ ሲፈጥር የሰውን ልጅ በአጠቃላይ በስልጣን ላይ ሊቀመጥ አይደለም። ሁሉ ባለስልጣን ከሆነ ማን ታዛዥ ይሆናል? ሁሉ ሃብታም የሆነ እንደሆነ ማን ድሃ ይሆናል? እኩል መሪ እኩል ተመሪ፤ እኩል ሃብታም እኩል ድሃ ሊሆነው አላህ የፈጠረን።...ፈጣሪ ጌታችን አላህ ያለው እኔ ስልጣን ላይ ሳስቀምጥላችሁ አክብሩት፣ ውደዱት፣ ምከሩት፣ አገዙት ነው እጂ ያለው አውግዙት አላለም።...ባለስልጣን ይሰደባል፣ ሀብታም ይሰደባል፣ ምሁር አዋቂ ይሰደባል፣ ...ምንድነው ይሄ ? ከየት መጣ ? ማን አመጣው? እኛው አመጣነው። የሀይማኖት አባቶችም ጉድለት ይኖረናል፤ እውነት የሃይማኖት አባት ብንሆን፣ እውነተኛ ብንሆን፤ አቋማችን የተስተካከለ በስልጣን በጥቅም የማንሞኝ ብንሆን ህዝብ #ይሰማናል ቀጥ ብሎ ይከተላል።"
#TIKVAH_ETHIOPIA

#update የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል የአዲሱን ዓመት በዓል ምክንያት በማድረግ ደም ለገሱ። ዶክተር ደብረጺዮን በዛሬው ዕለት የሚከበረውን አዲስ ዓመት በዓል ምክንያት በማድረግ በደም እጦት ችግር ምክንያት ህይወታቸው የሚያልፉ ዜጎችን ለመታደግ የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ ነው ደም የለገሱት። በዚህ ወቅትም ወጣቶች በአዲሱ ዓመት በወሊድ ወቅት በደም እጦት ችግር ምክንያት ህይወታቸው የሚያልፉ እናቶችንና ሌሎች ዜጎችን ህይወት ለመታደግ ደም እንዲለግሱ ጥሪ ማቅረባቸውን ከብሄራዊ ደም ባንክ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#DESSIE የዘመን መለወጫ በዓልን ምክንያት በማድረግ በደሴ ከተማ ለሚገኙ የኢኮኖሚ አቅም ለሌላቸው አረጋዊያን የምሳ ግብዣ ተደረገ። የደሴ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ዶክተር መለስ መኮንን በእዚህ ወቅት እንደገለጹት ግብዥው የተደረገው አረጋዊያን በዕድሜ ዘመን ቆይታቸው ለሃገራቸው ያበረከቱትን ውለታ በማሰብ የተደረገ ነው። አረጋዊያን መደገፍና ማገዝ የወጣቱን የመርዳት ባህል ከማሳደጉም ባለፈ በዕድሜ ቆይታ ጉልበታቸው የደከመ አረጋዊያን በህዝባቸው ኩራትና ደስታ እንዲሰማቸው የሚያደርግ መሆኑን ተናግረዋል። ከንቲባው እንዳሉት ለአረጋዊያኑ የምዛ ግብዥ ከማድረግ በተጨማሪ የአልባሳት ድጋፍ ተደርጓል። ድጋፉን ከተማ አስተዳደሩ ከወሎ ዩኒቨርሲቲና ከፍሬው የአረጋውያን በጎ አድራጎት ማህበር ጋር በጋራ ያዘጋጁት መሆኑንም ተናግረዋል።
Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ባየሽ ኮልፌ⬆️
"ተወዳጇ አርቲስት አልማዝ ሀይሌ(ማሚ) 74ኛ አመቷን ኮልፌ ተገኝታ ከብቸኞቹ አረጋውያን እና ህፃናቱ ጋር እንዲህ በፍቅር አክብራለች! የባይሽ ኮልፌ ቤተሰብን ደስ እያላት ተቀላቅላለች! "እስከ ዕለተ ሞቴ በምችለው ሁሉ ከእናንተ ጋር ነኝ"ብላናለች!!ማሚዬ ረጅም እድሜ ከጤና ጋር እንመኝልሻለን!!!ሁሌም ሳቂልን! እንኳን አደረሰን! "ለመልካም ስራ ረፍዶ አያውቅም!!" ባይሽ ኮልፌ
@tsegabwolde @tikvshethiopia

#ADDISABEBA
በአዲስ አበባ ከተማ የአዲስ ዓመት በዓል የድንገተኛ አደጋና ከወንጀል ድርጊቶች ነጻ በሆነ መልኩ በሰላማዊ መንገድ መከበሩን የከተማዋ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። የኮሚሽኑ የኢንዶክትሪኔሽንና የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮማንደር ፋሲካ ፈንታው ለኢዜአ እንደገለጹት፤ የአዲስ ዓመት በዓል ከዋዜማው ጀምሮ እጅጉን #ሰላማዊ በሆነ መልኩ ተከብሯል። ይህ ዜና እስከተዘገበበት ድረስ “በትራፊክ አደጋ ሰው አልሞተም፤ ከባድ የአካል ጉዳት አልደረሰም፤ ከጸጥታና ከወንጀል ጉዳይ ጋር በተያያዘም ምንም የተከሰሰተ ነገር የለም” ብለዋል።
Via ኢዜአ

ሁላችሁም እንኳን አደረሳችሁ ተብላችኃል 🇪🇹
"ሻለቃ ደሳለኝ መስፍን ነኝ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ እንኳን ለ2012 ዓ/ም አዲስ ዓመት በሠላም አደረሳችሁ። ከሱዳን አብዬ ሠላም ማስከበር UNISFA FHQ LFE"
.
.
"መቶ አለቃ ብስራት አድማሱ ነኝ ከሱዳን አብዬ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብና በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ ላሉት ለጀግናው የመከላከያ ሠራዊታችን አባላትና እኛን ለሚናፍቁን ቤተሰቦቻችን። መልካም አዲስ ዓመት! እንወዳቹሀለን!"
TIKVAH-ETH በአብዬ ሠላም ማስከበር ላይ ለምትገኙ ቤተሰቦቻችን በሙሉ እንኳን አደረሳችሁ!! መልካም አዲስ አመት ለማለት ይወዳል!!
ፎቶ📸ፋይል

በቡራዩ ከተማ በሚገኝ የኦሮሚያ ፖሊስ ካምፕ ላይ በትናንትናው እለት የቦምብ ጥቃት ደርሷል!
የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳስታወቀው፥ በቡራዩ ከተማ በሚገኝ የኦሮሚያ ፖሊስ ካምፕ ላይ በትናንትናው እለት የቦምብ ጥቃት ደርሷል። በትናንትናው እለት ከምሽቱ 1 ሰዓት ከ30 ደቂቃ ገደማ ሽፍታ በወረወረው የእጅ ቦምብ በደረሰው ጥቃትም በ9 ሰዎች ላይ ቀላል ጉዳት መድረሱን ተገልጿል።
በጥቃቱ ጉዳት ከደረሰባቸው ውስጥ አንዱ የፖሊስ አባል እዛው ህክምና ያገኘ ሲሆን፥ ሎሌች ቀሪ ስምንት ሰዎች ደግሞ ለህክምና አዲስ አበባ ወደ ሚገኘው የፖሊስ ሆስፒታል ተወስደዋል። ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ፖሊስ ሆስፒታል ከተወሰዱት ውስጥም አብዛኞቹ ህክምና ወስደው በመመለስ ላይ መሆኑናቸውንም ቢሮው አስታውቋል።
በትናንት ምሽቱ የቦምብ ጥቃት ጉዳት ከደረሰባቸው ውስጥ አንዷ በካምፑ ውስጥ ለሚገኙ ፖሊሶች ምግብ አዘጋጅ እንደሆነችም ተገልጿል። በአሁኑ ወቅትም በኦሮሚያ ፖሊስ ካምፕ ላይ ጉዳት በማድረስ የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው እየተጣራ መሆኑንም ነው ቢሮው ያስታወቀው።
Via FBC

ናሚቢያ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርትን በኢንተርኔት መረብ ልትሰጥ ነው!
ተቀማጭነቱ ዊነድ ሆክ የሆነው የናሚቢያው ኮንስታንቲያ የግል ትምህርት ቤት እንዳስታወቀው በ2020 እ.ኤ.አ በናሚቢያ ሙሉ በሙሉ በበየነ-መረብ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርትን መስጠት እንደሚጀምር አስታውቋል፡፡ ትምህርት ቤቱም ከናሚቢያ ትምህርት ሚኒስቴር እውቅና ማግኘቱ ተገልጿል።
“የናሚቢያን የትምርት ጉድለት ማረም አልተቻለም በሚል የሚነሳውን ትችት በመቅረፍ አለም አቀፍ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ላለፉት ሰባት አመታት ተሞክሮ ውጤታማነቱ ተረጋግጧል “ያሉት የትምህርት ቤቱ ርእሰ መምህር አማንዳ ሞርስች ናቸው፡፡ ይህም የትምህርት ጥራት በሁሉም ቦታና ግዜ ማረጋገጥን ኢላማ ያደረገ ነው ያሉት አማንዳ ሞርስች፡፡
“ትምህርት ቤታችን በናሚቢያ እ.ኤ.አ በ2020 ቢጀምርም ተማሪዎች ኢንተርኔት ባለበት የትኛውም ስፍራ ወይም ሀገር ሆነው በማንኛውም የአንድሮይድ ሲስተም፣በሞባይልና ኮሚፒውተር አለያም ላፕ ቶፕ ተጠቅመው መተግበሪያ ማውረድ ሳይጠበቅባቸው መማር ይችላሉም “ነው ያሉት።
ተማሪዎችም ሆኑ ወላጆች አገልግሎቱን ለማግኘት የመለያ ቁጥር 24/7 በማስገባት ትምርቱን በድምጽ፣ በምስልና ፈተናዎችን መውሰድ ይቻላል ነው የተባለው። በፈተናውም 50 በመቶ ካመጡ ወደ ቀጣዩ ምእራፍ መሸጋገርና ውጤታቸውንም በፍጥነት እዛው ማየት እንደሚችሉም ተገልጿል። ተማሪዎች የፈተናም ሆነ መጽሀፍትን ማውረድ አይጠበቅባቸውም ሲሉ ሞርስች መናገራቸውን የዘገበው ሲጂቲኤን ነው።
Via CGTN/ENA

ሰላማችን የፀና ይሁን!
በዕንባ የተሞላው የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የአዲስ ዓመት መልእክት፦
"...እግዚአብሔር ቸርነቱን፣ ረድኤቱን የሚያወርድልን እኛ #ሰላማዊያን የሆንን እንደሆነ ነው። እኛ በእግዚያብሄር ትዕዛዝ የቆምን እንደሆነ ነው።...ሰላማችንን የፀና እንዲሆን የእግዚያብሄር ረድኤትም ከኛ ጋር እንዲሆን ሰላማችን የፀና ይሁን!"
በድጋሚ መልካም አዲስ አመት!

ሥጋትና ተስፋን ያረገዘው የ2012 አገራዊ ምርጫ!
ኢትዮጵያ በ2012 ዓ.ም ብሔራዊ ምርጫ ታካሂዳለች። ምርጫውን አሳሳቢ ያደረገው ላለፉት አራት ዓመታት ኢትዮጵያን ሲንጣት ከቆየው ሕዝባዊ ዓመፅ ቀጥሎ መምጣቱ ብቻ ሳይሆን፤ ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ ተከፋፍሏል ተብሎ በተሠጋበት፤ በሽብርተኝነት ተፈርጀው የነበሩ የፖለቲካ ድርጅቶች ወደ ፉክክሩ እንገባለን ባሉበት ወቅት የሚካሄድ በመሆኑ ነው።
ምርጫው ምናልባትም ከምርጫ 1997 ዓ.ም ወዲህ ከፍተኛ ፉክክር የሚታይበትና የአገሪቷን መጪውን እጣ ፈንታ ይወስናል ተብሎ የተጠበቀ ቢሆንም፤ ምርጫው ፍትሐዊና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ተካሂዶ በህዝብ የተመረጠ መንግሥት ወደ መንበረ ዙፋኑ እንዳይመጣ ሊያደርጉ የሚችሉ ተግዳሮቶች ይኖሯሉ በሚል በብዙዎች ዘንድ ሥጋት አንዣቧል። ሥጋቶቹ ምንድ ናቸው? መፍትሄዎቹስ? በማለት አዲስ ዘመን የተለያዩ የፖለቲካ ምሁራኖችን አነጋግሯል።
በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ትምህርት ክፍል መምህርና የብሉ ናይል የውሃ የምርምር ተቋም ተመራማሪ ተባባሪ ፕሮፌሰር ውሂብእግዜር ፈረደ እንደሚገልፁት፤ በአፍሪካ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ሽንፈታቸውን በፀጋ ስለማይቀበሉና ገዢው ፓርቲ በበኩሉ በምርጫው ቢሸነፍም ሽንፈቱን በፀጋ ተቀብሎ ሥልጣኑን በሰላማዊ መንገድ ስለማያስረክብ በቅድመና በድህረ ምርጫ ግጭቶች ይቀሰቀሳሉ። በኢትዮጵያም ከመቼውም ጊዜ የገዘፉ ችግሮች ስላሉ በ2012 ዓ.ም የምታካሂደው ምርጫ በተያዘለት ጊዜ ቢካሄድ ግጭቶች የሚባባሱበት ሁኔታ ያጋጥማል።
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-13-2

የባንክ ቤት ሰራተኛው የ3,333,333 ብር የሽልማት ቼኩን ተረከበ!
በወላይታ ዞን ጉኑኖ ከተማ ነዋሪ የሆነው አቶ ማቲዎስ ሾንጋ በትንሳዔ ሎተሪ 1ኛ ዕጣ በሁለት ነጠላ ትኬቶች የ3,333,333 ብር እድለኛ በመሆኑ የሽማት ቼኩን በዛው በሚኖርበት ከተማ ተረከበ፡፡ እድለኛው የ27 ዓመት ወጣት ሲሆን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጉኑኖ ቅርንጫፍ የባንክ ባለሙያ ነው፡፡ ከሥራ ሲወጣ በ20 ብር የቆረጣቸው ሁለት ነጠላ ትኬቶች ዕድለኛ ሊያደርጉት እንደቻለ ተናግሯል፡፡ ዕድለኛው በደረሰው ገንዘብም በወላይታ ሶዶ ከተማ ቤት ለመግዛት እንዳሰበ ገልጿል፡፡
Via የብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር

የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዘዳንት መንግስቱ ኃ/ማርያም ፈፅሞ ወደኢትዮጵያ መመለስ አይፈልጉም!
ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም ወደ ኢትዮጰያ ምህረት ቢደረግለትም የመመለስ ፍላጎት የለውም። በዝንቧቤ ለመንግስት ጋዜጣ የሚሰራ አንድ ጋዜጠኛ እንደተናገረው የቀድሞ የኢትዮጰያ ፕሬዝዳንት እና የአሁኑ የዝነንቧቤ ፕሪዝዳንቱ ፀጥታ አማካሪ ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም የኢትዮጰያ መንግስት ከተፈረደበት ፍርድ ምህረት በያደርግለት እንኳን ሀገሩ #ፈፅሞ መሄድ እንደማይፈልግ ጋዜጠኛው ከሶስት ወር በፊት ቢሮው ለስራ በሄደበት እንዳጫወተው ገልጿል። "እድሜው ቢገፋም ሰውነቱ አሁንም ለስራ ብቁ ነው። እኛ ዝምቧቤያዉያን በሚድያ አይተነው #አናውቅም። ቢሮው ስንሄድ የመጫወት ችግር የለበትም። ድምፁን እንድትቀዳ፣ ፎቶ እንድታነሳው ወይንም ማስታወሻ ይዘክ እንድታወራው አይፈልግም። ወዳጁ ሙጋቤ ቢሞትም ፕሬዝዳንት ምንጋጋዋ ለመንግስቱ ከፍተኛ አክብሮት አለው። ወዳጅነታቸውም የቆየ ነው።" ብሏል ጋዜጠኛው።
ምንጭ፦ ተስፋዬ ጌትነት/ከካፒታል ጋዜጣ/

#NewsAlert
ከቡራዩ ጥቃት ጋር ተያይዞ 22 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ። ከቡራዩ ጥቃት ጋር ተያይዞ የኦነግ- ሸኔ አባላትና ሌሎች ከእነሱ ጋር ትስስር ያላቸው 22 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን EBC የኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃን ጠቅሶ ዘግቧል።

የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ዛሬ 10፡00 ሰዓት ላይ ይለቀቃል!
የዘንድሮው የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ዛሬ ከሰዓት በኋላ እንደሚለቀቅ የትምህርት ሚኒስቴር የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ወ/ሮ ሀረጓ ማሞ ለኢቢሲ ተናግረዋል፡፡ ውጤቱ ዛሬ ከ10 ሰዓት ጀምሮ በሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ እንደሚለቀቅ ወ/ሮ ሀረጓ ገልፀዋል፡፡ ተፈታኞች ውጤታቸውን በኤጀንሲው ድረ-ገጽ www.neaea.gov.et/app. ወይም neaea.gov.et እንዲሁም በአጭር የጽሁፍ መልእክት 8181 ላይ ID- ብለው የአድሚሽን ቁጥራቸውን በማስገባት መመልከት እንደሚችሉ አስታውቀዋል፡፡
Via #EBC

ከትምህርት ሚኒስቴር!
የ10ኛ ክፍል ውጤት ዛሬ ከ10 ሠዓት ጀምሮ እንደሚለቀቅ ተገልጿል፡፡ የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የ10ኛ ክፍል ውጤት ዛሬ መስከረም 02/2012 ዓ.ም ከ10 ሰዓት ጀምሮ እንደሚለቀቅ ገልጾ ተማሪዎች በኤጀንሲው ድህረ ገጽ www.neaea.gov.et/app . neaea.gov.et ወይም በአጭር የጽሁፍ መልእክት 8181 ላይ ID- በማለት አድሚሽን ቁጥራቸውን በማስገባት መመልከት እንደሚችሉ አሳውቋል፡፡
ምንጭ፦ ትምህርት ሚኒስቴር