ለሚመለከተው ሁሉ🔝
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #ዐቢይ_አሕመድ ስለማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ያስተላለፉት መልዕክት::
Via PMOEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia

#update በኳታር ጉብኝት በማድረግ ላይ የሚገኙት ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአስፓየር ዞን ፋውንዴሽን ከዋና ሥራ አስፈጻሚው #መሐመድ_ኸሊፋ_አል_ሱዋዲ ጋር ታይተዋል። ይኸ ተቋም የቅንጡ ስፖርታዊ ውድድሮች ማካሔጃዎች ባለቤት ነው። ከስፓርት ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ ጥናትና ምርምር ይሰራል። ለተጎዱ አትሌቶች ሕክምናና የማገገሚያ አገልግሎትም ያቀርባል። ጠቅላይ ምኒስትሩ ወደ ኳታር ሲያቀኑ ከዚህ ማዕከል ጋር በተያያዘ ሥራ ይኖራቸው እንደሁ የታወቀ ነገር የለም።
Via Eshet Bekele
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via Eshet Bekele
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"አትናገር፤ ተናገር ካሉህ ግን እውነቱን ብቻ ተናገር!" ቢኒ
ጌዴዎ እንደወረት ሰሞኑን በጌዴዎ ተፈናቅለው ለምግብ እጥረት፣ አካላዊ ህመም እና ስነ ልቦናዊ ቀውስ እንዲሁም ለሞት ተዳርገው የሚገኙ ኢትዮጵያዊ ወገኖቻችንን ጉዳይ በማህበራዊ ሚዲያው እያየን ፣ ሀዘን በወለደው ስሜታዊ መነሳሳት ሁሉም በተቻለው ሁሉ ድምጹን በማሰማት አስተጋብቷል። ጉዳዩ ከመንግስት አይን እና ጆሮ እርቆ በሀገር ውስጥ የተደረገ እስከማይመስል ድረስ ትኩረትን አጥቶ ነበር። ከማህበራዊ ሚዲያው ጩኸት ብዛት ትኩረት ያገኘ እና የተፈታ መስሎ ፡ የአንድ ሰሞን ወሬ ሆኖ አልፏል።
‘‘ማን ያውራ የነበረ፡ማን ያርዳ’’ የቀበረ ነውና ፡በቦታው ተገኝተን ሁኔታውን ለመመልከት ችለናል። ያየነውን እንናገራለን፣ በምስል ያስቀረነውን እናጋራለን፣ ስላለው ችግር በድጋሚ እንጮሃለን።
"አትናገር፤ ተናገር ካሉህ ግን እውነቱን ብቻ ተናገር!" ቢኒ
ጌዴዎ ከአዲስ አበባ 365 ኪ.ሜ. ወደ ደቡብ ፣ ከሀዋሳ ደግሞ 96 ኪ.ሜ. ላይ የሚገኝ ዞን ሲሆን ፣ በውስጥ መፈናቀል ምክናያት የበርካታ ኢትዮጵያውያን ህይወት አደጋ ላይ የወደቀባቸውን ገደብ እና ጎቲት ለመጎብኘት ችለናል።
በቦታው በርካታ ህጻናት በምግብ እጥረት ምክንያት የጎድን አጥንታቸው ወጥቶ ፣ ሆዳቸው ተነፍቶ እና እግራቸው አብጦ ላየ ፣አንጀትን የሚበላ አሳዛኝ ክስተት ይረዳዋል። ከዚህ በተጨማሪ ሌሎች ተያያዥ የህክምና ችግሮች ተመልክተናል።
እነርሱም የቆዳ እከክ በሽታ፣ የአይን ማዝ በሽታ እንዲሁም ተቅማጥ ዋናዎቹ ናቸው።
ለመርዳት በምናረገው ጥረት የመድሐኒት እጥረትም ነበር።
ለምሳሌ ORS, BBL, Permethrin, Zink, omeprazole, Augmentin, እና Azithromycine እጥረት ነበር።
ውሃ ለእኛ እንካን ምግብ አልበላንም ነበር ለምን ... ከበደን ሰው አይደለን...
ከአዲስ አበባ፣ሀዋሳና ዲላ ከተማ ከመጡ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች እና ጤና ባለሙያዎች ጋር በመሆን የምንችለውን ያህል ለመርዳት ሞክረናል።
ሰውን መርዳትን የመሰለ ነገር የለም እና ድካምን እና ምቾት ማጣትን ሳንቆጥር እርዳታ ለማድረግ ሞክረናል።
ለማሳሰብ የምንፈልገው ነገር ግን ፣ ይህ ችግር ቀላል እንዳልሆነና በቂ ትኩረት እንደሚሻ ነው።
ጥቆማ
ብዙ ሚልየኖች በስማቸው ቢሰበሰብም፣ በጊዜ ደርሶ ህይወታቸውን ካልታደገው ዋጋ አይኖረውም
የመድሐኒትና የጤና ባለሙያ እጥረቱ በቶሎ መፍትሔ ሊሰጠው ይገባል።
በ FB ከ100 በላይ ጤና ባለሙያዎችን
በፈቃደኝነት መመዝገብ ተችሏል።
ቦታው ላይ ደርሰው እርዳታ ለመስጠት ግን ጊዜ እየወሰደ ይገኛል። ለምን የምኪና ችግር መኪና ያላቹ ብትተባበሩን ደስ ይለናል። ውሃ በጣም በጣም ያስፈልጋል። በተለይ ለሴቶች እና ለህፃናት በተለይ ውሃ ስሌለህ ሴቶች የምትረድት ይመስለኛል። ከላይ የጠቀስኩትን መርዳት የምትፋልጎ ቢንያም 0927707000 ወይም 0915955656 ላይ ማናገር የምትችሎ መሆኑን አሳውቃለው
ውሃ የምትሸጡ አንድ በሉን ለሴቶች ስትሉ!
አዘጋጅ፦
TIKVAH-ETHIOPIA ከሰው ሁን ከሰውም ሰው ሁን ጋር በመተባበር የቀርበ
@Tsegabwolde @tikvahethiopia

#update የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከኳታር ጠቅላይ ሚኒስትር አብዱላሂ ቢን ናስር ቢን ካሊፋ አል ታሃኒ ጋር ተወያይተዋል፡፡
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
'መጥፎ ዕድል' አውሮፕላኑ የወደቀበት ስፍራ ስያሜ እንደሆነ ያውቃሉ?
.
.
በመጥፎ አጋጣሚ መጋቢት 1 ቀን 2011 ዓ.ም ዕለተ እሁድ በኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን የበረራ ቁጥር ኢቲ 302 የተሳፈሩ 157 ተጓዦች አውሮፕላኑ ጊምቢቹ ወረዳ ቱሉ ፈራ ተብሎ በሚታወቅ አካባቢ ተከስክሶ አንዳቸውም አለመትረፋቸው ዓለምን አስደንግጧል።
አደጋው የደረሰበት አካባቢ ነዋሪዎች ለማያውቋቸው የአደጋው ሰለባዎች ልባቸው በሀዘን ተሰብሮ ከመጣው ጋር ሲያለቅሱና ሃዘናቸውን ሲገልጹ የሰውነት ሩህሩህነታቸውን ለዓለም አሳይተው ርዕስ ሆነው ሰንብተዋል።
ከሁሉ ከሁሉ ይህን የአውሮፕላን አደጋ መጥፎ ዕጣ የደረሰበት ቦታ ስያሜ የነገሮችን ግጥምጥሞሽ አነጋጋሪ ያደርገዋል። 'ቱሉ ፈራ' የሚለው የኦሮሚኛ ስያሜ 'መጥፎ ዕድል' እንደማለት እንደሆነ የይነገራል።
በእርግጥም የዚህ ተራራ ስያሜ ከመጥፎው አጋጣሚ ጋር የሚመሳሰል መሆን አለመሆኑንና እንዴትስ ስያሜውን እንዳገኘ ለማወቅ ቢቢሲ የአካባቢውን አዛውንቶች አነጋግሯል።
አቶ ባትሪ ለማ በአካባቢው ከሚኖሩ አዛውንት አንዱ ናቸው። "ቱሉ ፈራ ይህን ስም ያገኘው በአካባቢው ባለው የአየር ሁኔታ ነው" ይላሉ።
ቦታው ከፍታማ ስለሆነ የንፋሱ አቅጣጫ ወዴት እንደሚነፍስ ለማወቅ ያስቸግራል የሚሉት አቶ ባትሪ "በስፍራው ያለው ቅዝቃዜው ኃይለኛ ከመሆኑ የተነሳ ሰዎች በተራራው ላይ መኖር ሲያቅታቸው ቱሉ ፈራ ብለው ሰየሙት። በአማርኛ የመጥፎ እድል ማለት ነው" በማለት ነው ይላሉ።
እንደ አቶ ባትሪ አገላለፅ የአካባቢው ቦታዎች በሙሉ የተሰየሙት ባለው የአየር ሁሌታ ላይ ተመስርተው ነው። ለምሳሌ አውሮፕላን የወደቀበት ቦታ ሃማ ይባላል። ይህ ማለት ክፉ ወይም መጥፎ ማለት ነው።
በአካባቢው የሚገኝ ተራራ ደግሞ ፈራ ተራራ ይባላል። አውሮፕላኑ ከወደቀበት ቦታ ቀጥሎ ያለው ደግሞ ነኑ እኩቢ ሲባል የበሽታ አካባቢ ማለት እንደሆነ አቶ ባትሪ ያስረዳሉ።
በኦሮሚኛ ቱሉ ፈራ የሚሉት ቃላት በቀጥታ ሲተረጎሙ "መጥፎ ዕድል" የሚል ትርጉምን ይይዛሉ። በእርግጥም በአካባቢው ያጋጠመው አደጋ ሰለባዎች መጥፎ እድል ገጥሟቸው ሃዘኑ ከሃገር አልፎ ለዓለም ተርፏል።
ይሁን እንጂ ከአካባቢው ስያሜ አመጣጥ ጋር የተለያዩ ትርጉም የሚሰጡ ታሪካዊ ዳራዎችን የሚየጠቅሱ የአካባቢው አዛውንቶች አልጠፉም።
ለዚህም ሌላኛው የጊምቢቹ ወረዳ አዛውንት አቶ ደቻሳ ጉተማ የሃማ ቁንጥሹሌ ቀበሌ ነዋሪ ሲሆኑ፤ የፈራ ተራራ ስያሜ ምንጩ ሌላም ታሪክ እንዳለው ይጠቅሳሉ።
እሳቸው እንደሚሉት ከሆነ ተራራዎች ስያሜያቸውን ያገኙት በጥንት ዘመን አካባቢውን ሲያስተዳድሩ ከነበሩ ነገሥታት ጋር ተያይዞ እንደሆነ ይናገራሉ።
"የፈራ ተራራ ስያሜውን ያገኘው በአፄ ዘረ ያዕቆብ ዘመን ነው። ለምሳሌ አንዱ የወቅቱ የአካባቢው አስተዳዳሪ የነበሩት መሪ ስም ቦካ ይባል ነበር። እሳቸውም ይኖሩበት የነበረውን ተራራ በስማቸው ጋራ ቦካ በማለት ሰይመውታል" ይላሉ አቶ ደቻሳ።
በተመሳሳይ የፈራ ተራራ ስያሜ ከአህመድ ግራኝ ወረራ ጋር ተያያዥነት አለው ይላሉ። "ከአባቶቻችን እንደሰማነው ግራኝ አህመድ ወታደሮቹን ይዞ አካባቢውን መውረር ሲጀምር ለቦካ መልዕክት ላከ። መልዕክቱ 'ጭካኔን እንደ እናቴ መከታዬን ደግሞ እንደ አባቴ ሆኜ እየመጣሁልህ ነውና ተዘጋጅተህ ጠብቀኝ' የሚል ነበር" ይላሉ።
አቶ ደቻሳ እንደሚሉት ቦካ የአህመድ ግራኝን መልዕክት እንደተቀበሉ ለሌላኛው የአካባቢው አስተዳዳሪ ለአቶ ቱሉ እየመጣብን ያለውን ጦርነት አብረን እንመክት ብሎ ጥያቄ አቀረቡ።
መልዕክት አድራሹም ከአቶ ቱሉ ጋር ሲመለስ እንዴት እንደተሰማቸው ቦካ ሲጠይቁት ጦርነቱ እንዳስፈራቸውና እንዳሳሰባቸው ተገንዝቤአለሁ አላቸው ይላሉ አቶ ደቻሳ።
ቦካም ይህንን ሲሰሙ 'አዪ! ቱሉ ፈራ ማለት ነው' በማለት የተራራው ስም ከዚያ በኋላ ቱሉ ፈራ ተብሎ እንደቀረ እንደተነገራቸው ያስረዳሉ።
ሁለቱም አዛውንቶች ለስፍራው ለተሰጠው ለተሰጠው ስያሜ የተለያየ ምክንያት ቢሰጡም የሚስማሙበት አንድ ሃሳብ ግን ቱሉ የሚባል የአካባቢው አስተዳዳሪ በተራራው ላይ ይኖሩ እንደነበር ነው።
አቶ ባትሪ ግን ሆን ተብሎ የተራራው ስያሜ ከአካባቢው የአየር ሁኔታ የመነጨ እንደሆነ አጠንክረው ይከራከራሉ። እንደሳቸው አባባል የአካባቢው አስተዳደር የነበሩት ሁሉ ጦርነት የሚፈሩ አልነበሩም።
ምንጭ፦ BBC

Fake News Alert‼️
‹‹የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአማራ ክልል ለሚገኙ ተፈናቃዮች 20 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ሰጠ ›› ተብሎ በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨው መረጃ ሀሰት መሆኑን ባንኩ አስታወቀ። በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቢዝነስ ዴቨሎፕመንት ኃላፊ አቶ ይስሃቅ መንገሻ ባንኩ በአማራ ክልል ብቻ ሳይሆን በመላ ሃገሪቱ ያሉትን መፈናቀሎች ጥናት በማድረግ ላይ መሆኑንና ከሳምንት በኋላ የደረሰበትን ጭብጥ እንደሚያሳውቅም ገልጸዋል።
ባንኩ የሕዝብ ሃብት በመሆኑ ድጋፍ ለማድረግ የቦርድ ውሳኔ ሳይሆን የማኔጅመንት ስብሰባ ብቻ በቂ መሆኑንም ነው የተናገሩት።
Via አብመድ

👆የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት #የፌስቡክ እና #የቴሌግራም ምስል በማድረግ...ሁላችም ሀገራችንን አደጋ ላይ የጣለውን የጥላቻ ንግግርን እናውግዝ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia