TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
ስካይ ላይት ሆቴል ነገ ይመረቃል!!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ60 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ወጪ ያስገነባው #የስካይ_ላይት_ሆቴል በነገው ዕለት ተመርቆ ወደ ሥራ እንደሚገባ ተገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ እኤአ በ2025 በዓለምአቀፍ ደረጃ እጅግ ተወዳዳሪ አየር መንገድ ለማድረግ የሚያደርገውን ጥረት ለማሳካት መሰል የሆቴል ግንባታዎች ሚናቸው ከፍተኛ መሆኑን በአየር መንገዱ የመሠረተ ልማት ክፍል ኃላፊ አቶ አብርሃም ተስፋዬ ለዋልታ ተናግረዋል፡፡

ስካይ ላይት ሆቴል ለሶስት አመታት ያህል የግንባታው ሥራ ሲከናወን የቆየ ሲሆን ሙሉ ለሙሉ አገልግሎት መሥጠት ሲጀምር የባለ 5 ኮከብ ደረጃን ያገኛል ተብሎ ይጠበቃል። ሆቴሉ በመላው ዓለም የሚገኙ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ትራንዚተሮችን ከማስተናገድ ረገድ ትልቁን ድርሻ እንደሚወጣ ተገልጿል፡፡

ሆቴሉ በአጠቃላይ 373 የማረፊያ ክፍሎች፣ አራት ደረጃቸውን የጠበቁ ሪስቶራንቶች፣ የመዋኛ ገንዳ፣ የአዳራሽ አገልግሎትና ሌሎችም ዘርፈ-ብዙ የሆቴል አገልግሎቶችን በሟሟላት ሀገሪቱ በትኩረት እየሠራች የሚትገኘውን የቱሪዝም ኢንዱስትሪን ይበልጥ እንደሚያግዝም ታምኖበታል፡፡ በነገው ዕለት ተመርቆ ወደ ሥራ የሚገባው ስካይ ላይት ሆቴል የቱሪዝም ኮንፌረንሱን በማገዝም የጎላ አስተዋፅዖ አለው ተብሏል፡፡

ምንጭ፦ ዋልታ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከአዲስ አበባ...

"ጠ/ሚ ዶክተር #አብይ_አህመድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያስገነባውን ሆቴል #ይመርቃሉ፤ እንዲሁም የኢንተርናሽናል ኤርፖርት ተርሚናል ማስፋፊያ ግንባታን ተዘዋውረው ይጎበኛሉ።"

©S(TIKVAH-ETH)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሶሪያ ስደተኞች~ሃዋሳ‼️

በአሁኑ ወቅት #በሀዋሳ_ከተማ በልመና ስራ ተሰማርተው የሚገኙ ጥቂት የሶሪያ ዜጎች መኖራቸውን የኢሚግሬሽን የዜግነትና ወሳኝ ኩነቶች ኤጀንሲ አስታውቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ድሬዳዋ አንፃራዊ ሰላም ሰፍኗል‼️

ሰሞኑን #በድሬደዋ_ከተማ የነበረውን ያለመረጋጋት ተከትሎ የመከላከያ ሰራዊት ከፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት በወሰደው የማረጋጋት ስራ በከተማዋ አንፃራዊ #ሰላም መታየቱን የምስራቅ እዝ አስታወቀ፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲስ አበባ‼️

የጎዳና ተዳዳሪዎችን በዘላቂነት ለማቋቋም የሚያስችል የማህበራዊ ትረስት ፈንድ የኢፌዲሪ ፕረዝደንት ወ/ሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ ኢ/ር ታከለ ኡማ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የካቢኔ አባላት፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አሪቲስቶች እና አትሌቶች በተገኙበት በዛሬው ዕለት ይፋ ሆኗል፡፡

በመድረኩ ላይ ኢ/ር ታከለ ኡማ የጎዳና ላይ ነዋሪዎችን እንደ ማንኛውም የከተማው ነዋሪ የመጠበቅ፣ የመንከባከብ እና የመደገፍ ግዴታ አለብን ብለው የከተማ አስተዳደሩ ለዚህ ተግባር የሚውል የ 100 ሚሊዮን ብር የመነሻ በጀት መመደቡንም አሳውቀዋል፡፡

ቀጥለውም ለዚህም በጎ ተግባር የከተማው ነዋሪ፣ ትምህርት ቤቶች፣ የሃይማኖት ተቋማት፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ ባለሃብቶች እና የመንግስት ተቋማት ከከተማ አስተዳደሩ ጎን እንዲቆሙ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

ምንጭ፦Mayor Office of Addis Ababa
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የማህበራዊ ትረስት ፈንዱን ለመደገፍ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የሚሳተፍበት አጭር የፅሁፍ መልዕክት መላኪያ ቁጥርም ይፋ ሆኗል፡፡ ስለዚህ ህብረተሰቡ በ6400 ላይ A ብሎ በመላክ የጎዳና ላይ ተዳዳሪ ወገኖቻችንን ህይወት በመቀየር ማህበራዊ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ ቀርቧል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቴዲ አፍሮ!!

ዝነኛው ድምፃዊ፣ የዜማና ግጥም ደራሲ ቴዎድሮስ ካሳሁን ገርማሞ (#ቴዲ_አፍሮ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጎዳና ተዳዳሪ ህፃናትን ለማቋቋም እያደረገ ያለውን ጥረት ለማገዝ በቅርቡ #ነፃ የሙዚቃ ኮንሰርት ያዘጋጃል።

ምንጭ፦ ጴጥሮስ አሸናፊ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ስካውት" 100 ዓመት!!

#ስካውት ማለት ትምህርታዊ የሆነ የወጣቶች እንቅስቃሴ ሲሆን በዘር በቀለም በሀይማኖት በጎሳ ልዩነት የማያደርግ ከፖለቲካ አመለካከት #ነፃ የሆነ ማንኛውም ሰው ያለ ማንም አስገዳጅነት አባል መሆን የሚችልበት ዓለም አቀፋዊ እንቅስቃሴ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ስካውት ማህበር እንቅስቃሴው ከተጀመረበት ጌዜ ጀምሮ ላለፉት 100 ዓመታት ስካውታዊ ግልጋሎቶችን ሲሰጥ የቆየ ሲሆን እንሆ ከ7ኛ የኢትዮጵያ ስካውቶች ጃምቦሬን ከመቶኛ አመቱ ጋር ሊያከብር ቀን ቀጠሮ ቆርጦ እየተጠባበቀ ይገኛል፡፡ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው ይህ በዓል ከጥር 26- የካቲት3 ድረስ ይከበራል፡፡ ጃምቦሬውን (የስካውት በዓል) ከሌሎች ጃምቦሬዎች ለየት የሚያደርገው ከየክልሉ ከሚጋበዙ እንግዶች ባለፈ ከinternational ተጋባዥ እንግዶች መኖራቸው ነው፡፡ በዓሉ ስካውቶች ስካውታዊ እውቀት የሚገበዩበት ጥሩ ትዝታን የሚያሳልፉበት ስካውትነታቸው የሚፈተሹበት አንዳቸው ከሌላቸው እውቀት የሚቀስሙበት ትልቅ በዓል ነው፡፡

ቦታ= የኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ

"መቶ ዓመታትን በበጎ ፍቃድ አገልግሎት እና ብቁ ዜጋን በማፍራት"
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#update ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ #ሙስጠፋ_ዑመር እና የሶማሌ ክልል ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር #አህመድ_ሽዴ ጋር በክልሉ ልማትና ፀጥታ ጉዳይ ላይ ተወያዩ።

Via etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲስ አበባ ከሰሞኑን #አስደንጋጭ ወንጀል አስተናግዳለች...

ምንጭ፦ ኢትዮጵፒካሊንክ የተሰኘ የሬድዮ ዝግጅት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአፈልጉኝ ጥሪ‼️
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
የሚወዷቸውን ኢትዮጵያዊ ምግብ እየተመገቡ የሰውነት ክብደትን ማስተካከል እንዲሁም የኑሮ ዘይቤን ማሻሻል ይቻላል?

የውፍረት ችግር፤ የስብ ክምችት መበዛት፤ የጡንቻ መዳክም፤ የአቅም ማጣት እንዲሁም ከዚህ ጋር ተያይዘው ሚመጡ ምቾትና ጤና የሚነሱ ነገሮች እያስቸገርዎት ነው?

ሳይንሳዊና ጤናማ የሆነ ክብደትን የማስተካከል መንገድ በመጠቀም የኒድ የስነምግብ ባለሙያዎች የብዙዎችን ህይወት ቀይረዋል!!

የምንከተለው ሳይንሳዊ ዘይቤ ለአተገባበር ቀላል የሆነና ከኑሮ ዘይቤዎ ጋር እንዲስማማ ተደርጎ የሚነደፍ ነው፡፡

በተጨማሪም ልዩ ፍላጎት ላላቸው ለዲያቤቲክ፣ ለቬጋን፤ ለደም ግፊት ላለባቸው ደንበኞች ልዩ የስነምግብ አገልግሎት እናበረክታለን፡፡

#በፋና_ቲቪ የሚተላለፈውን በስነ ምግብ ዙሪያ የሚያጠነጥነውን ሰውኛ የተሰኘ የቲቪ ፕሮግራማችንን ዘወትር ሰኞ ከ8-30 ጀምሮ እና አርብ ከ10፡30 ጀምሮ ይከታተሉ፡፡

አድራሻ፦ Morning star mall 1st floor/ no 35
+251942-18-43-18
+251953-11-93-29

በቴሌግራም፦ https://yangx.top/Neednutrition
ስካይ ላይት ሆቴል!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያስገነባው ስካይ ላይት ሆቴል ዛሬ ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት በይፋ ተመርቆ ተከፍቷል፡፡ የአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ የመንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል ማስፋፊያ ፕሮጀክትም ዛሬ ይመረቃል፡፡

ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia