TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.7K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#ሀምሌ22

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማኅበር

የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር፦

በሀገር አቀፍ ደረጃ ሐምሌ 22/2011ዓ.ም የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ይካሄዳል፡፡ ስፖርት ማህበራችንም በዚህ በጎ ተግባር ላይ ይሳተፋል ስለሆነም መላው የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር አባላትና ደጋፊዎች የፊታችን ሰኞ ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ ሆላንድ ኤምባሲ(Holland embassy) አጠገብ በመገናኘት የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር እንድናከናውን ስፖርት ማህበሩ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማኅበር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሞስኮ

የሩስያ ፖሊስ በዋና ከተማዋ ተቃውሞ የወጡ ከአንድ ሺ በላይ ሰልፈኞችን ማሰሩ ተሰማ። ሩስያ ለምርጫ መወዳደደር የሚያበቃቸውን ፊርማ አላሰባሰቡም ስትል ተቃዋሚ ተወዳዳሪዎችን ከምርጫው ማገዷ ይታወቃል፡፡ ይህን ተከትሎም በሞስኮ ከተማ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ነዋሪ ለተቃውሞ ሰልፍ መውጣቱን ቢቢሲ አስነብቧል፡፡

ነገሩ ያልጣመው የሩስያ ፖሊሲም ተቃዋሚ ሰልፈኞችን አንዲበተኑ አድርጓል ይላል ዘገባው፡፡ ለምን ይታገዳሉ ሲሉ ሰልፍ ከወጡት መካከልም ፖሊስ ከአንድ ሺ በላይ ማሰሩንም ቢቢሲ ጨምሮ አስነብቧል፡፡ ተፎካካሪዎቹ ለምርጫ የማያበቃቸውን ፊርማ ስላልሰበሰቡ ሳይሆን ፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ሲባል ነው ክምርጫው እንዲወጡ የተደረገው ሲሉ ሰልፈኞቹ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል፡፡

ሰልፉን ለመበተን ፖሊስ የሄደበት መንገድ በጣም አደገኛ አገሪቱን ወደ ችግር የሚወስዳት እንደሆነ የቢቢሲ ዘገባ ያመለክታል፡፡ ሩስያ እኤአ መስከረም ስምንት 2019 የምታካሂደውን ምርጫ ተከትሎ ጥቂት ከምርጫው የታገዱ ተቃዋሚ ተወዳዳሪዎችን ማሰሯ ታውቋል፡፡ እስካሁንም 30 ተፎካካሪዎች በቂ ፊርማ ባለማሰባሰባቸው ከምርጫው ታግደዋል ይላል የቢቢሲ ዘገባ፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጋምቤላ

የጋምቤላ ህዝቦች ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ለ2012 የበጀት ዓመት የልማት እቅድ ማስፈፀሚያ ከ2 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት፣ዓዋጆችንና ሹመት በማጽደቅ ተጠናቀቀ።

የክልሉን ህዝብ የልማትና የመልካም አስተዳዳር ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት በአዲሱ በጀት ዓመት ባለድርሻ አካላት እንዲሰሩ የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አሳስበዋል።

ጉባዔው በሁለት ቀናት ቆይታው በክልሉ በ2011 እቅድ አፈፃፀም ላይ ከመከረ በኋላ የ2012 በጀት ዓመት የልማትና መልካም አስተዳደር ግቦችን ለማሳካት ከ2 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት አጽድቋል፡፡

ከጸደቀው በጀት መካከል 1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ለክልል መንግሥት፣ ለዘላቂ ልማት ግቦች ማስፈጸሚያ፣ ለመደበኛና ለመጠባበቂያ ተመድቧል። ቀሪው ለዞንና ለወረዳዎች እንደተመደበ ተብራርቷል።

የጸደቀው በጀት ከክልሉ ከተለያዩ የገቢ ምንጮች፣ከፌደራል መንግሥት ድጎማ እንዲሁም ከውጭ ብድርና እርዳታ እንደሚሸፈንም ተመልክቷል፡፡ በክልሉ የጸደቀው በጀት ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር ከ251 ሚሊዮን ብር በላይ ብልጫ እንዳለውም ተገልጿል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ባቱ

"ሓምሌ 22/2011 ዓ/ም 200 ሚሊዮን ችግኝ ለመትከል የተያዘውን ሀገራዊ እቅድ በኦሮምያ ክልል ብቻ 300 ሚልየን ለመትከል ዝግጅት ተጠናቋል፣ እኛም በባቱ(ዝዋይ) ከተማ ዝግጅት ላይ ነን"~ሰይፉ ታደሰ/TIKVAH-ETH/

@tsegabwolde @tikvahethiopia
እንኳን አደረሳችሁ!!

እየመጣችሁ የምትገኙ የTIKVAH_ETHIOPIA ቤተሰብ አባላት በየቦታው አቅጣጫ ጠቋሚ ባነሮች ተሰቅለዋል። #ETHIOPIA

በGoogle Map ላይ
https://maps.google.com/?cid=14408072496157346285 ማግኘት ይቻላል፡፡

መደወል ትችላላችሁ፦

+251913134524/በረከት ጉዲሳ/
+251920486685/አቅለሲያ ሲሳይ/
+2519 29 04 41 03/ፀጋዬ/
+2519 09 91 16 68/ፀጋዬ/
Live!! FanaTV #TIKVAH_ETH
#ጅማ_ዩኒቨርሲቲ #አረንጓዴ_አሻራ ነገ በኪቶ ፉርዲሳ ካምፓስና አካባቢው!!
እንኳን ደስ አለን!!

ለበርካታ ወራት ተቋርጦ የነበረው የTIKVAH-ETH የቋንቋ ትምህርት ከነሃሴ 1 ጀምሮ ይቀጥላል!!

#አፋን_ኦሮሞ
#ትግርኛ
#ግዕዝ.... በቀጣይ የሚካተቱት ቋንቋዎች እንደተጠበቁ ናቸው። ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል!

ኢትዮጵያን መውደድ ማለት~ቋንቋዋን፣ ባህሏን፣ ህዝቦችን መውደድ ነው!!

@Tikvahethedu በድጋሚ እንኳን ደስ አለን!

https://yangx.top/joinchat/AAAAAEWA_-Jt2zIM5COJqw
#NewsAlert በቻግኒ 4 ክላሽንኮቭ፣ 2903 የክላሽንኮቭ፣ 6244 የአብራራውና የመትረዬስ ጥይቶች ከ1 ግለሰብ ቤት መገኘቱን ፖሊስ ለአማራ ቴሌቭዥን አስታውቋል። በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር የምትገኘው ቻግኒ ከባሕር ዳር 170 ኪ.ሜ. ገደማ ስትርቅ ለቤኒሻንጉል ቅርብ ነች።

Via እሸት በቀለ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የየመን ሆውቲ አማፅያንን የሚዋጋው የሳውዲና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ጥምር ጦር በመቶዎች ለሚቆጠሩ ህፃናት ሞትና መቁሰል ምክንያት በመሆኑ በተባበሩት መንግስታት ለሶስተኛ ግዜ በጥቁር መዝገብ መስፈሩን አልጀዚራ ተመለከትኩት ያለውን ሪፖርት ጠቅሶ ዘግቧል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ለፀጥታው ምክር ቤት ባቀረቡት ሪፖርት እእአ በ2018 ጥምር ጦሩ ለ729 ህፃናት ሞትና መቁሰል ምክንያት ሆኗል፡፡
ጥምርጦሩ በጦርነት በዳሸቀችው የመን ከሚሞቱ ህፃናት ለግማሽ ያህሉ ተጠያቂ ነውም ተብሏል፡፡

የተባበሩት መንግስታት አረጋገጥኩት ባለው መረጃ በየመን ባለፈው አመት በህፃናት ላይ 1 ሺህ 689 አደጋዎች ደርሰዋል ከዚህም ውስጥ 576 ያህሉ ሲሞቱ 1 ሺ 113 ያህሉ ቆስለዋል፡፡

ቁጥሮቹ አሻቅበው የተገኙት ሰው ባዛ ብሎበሚኖርበት ስፍራ እና የህዝብ አገልግሎት መስጫዎች ኢላማ በመደረጋቸው ነው ተብሏል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Hawassa በሀዋሳ ከተማ ያሉ #ሆቴሎች በቅርቡ በተፈጠረው አለመረጋጋት ምክንያት የሆቴል አልጋዎች ገበያ በ94 በመቶ #መቀነሱ ተነገረ። የመጠጥና የምግብ አገልግሎት ገበያም በ70 በመቶ ቀንሷል ተብሏል።

Via Tesfaye Getnet/ካፒታል ጋዜጣ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሀገረሰላም

በሲዳማ ዞን ሰሞኑን ተፈጥሮ በነበረው የፀጥታ ችግር ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ የሁላ ሀገረሰላም ወረዳ ነዋሪዎች በአዲስአበባና ሀዋሳ ከተማ የሚኖሩ የአካባቢው ተወላጆች 200 ሺህ ብር ግምት ያላቸው የምግብና አልባሳት ድጋፍ አደረጉ፡፡ የአካባቢው ተወላጆች በወረዳው አስተዳደር ቅጥር ግቢ ተጠልለው የሚገኙ ወገኖችን በመጎብኘት 20 ኩንታል ዱቄትና አልባሳት አበርክተዋል፡፡

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር አዮ ጓጉሳ ወረዳ በሚገኘው አዮ ወንዝ ላይ ሲገነባ የነበረው ድልድይ ተጠናቆ ተመረቀ፡፡ በምረቃ ሥነ ሥረዓቱ የአማራ ክልል መንገድ እና ትራንስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ፈንታ አዋየው እና ሌሎች የብሔረሰብ አስተዳደሩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#OSA

ኦሮሞ ስተዲስ አሶስዬሽን(ኦሳ) [የኦሮሞ ጥናት ማህበር] 33ኛው ጉባኤ ዛሬ ለ3ኛ ቀን በአዲስ አበባ በሪፍት ቫሊ ዩኒቨርስቲ ቀጥሎ እየተካሄደ ነው።

Photo: OMN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#OSA #ኢንጂነር_ታከለ_ኡማ

ለመጀመሪያ ጊዜ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ እየተካሄደ ባለው የኦሮሞ ጥናት ማህበር ጉባኤ ላይ (ኦሳ) ዛሬ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) ማህበሩ ማዕከሉን አዲስ አበባ ላይ እንዲያደርግና ከዚህ በኋላ ዝግጅቱን ለማካሄድ ወደ ባዕድ ሃገር መመልከት የለበትም ብለዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ #BBC👇
https://telegra.ph/OSA-07-28
#2ተኛ_አመት 🎂 በአሁን ሰዓት በአበበች ጎበና የህፃናት እንክብካቤና ልማት ድርጅት እየተከናወነ በሚገኘው ዝግጅት ላይ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ኦባንግ ሜቶ፣ ፕሮፌሰር ደጀኔ አየለ፣ ዶክተር ኤልያስ ገብሩ፣ ከትምህርት ሚኒስቴር ደግሞ ወ/ሮ ፂዮን ቤተሰቡን ተቀላቅለው ቀኑን እያከበሩ ይገኛሉ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በዘፈቀደ የሚተገበረው የታክሲ ታሪፍ፦

በአዲስ አበባ የትራንስፖርት መጨናነቅና እጥረት መኖሩ ታክሲዎች በዘፈቀደ እንዲያስከፍሉ ምክንያት ከሆነ ሰንብቷል፡፡ በአብዛኛዎቹ የትራንስፖርት ቦታዎች ላይ የሚታዩ የተለያዩ ችግሮችን ተቋቁመው አገልግሎቱን ለማግኘት የሚጋፉ ሰዎችም ለስርቆት ሲዳረጉ ማየቱ የአደባባይ ሚስጥር ነው፡፡

በአገሪቱ የሚታዩ ክፍተቶችን በመጠቀም ዋጋ መጨመርና ኅብረተሰቡን ማማረር የተለመደ ከሆነባቸው ዘርፎች አንዱ ትራንስፖርት ነው፡፡ የትራንስፖርት አገልግሎት ለማግኘት ከሜክሲኮ ዓለም ባንክ ለመሄድ ተሠልፈው ያገኘናቸው አቶ ኬራሚድ ሙራድ፣ በተለያዩ ቦታዎች መሄድ የሚፈልጉ ተሳፋሪዎችን እንግልት በመመልከት፣ መንግሥት ካወጣው ታሪፍ በላይ በመጠየቅ ተሳፋሪውን አማራጭ የሚያሰጡ፣ በኑሮ ውድነት ላይ ሰውን የሚያማርሩ የታክሲ ትራንስፖርት ሰጪዎች መበራከታቸውን ይገልጻሉ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ #ሪፖርተር_ጋዜጣ👇
https://telegra.ph/AA-07-28-3