TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#update የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክሪያሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን) ማዕከላዊ ኮሚቴ ልዩ ስብሰባውን ማካሄድ ጀመረ፡፡ የንቅናቄው ሊቀ መንበርና የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈርያት ካሚል በልዩ ስብሰባው ሀገራዊና ክልላዊ የጸጥታና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚካሄድ ገልጸዋል፡፡ በማዕከላዊ ኮሚቴው ልዩ ስብሰባ የተለያዩ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት እንደሚካሄድባቸውም ተጠቁሟል፡፡ ልዩ ስብሰባው በአዲስ አበባ የሚካሄድ ሲሆን ለሶስት ቀናት ይቆያል፡፡

Via #fbc
🗞ቀን ሰኔ 28/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
“የቻላችሁትን ያህል ክፍሉ…”

“በዚህች ምድር ለብቻችን አይደለም የምንኖረው፤ አንዳችን ለሌላችን እንደምንኖር ነው የማምነው፡፡ ስለዚህም ማንም ቢሆን… የገቢ መጠኑ የቱንም ያህል ይሁን መሰረታዊ የሕክምና አገልግሎት ማግኘት አለበት ብዬ ነው የማምነው” ዶ/ር ፓውሎ ዴ ቫልዶሌሮስ…

“10 ራንድም የሚከፍል አለ፤ 500 ራንድም የሚከፍል እንደዛው፡፡ ሁሉም ሕክምናውን ካገኘ በኋላ የቻለውን ይከፍላል” ይላል ደቡብ አፍሪካዊው ዶ/ር ፓውሎ ዴ ቫልዶሌሮስ፡፡

ዶ/ሩ የዛሬ አራት ሳምንታት ግድም፣ በደቡብ አፍሪካዋ ብሎምፎንቲየን ከተማ የከፈተው የቀዶ ሕክምና አገልግሎት የሚሰጥ ክሊኒኩ መነጋገሪያ ሆኗል፡፡

የዚህ ምክንያቱ ደግሞ … ወደ ክሊኒኳ ያለ ቀጠሮ ዘው ብለው ገብተው፣ ሕክምናዎትን አግኝተው ሲያበቁ የሚከፍሉት “የቻሉትን ያህል” ብቻ በመሆኑ ነው፡፡ በቀን 20 ያህል በሽተኞችን የሚያክመው ዶ/ሩ የታካሚ ቁጥር እንደጨመረ ይገልፃል፡፡ዶክተሩ፣ የሕክምና አገልግሎቱን እና መሰረታዊ የሚባሉ መድሃኒቶችን ለሕመምተኛው ከሰጠ በኋላ ታካሚው የሚችለውን ከፍሎ ይሄዳል፡፡

“ይህ አሰራር ያዋጣሃል ወይ” ተብሎ የተጠየቀው ዶ/ር ፓውሎ ዴ ቫልዶሌሮስ፣ “ኑሮዬን በገቢዬ መጠን አደርገዋለሁ፡፡ ደግሞም … እኔ ዶክተር ነኝ፤ የእኔ ሃላፊነት የሕክምና አገልግሎት መስጠት ነው፡፡ ሃላፊው እግዚአብሄር ነው” ብሏል፡፡ ቢቢሲ እንደዘገባው … ዶ/ሩን ለመርዳት ገንዘብ የሚያሰባስቡ ሰዎች እየመጡ ነው፡፡

ምንጭ - ቢቢሲ/#ሸገርFM
🗞ቀን ሰኔ 28/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
38 ጋዜጠኞች ተገድለዋል...

እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከጥር 2019 እስከ ሰኔ ባለው ግዜ በ20 የኣለም አገራት የሚገኙ 38 ጋዜጠኞች መገደላቸው ተገልጿል፡፡

Press Emblem Campaign (PEC) የተባለው ተቋም ያወጣው ሪፖርት እንደሚያሳየው በዚህ ስድስት ወራት የሞቱት የጋዜጠኞች ቁጥር ከላፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻፀር በ42 ከመቶ ቀንሷል፡፡ ሆኖም ከሞቱት ጋዜጠኞች መካካል 9 በሜክሲኮ እና 6 ደግሞ በአፍጋኒስታን ብቻ መሆኑ አሳሳቢ ነው ተብሏል፡፡

በአፍጋኒስታን አሸባሪ ቡድኖች እንዲሁም በሜክሲኮ የተደራጁ ወንጀሎች ለሞቱት ጋዜጠኞች ምክንያት መሆናቸው ነው በሪፖርቱ የተጠቀሰው፡፡

የላቲን አሜሪካ አገራት ከሟቾች ቁጥር 15 በመያዝ ችግሩ በስፋት የሚታይባቸው አገራት መሆናቸው ተገልጿል፡፡

በመካከለኛው ምስራቅ የሶርያና በኢራቅ የግጭት ሁኔታ መቀነስ ማሳየቱን ተከትሎ የጋዜጠኞች ሞት ቀንሷል ተብሏል፡፡

አገራት የጋዜጠኞች ጥቃትና መብት ማስከበር የማይችሉ ከሆነ የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ጋዜጠኞች መብታቸው የሚከበርበት እና ከጥቃት የሚታደግበት መላ ሊዘይድ ይገባል ብለዋል Press Emblem Campaign (PEC) ዋና ጸሃፊ ብሌዝ ለምፔን።

Via #ዥንዋ/ENA
🗞ቀን ሰኔ 28/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮ-ቴሌኮም እና የስኳር ፋብሪካዎች ፕራይቬታይዜሽን ሂደትን በተመለከተ የኢፌዴሪ የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ኢዮብ ተካልኝ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫው ላይ እንዳመለከቱትም የቴሌኮም ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ የፓይቬታይዜሽን ሂደቱን በተመለከተ መንግሥት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት ከኢትዮ ቴሌኮም በተጨማሪ ሌሎች ሁለት ዓለም አቀፍ የቴሌኮም ኦፕሬተሮች ወደ ገበያ እንዲገቡ ያደርጋል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ኢትዮጵያ-ሁለት-ዓለም-አቀፍ-የቴሌኮም-ኦፕሬተሮችን-በጨረታ-ወደ-ቴሌኮም-ገበያ-ልታስገባ-ነው-07-05
#update በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን 4 ሺህ ሄክታር በሚጠጋ የበቆሎና የማሽላ ማሳ ላይ ፈጣንና ሁሉን አውዳሚ #ተምች መከሰቱ ታውቋል፡፡

የዞኑ ግብርና መምሪያ የሰብል ልማት ባለሙያ አቶ #ገበየሁ_ሽፈራው እንደገለፁት ተምቹ 3ሺህ 587 ሄክታር መሬት ላይ በተዘራ በቆሎና ማሽላ ሰብል ላይ ጉዳት እያደረሰ ነው፡፡ በዚህም ከ9 ሺህ በላይ አርሶ አደሮች ተጎጅ እንደሆኑ ነው ባለሙያው ያስታወቁት፡፡

ችግሩ በኤፍራታና ግድም፣ በአንፆኪያና ገምዛ፣ በሸዋሮቢት፣ በአንኮበርና በጣርማ በር ወረዳዎች በስፋት መከሰቱም ተነግሯል፡፡

ተምቹ በመስኖ በሚለሙ ሰብሎች ላይ ዓመቱን ሙሉ እንደቆዬና ከያዝነው ሰኔ ጀምሮም በበቆሎና በማሽላ ሰብሎች ላይ እየጨመረ መምጣቱን ባለሙያው ተናግረዋል፡፡

ከግብርና ሚኒስቴር 1ሺህ 600 ሊትር ፀረ ተምች ኬሚካል ቀርቦ ለመከላከል ሥራው እየተሰራጨ እንደሆነም ታውቋል፡፡

የሰሜን ሸዋ ዞን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ያጠናቀረው መረጃ እንዳመላከተው አሁን ላይ ተምቹን በኬሚካልና በባህላዊ መንገዶች ለመከላከል ጥረት እየተደረገ ነው፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
🗞ቀን ሰኔ 28/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ስምምነት ላይ ለደረሱት ለሱዳን ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤት ፣ለተቃዋሚ ሀይሎች እና ለሀገሪቱ ህዝቦች የደስታ መልክት አስተላለፉ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስምምነቱ በሱዳን ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን የሚያሰችል ነው ብላዋል ባስተላለፉት መልዕክት፡፡

የሀገሪቱ የፓለቲካ ሀይሎች ስምምነት ላይ እንዲደርሱ ከፍተኛ ሚና ለነበራቸው አምሳደር መሀመድ ድሪር እና መሀመድ ሀኬን አል ላባትም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቀጣይ ጊዜ ለሱዳን የሰላምና የብልፅግና እንዲሆን ምኞታቸው አስተላልፈዋል፡፡

🗞ቀን ሰኔ 28/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የ40/60 ቦሌ-ቦሌ አያት 1-ሳይት 1 የውል መርሀ ግብር(Program)፦

•ቤቱ የሚገኝበት ክ/ከተማ - ቦሌ
•ቤቱ የሚገኝበት የሳይት ስም - ቦሌ አያት 1 - ሳይት 1
•ብሎኮች ብዛት - 14
•በብሎኮቹ የሚገኙ ቤቶች ብዛት - 299

ወረዳ የሚሞላ(ቅጽ 9) መውሰድና ማስሞላት ለሳይቱ የተሰጠው ቀን አርብ 28 እስከ ሰኞ 1/11/201

የክፍያ ሰነድ(ቅጽ 3) ወስዶ ክፍያ መፈጸም አና ውል ለሳይቱ የተሰጠው ቀን ከማክሰኞ 2 እስክ ሀሙስ 4/11/2011

ማሳሰቢያ፦

•የስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2:30-6:30 እና ከሰዓት ከ7:30-11:00 በተጨማሪም ቅዳሜ ከ2:30-6:30

ወደ አዳራሽ መግባት የሚችለው ለአንድ ቤት የቤቱ ባለቤት ወይም ህጋዊ ወኪሉ ብቻ ነው። ወደ አዳራሽ ሲገቡ መታውቂያና የባንክ ቡክ ማሳየት ግዴታ ነው።

Via #addiscondowinners
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የ40/60 ቦሌ - ቦሌ አያት 1 - ሳይት 2 የውል መርሀ ግብር(Program)፦

•ቤቱ የሚገኝበት ክ/ከተማ-ቦሌ
•ቤቱ የሚገኝበት የሳይት ስም: ቦሌ አያት 1 - ሳይት 2
•ብሎኮች ብዛት:38
•በብሎኮቹ የሚገኙ ቤቶች ብዛት:1865

ወረዳ የሚሞላ(ቅጽ 9) መውሰድና ማስሞላት ለሳይቱ የተሰጠው ቀን: ከማክሰኞ 2 እስክ ሀሙስ 4/11/2011

የክፍያ ሰነድ(ቅጽ 3) ወስዶ ክፍያ መፈጸም አና ውል ለሳይቱ የተሰጠው ቀን: አርብ 5 እስከ ሀሙስ 11/11/2011

ማሳሰቢያ፦

🕰የስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2:30-6:30 እና ከሰዓት ከ7:30-11:00 በተጨማሪም ቅዳሜ ከ2:30-6:30

ወደ አዳራሽ መግባት የሚችለው ለአንድ ቤት የቤቱ ባለቤት ወይም ህጋዊ ወኪሉ ብቻ ነው። ወደ አዳራሽ ሲገቡ መታውቂያና የባንክ ቡክ ማሳየት ግዴታ ነው።

Via #addiscondowinners
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የ40/60 ቦሌ - ሰሚት የውል መርሀ ግብር(Program)፦

•ቤቱ የሚገኝበት ክ/ከተማ: ቦሌ
•ቤቱ የሚገኝበት የሳይት ስም: ሰሚት
•ብሎኮች ብዛት: 10
•በብሎኮቹ የሚገኙ ቤቶች ብዛት: 187

ወረዳ የሚሞላ(ቅጽ 9) መውሰድና ማስሞላት ለሳይቱ የተሰጠው ቀን : አርብ 28 እስከ ሰኞ 1/11/201

የክፍያ ሰነድ(ቅጽ 3) ወስዶ ክፍያ መፈጸም አና ውል ለሳይቱ የተሰጠው ቀን : ከማክሰኞ 2 እስክ ሀሙስ 4/11/2011

ማሳሰቢያ፦

🕰የስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2:30-6:30 እና ከሰዓት ከ7:30 -11:00 በተጨማሪም ቅዳሜ ከ2:30-6:30

ወደ አዳራሽ መግባት የሚችለው ለአንድ ቤት የቤቱ ባለቤት ወይም ህጋዊ ወኪሉ ብቻ ነው። ወደ አዳራሽ ሲገቡ መታውቂያና የባንክ ቡክ ማሳየት ግዴታ ነው።

Via #addiscondowinners
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የ40/60 የእህል ንግድ እና ህንጻ አቅራቢ እድለኞች፦

የ2ተኛ ዙር የ40/60 የእህል ንግድ እና ህንጻ አቅራቢ የቤት እድለኞች ካርታ ተሰርቶላቸው ወደባንክ ለብድሩ ማስያዣ የተላኩ ስም ዝርዝር ይመልከቱ👇
https://telegra.ph/4060-ባለእድለኞች-07-05-2

©#AddisCondoWinners
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአማራ ምሁራን መማክርት ጉባዔ ሰኔ 15/2011 የተከሰተውንና የመሪዎችን ህይወት የቀጠፈውን ድርጊት አወገዘ፡፡ ጉባዔው በክልሉ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በመምከር ባለ 11 ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥቷል፤ የመግለጫውን ሙሉ ቃል ይመልከቱ👇
https://telegra.ph/A-07-05-2

Via #AMMA
🗞ቀን ሰኔ 28/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde. @tikvahethiopia
ኢትዮጵያ🛫ኳታር

ከኢትዮጵያ ወደ #ኳታር የሚደረገው ሕጋዊ የውጭ ሀገር የሰራተኛ ስምሪት በዛሬው ዕለት ጀምሯል። በውጭ ሀገር ለስራ የሚሄዱ ዜጎችን ደህንነት እና ክብር ለማስጠበቅ ሲባል ወደ ውጭ ሀገራት የሚደረግ ጉዞ ታግዶ መቆየቱ የሚታወስ ነው።

Via #fbc
🗞ቀን ሰኔ 28/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከጅማ ዞን📩

"በጅማ ዞን #የፓስፖርት ጉዳይ አሳሳቢ ነው፤ በተለይ ለወንዶች፤ ፓስፖርት ለማውጣት ስንፈልግ #ስልጠና ውሰዱ ይሉናል ለወንዶች ስልጠና የሚሰጥ አካል ግን የለም። ለሚመለከተው አካል ብንናገርም ምላሽ ሚሰጠን ሰው የለም።" #አለልኝ

መላሽ የሚሰጥ አካል ካለ @tsegabwolde
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ethio_telecom ከሰሞኑ ለተፈጠረው የአገልግሎት መቋረጥ ይቅርታ ጠይቋል፤ ደንበኞቹ ላሳዩት ትዕስትም ምስጋና አቅርቧል። ወደፊት መሰል ችግሮች ሲከሰቱ በደንበኞች ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ በማያሳድር መልኩ ለመቅረፍ ሁኔታዎችን እያመቻቸ እንደሆነ አስታውቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ዜጎች በሀገራቸው ያለስጋት መኖር እንዲችሉና የሕግ የበላይነት እንዲረጋገጥ ኅብረተሰቡ በተደራጀ አግባብ ተንቀሳቅሶ የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፕሬስ ሴክሬታሪ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ጠየቁ፡፡ ከደቡብ ወሎ ዞንና ደሴ ከተማ መሪዎች ጋር በደሴ ከተማ ውይይት ያደረጉት የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፕሬስ ሴክሬታሪ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ንጉሱ በዚህ ወቅት በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች በሚስተዋለው ሥርዓት አልበኝነት፣ የስልጣን ጥማት፣ የግል ጥቅም ፍለጋ፣ የደቦ ፍርድና #የሀሰት_መረጃ የሕግ የበላይነትን እየሸረሸረ እንደመጣ ገልፀዋል፡፡

Via ኢዜአ
🗞ቀን ሰኔ 28/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በትናንቱ የሊቢያው አየር ጥቃት ከሞቱት ስደተኞች መካከል አንዷ ከሱማሌ ክልል የሄደች #ኢትዮጵያዊት ሱማሌ መሆኗን የሐርጌሳው ዜና ምንጭ ሆርን ዲፕሎማት ዘግቧል፡፡ ስደተኛዋ ለህልፈት የተዳረገችው በድብደባው ሳቢያ የግምብ ፍርስራሽ ተጭኗት መሆኑን አስከሬን የሚለዩ አካላት ገልጸዋል ተብሏል፡፡ በጥቃቱ እስካሁን 53 ስደተኞች እንደሞቱ ተረጋግጧል፡፡

Via #wazema
🗞ቀን ሰኔ 28/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UpdateSport ትናንት ምሽት #በሉዛን በተካሄደ የዳይመንድ ሊግ ውድድር በወንዶች 5 ሺህ ሜትር አትሌት ዮሚፍ ቀጀልቻ አሸንፏል። ዮሚፍ ርቀቱን በ13 ደቂቃ ከ56 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት አሸናፊ ሆኗል።አትሌት ሰለሞን ባረጋ ደግሞ 13 ደቂቃ ከ1 ሰከንድ ከ99 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት ውድድሩን 2ኛ በመሆን አጠናቋል። አትሌት ጥላሁን ሃይሌ 13 ደቂቃ ከ3 ሰከንድ ከ9 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት 3ኛ ደረጃን ይዟል።በወንዶች 1 ሺህ 500 ሜትር ደግሞ አትሌት አያንለህ ሱሌይማን 3 ደቂቃ ከ30 ሰከንድ ከ79 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት ውድደሩን በሶስተኝነት ጨርሷል።

Via #fbc
🗞ቀን ሰኔ 29/2011 ዓ/ም
@tikvahethsport
🏷ሃረማያ ዩኒቨርሲቲ
🏷ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ
🏷ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ
🏷ጎንደር ዩኒቨርሲቲ
🏷አርባምንጭ ዪኒቨርሲቲ
🏷ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ
🏷ጅማ ዩኒቨርሲቲ
🏷ወሎ ዩኒቨርሲቲ
🏷ሰመራ ዩኒቨርሲቲ
🏷ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ
🏷ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ
🏷ኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ
🏷አዲግራት ዩኒቨርሲቲ
🏷የደሴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች በዛሬው ዕለት #እያስመረቁ ይገኛሉ፡፡

🎓TIKVAH-ETH ለመላው ተመራቂዎችና የተመራቂ ቤተሰቦች በሙሉ እንኳን ደስ ያላችሁ ለማለት ይወዳል፡፡

🗞ቀን ሰኔ 29/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ ፕሮግራሞች በመጀመሪያና ሁለተኛ ዲግሪ ያስተማራቸውን 6 ሺህ 857 ተማሪዎች ዛሬ አስመርቋል። ከተመራቂዎች ውስጥ 5 ሺህ 728 በመጀመሪያ ዲግሪ፣ 578 የማስተርስ ዲግሪ እና 551 ተማሪዎች ለ2ኛ ደረጃ ት/ቤት መምርነት በድህረ ምረቃ የማስተማር ሙያ ዲፕሎማ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ መሆናቸውን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዳምጠው ዳርዛ በምረቃ ስነስርዐቱ ወቅት ገልፀዋል።

Via #EPA
🗞ቀን ሰኔ 29/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የጋሞ አባቶች እውቅና ተሰጣቸው!

የጋሞ አባቶች በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መካከል ተፈጥሮ በነበረው ግጭት #እርጥብ_ሳር ይዘው በመንበርከክ ጉዳት እንዳይደርስ ላደረጉት ሀገራዊ ተምሳሌትነት ዛሬ ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ፣ ከአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ በጎ አድራጎት ክበብ እና ከቀድሞ የአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎችና ባልደረቦች እውቅና ተሰጥቷቸዋል።

Via #EPA
🗞ቀን ሰኔ 29/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢትዮ ቴሌኮም 49 በመቶ ለግል ድርጅት ሊተላለፍ ነው!

በመንግሥት ይዞታ ስር የሚገኙ ተቋማትን ወደግል ለማዞር በሚደረገው ጥረት ኢትዮ ቴሌኮምን ለሁለት በመክፈል 49 በመቶው ወደግል ድርጅት ለማዞርና በተጨማሪ ሁለት የቴሌኮሙዩኒኬሽን ኩባንያዎች እንዲሰማሩ አቅጣጫ መቀመጡን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ። በስኳር ልማት ዘርፉ ከ13 ፋብሪካዎች ስድስቱን በቀጣይ ዓመት ወደግል ለማዞር የሚያስችል ሥራ እንደሚከናወን ተገልጿል።

🗞ቀን ሰኔ 29/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia