TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#NewsAlert የኢትዮጵያ ምግብ መድሃኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደር ቁጥጥር ባለስልጣን 57 የምግብ ምርት አይነቶችን ህብረተሰቡ እንዳይጠቀም አሳሰበ። ባለስልጣኑ ለfbc በላከው መግለጫ በምግቦቹ ጥራትና ደህንነት ላይ ባደረገው የገበያ ጥናት የምግብ ምርቶቹ መሰረታዊ የገላጭ የፅሁፍ ክፍተት ያለባቸው፣ የሚመረቱበት ቦታ የማይታወቅ፣ የንጥረ ነገር ይዘት የሌላቸው፣ አምራች ድርጅቶቹ የማይታወቁ፣ የምርት መለያ ቁጥር፣ የተመረቱበት ጊዜ እና የምርቱ ማብቂያ ጊዜ ገላጽ ፅሁፍ የሌላቸው ናቸው ብሏል። ከዚህር ተያይዞም ምርቶቹን ህብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸውና ተቆጣጣሪ አካላት ምርቶቹን በአፋጣኝ ከገበያ ላይ እንዲሰበስቡም ጥሪውን አቅርቧል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert ህብተረሰቡ እንዳይጠቀማቸው የተከለከሉ የምግብ አይነት ዝርዝሮች፦

የከረሚላ ምርቶች

•ጆሊ ሎሊፖፕ
•አናናስ ከረሚላ
•ኮላስ ከረሚላ
•ኦሊ ፖፕ
•ቤስት ከረሚላ
•የስ ከረሚላ (ኮፊ ከረሚላ)
•ማሚ ሎሊ ፖፕ
•ሳራ ከረሚላ
•ጃር ሎሊ ፖፕ
•ጸሃይ ሎሊ ፖፕ
•ዩኒክ ሎሊ ፖፕ
•እንጆሪ ከረሚላ
•ብርቱካን ከረሚላ
•ይናቱ ሎሊ ፖፕ እና ሃላዋ ከረሚላ

የማር ምርቶች፦

•አፍያ የተፈጥሮ ማር
•ሪትም ማር እና በላይ ማር

የገበታ ጨው፦

•ዊዲ
•ሱላ
•ናይ
•ሃያት
•አቤት
•በእምነት
•እናት
•አባይ
•አባት፣ ሴፍ እና ጣዕም የገበታ ጨው

የለውዝ ቅቤ፦

•ደስታ
•አስነብ
•ኑኑ
•አቢሲኒያ
•ብስራት
•ፈሌ
•ሳባ፣ አዳ እና አደይ የለውዝ ቅቤ

የኑግ ዘይት፦

•አደይ አበባ እና ቀመር የኑግ ዘይት

አልሚ የህጻናት ምግቦች፦

•ምሳሌ የህጻናት ምግብ
•ኤልሞ የልጆች ምግብ
•ሂሩት የህጻናት አጃ
•ዘይነብ የህጻናት አጥሚት
•ተወዳጅ ገንቢ የህጻናት አጥሚት
•ተወዳጅ የህጻናት ሽሮ እና ፋሚሊ ሃይል ሰጭና ገንቢ የህጻናት ሽሮ

ቪንቶ፦

•ዴኮ
•እስፔሻል
•ዳና
•ቃና
•ላራ
•ዛጎል አቼቶ
•ናይስ አቼቶ
•አምቴሳ አቼቶ
•ማይ አቼቶ
•መስ አቼቶ እና ቫይኪንግ አቼቶ ምርቶች ህብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸው #ታግደዋል

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ፍኖተ_ሰላም

ሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ.ም በአማራ ክልል ከፍተኛ መሪዎች ላይ በተፈፀመው ጥቃት ሳቢያ በደረሰው ጉዳት እና ከዚያም በኋላ የነበረውን የሠላማዊ ሕይወት ማስቀጠል በሚቻልበት ርዕሰ ጉዳይ ዙሪያ የአማራ ክልል የፀጥታ አካላት እየመከሩ ነው። በፍኖተ ሠላም ከተማ አስተዳደር እየተካሄደ ባለው ምክክር የምሥራቅ ጎጃምና የምዕራብ ጎጃም ዞኖች፣ የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደርና ከክልል የተውጣጡ የፀጥታ ኃይል ኃላፊዎች እየተሳተፉ ነው፡፡

Via #AMMA
🗞ቀን ሃምሌ 3/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የሲዳማ ህዝብ ላቀረበው የክልልነት ጥያቄ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ፈጣን ምላሽ ሊሰጥ እንደሚገባ በብሄሩ ስም የሚንቀሳቀሱ ሶስት የፖለቲካ ፓርቲዎች አስታውቀዋል። የሲዳማ አርነት ንቅናቄ/ሲአን/፣የሲዳማ ብሄራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ/ሲብዴፓ/ እና የሲዳማ ሀድቾ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት/ሲሀዴድ/ በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ቦርዱ የህዝበ ውሳኔ ማድረጊያ ቀኑን ቆርጦ እንዲያሳውቅ ጠይቀዋል።

ተጨማሪ የንብቡ👇
https://telegra.ph/SRS-07-10
#NewsAlert በቤኔሻንጉል ጉሙዝ ክልል ማንዱራ ወረዳ በፀጥታ ችግር ቀያቸውን #ትተው የሄዱ ሰዎችን #ንብረት የፀጥታ አካላት ሲዘርፉ #በቁጥጥር_ሥር መዋላቸው ተሰምቷል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/BGU-07-10
#NewsAlert ዓለም አቀፉ የስደተኞች መርጃ ድርጅት (IOM) 110 አዳጊዎችን ጨምሮ በየመን መፈናፈኛ አጥው የነበሩ 132 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች አዲስ አበባ መድረሳቸውን አስታውቋል። ዛሬ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ከደረሱት ኢትዮጵያውያን መካከል #ትናንሽ ልጆች ይገኙበታል።

Via #DW
🗞ቀን ሃምሌ 3/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የኤሌክትሪክ ትራንስፎርመር #ስርቆት በአዲስ አበባ አሳሳቢ ሆኗል። #ADDISABEBA #FBC

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ባህር_ዳር

በባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ዳግማዊ ቴዎድሮስ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ‹ዲያስፖራ ሰፈር› እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የግለሰብ መኖሪያ ቤትን በመከራዬት ከኑግ ተረፈ ምርት (ፋጉሎ) ዘይት ሲመረት በማኅበረሰቡ ጥቆማ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡ በቁጥጥር ስር የዋሉት ሠራተኞች እንደተናገሩት ሕገ-ወጥ ሥራው የሚሠራው በሌሊት እንደሆነና ቀን ደግሞ ለእንስሳት መኖ አገልግሎት የሚውል ተረፈ ምርት ሲያመርቱ ይውላሉ፡፡ ሠራተኞቹ በቀን 120 ብር እንደሚከፈላቸውም ተናግረዋል፡፡ የሚመረተውን ዘይትም ጧት እና ማታ ወደ ሌላ አካባቢ በመውሰድ እንደሚሸጡም ገልጸዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/BDR-07-10
#NewsAlert የህወሃት /T.P.L.F/ ማዕከላዊ ኮሚቴ ሲያደርግ የነበረውን #አስቸኳይ ስብሰባ ባለ 7 ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል።

መግለጫው እንደደረሰን የሚቀርብ ይሆናል!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert

የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ መግለጫ!
መግለፂ ማእኸላይ ኮሚቴ ህወሓት
👇
____ https://telegra.ph/AD-07-06
#NewsAlert ለባለስልጣናቱ #ግድያ አዴፓ ራሱን ተጠያቂ እንዲያደርግ ህወሐት ጠየቀ። ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የነበረው የህወሐት ማዕከላዊ ኮሚቴ አስቸኳይ ስብሰባ ዛሬ ተጠናቋል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/TPLF-07-10

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአሜሪካ የብሪታኒያ አምባሳደር ኪም ዳሮች የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕን አስተዳደር የሚተቸው የኢ-ሜይል መልዕክታቸው አፈትልኮ ለአደባባይ መብቃቱን ተከትሎ ከስልጣናቸው ለቀዋል። ከአምባሳደሩ ኢ-ሜይል አፈትልከው የወጡ መልዕክቶች የትራምፕን አስተዳደር “አቅመ ቢስና ክህሎት የሌለው” ሲሉ የተቹ ናቸው። ይህን ተከትሎ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራም አምባሳደር ኪም ዳሮችን “ጋጠ ወጥ” ሲሉ በስድብ ወርፈዋቸዋል። አምባሳደር ኪም መልዕክታቸው አፍተልኮ መውጣቱን ተከትሎ በስራየ ለመቀጠል እቸገራለሁ ሲሉ መልቀቃቸውን ትላንት ተናግረዋል።

ምንጭ፦ሬውተርስ
🗞ቀን ሃምሌ 4/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvagethiopia
#update ሰኔ 15 ቀን በክልልና በፌደራል ደረጃ በተፈጸመው ጥቃት ሳይደናገጡ፣ ክልላቸውንና ዞናቸውን ለማረጋጋትና ሠላም ለማስፈን በላቀ ዝግጁነት ላይ መሆናቸውን በሰሜን ወሎ ዞን የሚገኙ የመቅደላ ብርጌድ የልዩ ኃይል አባላት ተናገሩ።

በእዙ ስር የሚገኙ ከ1 ሺ 300 በላይ ልዩ ኃይሉን የሚመሩት ከሻምበል አመራር በላይ የሆኑ መሪዎች ለሁለት ቀናት የሚቆይ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው፡፡ አባላቱ እርስ በእርሳቸው በመወያዬትና በመመካከር ችግሮችን በመፍታት በቀጣይ የአማራ ክልል ሕዝብን ካሉበት ውስጣዊ እና ውጫዊ የፀጥታ ስጋቶች ለመታደግ ለመሥራት ዝግጁ መሆናቸውን ለአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ገልጸዋል።

ኅብረተሰቡ በተፈጠረው ድርጊት ሳይረበሽ እና ሳይደናገጥ ከፀጥታ መዋቅሩ ጎን በመሆን የፀጥታ ኃይሉ ሕግን ለማስከበር የሚያከናውነውን ሥራ እንዲያግዝም የልዩ ኃይል አባላቱ ጥሪ አቅርበዋል።

በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲዎች ልዩ ኃይሉን አስመልክቶ የሚናፈሰው አሉቧልታ መሠረተ ቢስ መሆኑን መረዳት እንደሚገባ ያሳሰቡት አባላቱ በፀጥታ መዋቅሩ ልዩነት እና ክፍፍል አለመኖሩን አረጋግጠዋል።

በውይይቱ እየተሳፉ የሚገኙት ከ1 ሺህ 300 በላይ የልዩ ኃይሉን የሚመሩት ከሻምበል አመራር በላይ የሆኑ መሪዎች ናቸው። እነዚህ መሪዎች ለአባሎቻቸው የውይይቱን ሐሳብ እንደሚያወርዱም ይጠበቃል።

Via #AMMA
🗞ቀን ሃምሌ 4/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የመከላከያ ሰራዊት የጋራ መኖሪያ ቤት እጣ ሃምሌ 13 ይወጣል። #FBC

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ቶምቦላ2011
/#ሼር #Share/

ሰኔ 30 የወጣው የቶምቦላ 2011 ሎተሪ የአሸናፊ ቁጥሮች ከላይ የምትመለከቷቸው ናቸው። National Lottery Administration #ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የደኢህዴን ስብሰባ ዛሬም ቀጥሏል...

የደኢህዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ልዩ ስብሰባ ዛሬም በመካሄድ ላይ ነው፡፡ ደኢህዴን የተለያዩ ሀገራዊና ክልላዊ ፖለቲካዊ፣ የማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ እና የፀጥታ ጉዳዮችን በጥልቀት እየገመገምኩ እገኛለሁ ብሏል። የግምገማ መድረኩ በጥሩ የመግባባት መንፈስ እየተከናወነ ነው፤ ሲጠናቀቅም የውሳኔ ሀሳቦችን በዝርዝር መግለጫ እሰጣለሁ ሲል ገልጿል።

🗞ቀን ሃምሌ 4/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የሶማሌ ክልል ምክር ቤት ዘጠናኛ መደበኛ ጉባኤ #ለ2012 በጀት ዓመት ለሚከናወኑ ስራዎች ማስፈጸሚያ የሚውል 18 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር በጀት አፀደቀ። በጀቱ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጻር በ646 ሚሊየን ብር ብልጫ እንዳለው ተመልክቷል።

Via #fbc
🗞ቀን ሃምሌ 4/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert በሱዳን ለሳምንታት ተቋርጦ የነበረው የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎት ተለቋል። ኢንተርኔቱ የተዘጋው በአገሪቱ ዋና ከተማ ካርቱም ለበርካቶች ሞት እና ጉዳት ምክንያት የሆነውን እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ጁን 3 በፀጥታ ሃይሎች እና ተቃዋሚዎች የተከሰተው ግጭት ተከትሎ ነበር፡፡

ኢንተርኔት በመዘጋቱ #ክሱን ያቀረቡት የህግ ባለሙያው አብደል አዚም ሃሰን እንዳሉት የካርቱም አከባቢ ፍ / ቤት ዛየን ለተባለው ኩባንያ የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲለቅ ትዕዛዝ ማስተላለፉን ገልጸዋል፡፡ ይህን ተከትሎ ለ37 ቀናት ተቋርጦ የቆየውን የኢንተንኔት አገልግሎት በከተማው መስራት መጀመሩን ተገልጿል፡፡ ፍርድቤቱ በተመሳሳይ ኤምትኤን እና ሱዳኒ ለተባሉ ተቋማትም ኢንትርኔት አገልግሎቱን እንዲለቁ ወስኗል፡፡

ወታደራዊ የሽግግር መንግስቱ ከዓለም አቀፍ ተቋማት #የኢንተርኔት አገልግለቱን ክፍት እንዲያደርግ ግፊት ሲደረግበትም ቆይቷል፡፡ ወታደራዊ የሽግግር መንግስቱ ከተቃዋሚዎች ከስምምነት መድረሱን ተከትሎ የኢንተርኔት አገልግሎት ለመጀመር ከስምምነት ደርሶ እነደነበርም ተገልጿል፡፡

ምንጭ፦ ዘ ኢስት አፍሪካ ኒውስ/ሱዳን ትሪቡን/#ENA/
🗞ቀን ሃምሌ 4/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ባህር_ዳር የአዴፓ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ዛሬ ስብሰባ ጀምሯል፡፡ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባውን እያካሄደ የሚገኘው በባሕር ዳር ከተማ ነው፡፡

Via አብመድ
🗞ቀን ሃምሌ 4/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሲኣን "የለውጥ ሀይሉ ከትክክለኛ #ለውጥ ፈላጊዎች ጋር ሊናበብ ይገባል" - አቶ ዱካሌ ላሚሶ የሲዳማ ኣርነት ንቅናቄ (ሲኣን) ሊቀመንበር

ተጨማሪ የንብቡ👇
https://telegra.ph/SID-07-11-2
#ዜና_ዕረፍት:የቀድሞው የዓረና ፓርቲ ሊቀመንበር እና ያሁኑ የማእከላዊ ኮሚቴ አባል አቶ ብርሃኑ በርኸ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

Via አብርሃ ደስታ
@tsegabwolde @tikvahethiopia