ደንቢ ዶሎ...
የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ከቄለም ወለጋ ዞን ከተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች እና ከደንቢ ዶሎ ነዋሪዎች ጋር #እየተወያዩ ይገኛሉ፡፡
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ከቄለም ወለጋ ዞን ከተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች እና ከደንቢ ዶሎ ነዋሪዎች ጋር #እየተወያዩ ይገኛሉ፡፡
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ እንገናኝ!
(TIKVAH-ETHIOPIA)
ነገ #StopHateSpeech እንቅስቃሴ በሀዋሳ ዩንቨርስቲ ይካሄዳል። ውድ የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ማህበረሰብ አካላት ነገ ቻናላችን #በአፍሪካ_ህብረት_አዳራሽ ባዘጋጀነው ልዩ ዝግጅት ላይ እንድትገኙ ጋብዘናችኃል። የሀገራችን ጉዳይ የሚያሳስባችሁ፤ የማህበራዊ ሚዲያ አጠቀቃማችን መታረም አለበት የምትሉ፤ ፍቅር በሀገራችን እንዲስፋፋ እንፈልጋለን የምትሉ፤ ጥላቻ ክፉ ነው የምትሉ፤ ሰላም ከሁሉም ነገር ይቀድማል የምትሉ፤ ለሌሎች የሀገሪቱ ወጣቶች አርአያ እንሆናለን የምትሉ ሁሉ በአዳራሹ እንገናኝ!! የክብር እንግዶች ከዩኒቨርሲቲው አመራሮች ይገኛሉ።
ነገ ቅዳሜ ምሽት 12:00 ሌላ ቀጠሮ እንዳትይዙ! ከሀገራቹ፤ ከፍቅር የሚበልጥ አንዳች ነገር የለም።
ፍቅርን እንዝራ!!
ኢትዮጵያን በፍቅር እንገንባ!!

የጥለቻ ንግግር ወጊውን መልሶ #ይጎዳል!
(በሚራክል እውነቱ)
የጥላቻ ንግግር የተወሰኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን በፖለቲካዊ አመለካከት፣ በሚከተሉት እምነት፣ በዘር፣ በትምህርት ደረጃ፣ በሃብት ደረጃ በቀለማቸው በእነዚህና በሌሎችም ምክንያቶች ከእኛ ሃሳብ ተቃራኒ ናቸው ብለን የምንፈርጃቸውን ሰዎች ስብእናቸውን በመጋፋት፣ ማንነታቸውን ጭምር በሚያሳንስና በሚያዋርድ መልኩ የሚሰነዝር ቃል ነው፡፡ አለፍ ሲልም ሰዎችን በማይሆን ፍረጃ ይገደል ይታሰር ይሰደድ የሚል ፍርድ በማሳለፍ ጭምር ሚዛናዊነትን የሚያስት ነው የጥላቻ ንግግር፡፡ እከሌ እንዲህ ካልሆነ፤ እክሌ ይሄ ፍርድ ይገባዋል፣ እክሌ ንፁህ ነው፤ ይሄኛው ደግሞ በደሉ ክልክ በላይ ሆኗል፤ ይሄ ወገን ይሄ ፍርድ ይገባዋልና መሰል የጥላቻ መርዞችን በመርጨት የሰዎችን አብሮ የመኖር እሴት እንዲሸረሸር የማድረግ አባዜ ነው፡፡
በግለሰቦች ላይ የሚሰነዘር የጥላቻ ንግግር የሰዎችን ስብዕና በመጋፋት ማህበራዊ ቀውስ ውስጥ እንዲገቡ ሊያደርግ እንደሚችል መገመት አያዳግትም፡፡ ጠንካራ ስነልቦና ያለው ሰው እንኳን በተለይ በማህበራዊ ሚዲያ በሚሰራጩ ክብረ ነክ በሆኑ የጥላቻ ንግግሮች ከፍተኛ ቀውስ ውስጥ ሲገቡ ይስተዋላል፡፡ የዚህን ትርፍና ኪሳራ መመዘን እንግዲህ የባለቤቱ ነው፡፡
ማንም ሰው ወደዚህ ምድር የመጣው በምክነያት ነው፡፡ እኔ የተፈጠርኩት በምክንያት ነው ብሎ ማመን ግድ ይላል፡፡ ያኔ እያንዳንዳችን በምንዘራው ልክ የምናጭድ መሆናችን ይገባናል፡፡ በጎ በጎውን ተናግሮ ተፅእኖ መፍጠርና የተሳሳተ አስተሳሰብ ማራመድና የጥላቻ ንግግር የሚያመጣውን መመዘን ይገባል፡፡
በመሆኑም በግለሰቦች ወይም በህዝቦች መካከል አለመግባባት፣ ብሎም #ግጭትን ሊቀሰቅሱ የሚችሉ የጥላቻና #አደገኛ ንግግሮች መባባስ የማህበራዊ ሚዲያዎች አሉታዊ አስተዋጽኦ በእጅጉ የጎላ መሆኑ እርግጥ ነው በመሆኑም የሚጠቅመውን መምረጥ ግድ ይላል ማለት ነው፡፡
ማህበራዊ ሚዲያዎች ማህበረሰቡን ለሚጎዱ መጥፎ ተግባራት ማራመጃነት እንዳይውሉ ይልቁንም ለአገር #ሰላምና የጋራ #መግባባት በጎ አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ለማድረግ ሁሉም ከራሱ ጀምሮ ከጥላቻ ንግግር ራሱን መቆጠብ ይገባዋል፡፡ መጨረሻው ለራስ የሚኖር ግምት ያነሰ እንዲሆን በማድረግ ራስን ጭምር ለማህበራዊ ቀውስ የሚከት ነውና፡፡

ያስተዛዝባል...ቅን ልብ ቢኖረንስ??
(ውስጣችን ንፁህ ስላልሆነ ይሆን የምንፈራው?)
ይህን ፅሁፍ ያገኘሁት ከአንድ ከ200,000 በላይ ተከታዮች ካሉት የፌስቡክ ገፅ ነው። መልዕክቱ ብዙዎች ጋር ደርሶ ሰዎችን #መቀየር ይችላል ግን አይተን እንዳላየን ያለፍነው ብዙዎች ነን!! ሼር ያደረጉት እንኳን 13 ሰዎች ናቸው። ይሄኔ ግጭት፣ ረብሻ፣ የጦርነት ቅስቀሳ፣ የሀሰት ዜና...ቢሆን #በሺዎች የምንቆጠር ሰዎች ነበርን #ላይክ እና #ሼር የምናደርገው። ያሳዝናል! እውነት ሰላም እና ፍቅርን የምንፈልግ፤ እውነት #ፍትህ እና #እኩልነት የምንፈልግ ሰዎች ከሆንን ውስጣችን #ቅን ሊሆን ይገባዋል፤ ለሀገር እና ለህዝብ የሚጠቅሙ ነገሮችንም ማጋራት አለብን።

#update በጋምቤላ ክልል 52 ክላሽንኮቭ ጠመንጃዎች እና 10 ኪሎ ግራም ሐሺሽ በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። በተጨማሪም ከአንድ ሺህ በላይ የብሬን መትረየስና ክላሽንኮቭ ጥይቶች ከሁለት ተጠርጣሪዎች ጋር ተይዘዋል። የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ቱት ኮር እንደገለጹት የጦር መሳሪያዎቹና ሐሺሹ በቁጥጥር ሥር የዋለው ከሕዝብ በደረሰ ጥቆማና በኬላዎች በተደረገ ፍተሻ ነው። የጦር መሣሪዎቹና ሐሺሹን ከሁለት ተጠርጣሪዎች ጋር በቁጥጥር ሥር የዋሉት ከሚያዚያ 6 እስከ 9፣ 2011 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ መሆኑን ተናግረዋል። የጦር መሣሪዎቹ የተያዙት በባጃጅ ተሽከርካሪዎችና አዘዋዋሪዎች በመንቀሳቀስ ላይ እያሉ መሆኑም ተገልጿል፡፡ ሐሺሹ ከአዲስ አበባ በሕዝብ ማመላለሻ በመኪና ጎማ ውስጥ ተጭኖ ወደ ጋምቤላ ከተማ በመግባት ላይ እንደነበረም ነው ምክትል ኮሚሽነሩ የሚናገሩት። በቁጥጥር ስር የዋሉት ሁለት ተጠርጣሪዎች ጉዳያቸው በመጣራት ላይ እንደሚገኝ አስረድተዋል። በሌሎች ተጠርጣሪዎች ላይ ክትትል እየተደረገባቸው መሆኑንም ምክትል ኮሚሽነሩ ተናግረዋል። ኮሚሽኑ ክልሉ ከደቡብ ሱዳን ጋር ሰፊ የድንበር ወሰን ያለው ከመሆኑ ጋር ተያይዞ እየተስፋፋ ያለውን ሕገ- ወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውር ለመግታት ከሕዝብና ከፌደራል የጸጥታ አካላት ጋር በቅንጅት በመሥራት ላይ መሆኑን ገልጸዋል።
ምንጭ፡- ኢ ዜ አ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ፡- ኢ ዜ አ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ🔝
በግዥ ኤጀንሲ እና ንብረት አስተዳደር አማካኝነት በሃዋሳ ዩኒቨርስቲ ለአራተኛ ጊዜ የደቡብ ክላስተር ከተለያዩ ዩኒቨርስቲ ለተወጣጡ ከፍተኛ አመራሮች : የግዥ ባለሞያዎች እና የግዥ ጨረታ አፅዳቂ ኮምቴ አባላት ከሚያዚያ 10-12 ቀን 2011 ዓ.ም ድረስ እየመከረ ይገኛል። ከዚህም መነሻ በቀጣይ የግዥ ሂደት ላይ ከፍተኛ ለውጥ ይመጣል ተብሎም ይታሰባል። በዚህን ሰዓት ወ/ሮ ማርታ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ በመስጠት ላይ ይገኛሉ።
Via BjT(TIKVAH-ETH)

ጅማ ዩኒቨርሲቲ🔝
ጥያቄ ያላቸው እና ጥያቄዎቻቸውን በተለያየ መንገድ ሲያሰሙ የነበሩ የጅማ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ተማሪዎች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት በማድረግ ላይ ይገኛሉ።
ፎቶ: ቃል(TIKVAH-ETH)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጥያቄ ያላቸው እና ጥያቄዎቻቸውን በተለያየ መንገድ ሲያሰሙ የነበሩ የጅማ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ተማሪዎች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት በማድረግ ላይ ይገኛሉ።
ፎቶ: ቃል(TIKVAH-ETH)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) እና ኢቢኤስ ቴሌቭዥን ከ22 ሚሊዮን ብር በላይ ተቀጡ፡፡ ጣቢያዎቹ ከ22 ሚሊዮን ብር በላይ የተቀጡት የተሳሳተ ማስታወቂያ በማስተላለፍ ሸማቹ እንዲታለል አድርጋችኋል ተብለው ነው፡፡ በግማሽ ቅድመ ክፍያ ሲኖ ትራክ መኪና ከውጪ እናስመጣለን በሚል በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ሰብስቦ ተሰውሯል የተባለው ዙና ትሬዲንግ ባለፈው ሐምሌ ወር ያላግባብ የሰበሰበውን 58 ሚሊዮን ብር ለ98 ከሳሾች እንዲመልስ መደረጉ ይታወሳል፡፡ በጉዳዩ ሁለተኛ ተከሳሽ የሆኑት ኢቢኤስና ኢቢሲ ደግሞ ሀሰተኛ ማስታወቂያ በማሰራጨታቸው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 6ኛ ፍትሐ ብሔር ችሎት ከትናንት በስትያ ከ22 ሚሊዮን ብር በላይ እንዲከፍሉ ወስኖባቸዋል፡፡ በጊዜው በቴሌቪዥን ጣቢየዎች የተሰራጨው የዙና ትሬዲንግ ማስታወቂያ ከውጭ ያስመጣቸው መኪኖች እንዳሉት የሚናገርና መኪኖች ተደርድረው በምስል የሚታዩበት ነበር፡፡ ይሁንና ድርጅቱ አንድም መኪና ከውጭ አለማስገባቱ በመረጋገጡ በሀሰተኛ ማስታወቂያ ህብረተሰቡ እንዲያምነውና ዙና ትሬዲንግ ያላግባብ 58 ሚሊዮን ብር እንዲሰበሰብ ምክንያት ሆነዋል በሚል የሚድያ ተቋማቱ ባሰራጩት ማስታወቂያ ፍርድ ቤቱ ተጠያቂ አድርጓቸዋል፡፡
ምንጭ - ሸገር ኤፍ ኤም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ - ሸገር ኤፍ ኤም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በትላንትናው ዕለት በጄነራል ዋቆ ጉቱ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በልታወቀ ምክንያት እራሳቸውን ስተው በህክምና ላይ የነበሩ ተማሪዎች ታክመው በሰላም ወደ ቤታቸው መመለሳቸውን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ገለፀ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በስልክ ባደረሱን መረጃ መሰረት በትላንትናው ዕለት ባልታወቀ ምክንያት 37 ተማሪዎች እራሳቸውን በመሳት በቤቴል ሆሲፒታል ህክምና ስደረግላቸው ቆይተው ወደ ቤታቸው በሰላም መመለሳቸውን ገልፀዋል፡፡ ምክንያቱ እሳከሁን ባይታወቅም በትምህርት ቤቱ የሚገኙ የተለያዩ ናሙናዎች ተወስደው በመጠናት ላይ ሲሁን ውጤቱም እንደታወቀ ለህዝብ ይፋ እንደሚደረግ አስታውቀዋል፡፡እስካሁን የመማር መስተማሩ ሂደት የተስተጓጎለ ሲሆን ከመጪው ማክሰኞ ጀምሮ ትምህርት እንደሚቀጥል አቶ ዘላለም ተናግረዋል፡፡
Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአዲስ አበባ-ጅቡቲ ባቡር ከ2 ቀናት በኋላ ላልተወሰነ ጊዜ እንዲቋረጥ ትራንስፖርት ሚንስቴር ማዘዙን ሸገር ዘግቧል፡፡ ከ15 ቀናት በፊት ባቡሩ ሐዲዱን ስቶ ወጥቶ አደጋ ከደረሰበት በኋላ ሐዲዱ ጥገና ተደርጎለት ቀድሞ ግዴታ የተገባባቸውን ኮንቴነሮችንና አንዳንድ ዕቃዎችን ሲያጓጉዝ ሰንብቷል፡፡ አሁን ግን ችግሩ ሁነኛ መፍትሄ እስኪያገኝ የመንገደኛና ዕቃ ማጓጓዣ አገልግሎቱን እንደሚያቋርጥ የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማሕበር ሥራ አስኪያጅ ተናግረዋል፡፡ አደጋውን ለመመርመር የተቋቋመው ኮሚቴ እስካሁን ግኝቱን ይፋ አላደረገም፡፡
Via ሸገር 102.1(በዋዜማ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via ሸገር 102.1(በዋዜማ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳና እና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ዛሬ አሶሳ ላይ ተወያዩ። በውይይታቸው ላይ በሁለቱ ክልሎች መካከል የህዝቦችን ግንኙነት ለማጠናከር በጋራ እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።
Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የሥራ ማቆም አድማ መትተዉ የነበሩት #የኮይሻ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ ሠራተኞች ወደ ሥራ ገበታቸዉ ለመመለስ #ተስማሙ። የአሠሪዉ ኩባንያ ኃላፊዎችና የሠራተኞቹ ተወካዮች በተከታታይ ሲደራደሩ ነበር። የሠራተኞቹ ተወካዮች ለDW እንደነገሩት ሠራተኞቹ ነገ #ሥራ ለመጀመር ተስማምተዋል። ሠራተኞቹ አድማዉን አቁመዉ ወደ ሥራ ለመመለስ የወሰኑት በደል አድርሰዉብናል በማለት ቅሬታ አቅርበዉባቸዉ ከነበሩ ኃላፊዎች ሁለቱን አሠሪዉ ድርጅት ከሥራ #በማገዱ ነዉ። የዶቸ ቬለ ምንጮች እንዳረጋገጡት እገዳ የተጣለባቸው ሁለቱ ኃላፊዎች ግድቡን በኮንትራት በሚገነባዉ በሳሊኒ ኩባንያ ወስጥ በከፍተኛ የሰው ሀብትና የፋይናንስ ኃላፊነት ቦታዎች ላይ ይሠሩ የነበሩ ናቸዉ።ወደ ስድስት ሺሕ የሚጠጉ የኮይሻ ግድብ ሠራተኞች የስራ ማቆም አድማ የመቱት ባለፈዉ ሳምንት ማብቂያ ነበር።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia