TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
ተጠርጣሪዎቹ እየታደኑ ነው...

አክሱም ዩኒቨርሲቲ ውስጥ በተፈጠረው ግጭት ተሳትፈዋል የተባሉ ተማሪዎችን #ፖሊስ በቁጥጥር ስር ለማዋል ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ገልጿል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ተፈታኞች ተጠንቀቁ...

የሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኞች ስህተት የሆኑ መልሶችን "የፈተና መልስ ነው" ብለው የሚሸጡ ግለሰቦች ስለሚኖሩ ከወዲሁ ጥንቃቄ እንድታደርጉ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በትግራይ ክልል በዓድዋ ከተማ በአንድ ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ብር ወጪ የተገነባው አጠቃላይ ሆስፒታል አገልግሎት መስጠት ጀመረ። ሳሊዝያን ኪዳነ ምህረት አጠቃላይ ሆስፒታል የተገነባው በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የዓዲግራት ሀገረ ስብከት ነው፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"የጎንደር ሃረገ ስብከት መንግስትን አስጠነቀቀ!"

#መንግስት ይህን #ሐጢአትም #ወንጀልም የሆነዉን ከኢትዮጵያዉያን ባህልና ሐይማኖት ስነልቦናም ጋር የማይጣጣመዉን #ግብረሰዶማዊነትን ለማስፋፋት በግብረሰዶማዉያን የተጀመረዉን እንቅስቃሴ #እንዲያስቆም የሰሜን ጎንደር ሃገረ ስብከት ጠየቀ፡፡ እንዲሀም ሲል የማስጠንቀቂያ መልዕክቱን ለመንግስት አስተላልፏል፡-

1) ጉብኝቱ ከሐይማኖት፣ ከህግ፣ ከሞራልና ከሃገሪቱ ባህል ጋር የሚጻረር ስለሆነ ፈቃድ እንዳይሰጠዉ፤ ከተሰጠዉም እንዲታገድ እንጠይቃለን፤

2) መንግስት በዚህ የጉብኝት መርሃ ግብር ላይ ያለዉን አቋም በአጭር ጊዜ ዉስጥ እዲያሳዉቀን እንጠይቃለን።

3) ይህ ሳይሆን ቀርቶ መርሀ ግብሩን ወደ ተግባር ለማዋል ቢሞክር ለሚፈጠረዉ ማንኛዉም ችግርና ቀዉስ መንግስት ተጠያቂ ይሆናል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለመንግስት የተሰጠ ማስጠንቀቂያ...

የአክሱም አስጎብኝ ማህበር ግብረሰዶማውያን በኢትዮጵያ ለማድረግ ስላቀዱት ጉብኝት ለኢፌድሪ ባህልና ቱሪዝም ሚንስትር #የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ፃፉ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የግብረ ሰዶማውያኑ ጉብኝት...

ከኢትዮጵያ ባህልና ልማድ #የተቃረነ ነው ተብሎ በህግ #ክልከላ የተጣለበት፣ የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪያን ወደ ኢትዮጵያ ለመምጣት የሚያደርጉት ዝግጅት፣ የሚያወጡት መግለጫ የተቃውሞ መልስ እየተሰጠው ነው፡፡ ይህንንም የማይገባ ግብር የሚያደርገው ቡድን ወደ #ኢትዮጵያ መግባት እንደሌለበት እና ወደ ቅጣትም እንደሚገባ በዚሁ ጉዳይ ላይ ወደ ኋላ እንደማይል የአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ እወቁልኝ ብሏል።

Via #ShegerFM
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Breaking የኢትዮጵያ ወንዶች ኘሪሚየር ሊግ ውድድር ለጊዜው እንዲቋረጥ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ውሳኔ አስተላልፏል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፕሪሚየር ሊጉ እንዲቋረጥ ተወስኗል‼️

የኢትዮጵያ የወንዶች ፕሪምየር ሊግ ውድድር ለጊዜው እንዲቋረጥ ውሳኔ ተላለፈ። የፌዴሬሽኑ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በዛሬው እለት አስቸኳይ ስብሰባውን አካሂዷል።

በዚህም በ27ኛው ሳምንት መካሄድ የነበረበት የኢትዮጵያ ቡና እና የመቐለ 70 እንደርታ ጨዋታ በፀጥታ ስጋት ምክንያት አለመካሄዱ በሊጉ ውድድር ላይ የሚኖረውን ተፅዕኖ በመገምገም ውሳኔዎችን አሳልፏል። በዚህም መሰረት በሁለቱ ከለቦች መካከል በነገው እለት እንዲካሄድ የወሰነው ውሳኔ እንዲሻር መወሰኑን ከፌዴሬሽኑ የተገኝ መረጃ ያመላክታል፡፡

ከዚህ ባለፈም ቀጣይ የፕሪሚየር ሊግ ውድድሮች በተገቢው ሁኔታ እንዲካሄዱ ከክለቦችና ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ተነጋግሮ ዘላቂ መፍትሄ እስከሚሰጠው ድረስ ውድድሩ ላልተወሰነ ጊዜ እንዲቋረጥም ነው የወሰነው። የተለያዩ ወጪዎች እና ሌሎች ጉዳዮች በደንቡ መሰረት የሚጠየቁ ጥያቄዎች በፌዴሬሽኑ የዲሲፕሊን የውድድር ደንብ መሰረት እንዲታዩም ውሳኔ አሳልፏል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Breaking የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበርን በፕሬዚዳንትነት የመሩት እና ሰፊ ተመልካች ያገኘው የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ውድድር ለመመሰረቱ ጉልህ ሚና የነበራቸው ሌናርት ጆሃንሰን በአጭር ቀናት ህመም በ89 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopi
#update ግጭት፣ መፈናቀልና ድርቅ በተከሰተባቸው አካባቢዎች ትምህርታቸውን ላቋረጡ ተማሪዎች የክረምት ማካካሻ ትምህርት እንደሚሰጥ የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

√300 ሺህ የሚሆኑ ተማሪዎች የትምህርት ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ሲሆን ያቋረጡትን ለማካካስ ከሰኔ 2011 ዓም እስከ መስከረም 30 ቀን 2012 ዓም ትምህርት ይሰጣል

√ስድስት ሺህ ተመራቂ ተማሪዎች በእነዚህ አካባቢዎች ተሰማርተው በበጎ ፈቃድኝነት ትምህርት የሚሰጡ ይሆናሉ

√ይህን የትምህርት አገልግሎት ለመስጠት በአጠቃላይ 1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር የሚያስፈልግ ሲሆን ከግል ትምህርት ቤቶች፣ ከአጋር አካላት፣ ከክልል ትምህርት ቢሮዎች፣ ከግለሰቦች፣ ከተማሪዎችና ከሌሎችም የህብረተሰብ ክፍሎች ለመሰብሰብ ታቅዷል

√ባለሃብቶችን ያሳተፈ ገቢ ማሰባሰቢያ ሁለት የእራት ፕሮግራሞችን ይካሄዳሉ

√ለተማሪዎቹ ከመደበኛ ትምህርት በተጨማሪ የትራፊክ አገልግሎት፣ የአካባቢ ጉዳዮች፣ የጤና እና ሌሎችንም ትምህርቶች እንዲያገኙ ይደረጋል

√ካለፈው ታህሳስ ወር ጀምሮ በድርቅ፣ በመፈናቀልና በግጭት ምክንያት 813 ትምህርት ቤቶች ተዘግተው ነበር በአሁኑ ወቅት 564ቱ ተከፍተዋል

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በነገው እለት ከመላ ሀገሪቱ ከተውጣጡ የፍትሕ አካላት አባላት ጋር ይወያያሉ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኦሮምኛ ድምጻዊ ዳዲ ገላንን ገድሏል የተባለው የእድሜ ልክ እስራት ተፈረደበት👇
ድምጻዊ ዳዲ ገላንን ገድሏል የተባለው ተከሳሽ፣ ከተማ ረጋሳ፣ የእድሜ ልክ እስራት ተበየነበት።

የምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዛሬ ግንቦት 28 2011ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ ከተማ ረጋሳ ድምጻዊ ዳዲ ገላንን ለመግደል ሆነ ብሎና አቅዶ የካቲት 4 2011 ዓ.ም. ከምሽቱ 5፡30 ላይ በሊበን ጩቃላ ወረዳ በሽጉጥ ሁለት ግዜ ተኩሶ ደረቱን መትቶ መግደሉ ተረጋግጧል ብሏል።

ድምጻዊ ዳዲ ገላን በጥይት ተመትቶ የሞተ ዕለት አሟሟቱ ለደስታ በተተኮሰ ጥይት እንጂ ሆነ ተብሎ የተደረገ አይደለም የሚል እምነት ነበር።

በወቅቱ ቢቢሲ ያነጋገራቸው የድምጻዊው ጓደኛ እና የሊበን ጩቃላ ወረዳ ፖሊስ ፅፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ግርማ ሚደቅሳ ድምጻዊው ለደስታ በተተኮስ ጥይት መገደሉን ገልጸው ነበር።

የአስክሬን የምረመራ ውጤት አርቲስቱ ሁለት ግዜ በሽጉጥ ጥይት ተመትቶ መገደሉን ያረጋገጠ ሲሆን አንድ ጥይት የሟች አስክሬን ውስጥ ተገኝቷል ተብሏል።

ፍርድ ቤቱ በተጨማሪም ከሟች አስክሬን ውስጥ የወጣው ጥይት አይነት ተከሳሽ ከሚይዘው ሽጉጥ የተተኮሰ መሆኑ ተረጋግጧል ብሏል።ተከሳሹ ግድያውን አልፈጸምኩ ሲል ቢከራከርም የቀረበበትን ማስረጃ መከላከል ግን አልቻለም።

አቃቤ ሕግ በተከሳሹ ላይ የቅጣት ማክበጃ ሃሳብ የለኝም በማለት ፍርድ ቤቱ ውሳኔ እንዲያስተላልፍ ጠይቋል።

የተከሳሽ ጠበቃ በበኩላቸው ደንበኛቸው ከዚህ በፊት ተከስሰው እንደማያውቁ፣ የተመሩ ሰው አለመሆናቸውን፣ የጦር መሳሪያ አጠቃቀም ላይ ያላቸው ግንዛቤ አነስተኛ መሆኑን እንዲሁም የበርካታ ቤተሰብ አስተዳዳሪ መሆናቸውን በመጥቀስ ቅጣቱ እንዲቀንስ ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል።

ተከሳሹም አቅመ ደካማ የሆኑ ሰዎችን ጨምሮ 9 የቤተሰብ አባላት አስተዳዳሪ መሆናቸውን በመጥቀስ ፍርድ ቤቱ ቅጣቱን እንዲቀንስላቸው ተማጽነዋል።

የግራ ቀኙን ክርክር ያደመጠው የምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተከሳሸ ከተማ ረጋሳ ድምጻዊ ዳዲ ገላንን መግደሉ በመረጋገጡ የእድሜ ልክ ጽኑ እስራት በይኖበታል።

ድምጻዊ ዳዲ ገላን ፓለቲካዊ ይዘት ያላቸውን የኦሮምኛ ሙዚቃዎችን በመጫወት የሚታወቅ ሲሆን በዘፈኖቹ በተደጋጋሚ ለእስር ተዳርጎ ነበር።

Via #BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአቶ ኢሳያስ ዳኘው ጠበቆች የፌዴራሉ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ በደንበኛቸው ላይ አሻሸሎ ያቀረበው ክስ ከፍርድ ቤቱ ትእዛዝ ውጭ መሆኑን በመግለጽ አቤቱታ አቀረቡ።

የቀድሞ የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር የነበሩት ሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው ወንድም አቶ ኢሳያስ ዳኘው ዛሬ በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15ኛ ወንጀል ችሎት ቀርበዋል።

የፌዴራሉ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ግንቦት 16 ቀን 2011 ዓ.ም በእነ አቶ ወልደጊዮርጊስ ወልዱ የክስ መዝገብ ሁለተኛ ተከሳሽ በሆኑት በአቶ ኢሳያስ ዳኝው ላይ የተሻሻለ ክሱን ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል።

የአቶ ኢሳያስ ዳኝው ጠበቆች ዛሬ ለፍርድ ቤቱ በጽሑፍ ያቀረቡት አቤቱታ አቃቤ ሕግ አሻሽሎ ባቀረበው በዚህ ክስ ላይ ቃላትና ቁጥር አውጥቶ ከፍርድ ቤቱ ፈቃድ ውጪ ሶስት ምስክሮችን አቅርቧል ይላል።

በመሆኑም አቃቤ ሕግ ለፍርድ ቤቱ ያቀረበውን ክስ አቀራረብ በተለይም የማስረጃዎችን ጉዳይ ለመረዳት አዳጋች ሆኖብናል በማለት አስታውቀዋል።

አቃቤ ሕግ ያሻሻለው የክስ አቀራረብ በተለይም የማስረጃ ጉዳዩን ለመረዳት አዳጋች አድርጎብናል በዚህም ምክንያት ጉዳዩን በምን መልኩ ማስኬድና ደንበኞቻችንን ማማከር እንዳለብን ለመወሰን ተቸግረናል ነው ያሉት።

እናም ፍርድ ቤቱ በቀረበው አቤቱታ ላይ የሚሰጠውን ትዕዛዝ ተመልክተን በተሻሻለው ክስ ላይ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ እናቅርባለን ወይም ቀጥታ ምስክር ወደማሰማት ሂደት እንገባለን የሚለውን እንመለከታለን ብለዋል ጠበቆቹ።

የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ለአቤቱታው ምላሽ ለመስጠት ለግንቦት 30 ቀን 2011 ዓ.ም ቀጠሮ ይዟል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአክሱም ዩኒቨርሲቲ በተማሪዎች መካከል በተፈጠረው ግጭት ለአንድ ተማሪ ህልፈት ምክንያት የሆኑ #ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር የማዋል ስራ መጀመሩን የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረጽዮን ገለጹ።

ምክትል ርዕሰ መስተዳደዱ ዛሬ ከሰዓት በኋላ በሰጡት መግለጫ ላይ በተማሪው ሞት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልጸዋል።

ህይወቱ ላለፈው ተማሪ ቤተሰቦችና ጓደኞች መፅናናትን የተመኙት ዶክተር ደብረጽዮን፥“ድርጊቱ አስነዋሪ ነው” ብለዋል።

“ትግራይ የብሄሮችና ብሄረሰቦች መኖሪያ መሆኗን አምኖ ለመጣ ተማሪ እንዲህ አይነት ተግባር መፈፀም ሰላም ወዳዱን የክልሉን ህዝብ ባህልና ታሪክ የማይገልፅ ነው” ብለዋል።

ድርጊቱን የፈፀሙ ተማሪዎች በቁጥጥር ስር የማዋሉ ተግባር መጀመሩን አስረድተው፥ ተጠርጣሪዎቹ ጥፋታቸውን በማጣራት የክልሉ መንግስት ወደ ህግ የሚያቀርባቸው መሆኑን ገልፀዋል።

በመስዋእትነት የተረጋገጠው ሰላም በጥቂት ግለሰቦች አይደፈርስም ያሉት ምክትል ርእሰ መስተዳድሩ፥ “ህብረተሰቡ ሰላሙን ለማስጠበቅ ከመቼውም ጊዜ በላይ መነሳት ይኖርበታል” ነው ያሉት።

በክልሉ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተለይም በአክሱም ዩኒቨርስቲ የሚማሩ ተማሪዎች ተረጋግተው ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ የጠየቁት ዶክተር ደብረጽዮን፥ የክልሉ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግም ጠቁመዋል።

ምንጭ፦ ኤዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ADP

ግንቦት 27 ቀን 2011 ዓ.ም. በአክሱም ዩኒቨርስቲ የ2ኛው አመት የሜካኒካል ኢንጅነሪንግ ተማሪ በነበረው ዮሐንስ ማስረሻ ሰይፈ ላይ የተፈፀመውን ግድያ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት አጥብቆ ያወግዛል፡፡

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በተማሪ ዮሐንስ ማስረሻ ሞት የተሰማውን መሪር ሃዘን እየገለጸ ለሟች ቤተሰቦች፣ ጓደኞቹና ለዩኒቨርሲቲው ማሕበረሰብ በሙሉ መጽናናትን እንመኛለን።

በአክሱም ዩኒቨርሲቲ አካባቢ የሚገኙ የመስተዳድር እና የጸጥታ አካላት እንዲህ አይነት አስነዋሪ ድርጊቶች ወደፊት እንዳይደገሙ አስቀድሞ በመከላከል ረገድ እንዲሁም የተማሪዎችን ደህንነት የማስጠበቅ ኃላፊነት እንዳለባቸው ግልጽ ሊሆን ይገባል፡፡

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ይህንን አጸያፊ ድርጊት የፈጸሙ ወንጀለኞች በአስቸኳይ ተለይተው ለፍርድ እንዲቀርቡ ለማድረግ እና ወደፊትም ተመሳሳይ ችግሮች እንዳይከሰቱ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅርበት እየሰራ መሆኑን ይገልጻል፡፡

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት
ግንቦት 28 ቀን 2011 ዓ.ም.
ባህር ዳር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የግብረ ሰዶማዊያኑ ጉዞ ተወገዘ...

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሲኖዶስ አንድ የግብረ ሰዶማዊያን ቡድን በኢትዮጵያ ጉብኝት ለማድረግ ማቀዱን አውግዟል፡፡ ጉብኝቱን ያዘጋጀው “ቶቶ” የተሰኘ መቀመጫውን አሜሪካ ያደረገ አስጎብኝ ድርጅት ሲሆን ሲኖዶሱ ይህንኑ ድርጅትም መውቀሱን ፋና ብሮድካስት ዘግቧል፡፡ ቡድኑ ጉብኝቱን ሊያደርግ ያሰበው በላሊበላ ጥንታዊ አብያተ ክርስቲያናት ነው፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዝግጅቱ ተጠናቋል...

ለሀገር አቀፍ የ8ኛ፣ 10ኛ እና 12ኛ ክፍል ፈተናዎች አስፈላጊው ዝግጅት መጠናቀቁን ሀገር አቀፍ የፈተናዎች ኤጀንሲ አስታውቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በነአቶ በረከት እና ታደሰ ክስ ላይ የዐቃቢ ሕግ ምስክሮች ሲያዳምጡ ውለዋል፤ የክልሉ ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ይፋ ባደረገው ዘገባ ደግሞ ማብራሪያ እንዲሰጥ በፍርድ ቤቱ ተጠይቋል፡፡

አቶ በረከት ስምዖን እና አቶ ታደሰ ካሳ በተከሰሱባቸው መዝገብ ቁጥር 2፣ 3 እና 4 ዛሬ ከሰዓት በፊት በተሰየመው ችሎት የዐቃቢ ሕግ ምስክሮችን ቃል መስማት የጀመረው ፍርድ ቤቱ ከሰዓት በኋላም የአንድ ምስክር ቃልን አድምጧል፡፡ የቀሪ ምስክሮችን ቃል ለመስማትም ለነገ ግንቦት 29 ቀን 2011ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

ፍርድ ቤቱ ከዚህ በፊት በተሰየመው ችሎት ያዳመጠውን የዐቃቢ ሕግ ምስክሮች ቃል ወደ ጽሑፍ ሳይቀየር እና ትክክለኛነቱን ፍርድ ቤቱ ሳያረጋግጥ የክልሉ ፀረ ሙስና ኮሚሽን መዘገቡን ተከትሎ የኮሚሽኑ ኮሚሽነር እና የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ ነገ ግንቦት 29 ቀን 2011 ዓ.ም ለፍርድ ቤቱ ቀርበው ማብራሪያ እንዲሰጡ ትዕዛዝ አስተላልፏል፡፡

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ...

ተማሪዎች በመማሪያ ክፍላቸው በመገኘት ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ጥብቅ ማሳሰቢያ ሰጠ። ትምህርታቸውን በማይከታተሉ ተማሪዎች ላይ ዩኒቨርሲቲው ደረጃ በደረጃ ማናቸውንም አገልግሎቶች የሚያቆምና አስተዳደራዊ እርምጃ እንደሚወስድ ገልጿል።

አተያየታቸውን ለTIKVAH-ETH የሰጡ ተማሪዎች በበኩላቸው፦ ዩኒቨርሲቲው አሁንም ወደቀደመው ሰላሙ እንዳልተመለሰና የደህንነት ስጋት እንዳለባቸው ገልፀው የሚመለከተው አካል ችግሮችን #በዘላቂነት ሊፈታ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
/የአክሱም ዩኒቨረስቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ፀሐይ አስመላሽ/ የተናገሩት፦
.
.
"ከአክሱም ከተማ ነዋሪዎች፣ ከሃገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት መሪዎች ጋር በመሆን ውይይት ተጀምሯል፤ የተደረገው ውይይት ተማሪዎችን ለማረጋጋት ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል"

"በድርጊቱ የተሳተፉ አካላትን ለህግ ለማቅረብ ፖሊስ ምርመራ የጀመረ ሲሆን ህብረተሰቡም መረጃ በማቅረብ ትብብር እያደረግ ይገኛል"

"የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ከመሰል ድርጊቶች ራሳቸውን በማራቅ ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለመጡበት ዓላማ ሊቆሙ ይገባል"

Via #ፋና
@tsegabwolde @tikvahethiopia