TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
መልካም የፋሲካ በዓል~~እናሳክማቸው!
(26,500 ብር ደርሰናል አግዙን)

/ቤተሰባችን(TIKVAH) እስካሁን 26,500 ብር ለእነዚህ ታዳጊዎች የነገ ሀገር ተረካቢዎች #በጥቂት ቀናት ማሰባሰብ ችሏል፤ የተለያዩ ስራዎች በበጎ አድራጎት እንቅስቃሴዎቻችን ላይ ጊዜ እየተሻሙብን ይገኛሉ ይህን ችግር ለመፍታት እና ለወገኖቻችን ከጎናቸው ለመሆን በርካታ አማራጮች ላይ እየሰራን እንገኛለን/

~~እናሳክማቸው~~
#1

√ሳምራዊት አረጋ
√እድሜ 22
√የአድማስ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ
√በደረሰባት ድንገተኛ የኩላሊት ህመም በአልጋ ላይ የወደቀች እህታችን...ልጃችን
.
.
.
#2

√ምህረቱ መንግስቴ
√ከ8ተኛ ክፍል ትምህርቱን አቋርጦ ለ11አመታት በየሆስፒታሉ ሲንከራተት የቆየ በሰው እቅፍ ካልሆነ መንቀሳቀስ የማይችል ሲመገብም ሆነ ለተፈጥሮ ግዳጅ መቀመጥ የማይችል
√በከፋተኛ የአጥንት ቁስለት እየተሰቃየ ከግራታፋው 5 የተለያዩ ቁስለቶች ፈሳሽ የሚፈሰው
√ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ውጭ ሀገር እንዲታከም ሪፈር የፃፈለት 1.2ሚሊየን ብር የተጠየቀ ነገር ግን ወላጁን በሞት ያጣና ምንም ገቢ የሌለው አሳዛኝ የ21 አመት ታዳጊ
.
.
.
#3

√ካሊድ ኡመር
√የ16 አመት ታዳጊ
√በኩላሊት ህመም የሚሰቃይ ልጃችን...ወንድማችን


በሞባይል ባንኪንግ..

1000278664612 ~ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
በሶስቱም ስም የተከፈተ አካውንት ነው!!

500,000 ብር ሊሰበሰብ የታቀደው!
#TIKVAH_ETHIOPIA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የፋሲካ በዓል እየተከበረ ይገኛል...

በመላው ሀገሪቱ በሚገኙ የክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ የፋሲካ በዓል በመከበር ላይ ይገኛል። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን፣ በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን እና በኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ለሊቱን የተለያዩ መንፈሳዊ ስነ ስረዓቶች ተከናውነዋል።

በዓሉን አስመልክቶ መልዕክት ያስተላለፉት የሀይማኖት አባቶች የትንሳዔን በአል ስናከብር የተቸገሩ እና ረዳት የሌላቸውን ወገኖች በማስታወስ ሊሆን እንደሚገባ የክርስትና እምነት አባቶች አሳስበዋል። አባቶቹ ባስተላለፉት መልእክትም ከበዓሉ መልካምነትን ፣ አንድነትን እና ፍቅርን በመማር ክርስቲያናዊ እና ሰባዊ ሃላፊነታችንን ልንወቀጣ ይገባል ሲሉም ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብጹእ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ባስተላፉት ምልእክት፥ ህዝበ ክርስቲያኑ በዓለ ትንሳኤን ከማክበር ባለፈ ከበዓሉ መንፈሳዊ እና ሰብአዊ ሞራላችንን በህግ እና በፍቅር ልናድስ ይገባል ብለዋል።

በሀገሪቱ የሚስተዋሉ አሳሳቢ ሁኔታዎችን ወደ አስተማማኝ መንገድ ልንመልስ የምንችለው በአእምሯችን መሽገው የሚገኙ ጭፍን አስተሳሰቦችን ከጭንቅላታችን ማስወጣት ስንችል ነው ሲሉም ተናግረዋል።

የኢዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ብጹእ ካርዲናል ብርሃነ ኢየሱስ በበኩላቸው፥ ለካቶሊክ እምነት ተከታዮች እና ለህዝበ ክርስቲያኑ በሙሉ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ካርዲናል ብርሃነ ክርስቶስ አክለውም፥ የhገርን ሰላም ለማስቀጠል ሁላችንም በፍቅር ልንጓዝ ይገባል ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ እየሱሰ ፕሬዚዳንት ቄስ ዮናስ ይገዙም ለእምነቱ ተከታዮች ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክታቸው ህብረተሰቡ በዓሉን በመተሳሰብና በመደጋገፍ እንዲያከብር ጥሪ አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ፕሬዚደንት ፓስተር ጻድቁ አብዶም የእንኳን አደረሳችሁ መልእክታቸውን በማስተላለፍ፥ በዓሉን ከማክበር ባለፈ የሀጀገር እንድነትን ልንጠብቅ እና በፍቅር ልንጓዝ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

በዓሉን ስናከብር ባለን አቅም ደካሞችን እና ረዳት የሌላቸውን ወገኖች በማሰብ ሊሆን ይገባል ያሉት የሀይማኖቱ መሪዎቹ፥ በዓሉ የመተሳሰብ እና የፍቅር እንዲሆንም መልካም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል።

Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአክሱም ሀውልትን ለመጠገን ጣሊያን አስፈላጊውን ድጋፍእንደምታደርግ ገለፀች። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከጣሊያኑ አቻቸው ጋር ተወያይተዋል። ሁለቱ መሪዎች በቻይና ከሮድ ኤንድ ቤልት ጉባኤ ጎን ለጎን ባደረጉት ውይይት አንቶኒዮ ኮንቴ ሀገራቸው የአክሱም ሀውልትን ለመጠገን አስፈላጊውን ድጋፍ እንደምታደርግ ገልፀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የቻይና ቆይታቸውን አጠናቀው #ተመልስዋል

Via #etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደሀገር ተመልሰዋል...

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የቻይና ቆይታቸውን አጠናቀው ወደሀገራቸው #ተመልሰዋል

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአፍሪካ የሰብዓዊና ህዝቦች መብቶች ኮሚሽን በአፍሪካ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ስደተኞች በማስተናገድ ሁለተኛውን ደረጃ በመያዟ ለሀገራችን ለኢትዮጵያ ሽልማት አበርክቷል፡፡ የሽልማት ስነ-ስርዓቱም በሻርማልሼክ ግብጽ በተካሄደው የOAU Convention Governing Specific Aspects of Refugee Problems in Africa 50ኛ ዓመት ክብረ-በዓል ላይ ተበርክቷል፡፡

Via የሰላም ሚኒስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ የቀብር ሥነ ሥርዓትን በተመለከተ ብሔራዊ ኮሚቴ ይቋቋማል ተብሏል። ዝርዝር ጉዳዮችም በየጊዜዉ እንደሚገለፁ ነው የተሰማው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር በእድሳት ምክንያት እስከ ግንቦት 01 ቀን 2011 ዓ.ም ድረስ #ዝግ ስለሚሆን ትርዒቶች #እንደማይቀርቡ አስታውቋል። እድሳቱን የሚያደርገው የአውሮፓ ህብረት ነው።

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ትላንት የአሜሪካ ጦር በሶማሊያ የአይሲስ ታጣቂዎች ላይ በወሰደው የድሮውን ጥቃት ሶስት የአይሲስ አሸባሪዎችን በሀገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል ገድሏል፡፡ በአፍሪካ የአሜሪካ ጦር እዝ እንዳስታወቀው ታጣቂዎቹ የአካባቢውን ህብረተሰብ ሲያስጨንቁ እንደነበረ አስታውሶ ጦሩ በታጣቂዎች ላይ በወሰደው እርምጃ አንድም ሰላማዊ ሰው ጉዳት እንዳልደረሰበት ተናግረዋል፡፡ ጦሩ አሁኑ የወሰደው እርምጃ በወር ውስጥ ለ2ኛ ግዜ ሲሆን የመጀመሪያው ባለፈው ሚያዝያ 14 ባደረገው ጥቃት የአይሲስ ታጣቂዎች ሁለተኛ መሪ የሆነውን አብዱልሃኪም ዳቁባ መድግደሉ ይታወሳል፡፡ ሶማሊያ በአልሸባብ ታጣቂዎች ለአመታት በመታመሳ ለ10 ሺዎች ሞትና ለሚሊዮኖች ስደት መዳረጉን ዘገባው አመልክቷል፡፡

ምንጭ፡- ሲጂቲኤን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#TIKVAH_ETH 🇪🇹 #StopHateSpeech

•ሚያዚያ 23
•ሚያዚያ 25 እና 26

√ረቡዕ - ወሎ ዩኒቨርሲቲ
√አርብ እና ቅዳሜ - መቀለ ዩኒቨርሲቲ

ወደ #ወሎ_ዩኒቨርሲቲ እና #መቀለ_ዩኒቨርሲቲ የሚጓዙት፦

√የአርባምንጭ ዩንቨርስቲ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት

√የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት

√የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት

√የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት

ከ100 የሚበልጡ #የሰላም እና #የፍቅር አምባሳደሮች በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ይሰባሰባሉ!!

ኑ ኢትዮጵያን #በፍቅር እንገንባ!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ትኩረት~~ማንቡክ ለሚገኙ ዜጎች‼️

በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ዳንጉር ወረዳ ማንቡክ ቀበሌ እየተፈፀመ ያለውን የዜጎች #ስቃይ እና #እንግልት የፌደራሉ መንግስት በአስቸኳይ ሊያስቆመው ይገባል፤ ወንጀለኞችንም ሳይውል ሳያድር ለፍርድ ሊያቀርብ ይገባል። ዜጎች በገዛ ሀገራቸው ወጥተው ለመግባት #የሚሳቀቁበት እና #የሚፈሩበት ምክንያት ሊኖር አይገባም።

ለሀገር መከላከያ ሰራዊት
ለፌደራል ፖሊስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ትላንት የወጣው #የትንሳኤ_ሎተሪ ዕጣ መግለጫ...
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ: ETRSS-1 በሃገረ ቻይና ቤይጂንግ በመገጣጠም ላይ ያለች የመጀመሪያዋ የኢትዮጵያ ሳተላይት ናት። 70 ኪሎ ግራም የትመዝነው ETRSS-1 በያዝነው የፈረንጆቹ አመት 2019 ከመገባደዱ አስቀድማ እንደምትጠናቀቅ ይገመታል። ETRSS-1 ኢትዮጵያን ከምስራቅ አፍሪካ ከኬንያ በመቀጠል የራሷን ሳተላይት የተኮሰች ሃገር የምታደርጋት ሲሆን ፤ ከአፍሪካ ደግሞ ዘጠነኛ ታደርጋታለች። እስካሁን ጋና፣ ኬንያና አንጎላ አንድ አንድ ሳተላይት ሲያመጥቁ፤ ደቡብ አፍሪካ፣ ናይጄሪያ፣ ሞሮኮ፣ አልጄሪያና ግብፅ ሶስትና ከዚያ በላይ ሳተላይቶችን አምጥቀዋል።

Via Petros Ashenafi
@tsegabwolde @tikvahethiopia