TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ‼️

ጥር 17 አፄ #ቴዎድሮስ_ግቢ በ6 የተማሪ መኖሪያ ህንፃዎች በተደረገ #ድንገተኛ ፍተሻ፦

•395 ያልታደሰ፣ ሃሰተኛ እና ፎቶ የሌለው መታወቂያ ተይዟል።

•ከተማሪ መኖሪያ ክፍሎች ጩቤ፣ ድንጋይ፣ ብረት እና ዱላ ተገኝቷል።

•አንድ ተማሪ 9 ሲም ካርድ፤ ሌላ አንድ ተማሪ 7 ሲም ካርድ ይዘው ተገኝተዋል።

•8 ተማሪዎች አካውንት ላይ እያንዳንዳቸው ከ30 ሺ ብር እስከ 86 ሺ ብር ተገኝቷል።

•መታወቂያ ያልያዙ 37 ተማሪዎች ተይዘዋል።

•በቀን ጥር 16/2011 ዓ.ም. 3 ተማሪዎች 4 ጀሪካን ዘይት ጫካ ውስጥ ይዘው እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል፤ 3 ተማሪዎች ሴቶች ህንፃ ሲገቡ ተይዘዋል።

🔹ተጠርጣሪዎች ላይ ተገቢው ማጣራት እየተደረገ ይገኛል፤ በቅርቡ #እርምጃ ተወስዶ #ይፋ ይደረጋል ተብሏል።
.
.
ትምህርት የተቋረጠባቸው አፄ ቴዎድሮስ እና አፄ ፋሲል ግቢዎች ከሰኞ ጥር 20 ጀምሮ ተማሪዎች ትምህርት እንዲጀምሩ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል። ትምህርት የማይጀምሩ ተማሪዎች ግቢውን #ለቀው እንዲወጡ #ጥብቅ_ማሳሰቢያ ተላልፏል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
"አብራክ" ተገመገመ‼️

ኢትዮጵያን የሚንጣት #የዘር ፖለቲካን የወከሉ ገፀ ባህሪያት የተወከሉበትና የብሔር ፖለቲካና የብሔር ማንነት ጥልቀት፣ የፖለቲካ ከፋፋይነት ተደርሶበታል የተባለው “አብራክ” የተሰኘ መፅሐፍ ትናንት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተገምግሟል፡፡

Via Sheger FM 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ትግራይ ክልል ምክር ቤት‼️

የትግራይ ክልል ምክር ቤት በቅርቡ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፀደቀውን የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ #በመቃወም ውሳኔ አስተላለፈ።

ምክር ቤቱ ውሳኔውን ያስተላለፈው በመቐለ ከተማ እያካሄደ ባለው 5ኛ ዓመት 14 መደበኛ ጉባዔው ነው።

ምክር ቤቱ በውሳኔ ሀሳቡ አዋጁ የፌዴራል መንግስት በክልሎች ጉዳይ ጣልቃ በመግባት የክልላዊ አስተዳደር መብትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት ስልጣንን እንዲጋፋ የሚያደርግ ነው ብሏል።

በተጨማሪም በክልሎች፣ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች መካከል #መጠራጠር እንዲፈጠር የሚያደርግ እንደሆነም ነው ምክር ቤቱ በውሳኔ ሀሳቡ የገለፀው።

ለዚህም ኮሚሽኑ የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች በሕገ መንግስት የተሰጣቸውን ስልጣን ተክቶ የወሰንና የማንነት ጉዳዮችን ለመመልከት መቋቋሙ ስሕተት ነው ሲል በውሳኔ ሀሳቡ አስፍሯል። ምክር ቤቱ በመጨረሻም አዋጁን በመቃወም የተዘጋጀውን የውሳኔ ሀሳብ አፅድቋል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ከትራንስፖርት ሚኒስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ እና ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/እግዚአብሔር ጋር በመሆን በዛሬው ዕለት በሞጆ ደረቅ ወደብ ተገኝተው 13 አዳዲስ የዕቃ መጫኛና ማውረጃ ( ሪች ስታከር) ማሽኖችን መርቀው ስራ አስጀምረዋል፡፡

Via EPA
@tsegabwolde @tilvahethiopia
ፎቶሾፕ🔝

"አዶቤ ፎቶሾፕ የተመሰረተው #በወንድማማቾቹ #ቶማስ_ኖል እና #ጆን_ኖል እኤአ በ1988 ዓ.ም ነበር። ከዛ ግዜ ጀምሮ ኢትዮጵያውያንን እንዳወዛገበ ይገኛል!"

©ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት(AP)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ስካይ ላይት ሆቴል ነገ ይመረቃል!!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ60 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ወጪ ያስገነባው #የስካይ_ላይት_ሆቴል በነገው ዕለት ተመርቆ ወደ ሥራ እንደሚገባ ተገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ እኤአ በ2025 በዓለምአቀፍ ደረጃ እጅግ ተወዳዳሪ አየር መንገድ ለማድረግ የሚያደርገውን ጥረት ለማሳካት መሰል የሆቴል ግንባታዎች ሚናቸው ከፍተኛ መሆኑን በአየር መንገዱ የመሠረተ ልማት ክፍል ኃላፊ አቶ አብርሃም ተስፋዬ ለዋልታ ተናግረዋል፡፡

ስካይ ላይት ሆቴል ለሶስት አመታት ያህል የግንባታው ሥራ ሲከናወን የቆየ ሲሆን ሙሉ ለሙሉ አገልግሎት መሥጠት ሲጀምር የባለ 5 ኮከብ ደረጃን ያገኛል ተብሎ ይጠበቃል። ሆቴሉ በመላው ዓለም የሚገኙ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ትራንዚተሮችን ከማስተናገድ ረገድ ትልቁን ድርሻ እንደሚወጣ ተገልጿል፡፡

ሆቴሉ በአጠቃላይ 373 የማረፊያ ክፍሎች፣ አራት ደረጃቸውን የጠበቁ ሪስቶራንቶች፣ የመዋኛ ገንዳ፣ የአዳራሽ አገልግሎትና ሌሎችም ዘርፈ-ብዙ የሆቴል አገልግሎቶችን በሟሟላት ሀገሪቱ በትኩረት እየሠራች የሚትገኘውን የቱሪዝም ኢንዱስትሪን ይበልጥ እንደሚያግዝም ታምኖበታል፡፡ በነገው ዕለት ተመርቆ ወደ ሥራ የሚገባው ስካይ ላይት ሆቴል የቱሪዝም ኮንፌረንሱን በማገዝም የጎላ አስተዋፅዖ አለው ተብሏል፡፡

ምንጭ፦ ዋልታ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከአዲስ አበባ...

"ጠ/ሚ ዶክተር #አብይ_አህመድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያስገነባውን ሆቴል #ይመርቃሉ፤ እንዲሁም የኢንተርናሽናል ኤርፖርት ተርሚናል ማስፋፊያ ግንባታን ተዘዋውረው ይጎበኛሉ።"

©S(TIKVAH-ETH)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሶሪያ ስደተኞች~ሃዋሳ‼️

በአሁኑ ወቅት #በሀዋሳ_ከተማ በልመና ስራ ተሰማርተው የሚገኙ ጥቂት የሶሪያ ዜጎች መኖራቸውን የኢሚግሬሽን የዜግነትና ወሳኝ ኩነቶች ኤጀንሲ አስታውቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ድሬዳዋ አንፃራዊ ሰላም ሰፍኗል‼️

ሰሞኑን #በድሬደዋ_ከተማ የነበረውን ያለመረጋጋት ተከትሎ የመከላከያ ሰራዊት ከፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት በወሰደው የማረጋጋት ስራ በከተማዋ አንፃራዊ #ሰላም መታየቱን የምስራቅ እዝ አስታወቀ፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲስ አበባ‼️

የጎዳና ተዳዳሪዎችን በዘላቂነት ለማቋቋም የሚያስችል የማህበራዊ ትረስት ፈንድ የኢፌዲሪ ፕረዝደንት ወ/ሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ ኢ/ር ታከለ ኡማ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የካቢኔ አባላት፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አሪቲስቶች እና አትሌቶች በተገኙበት በዛሬው ዕለት ይፋ ሆኗል፡፡

በመድረኩ ላይ ኢ/ር ታከለ ኡማ የጎዳና ላይ ነዋሪዎችን እንደ ማንኛውም የከተማው ነዋሪ የመጠበቅ፣ የመንከባከብ እና የመደገፍ ግዴታ አለብን ብለው የከተማ አስተዳደሩ ለዚህ ተግባር የሚውል የ 100 ሚሊዮን ብር የመነሻ በጀት መመደቡንም አሳውቀዋል፡፡

ቀጥለውም ለዚህም በጎ ተግባር የከተማው ነዋሪ፣ ትምህርት ቤቶች፣ የሃይማኖት ተቋማት፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ ባለሃብቶች እና የመንግስት ተቋማት ከከተማ አስተዳደሩ ጎን እንዲቆሙ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

ምንጭ፦Mayor Office of Addis Ababa
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የማህበራዊ ትረስት ፈንዱን ለመደገፍ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የሚሳተፍበት አጭር የፅሁፍ መልዕክት መላኪያ ቁጥርም ይፋ ሆኗል፡፡ ስለዚህ ህብረተሰቡ በ6400 ላይ A ብሎ በመላክ የጎዳና ላይ ተዳዳሪ ወገኖቻችንን ህይወት በመቀየር ማህበራዊ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ ቀርቧል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia