አልማ🔝
የአማራ አቀፍ ልማት ማኅበር (አልማ) የዲያስፖራ እና ሌሎች ክልሎች ጽህፈት ቤት ከክልሉ ውጭ ከሚኖሩ ተወላጆች የሰበሰበውን 2 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር የሚገመት ሀብት ለሶስት ዞኖች #አከፋፈለ፡፡ አልማ አጠቃላይ ግምታቸው 2 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ 296 ኮምፒዩተሮች እና 17 ፕሪንተሮችን፣ 13 ዊልቸሮች እና 10 የህሙማን ማስተኛ አልጋዎችን ለምዕራብ ጎጃም፣ ምሥራቅ ጎጃም እና ደቡብ ጎንደር ዞኖች አከፋፍሏል፡፡ 10 የልብስ መስፊያ መኪኖችንም ሰጥቷል፡፡ የርክክብ ሥነ-ስርዓቱ ያሳለፍነው ሐሙስ በደብረ ማርቆስ እና ትላንት ዓርብ በባሕር ዳር ከተሞች ተፈጽሟል።
ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia

#uppdate ከሐረር ወደ ጅግጅጋ የሚወስደው መንገድ ሙሉ በሙሉ #መዘጋቱን የምሥራቅ ሐረርጌ ፖሊስ አረጋገጠ። ጀርመን ራድዮ ያነጋገገራቸው የዞኑ ፖሊስ መመሪያ ሃላፊ መንገዱ፣ መንግሥት መፍትሄ #አልሰጠንም በሚሉ ተፈናቃዮች መዘጋቱን ተናግረዋል። መንገዱን ለማስከፈትም ከህብረተሰቡ ጋር የመነጋገር እቅድ እንዳለም ገልጸዋል። ከትናንት በስቲያ ምሽት አንስቶ መንገዱ በመዘጋቱ ምክንያት አሸከርካሪዎች እና መንገደኞች እየተጉላሉ መሆናቸውን የጀርመን ራድዮ ያነጋገራቸው አሽከርካሪዎች አስታውቀዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠ/ሚር #ዐቢይ_አሕመድ በአሁኑ ጊዜ ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር #እየተወያዩ ይጋኛሉ። ይህ ታሪካዊና በኢትዮጲያ የፖለቲካ ታሪክና ትርክት አይነተኛ የውይይት መድረክ ከጥቂት ወራት በፊት በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋባዥነት ከተደረገው የቀጠለ ነው። ከዛሬው ውይይት አስተባባሪ አንዱ የሺዋስ አሰፋ እንዳሉት የመድረኩ ዋና አላማ በዚህ የፖለቲካው ሽግግር ወቅት የፖለቲካ አመለካከትን በሰላማዊ ሁኔታ መለዋወጥ ልምድን ለማሰደግ ነው። ከ4 የፖለቲካ ድርጅት አመራሮችም የውይይት ጽሁፍ ይቀርባል።
ምንጭ፦ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ፦ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሚድሮክ‼️
ትውልደ ኢትዮጵያዊው ሼክ መሀመድ አላሙዲን ከእስር ከተለቀቁ በሁዋላ ኢትዮጵያ ውስጥ ካላቸው ኢንቨስትመንት #እንዳልሆነ_ሆኖ የሚያገኙት የሜድሮክ ወርቅ ማዕድን ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበርን ነው።
ተጨማሪ...👇
https://telegra.ph/በሚድሮክ-ወርቅ-ላይ-የቀረበው-ውንጀላ-ሌላ-ገፅታ-02-02

Telegraph
በሚድሮክ ወርቅ ላይ የቀረበው ውንጀላ ሌላ ገፅታ
ትውልደ ኢትዮጵያዊውና ሼክ መሀመድ አላሙዲን ከእስር ከተለቀቁ በሁዋላ ኢትዮጵያ ውስጥ ካላቸው ኢንቨስትመንት እንዳልሆነ ሆኖ የሚያገኙት የሜድሮክ ወርቅ ማዕድን ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበርን ነው። ኢትዮጵያ በዚህ በጀት አመት ስድስት ወራት የተለያዩ ማእድናትን ለውጭ ገበያ አቅርባ ያገኘችው የእቅዷን አምስት በመቶ መሆኑን ይህም ፣ ከ30 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ብዙም ያልበለጠ ፣ በብዙ መለኪያም አጅግ…
ASTU🔝
በአሁን ሰዓት የአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ከተማሪ ቤተሰቦች ጋር ወቅታዊውን የዩኒቨርሲቲ ሁኔታ አስመልክቶ ውይይት በማድረግ ላይ ይገኛል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በአሁን ሰዓት የአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ከተማሪ ቤተሰቦች ጋር ወቅታዊውን የዩኒቨርሲቲ ሁኔታ አስመልክቶ ውይይት በማድረግ ላይ ይገኛል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ህፃን ሚሊዮን🔝
ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ #ዝናሽ_ታያቸው እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ህጻን ሚሊዮንን #በጉዲፈቻ ለማሳደግ ያቀረቡት ጥያቄ በፍርድ ቤቱ ተቀባይነት አገኘ።
ቀዳማዊ ቤተሰቡ ህጻን #ሚሊዮንን ከክበበ ህጻናት ማሳደጊያ ተቀብሎ #ለማሳደግ ጥር 14 ቀን 2011 ዓ.ም ለፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት 7ኛ የወንጀል ችሎት የህጻናትና ሴቶች ጉዳይ በፅሁፍ ማመልከቻ አቅርቦ ነበር። በማመልከቻቸው አመልካቾች የተፈራረሙበት የጉዲፈቻ ውል #እንዲጸድቅላቸው ጠይቀዋል።
ቀዳማዊ ቤተሰቡ ለህጻኑ #መልካም አስተዳደግ እንደሚሰጥና ህጻኑን ለማሳደግ በቂ ኢኮኖሚያዊ አቅም እንዳለው ጠቅሷል። ፍርድ ቤቱም ህጻን ሚሊዮን ከሁለት አመት እድሜ በታች በመሆኑ ችሎት ፊት ቀርቦ አስተያየት መስጠት ስለማይችል ችሎቱ የተለያዩ ማስረጃዎችን መርምሮ፥ አመልካቾች ህጻኑን በጉዲፈቻ ቢያሳድጉት ችግር የለውም ወይም መልካም ነው ብሎ በመወሰን ጥር 14 ቀን 2011 ዓ.ም የተፈራረሙትን ውል ተሻሽሎ በወጣው የቤተሰብ ህግ 213/92 አንቀጽ 93 ንዑስ አንቀጽ 1 መሰረት አጽድቆላቸዋል።
የውሳኔውን ግልባጭም ጉዳዩን ችሎት ፊት ቀርበው ለተከታተሉት ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው እንዲደርሳቸው ተደርጓል። የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ወይዘሮ መዓዛ አሸናፊ ለቀዳማዊ ቤተሰቡ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። አያይዘውም በጉዲፈቻ ልጅ ለማሳደግ መወሰናቸው ለሌሎች አርዓያ እንደሚሆንና ልጅ ማሳደግ ትልቅ ሃላፊነት መሆኑን እንዲሁም ህጻናትን በጉዲፈቻ ለማሳደግ ሁሉም እንዲያስብ ያደርጋል ብለዋል።
በእድሜያቸው ሶስት መንግስታት ማየታቸውን ያነሱት ፕሬዚዳንቷ ከፍተኛ የሃገር መሪዎችና ሃላፊዎች ፍርድ ቤት ቀርበው ጉዳያቸውን ሲያስፈጽሙ አይተው እንደማያውቁም ተናግረዋል። ቀዳማዊት እመቤቷ #ችሎት ፊት ቀርበው ጉዳያቸውን ማስፈጸማቸው ሁሉም ሰው በህግ ፊት እኩል መሆኑን ያመላክታልም ነው ያሉት።
ምንጭ፦ fbc

#update በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ግዜ "ኢትዮጵያ አትተኛም" በሚል መሪ ቃል የዘጠኝ ኪሎ ሜትር #የምሽት ጎዳና ላይ የሩጫ ዉድድር የካቲት 30 ከምሽት አንድ ሰዓት ጀምሮ በመስቀል አደባባይ ሊካሄድ ነው።
ከአዘጋጆቹ እንደሰማነው አላማዉ፦
1. የስራ ሰዓት ባህላችንን ማሳደግ
2. ወጣቶች ከቤተሰቦቻቸው፣ ከጓደኞቻቸው እና ከሚወዷቸው ጋር በመሆን ምሽታቸውን በመልካም እና በሚያንፅ ቆይታ አንዲያሳልፉ
3. ከዝግጅቱ ከሚገኝ ገቢም አካል ጉዳተኛና አረጋውያንን ለመርዳት ታቅዷል።
አዘጋጅ፦ ሚድ ናይት ራን ኢትዮጵያ እና የኢፌዲሪ ሠራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒሰቴር ከሌሎች አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር።
አዘጋጆቹን በእነዚህ አድራሻዎች ማግኘት ይቻላል፦ www.midnightrunethiopia.com
ስልክ ቁጥር +251116674717/ +251933252222 facebook page https://www.facebook.com/Night-Run-Ethiopia-6125770525262/