TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
ደራርቱ ውሳኔዋን አጥፋለች!

ደራርቱ ቱሉ ከኦሎምፒክ ኮሚቴ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልነት ራሷን ለማግለል ያሳለፈችውን ውሳኔ አጠፈች። በደብረ ብርሀን ከተማ በሚደረው የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ከሥራ አስፈፃሚነት ለመልቀቅ መወሰኗን የተናገረችው ደራርቱ በጠቅላላ ጉባኤው በርካታ ሰዎች ውሳኔዋን እንድታጥፍ ግፊት ማሳደራቸውን የስፖርት ጋዜጠኛ ኦምና ታደለ ለጀርመን ራድዮ ተናግሯል። ኦምና እንደሚለው ደራርቱ ግፊት ያሳደሩ ሰዎችን #ማሳዘን አልፈለገችም።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንን በፕሬዝዳንትነት የምትመራው ደራርቱ በውሳኔ አሰጣጥ ረገድ የምትመለከታቸውን ሕጸጾች ከዚህ በኋላ የማይታረሙ ከሆነ ከኦሎምፒክ ኮሚቴ ሥራ አስፈፃሚነት ራሷን እንደምታገል አስጠንቅቃለች።

በሁለት የኦሎምፒክ ውድድሮች የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ የነበረችው ደራርቱ ዶክተር አሸብር ወልደ ጊዮርጊስ ከሚመሩት የኦሎምፒክ ኮሚቴ ሥራ አስፈፃሚ አባልነት መልቀቋን ያሳወቀችው በዛሬው ዕለት ነበር። «ከዶክተር አሸብር ወልደ ጊዮርጊስ እና እርሳቸው ከሚመሩት የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ጋር በተፈጠረ መቃቃር ምክንያት» ከኦሎምፒክ ኮሚቴ ሥራ አስፈፃሚነት ደራርቱ ራሷን ለማግለል አስገድዷት ነበር።

ዶክተር አሸብር ሥመ-ጥሩዋን የሩጫ ንግሥት ወደ ሥራ አስፈፃሚነቷ ለመመለስ ቃል ገብተው ነበር። የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ በአማራ ክልል ደብረ ብርሀን ከተማ ጠቅላላ ጉባኤ እያካሔደ ነው።

Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
እንኳን አደረሳችሁ!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሕመድ ለ1 ሺህ 440ኛው ዓመተ ሒጅራ የኢድ-አል አድሐ (ዓረፋ) በዓል ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት፦

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ሙሉ መልዕክት👇
🏷https://telegra.ph/EID-08-10
Audio
የሀዋሳው ውይይት ከወታደራዊ ዕዝ ጋር!
ሰላም ማረጋገጥ ከተቻለ ወታደራዊ ዕዙ ግዳጁን በሁለት ወር ውስጥ አጠናቅቆ ይወጣል፤ የማይረጋጋ ከሆነ ግን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጭምር ሊታወጅ ይችላል!

በሃዋሳ ከተማ አሳቻ ሰዓትና ቦታ በመጠበቅ የሚፈፀሙ የወንጀል ድርጊቶችና የሰዎች ማንንት ላይ ያተኮሩ ትንኮሳዎች ነዋሪው ተርጋግቶ እንዳይኖርና ስጋት ውስጥ እንዲገባ አድርጓል ሲሉ የከተማዪቱ ነዋሪዎች ተናግረዋል።
 
ክልሉን እያስተዳደረ ካለው የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ አስፈፃሚ ዕዝ ጋር የከተማዪቱ ነዋሪዎች ተወካዮች በየተወያዩበት ወቅት ወታደራዊው ዕዝ እንዲያበቃና የመከላከያ ሠራዊትም ከከተማው #እንዲወጣ የጠየቁ ነበሩ።

በሌላ በኩል ደግሞ “የለም ሠራዊቱ መቆየት አለበት፤ ሰላም ያገኘነው ወታደራዊ ዕዙ፣ የመከላከያ ሠራዊትና ፌዴራል ፖሊስ ከተማዪን ከተቆጣጠሩ ወዲህ ነው” ያሉም ነበሩ። ሰላም ማረጋገጥ ከተቻለ ወታደራዊ ዕዙ ግዳጁን በሁለት ወር ውስጥ አጠናቅቆ እንደሚወጣ፤ የማይረጋጋ ከሆነ ግን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጭምር ሊታወጅ እንድሚችል ዕዙ አስታውቋል።

Via #VOAamharic
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በትግራይ በኤሊኖ ምክንያት ድርቅ ሊከሰት ይችላል!

በትግራይ ክልል ኤሊኖ ባስከተለው የዝናብ እጥረት ምክንያት ሊከሰት የሚችለውን ድርቅ ለመከላከል አርሶ አደሮች የመሬት እርጥበትን ይዞ ለማቆየት ከወዲሁ መትጋት እንዳለባቸው የክልሉ ግብርናና ገጠር ልማት ቢሮ አሳሰበ፡፡

በቢሮው የቅድመ ማስጠንቀቂያና አስቸኳይ የአደጋ ዝግጁነት ዳይሬክተር አቶ ገብረእግዚአብሄር አረጋዊ እንዳሉት በተያዘው የመኸር ወቅት በኤሊኖ የአየር መዛባት ምክንያት በክልሉ የድርቅ አደጋ ሊከሰት ይችላል የሚል ስጋት ተደቅኗል።

በዚሁ ምክንያት በትግራይ ምስራቃዊ፣ ደቡባዊ ምስራቅና ደቡባዊ ዞኖች የዝናብ መቆራረጥና የእርጥበት እጥረት መስተዋሉን ተናግረዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/TG-08-10
ታዳሚውን ያስለቀሰው የብሩክ የሺጥላ ንግግር...

"ከዛሬ ጀምሮ ይህቺ ምደገፍባት ነገር አታስፈልገኝም ለምን መሰላችሁ ሲደክመኝ ሚደግፈኝ #ኢትዮጵያዊ_ወንድም አለኝ፤ ሲርበኝ አይዞህ ብሎ የሚያበላኝ እህትና ወንድም አለኝ፤ እኔ ማውቃት ኢትዮጵያ ይህቺን ነው፤ እኔ #የኖርኩባት ኢትዮጵያ ይህቺ ነች፤ ልጄም ይህንን እውነት እንዲኖረው እፈልጋለሁ፤ #ልጆቻችንም ይሄንን እውነት የሆነ ኢትዮጵያ ኖረው እንዲያልፉ ሁሉንም ነገር #እናመቻችላቸው፤ ችግርን ከመፍጠር ይልቅ ብዙ ችግሮች አሉብን ስለ ችግሮቻችን ካወራን ችግሮቻችን አያልቁም። መሪዎቻችን ደግሞ ገና #በተመቻቸ ሁኔታ ላይ አይደሉም፤ እነሱ ላይ ብዙ ችግር አንፍጠርባቸው፤ እኛ የምንችለውን ችግር እንፍታ እነሱም ደግሞ መፍታት የሚችሉትን ያህል ችግር ይፍቱልን። የሚቀጥለው መሪ የተሻለ ወንበር እንዲያገኝ፤ የተመቻቸ ወንበር እንዲያገኝ፤ እኛንም ከዚህ በተሻለ በደንብ መምራት እንዲችል ሁሉን ነገር እኛ እናመቻችለት።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢድ ሙባረክ!

እንኳን #ለ1440ኛው ዓመተ-ሒጂራ የኢድ-አል-አድሃ (#ዓረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ። በዓሉ የሰላም፤የፍቅር፤ #የመተሳሰብ ይሁንልን!!

#TIKVAH_ETH🕋#EidAlAdha🕋#EidMubarak

@tsegabwolde @tikvahethiopia #EidMubarak
እንኳን አደረሳችሁ!

1 ሺህ 440ኛውን የአረፋ በዓል በመላዉ ሀገሪቱ በመከበር ላይ ይገኛል። በዓሉ በአዲስ አበባ ስታዲየም የእምነቱ ተከታዮች በሶላት እና በተለያዩ ሀይማታዊ ስነ ስርዓቶች በድምቀት በማክበር ላይ ይገኛሉ።

በዓሉን አስመልክተው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጅ ዑመር ኢድሪስ ለሕዝበ ሙስሊሙ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። በዚሁ መልዕክታቸው በዓሉን የተቸገሩትን በማሰብና በማካፈል በፍቅር ማሳለፍ እንሚገባ ተናግረዋል፡፡ ምዕመኑ በዓሉን ሲያከብርም እምነቱ በሚያዘው መሰረት አቅመ ደካሞችን በማሰብ፣ ያለውን በማካፈልና በማስደሰት መሆን እንዳለበትም ነው የገለጹት።

Via ኤፍ ቢ ሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አረፋ

1440ኛው የኢድ-አል-አድሐ (አረፋ) በዓል በቤኔሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች እየተከበረ ይገኛል። በክልሉ የአረፋ ሶላት ሥነ-ሥርዓት በመንጌ ወረዳ በፎቶ ይህንን ይመስላል፡፡

ፎቶ፡- ከቤኔሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አረፋ

1440ኛው የኢድ-አል-አድሐ (አረፋ) በዓል በጅማ ከተማ በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።

ፎቶ፡- TIKVAH-ETH Family
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዛሬ የፈተና ውጤት ይፋ እንደማይሆን ተገለፀ!

ከቀናት በፊት በተለያዩ የመንግስት ሀላፊዎች የፈተና ውጤት ዛሬ ነሀሴ 5 እንደሚለቀቅ ሲገለፅ ነበር። የፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ አርአያ ገ/እግዚአብሔር ከደቂቃዎች በፊት እንደገለፁት፦ "ውጤቱን ለማውጣት #ትንሽ ተጨማሪ ስራ መስራት አስፈልጎናል። ዛሬ ሳይሆን ከሁለት ቀን በሁዋላ አካባቢ ይለቀቃል። ይህ መራዘም ያስፈለገው ከዛሬው በአል ጋር በተገናኘ ሳይሆን ትንሽ ሌላ የምንሰራው ስራ ስላጋጠመን ነው" ብለዋል።

Via #EliasMeseret
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አቶ አርዓያ ገ/እግዚያብሄር የተናገሯቸው፦

√ ማክሰኞ ዕለት በኢትዮ ኤፍ ኤም ሬድዮ ጣቢያ በቀጥታ በስልክ ገብተው ከአርብ በፊት ለማድረስ እየተሰራ እንደሆነ ተናግረው ነበር።

√ ሀሙስ ዕለት ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 አቶ #አርዓያን ጠቅሶ ያወጣው ዘገባ ደግሞ ሀሙስ ወይም አርብ ከሰዓት ይፋ እንደሚሆን ነበር።

√ ሀሙስ አመሻሹን ኤጀንሲው በህጋዊና ትክክለኛ ገፁ ፈተናው ውጤት ነሃሴ 5 ነው የሚወጣው አለ። ተማሪውም ውጤቱን እንዴት መመልከት እንዳለበት ተገለፀ።

√ ዛሬ ነሃሴ 5 ነው ተማሪው ውጤቱን ለማየት ሲጠባበቅ አቶ አርዓያ ገ/እግዚያብሄር "ውጤቱን ለማውጣት #ትንሽ ተጨማሪ ስራ መስራት አስፈልጎናል። ዛሬ ሳይሆን #ከሁለት ቀን በሁዋላ አካባቢ ይለቀቃል። ይህ መራዘም ያስፈለገው ከዛሬው በአል ጋር በተገናኘ ሳይሆን ትንሽ ሌላ የምንሰራው ስራ ስላጋጠመን ነው" አሉ።

እኛ እንደTIKVAH-ETH ይቅርታ እንጠይቃለን!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"በሞራላችን ላይ ነው የተጫወቱብን" #ተማሪዎች

"ይህ ተቋም አሰራሩን ሊያስተካክልና ሊፈትሽ ይገባል" #የተማሪ_ወላጆች
.
.
የ12ኛ ክፍል/የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ፈተና/ ተፈታኝ ተማሪዎች ውጤታቸው ዛሬ እንደማይወጣ ከሰሙ በኃላ እጅግ በጣም እንዳዘኑ ገልፀዋል። ዘንድሮ ውጤታቸውን ከሚጠብቁ ተማሪዎች መካከል ያነጋገርነው ተማሪ ይህን ብሏል፦

"ከባለፈው ማክሰኞ ጀምሮ ምንም መረጋጋት አልቻልኩም፤ በዚህ ቀን ይወጣል ሲባል ስጨነቅ ነው የሰነበትኩት፤ ኤጀንሲው በሀሰተኛ መረጃ አትወናበዱ እያለ መልሶ ሀሰተኛ መረጃ ማቅረቡ ተገቢ አይደለም። በሞራላችን ላይ ነው የተጫወቱብን፤ እንዴት ለራሳቸው ልጆች አይጨነቁም? ይህን ስሜት ለማወቅ በቦታው ላይ መሆን ይጠይቃል።"

ሌላኛው አስተያየቱን እንዲሰጠን የጠየቅነው ተማሪ ደግሞ፦

"ፈተናዎች ኤጀንሲ ጭንቀታችንን ያወቀው አይመስለኝም፤ የማይወጣ ከሆነ መናገር የሚወጣም ከሆነ ትክክለኛውን መናገር ነው እንጂ አስር ጊዜ በሚዲያ እየቀረቡ የተለያየ ቀን መናገሩ ተማሪውን ካለማክበር የመነጨ ነው።"

ስለጉዳዩ የሰሙ የተማሪ ወላጆችም በነገሩ መበሳጨታቸውን ተናግረዋል። ተማሪው የተለያዩ መረጃዎችን ሲሰማ እንደሚወዛገብ ሊያውቅ ይገባል አሰራራቸውንም ሊያርሙና ሊያስተካክሉ ይገባል ብለዋል። ይህን መሰሉ ስራ ጥንቃቄ ይጠይቃል የትንንሽ ታዳጊዎችን ሞራል መጠበቅም ያስፈልጋል ሲሉ አክለዋል።

🏷የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዳይሬክተር የ12ኛ ክፍል ፈተና ዛሬ ይፋ እንደማይደረግ ከደቂቃዎች በፊት ተናግረዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠቅላይ ሚንስተር ዶ/ር አብይ አህመድ እና ኢ/ር ታከለ ኡማ ከሁለት ወራት በፊት የተጀመረውን ግዙፍ የዳቦ ፋብሪካ የግንባታ ሂደት ተመልክተዋል፡፡ ከሁለት ወራት በፊት ግንባታው የተጀመረው የዳቦ ፋብሪካ በአሁኑ ወቅት ግንባታው በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

የዳቦ ፋብሪካው ግንባታው ሲጠናቀቅ በሰዓት 80ሺ ዳቦ የሚያመርት ሲሆን መቶ ግራም ዳቦ በ0.75 ሳንቲም ለተጠቃሚው የሚያቀርብ ይሆናል፡፡ በሀገራችን በዓይነቱ የመጀመርያ የሆነው ይህ የዱቄትና የዳቦ ማምረቻ ፋብሪካ ግንባታው በ6 ወራት ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው፡፡በሆራይዘን ፕላንቴሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር ግንባታው እየተከናወነ የሚገኘው ይህ የዳቦ ማምረቻ ፋብሪካ ግንባታው ሲጠናቀቅ ለበርካታ የአከባቢው ወጣቶች የስራ ዕድል የሚፈጥር ይሆናል፡፡

Via MayorOfficeAA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኤጀንሲው ትክክለኛ የፌስቡክ ገፅ፦

ውድ የዩኒቨርስቲ መግብያ (12ኛ ክፍል) ብሄራዊ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎችና የተፈታኝ ተማሪ ወላጆች ነሐሴ 1/2011 ዓ.ም የተፈታኝ ተማሪዎች የፈተና ውጤት ዛሬ ነሐሴ 5/2011 ዓ.ም ይለቀቃል ብለን መረጃ መስጠታችን ይታወሳል፡፡ ኤጀንሲው በገጠመው ችግር ምክንያት በዛሬው እለት ውጤቱን መልቀቅ አለመቻሉን እየገለጸ ለተፈጠረው መዘግየት ይቅርታ እየጠየቀ ውጤቱን ከሁለት ቀን ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ የምንለቅ መሆኑን በትህትና እንገልጻለን፡፡

የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ

#share #ሼር

@tsegabwolde @tikvahethiopia
app.neaea.gov.et

ውድ የዩኒቨርስቲ መግብያ (12ኛ ክፍል) ብሄራዊ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎችና የተፈታኝ ተማሪ ወላጆች ነሐሴ 1/2011 ዓ.ም የተፈታኝ ተማሪዎች የፈተና ውጤት ዛሬ ነሐሴ 5/2011 ዓ.ም ይለቀቃል ብለን መረጃ መስጠታችን ይታወሳል፡፡ ኤጀንሲው በገጠመው ችግር ምክንያት በዛሬው እለት ውጤቱን መልቀቅ አለመቻሉን እየገለጸ ለተፈጠረው መዘግየት ይቅርታ እየጠየቀ ውጤቱን ከሁለት ቀን ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ የምንለቅ መሆኑን በትህትና እንገልጻለን፡፡

የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ

#share #ሼር

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፋሲል ከነማ አሸነፈ!

በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ቅድመ ማጣርያ የመጀመርያ ጨዋታ በሜዳው የታንዛኒያው አዛምን የገጠመው ፋሲል ከነማ በበዛብህ መለዮ ጎል 1-0 አሸንፏል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዶ/ር አብይ በኡድሁያ ፕሮግራም ላይ!

ዶ/ር አብይ አህመድ እና ኢ/ር ታከለ ኡማ የአረፋ በዓልን ምክንያት በማድረግ በኢትዮጵያ ቅዱስ ቁርዓን ማህበር በተዘጋጀው የኡድሁያ ፕሮግራም ላይ ተገኝተዋል፡፡ ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ እና ኢ/ር ታከለ ኡማ የዑመር ኢብኑ አል-ኸጠብ የቁርዓን ት/ቤት ከወላጅ አልባ ህፃናት ጋር የአረፋ በዓልን ለማክበር ባዘጋጀው ፕሮግራም ላይ ተገኝተዋል፡፡ የዑመር ኢብኑ አል-ኸጠብ ት/ቤት ከ700 በላይ የሚሆኑ ወላጅ አልባ ህፃናትን እና አቅመ ደካሞችን የሚደግፍ ማህበር ነው፡፡ የበዓል ፕሮግራሙ ላይ ንግግር ያደረጉት ዶክተር አብይ አህመድ ለህፃናቱ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
እቴጌ መነን ትምህርት ቤት!

ጠቅላይ ሚኒስተር ዶክተር አብይ አህመድ እና ኢንጂነር ታከለ ኡማ እቴጌ መነን ት/ቤት በመገኘት እድሳቱን ጎብኝተዋል፡፡ ዶክተር አብይ አህመድ እና ኢንጂር ታከለ ኡማ በ2012 የትምህርት ዘመን የአዳሪ ት/ቤት ከሚሆኑት ሁለቱ የመንግስት ትምህርት ቤቶች አንደኛው በሆነው የእቴጌ መነን ት/ቤት በመገኘት እድሳቱ ያለበትን ሁኔታን ተመልክተዋል፡፡ የእቴጌ መነን ት/ቤት በ2012 የትምህርት ዘመን 500 ሴት ተማሪዎችን ተቀብሎ በአዳሪ ፕሮግራም ለማስተማር ቅድመ ዝግጅት እያደረገ እያደረገ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን!

#1440ኛው የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል #በሰላም መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አሰታወቀ። በአል በሰላም እንዲጠናቀቅ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከሚመለከታቸው የፀጥታ አካላት፣ ከእምነቱ አባቶችና ከበጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ጋር ውይይት እንደተካሄደና ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ወደ ስራው የተገባ መሆኑ ፓሊስ አስታውቋል፡፡

በዚህ መሰረትም ምዕመኑ ለኢድ-ሶላት በሰላም ወጥቶ በሠላም እንዲገባ በዋና ዋና መንገዶች በተለይም በአዲስ አበባ ስታድየም እና በዙሪያው ከበዓሉ አስተባባሪ ወጣቶች ጋር በመቀናጀት ጠንካራ የፀጥታ ሰራ ተከናውኗል፡፡ ለስራው ስኬታማነት የእምነቱ ተከታዮች ላሳዩት ቀና ትብብር የአዲስ አበባ ፖሊሰ ኮሚሽን ምስጋናውን አቅርቧል፡፡

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኤጀንሲው ተማሪዎችንና የተማሪ ወላጆችን ይቅርታ ጠየቀ!

የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ/የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ የፈተና ውጤት #ዛሬ ይፋ ይደረጋል ቢባልም የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ በገጠመው ችግር ምክንያት ለ2 ቀናት #ማራዘሙን አስታውቋል፡፡ ኤጀንሲው ውጤቱን ከ2 ቀን ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ይፋ የሚያደርግ መሆኑን የኤጀንሲው የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ረዲ ሽፋ ተናግረዋል፡፡ ለተፈጠረው መዘግየትም ዳይሬክተሩ ለተፈታኞች እና ለተፈታኝ ወላጆች ይቀርታ ጠይቀዋል፡፡

Via #EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia