TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.5K photos
1.52K videos
215 files
4.13K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
ክፍት የስራ ቦታ ማስታወቂያ...

#ሰላም_ለኢትዮጵያ አስጎብኚና የጉዞ ወኪል!
አሶሳን በተኩስ ሲያውካት ያመሸው የፖሊስ አባል በቁጥጥር ስር ዋለ!

ባልተገባ ስነ-ምግባር በስካር መንፈስ በከፈተው ተኩስ የአሶሳ ከተማ ነዋሪዎችን ጸጥታ ሲያውክ ያመሸውን የፖሊስ አባል በቁጥጥር ስር ማዋሉን የከተማው ፖሊስ አስታወቀ።

የከተማው ፖሊሰ አዛዥ ኮማንደር አኑር ሙስጠፋ እንዳስታወቁት ትናንት ከምሽቱ አምስት ሰዓት ላይ አንድ የጸረ-ሽምቅ ፖሊስ አባል በስካር መንፈስ በመነሳሳት በከፈተው ተኩስ የአካባቢውን ሰላም አውኳል።

ግለሰቡ በቁጥጥር ሥር ሊያውሉት የሞከሩ ሌሎች የጸጥታ ሃይሎች ላይም መተኮሱን የገለጹት አዛዡ በዚህም የአካባቢውን ጸጥታ ለደቂቃዎች አውኮት እንደነበር አመልክተዋል።

የጸጥታ ሃይሎች የግለሰቡን ትጥቅ ያስፈቱ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በከተማው ወረዳ ሁለት ፖሊስ ጣቢያ በቁጥጥር ሥር ውሎ ምርመራ እየተደረገበት እንደሚገኝ አስታውቀዋል።

ግለሰቡ ባካሄደው ተኩስም ሆነ የጸጥታ ሃይሎች በቁጥጥር ሥር ለማዋል ባደረጉት ጥረት በሰውና በንብረት ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለም ኮማንደር አኑር ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት አስረድተዋል።

በአሁኑ ሰዓት ነዋሪው ዕለታዊ ተግባሩን በተረጋጋ ሁኔታ እያከናወነ እንደሚገኝ ገልጸው በጎ ፈቃደኛ ወጣቶችን እና ህብረተሰቡን ባሳተፈ መልኩ የተቀናጀ የፀጥታ ማስከበር ሥራ መቀጠሉን አዛዡ ጨምረው ገልጸዋል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የካሜሩኑ አምባሳደር አ/አ ውስጥ ሞተው ተገኙ!

በኢትዮጵያ የካሜሩን አምባሳደር ጃኩዌዝ አልፍሬድ ሞተው ተገኙ። አምባሳደር ጃኩዌ ትናንት በአዲስ አበባ መኖሪያ ቤታቸው ሞተው እንደተገኙ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ነቢያት ጌታቸው ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል። ለአምባሳደሩ ሞት ምክንያቱ በመጣራት ላይ እንደሆነ ተሰምቷል።

ምንጭ፦ ኢትዮ ኤፍ ኤም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለጥንቃቄ!

"ይህ የሚታየው አደጋ የተከሰተው ከቂሊንጦ ወደ ኮዬ ፈጬ ሰፈር መኪና ለመዝረፍ ታቅዶ የነበር ሲሆን፤ መጀመሪያ ሊፍት እንደመጠየቅ ብለው ነበር እና ለመዝረፍ ተብሎ በተወረወረ ድንጋይ የደረሰ አደጋ ነው። ጋቢና ከሹፌሩ አጠገብ በነበረው ሰው ላይ ቀለል ያለ ጉዳት ደርሶ ህክምና ላይ ይገኛል። ይሄ የሆነው ሀሙስ ከምሽቱ 2:30 ነው፤ ከዚህ አደጋ በመማር ሰዎች እንዲጠነቀቁ ነው። የታቀደው ዝርፊያ ሹፌሩን መትተው አቅጣጫ ስቶ ሲጋጭ እነሱ መኪናውን ለመውሰድ ነው።" #Lid

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ትምህርት ሚኒስቴር

#በመፈናቀል ምክንያት ትምህርት #ያቋረጡ_ተማሪዎች ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ ከቁሳቁስ እስከ ምገባ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሼክ መሐመድ ሁሴን አል አሙዲ በኢትዮጵያ የግሉ ክፍለ ኢኮኖሚና በኢንቨስትመንት መስክ ከፍተኛ ተሳትፎ በማድረግ በዋቢነት ይጠቀሳሉ፡፡ በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ውስጥ 74 ኩባንያዎች እንዳሏቸውም መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ከእነዚህ ውስጥም 26ቱ በሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ አመራር ሥር ይተዳደራሉ፡፡

አንዳንዶቹ ኩባንያዎች በተለያየ መንገድ ተጨማሪ ኢንቨስትመንት እየፈሰሰባቸውና የማስፋፊያ ሥራዎችም እየተካሄዱባቸው እንደሚገኙ ታውቋል፡፡ በሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ሥር ከሚንቀሳቀሱ ኩባንያዎች በሦስቱ ላይ ከ286 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በመመደብ የማስፋፊያ ሥራ ያካሄደባቸውን ድርጅቶች ከሰሞኑ አስመርቋል፡፡

ሐሙስ ነሐሴ 2 ቀን 2011 ዓ.ም. በዘመናዊ መንገድ የታደሱትና የማስፋፊያ ሥራ ተከናውኖባቸው የተመረቁት ሦስቱ ኩባንያዎች ሰሚት ፓርትነርስ፣ አዲስ ጋዝና ፕላስቲክ ፋብሪካ እንዲሁም ዋንዛ ፈርኒሺንግ የተሰኙት ናቸው፡፡ በሦስቱ ኩባንያዎች ላይ 286 ሚሊዮን ብር ወጪ በማድረግ ዕድሳትና ማስፋፊያ እንደተከናወነባቸው የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አረጋ ይርዳው (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡

Via #ሪፖርተር
ፎቶ፡ አዲስ ፎርቹን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የቺኩንጉንያ ወረርሽኝ በድሬዳዋ ተከስቷል ተባለ!

#በወባ ትንኝ ንክሻ የሚተላለፈው #የቺኩንጉንያ ቫይረስ ወረርሽኝ በድሬዳዋ #መከሰቱን የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ አስታውቋል። ትኩሳትና የመገጣጠሚያ አካላት ሕመም ያስከትላል። በሲዲሲ መረጃ መሰረት መከላከያ ክትባትም ሆነ መድሐኒት የለውም።

ምንጭ፦ እሸት በቀለ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቺኩንጉንያ ቫይረስ ምንድነው? ቺኩንጉንያ ቫይረስ (ቺክቭ) በትንኞች አማካኝነት ወደ ሰዎች ይተላለፋል። ቺክቭ ከፍተኛ የሆነ ትኩሳትና ድንገት የሚከሰት የመገጣጠሚያ ህምምን ያስከትላል። ቺክቭ አብዛኛው ጊዜ ሞትን አያስከትልም፣ ነገር ግን የሚወልዳቸው የጤና እክሎች ነገሮችን ከመስራት እስከማገድ የሚደርሱ ሆነው በተወሰኑ ሰዎች ላይ ደግሞ ለከባድ ተጨማሪ በሽታ ሊዳርጉ ይችላሉ። ቫይረሱን እና ኢንፈክሽኑ የምንከላከልባቸው መንገዶችን የተመለከተ እውቀት መጨበጥ ወሳኝ ነው። የሚወስዷቸው ጥንቃቄዎች ከሌሎች በትንኞች የሚመጡ በሽታዎችም ይከላከልልዎታል።

#DCSSH
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቺክቭ የሚስፋፋባቸው መንገዶች ምንድናቸው? ቺክቭ በአብዛኛው ጊዜ በቀን ጊዜ በሚናከሱ ትንኞች አማካኝነት ወደ ሰዎች ይተላለፋል። ትንኞቹ በቫይረሱ የተለከፈ ሰው በሚነክሱበት ጊዜ ይለከፋሉ። እነዚህ የተለከፉ ትንኞች ደግሞ ቫይረሱ በንክሻ ወደ ሌሎች ሰዎች ያስተላልፉታል። ቺክቭ በወሊድ ጊዜ አከባቢ ከእናት ወደ ልጅ የሚተላልፍበት እድል እጅግ ዝቅተኛ ነው። ቺክቭ ከሰዎች ጋር በሚደረግ ግንኙነት፣ ለምሳሌ በንክኪ ወይ መሳሳም፣ አይተላለፍም።

#DCSSH
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የቺኩንጉንያ ወረርሽኝ በድሬዳዋ!

በድሬዳዋ አስተዳደር የተከሰተውን የቺኩንጉንያ ወረርሽኝ ለመከላከል እየሰራ መሆኑን የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ አስታውቋል። የጤና ቢሮው በዛሬው እለት በሰጠው መግለጫ እንዳስታወቀው፥ ቺኩንጉንያ የተባለው የበሽታ ምልክት እስካሁን በ3 ሺህ 756 ሰዎች ላይ ተስተውሏል።

ሆኖም ግን በሽታው ከወባ እና ከደንጌ ጋር ተመሳሳይነት ስላለው ሁሉም ታማሚዎች ቺኩንጉንያ በተባለው በሽታ ስለመያዛቸው ሙሉ በሙሉ እንዳልተረጋገጠም ነው ቢሮው ያስታወቀው። የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ፉአድ ከድር እንደተናገሩት፥ በ10 ናሙናዎች ላይ በተደረገ ናሙና አራቱ ቺኩንጉንያ መሆናቸው በመለየቱ በሽታው በወረርሽኝ መልክ መከሰቱን ተረጋግጧል። #ከበሽታው ጋር በተያያዘ ግን እስካሁን የተመዘገበ ሞት እንደሌለም አስታውቀዋል። ቺኩንጉንያ የተባለው በሽታ “ኤደስ” በተባለች ነብሳት አማካኝነት የሚተላለፍ መሆኑንም ነው ዶክተር ፉአድ ያስታወቁት።

https://telegra.ph/DDC-08-13

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የቺክቭ ምልክቶች ምንድናቸው? አንድ ሰው በተለከፈ ትንኝ ከተነከሰ በኋላ ከ 3 እስከ 7 ቀናቶች ውስጥ ምልክቶች ይታዩበታል። የቺክቭ ምልክቶች ከሰው ወደ ሰው የሚለያዩ ሲሆን፣ የሚከተሉትን ያጠቃልላሉ፦
 በድንገት የሚከሰት ከፍተኛ ትኩሳት (>102°F)
 ከባድ የሆነ የመገጣጠሚያ ህመም በተለይ በክንዶች ወይም እግሮች ላይ
 ራስ ምታት
 የጡንቻ ህመም
 የጀርባ ህመም
 ሽፍታ (~50% ተጠቂዎች ላይ የሚያጋጥም)

በብዛት በሚከተሉት ሰዎች ላይ ይስተዋላሉ፦
 ህጻናት (<1 ዓመት)
 አረጋውያን (>65 ዓመት)
 እንደ ስኳር በሽታ፣ ከፍተኛ የደም ግፊት ወዘተ በመሳሰሉ ስር የሰደዱ በሽታዎች የተጠቁ ሰዎች።

*ከላይ የተጠቀሱት ሰዎች በትንኝ እንዳይነከሱ ከሌሎች የበለጠ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርባቸዋል።*

ቺክቭ እንዴት ነው የሚታከመው? ቺክቭ ለማከም የሚውል ተለይቶ የታወቀ መድሀኒትም ይሁን ክትባት #የለም

#DCSSH

#share #ሼር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በቺክቭ ተጠቂቻለሁ የሚል ጥርጣሬ ካደረብኝ ምን ማድረግ አለብኝ? ትኩሳት እና የመገጣጠሚያ ህመም ለመቀነስ መድሀኒቶችን መጠቀም ጥቅም ሊኖረው ይችላል። ሐኪም ያማክሩ።

ቺክቭ ይዞኝ ሉሆን ይችላል የሚል ጥርጣሬ ካደረብዎ፦
 የታይብዎ ምልክቶችን መዝግበው በመያዝ ወደ ሐኪም ይሂዱ።
 ራስዎን ተጨማሪ በትንኝ ከመነከስ ይከላከሉ።
 በቺክቭ ከተያዙ በሽታው ወደ ሌሎች ሰዎች ላለማስተላለፍ እራስዎን ከትንኝ ንክሻ መከላከል ይኖርብዎታል።

ምን ማድረግ አለብኝ?

#ይልበሱ
ረዥም፣ ቀለል ያለ እና ቀላል ቀለም ያለው ልብስ ይልበሱ።

#ፈሳሽ_ማድረቅ
እቤት ውስጥም ከቤት ውጪም ያለ ማንኛውም ያቆረ ውሃ ያስወግዱ።

#ማታ እና #ጠዋት
ማታና ጠዋት ትንኞች በብዛት የሚንቀሳቅሱበት ጊዜ በመሆኑ በተቻለ መጠን ከቤት አይውጡ።

#DCSSH

#share #ሼር

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለ31 ተማሪዎች ነፃ የትምህርት ዕድል ተሰጠ!

የቻይና መንግስት ለ31 ኢትዮጵያዊያን ተማሪዎች ነፃ የትምህርት ዕድል ሰጠ። በኢትዮጵያ የቻይና ኢምባሲ ነጻ የትምሀርት አድሉን አስመልከቶ ዛሬ ረፋድ 31 ተማሪዎች ነፃ የትምህርት ዕድል የምስክር ወረቅት ሰጥቷል። የትምህርት እድሉ የቻይና መንግስት ለኢትዮጵያ አቻው በሰጠው የትምህርት ነጻ አድል መሰረት ከመላው የአገሪቱ ዩንቨርሲቲዎች በተሰጠ ኮታ ተወዳድረው ላለፉት እንደተሰጠ በፕሮግራሙ ላይ ተጠቅሷል።

በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ታን ጃይን ነፃ የትምህርት ዕድል ለተሰጣቸው ተማሪዎች ፣ በኢትዮጵያና በቻይና ህዝብ እና መንግስት መካከል የወዳጅነት ድልድይ ሆናችሁ መገኘት አለባችሁ ብለዋል። ወደ ቻይና በምታድርጉት ጉዞም ከማንኛውም ሰው ምንም አይነት ምግብ ነክ ነገር መልዕክት አድርሱልኝ ከተባላችሁ እንዳትቀበሉ ሲሉም አምባሳደሩ አሳስበዋል።

ምንጭ፦ ኢትዮ ኤፍ ኤም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በኢትዮጵያ የካሜሩን አምባሳደርና በአፍሪካ ኅብረት የካሜሩን አምባሳደር እንዲሁም ልዩ መልዕክተኛ ጃኮስ አልፍሬድ ሰኞ፣ ነሐሴ 6/2011 ማለዳ ላይ ሞተው መገኘታቸውን የአፍሪካ ኅብረት ዋና ፀሐፊ #ሙሳ_ፋኪ_መሐመት በትዊተር ገፃቸው ላይ አስታውቀዋል። በአፍሪካ ኅብረት ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ ሞተው የተገኙት አምባሳደሩ፥ የህልፈታቸው ምክንያት በውል አልታወቀም። የአፍሪካ ኅብረትም #ለወዳጆቻቸው እና ለመላው #የካሜሩን ሕዝብ መፅናናትን ተመኝቷል።

Via #አዲስማለዳ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱና የተጠሪ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮችና መላ ሰራተኞች በተገኙበት የ2011 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ እና የ2012 ዓ.ም ዕቅድ ላይ ውይይት አካሂደዋል።

Via ትምህርት ሚኒስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምላሽ እየጠበቅን ነው!

የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ፈተና/የ12ኛ ክፍል/ #ውጤትን በተመለከተ ተማሪዎችና የተማሪ ወላጆች እየጠየቃችሁ ያለውን ጥያቄ ለሚመለከተው ክፍል አቅርበን ምላሽ እየጠበቅን እንገኛለን፤ የሚደርሰን መረጃ ካለ የምናቀርብላችሁ ይሆናል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢትዮጵያ በአካዳሚ አዋርድ...

“የንፋሱ ፍልሚያ” የተሰኘውና በውጭ አገር ዜጎች ተደርሶ ዳይሬክት የተደረገው ፊልም ኢትዮጵያ በአካዳሚ አዋርድ ዕጩነት አቀረበችው። በዕጩነት የቀረበው ፊልም በጊዜና ቴክኒካዊ ችግሮች ሳቢያ ከሌሎች #አገርኛ ፊልሞች ጋር ሳይወዳደር በብቸኝነት መመረጡም ታውቋል። በአውሮፓ የዘመን ቀመር 1929 የተመሰረተውና ተቀማጭነቱን በአሜሪካ #ካሊፎርኒያ ያደረገው አካዳሚ አዋርድ ዘንድሮ ለ92ኛ ጊዜ በየካቲት 2020 ይካሄዳል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሰበር_ዜና

የ12ኛ ክፍል ውጤት ዛሬ ከአንድ ሰዓት በኋላ ይለቀቃል ተባለ። የአገር አቀፍ ፈተናዎች ኤጀንሲ የ12ኛ ከፍል ውጤትን አስመለክቶ ከአንድ ሰዓት በኋላ መግለጫ ለመስጠት መገናኛ ብዙሃነን ጠርቷል። መግለጫው ከተጠናቀቀ በኋላ ተፈታኞች ከ11 ዐሰት ጀምሮ በኤጀንሲው ድረገጽ ላይ ገብተው ውጤታቸውን ማየት እንደሚችሉ ተገልጿል።

Via ETHIO FM
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከ11:00 በኃላ ውጤታችሁን ማየት ትችላላችሁ!

የ12ኛ ክፍል/የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤትን በተመለከት ከደቂቃዎች በኃላ መግለጫ ይሰጣል መግለጫው ከተጠናቀቀ በኋላ ተፈታኞች ከ11 ሰዓት ጀምሮ በኤጀንሲው ድረገጽ ላይ ገብታችሁ ውጤታቸውን ማየት እንደምትችሉ ተገልጿል።

ምንጭ፦ ኢትዮ ኤፍ ኤም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ውጤትን በተመለከተ...

የትምህርት ሚኒቴር ዴኤታን ወ/ሮ ፅዮን ተክሉን በስልክ እነጋግሬያቸው ነበር ከጥቂት ደቂቃዎች በኃላ መግለጫ እንደሚሰጥ #አረጋግጠውልኝ ተማሪዎችም ውጤታቸውን ከ11:00 በኃላ ማየት እንደሚችሉ ገልፀውልኛል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
app.neaea.gov.et

ተማሪዎች ውጤታችሁን በሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ድረ-ገጽ app.neaea.gov.et በመግባት Admission በሚለው ሳጥን ውስጥ የመፈተኛ ቁጥራቸውን (Registration Number) በማስገባትና go የሚለውን አንዴ click በማድረግ መመልከት ትችላላችሁ።

#ሼር #share

@tsegabwolde @tikvahethiopia