TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.5K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
7ኛው ዙር የአሼ ታለንት አንቲ ድራግ የጎዳና ላይ ትርኢት፤ ሩጫ እና የቁንጅና ውድድር!

More 0926449748 , 0911033992
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#update በኢትዮጵያ ያለው የፌደራሊዝም ስርዓት በዋናነት ብሄር እና ቋንቋ ላይ መመስረቱ አሁን ላይ ለተፈጠሩት ችግሮች ምክንያት መሆኑ ተገለፀ፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የትግራይ ዲያስፖራ ፌስቲቫል!

2ኛው ዓለምቀፍ የትግራይ ዲያስፓራ ፌስተቫል ለመካሄድ የሚያስችል ዝግጅት
#መጠናቀቁን የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት አስታውቋል፡፡

ፌስቲቫሉ በተለያዩ የዓለም ሃገራት የሚገኙ የትግራይ ዲያስፓራ ማህበረሰብ በክልሉ ብሎም በሃገራቱ እየተከናወኑ ባሉት የሰላም የዴሞክራሲና የልማት ስራዎች ተሳታፊ ለማድረግ ያለው ነው ተብሏል፡፡

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ የከተማ ልማትና ንግድ ኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር #አብርሃም_ተከስተ ዝግጅቱን አስመልክቶ በሠጡት መግለጫ ፌስቲቫሉ የትግራይ ዲያስፓራ ስለሃገራቸውና ስለ ክልላቸው ተጨባጭ ሁኔታ ተገንዝበው ለትግራይ ህዝብ ሰላምና ደህንነት በተደራጀ መልኩ የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ለማድረግ ነው፡፡

ፌስቲቫሉ ዲያስፓራውን በክልሉ በሚካሄደው የንግድ የኢንቨስትመንትና የኢንዱስትሪ ልማት እንቅስቃሴዎች ተሳታፊ ለማድረግ ነው ያሉት ዶክተር አብርሃም የፐብሊክ ዲኘሎማሲውን በማጠናከር በኢትዮ ኤርትራ የተጀመረውን የሰላም ግንኙነት ተጠናክሮ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ነው፡፡

ዋናው ፌስቲባል ከሃምሌ 24 -ሃምሌ 3ዐ/ 2ዐ11 ዓ.ም ድረስ የሚካሄድ ሲሆን የህዝባዊ ወያነ ሐርነት ትግራይ /ህወሓት/ የተመሰረተበትን ቀን ምክንያት በማድረግ ከየካቲት 11/2ዐ11 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ ስነ-ስርዓቶች እንደሚካሄደ ተገልጿል፡፡

ምንጭ፦ ebc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሩሲያ ኢንተርኔትን ለማቋረጥ እያሰበች ነው‼️

ሩሲያ እራሷን #በኢንተርኔት አማካይነት ከሚፈጸም ጥቃት ለመከላከል በምታደርገው ዝግጅት ለአጭር ጊዜ እራሷን ከዓለም አቀፉ የኢንትርኔት ትስስር #የማቋረጥ አማራጭን እያጤነች ነው።

ይህም ማለት የኢንትርኔት ግነኙነት በሃገር ውስጥ ብቻ የተገደበ ይሆናል። በዚህም ሩሲያዊያን የሚልኩት እና የሚቀበሉት መረጃ እርስ በርሳው እንጂ ከተቀረው ዓለም ጋር አይሆንም።

ለሙከራው የተቆረጠ ቀን ባይኖርም በቀጣዮቹ ሁለት ሳምንታት ውስጥ እንደሚከናወን ይጠበቃል።

የተቀሩት የዓለም ሃገራት ሩሲያን ከዓለም አቀፉ የኢንተርኔት አገልግሎት ቢያገሏት በእራሷ መቋቋም የሚያስችላት ረቂቅ አሰራር እየተገበረች ነው።

የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃልኪዳን ድርጅት (ኔቶ) ከዚህ ቀደም ሩሲያ #የሳይበር_ጥቃቶችን ታደርሳለች በማለት ማዕቀብ እንደሚጣልባት ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል።

ሩሲያ እንዴት ከተቀረው ዓለም የኢንተርኔት ትስስር እራሷን በማግለል በሃገሪቱ ውስጥ ብቻ የኢንተርኔት አገልግሎትን ማኖር ትችላለች? የሚለው የበርካቶች ጥያቄ ነው።

የዘርፉ በለሙያዎች ሲያስረዱ፤ "ኢንተርኔት የሚሰራበትን መንገድ መረዳት ይገባናል" ይላሉ። "በሺህዎች የሚቆጠሩ መረጃዎች የሚተላለፉባቸው ዲጂታል ኔትዎርኮች አሉ። እንዚህ ኔትወርኮች 'ራውተር' በሚባሉ መዳረሻዎች ይገናኛሉ። ሩሲያ ያቀደችው በራውተሮች በኩል ወደ ሃገር ውስጥ የሚገቡ እና የሚወጡ ዳታዎችን መቆጣጠር ነው።"

ይህን አካሄድ በመጠቀም ወደ ሃገር ውስጥ የሚገቡ መረጃዎችን በመቆጣጠር ረገድ ቻይና ውጤታማ ስለመሆኗ ይነገራል።

ሆን ተብሎም ባይሆን ሃገራት በተለያዩ አጋጣሚዎች ከተቀረው ዓለም ጋር የሚኖራቸው የኢንተርኔት አገልግሎት ከዚህ ቀደም ተቋርጧል። ባህር ውስጥ ያለ የኢንተርኔት ገመድ በመቋረጡ ከዚህ ቀደም አፍሪካዊቷ ሃገር ሞሪታኒያ ለሁለት ቀናት ከተቀረው ዓለም ተነጥላ ነበር።

ምንጭ፦ BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መርማሪ ፖሊሶቹ በቁጥጥር ስር ዋሉ‼️

በህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር የተጠረጠረ ግለሰብ እንዲያመልጥ ያደረጉ መርማሪ ፖሊሶች በቁጥጥር ሥር ዋሉ፡፡

በህገ-ወጥ አዘዋዋሪዎች ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 1 ሺህ 300 ጥይቶችና 43 ክላሽ ሸንኮቭ የጦር መሳሪያዎችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቆ ነበር፡፡

ከጋምቤላ አካባቢ ወደ ጎንደር በኤፍ ኤስ አር መኪና ሲዘዋወሩ የነበሩ 43 ክላሽ ሸንኮቭ እና 1 ሺህ 300 የክላሽ ጥይቶች ከነአሽከርካሪው መያዛቸውንም አይዘነጋም፡፡

በወንጀል ተጠርጣሪ አሽከርካሪው በፖሊስ ተይዞ ምርመራ ሲደረግበት ‹ዋናውን የጦር መሳሪያ አሰራጭ› ጠቁሞ ጎንደር ከተማ ላይ አስይዞታል፡፡ ጉዳዪን ለመከታተል ወደ ጎንደር የሄዱት ሁለት መርማሪ ፖሊሶች ዋናውን ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ አሰራጭ በቁጥጥር ሥር በማዋል ላይ እያሉም አሽከርካሪው (መጀመሪያ ላይ የተያዘው ተጠርጣሪ) አምልጧል፡፡

ተጠርጣሪ እንዲያመልጥ ማድረግ ደግሞ ወንጀል በመሆኑ ሁለቱም መርማሪ ፖሊሶች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን በአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀልና የትራፊክ አደጋ ምርመራ ዋና ክፍል ኃላፊ ኮማንደር #አትንኩት_ከበደ ተናግረዋል፡፡

ሁለት መርማሪ ፖሊሶችና ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ አከፋፋይ በሚል ተጠርጥሮ ጎንደር ላይ የተያዘው ግለሰብ አሁን ላይ በባሕር ዳር ስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ሆነው ምርመራ እየተካሄደባቸው መሆኑንም ኮማንደር አትንኩት ተናግረዋል፡፡

ምንጭ፦ ebc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ🔝

‹‹ለፖለቲካዊ ለውጡ ቀጣይነት›› በሚል ርዕስ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት ለሁለት ቀናት የሚቆይ የምክክር መድረክ በመካሄድ ላይ ነው፡፡ በመድረኩ ዶር. #አምባቸው_መኮንን፣ ፕሮፌሰር #መረራ_ጉዲና#ክርስቲያን_ታደለና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

ዶክተር አምባቸው በአንኳር ንግግራቸው ምሁራን ወቅቱ ባመጣው ለውጥ በፖለቲካው ተሳትፎ እንዲያደርጉ የሚያበረታታቸው በመሆኑ እንደዚህ አይነት የሃሳብ ፍጭቶች የሚካሄዱባቸው መድረኮችን ማዘጋጀት ይገባል ብለዋል፡፡

መድረኩ ለሁለት ቀናት የሚቀጥል ይቆያል፡፡ አቶ ክርስቲያን ታደለ እና ፕሮፌሰር መረራ ጉዲናን ጨምሮ በሌሎች ምሁራን አማካኝነት ጽሁፎች ቀርበው ውይይት ይደረጋል፡፡

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዳማ🔝

ለ7ኛ ጊዜ የሚከበረውን የመከላከያ ሰራዊትን ቀንን አስመልክቶ ህዝባዊ ውይይት በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ነው። በዚህ ውይይት የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር #አይሻ_መሀመድ ፣ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ #ለማ_መገርሳ ፣ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል #ሰዓረ_መኮንንን ጨምሮ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች፣ ሚኒስትሮችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

via fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ፦ አዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል🔝 በሀዋሳ ከተማ በ220 ሚሊዮን ብር እየተከናወነ የሚገኘው የአዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል #የማስፋፊያ_ግንባታ ከላይ #በፎቶው የምትመለከቱትን ይመስላል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#VisitEthiopia #VisitGambella

#Gambella’s waterways lay #claim to the #highest_diversity of fish in Ethiopia, and experts have described the bird life as “astounding.” Gambella is truly a hidden treasure. #LandofOrigins #Ethiopia

©MysticalEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ውድ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት...

የት ነው የምትኖሩት?? አካባቢያችሁ፤ ከተማችሁ ውስጥ ምን አይነት ተፈጥሯዊ ወይም ሰው ሰራሽ መስዕብ አለ?? እናተ ያያችሁት የኢትዮጵያ ድንቅ ቦታዎች ሌሎች እንዲያዩት የምትጠቁሙት ይኖር ይሆን??

•4 ምርጥ ፎቶዎችን ከአካባቢው ስም ጋር በመላክ የምትኖሩበትን አስተዋውቁን። የሀገር ውስጥ እና የውጭ ቱሪስቶችን ወደ አካባቢያችሁ ጋብዙ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia