TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
እናመግናለን!! #ዋቸሞ_ዩኒቨርሲቲ ለTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ላደረጋችሁት አቀባበል፤ ከልብ #እናመሰግናለን!!

ፍቅርን፤ ሰው ማክበርን አስተምራቹናልን!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ከሰኞ ጀምሮ ወደ ትምህርት በማይመለሱ የህክምና ሙያ ተማሪዎች እርምጃ እንደሚወሰድ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴሩ በተወሰኑ ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ የመጨረሻ አመት (ኢንተርን) ተማሪዎችና ስፔሻሊቲ (ሬዚደንት) ተማሪዎች ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጋር ውይይት ከተካሄደ በኋላ ላነሷቸው ጥያቄዎች እርምጃዎች እንደተወሰዱ ነው ያስታወቀው፡፡ ምላሽ ላላገኙ ጥያቄዎችም በዝርዝር አጥንቶ ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት አራት ግብረ ሃይል ተቋቁመው ወደ ስራ መግባቱን ሚኒስቴሩ አስታውሷል፡፡

ሆኖም አሁንም በተወሰኑ ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርት ያቋረጡ ተማሪዎች አሉ ሲል ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡ በመሆኑም ፍጹም ተቀባይነት የሌለው ተግባር መሆኑን ተማሪዎች ተገንዝበው በፍጥነት ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ በማለት አሳስቧል፡፡ ከሰኞ ጀምሮ ወደ ትምህርታቸው የማይመለሱትን ተማሪዎች ተቋማት ባላቸው የአካዳሚክ ህግ ቀጣይ እርምጃ እንዲወስዱ መመሪያ መተላለፉን ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለመላው የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች፦

#የStopHateSpeech መድረክ በLTH 7 ዛሬ ከቀኑ 9:00 ጀምሮ ይካሄዳል። ተማሪዎች ከመቐለ፣ ሀዋሳ፣ ወላይታ ሶዶ፣ አርባምንጭ፣ ወልቂጤ፣ ቤተሰቦቻችን ጋር ተገናኝተን እንወያያለን።

ከ9:00 ጀምሮ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Alert‼️

"ፀግሽ መካኒሳ #ቆሬ የሚገኘው ካምፕ ውስጥ #እሳት_አደጋ ተነስቷለል!!"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ❤️እናመሰግናለን!!

#እንዳከበራችሁን ፈጣሪ #ያክብራችሁ!!
#StopHateSpeech

መላው የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ፤ የተቋሙን #አመራሮችን እንዲሁም ተማሪዎችን ከልብ እናመሰግናለን!

በቀጣይ፦

#ጅማ_ዩኒቨርሲቲ/ግንቦት 17 እና 18/
#ሀረማያ_ዩኒቨርሲቲ/ግንቦት 24 እና 25/
#ጎንደር_ዩኒቨርሲቲ/ሰኔ 1 እና ሰኔ 2/
#ባህር_ዳር_ዩኒቨርሲቲ/ሰኔ 1 እና ሰኔ 2/
.
.
.
በሌሎች ግቢዎች የቀን መርሃ ግብር ይፋ ይደረጋል!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Alert‼️

"ፀጋብ ኤሬ የሚመለከተው አካል #መላ እንዲለን ድምፃችንን አሰማልን። #የድሬዳዋ_ዩኒቨርስቲ ነገር መላ ቅጡ ጠፍቷል። ትናንት ተማሪዎቹ ገብተው ሰላም ሰፈነ ስንል ይሄው ዛሬ ማታ አገርሽቶበታል። ኡፍፍፍ በጣም ነዉ የሚጨንቀዉ!"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ትናንት በንፋስ ስልክ ወረዳ ሁለት በሚገኝ የወታደሮች መኖሪያ ግቢ በተነሳ እሳት ቃጠሎ ጉዳት መድረሱን ሸገር ዘግቧል፡፡ በአደጋው የአንዲት ሴት ሕይወት ጠፍቷል፤ 3 ሰዎች ቀላልና ከባድ መቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል፡፡ 13 መኖሪያ ቤቶችም ተቃጥለዋል፤ በጠቅላላው 300 ሺህ ብር የሚገመት ንብረት ወድሟል ተብሏል፡፡

Via #ሸገርFM
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ትምህርት አቋርጠው የነበሩ አብዛኛዎቹ የህክምና ሙያ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው መመለሳቸውን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዲኤታው ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ በተወሰኑ ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ የመጨረሻ አመት (ኢንተርን) ተማሪዎችና ስፔሻሊቲ (ሬዚደንት) ተማሪዎች ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጋር ከተወያዩ በኋላ ጥያቄ ማቅረባቸውን አስታውሰዋል።

መንግስትም ላቀረቧቸው ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት እየሰራ እንደሚገኝም ሚኒስትር ዲኤታው ገልጸዋል።

ይሁን እንጅ በተወሰኑ ዩኒቨርሲቲዎች ባለፉት ቀናት ትምህርታቸውን አቋርጠው እንደነበርም በዛሬው እለት በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

ሚኒስቴሩም ከዛሬ ጀምሮ ወደ ትምህርት ገበታቸው በማይመለሱ ተማሪዎች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ መግለጹ የሚታወስ ነው።

በዛሬው እለትም ትምህርት አቋርጠው የነበሩ አብዛኛዎቹ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታ መመለሳቸውን ሚኒስትር ዲኤታው ተናግረዋል።

ሚኒስትር ዲኤታው ከዛሬ ጀምሮ ወደ ትምህርታቸው በማይመለሱ ተማሪዎች ላይም ተቋማት ባላቸው የአካዳሚክ ህግ እርምጃ እንደሚወስዱም ነው የተናገሩት።

የመጨረሻ አመት የህክምና ተማሪዎች ላነሷቸው ጥያቄዎችም በዝርዝር አጥንተው ዘላቂ መፍትሔ የሚሰጡ ግብረ ሃይሎች ተቋቁመዋልም ነው ያሉት።

ግብረ ሃይሎቹ በዛሬው እለት በቢሾፍቱ እየተወያዩ ሲሆን፥ በሳምንቱ መጨረሻ የጥናት ግኝታቸውን ለሚኒስቴሩ እንደሚያቀርቡ አስረድተዋል።

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወልዲያ ዩኒቨርስቲ!!


ሰሞኑን ከመጠጥ ውሃ አቅርቦት ጋር ተያይዞ በተማሪዎቻችን ተነስቶ የነበረው ቅሬታና አለመግባባት በውይይት ተፈትቷል፡፡

በውይይቱ በቅርቡ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር እንደ አዲስ ያደራጀውን ሀገራዊ የቦርድ አወቃቀር መነሻ በማድረግ የዩኒቨርሲቲው ስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው የተሰየሙት እና በም/ፕሬዚዳንት ማዕረግ የኦሮሚያ ክልል የኢኮኖሚክ ክላስተር አስተባባሪ የሆኑት ክቡር አቶ አህመድ ቱሳ፡ በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የአስተዳደር ጉዳዮች ጀኔራል ዳይሬክተር ክቡር አቶ ጌታቸው ፡የሰሜን ወሎዞን አስተዳዳሪና የዩኒቨርስቲው ስራ አመራር ቦርድ ም/ሰብሳቢ አቶ ወልደትንሳኤ መኮንንና የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ደሳለኝ ሞላን ጨምሮ ም/ፕሬዚዳንቶች ተገኝተዋል ፡፡ ውይይቱ ውዥንብሮች የጠሩበት ፡ ተማሪዎች በርካታ ጥያቄዎችን ያነሱበትና ዩኒቨርሲቲውም በተነሡት የግልፅነት መረጃዎችና ችግሮች ላይ ምላሽና ማብራሪያ የሰጠበት፡ የተቋሙም ሆነ የተማሪዎቹ ክፍተት የተጠቆመበት ነበር ፡፡

በአጠቃላይ ውይይቱ ስኬታማ በሆነ መንገድ የተጠናቀቀ ሲሆን ከዛሬ 12/9/2011 ዓ.ም ጀምሮ መደበኛው የመማር ማስተማር ስራው እንዲቀጥል የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል ፡፡

በመጨረሻም የተፈጠረውን አለመግባባት በውይይት ለመፍታት በተደረገው ጥረት ከጎናችን ለነበራችሁ ሁሉ ከፍ ያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን ፡፡ የተፈጠረውን መጠነኛ አለመግባባት መሠረት አድርገው የተዛባ መረጃ፡ ውዢንብሮችንና የሀሰት መረጃዎችን በመልቀቅ ተማሪዎቻችንን፡ የተማሪ ወላጆችንና የአካባቢውን ማህበረሰብ ጭምር ስጋት ላይ የጣሉ አካላት ተፅዕኖ ቀላል እንዳልሆነ እንረዳለን ፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በዛሬው ዕለት ስለክህምና ተማሪዎች በሚዲያ የተነገረው ሀሰት ኑው ሲሉ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ገልፀዋል:: አሁንም እየተነሱ የሚገኙትን ጥያቄዎች በአግባቡ እንዲመለሱ ተጠይቀል::

@tsegabwolde @tikvahethiopia