TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#update አባይ ኢንዱስትሪያል የልማት ማህበር በአማራ ክልል ደጀን ከተማ በ8.8 ቢሊዮን ብር ሲሚንቶ ፋብሪካ ለመገንባት ከቻይናው HY እና ከዴንማርኩ FLS ኩባንያዎች ጋር ሥምምነት ተፈራረመ፡፡ በ24 ወራት ውስጥ ይጠናቀቃል የተባለው ፋብሪካ በቀን 5,000 ቶን ሲሚንቶ የመፍጨት አቅም አለው ተብሏል። ዓባይ ኢንዱስትርያል የልማት ማህበር በአማራ ክልል መንግስትና በግል ባለሃብቶች ጥምረት የተቋቋመ ኩባንያ ነው።

via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድና ልዑካቸው ከአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ምክትል ፕሬዚዳንት እና የአውሮፓ ሕብረት የውጭ ጉዳይና ደህንነት ፖሊሲከፍተኛ ተወካይ ፌዴሪካ ሞግሄርኒ ጋር ስብሰባ አካሂዷል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አምቦ🔝

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥትና ኦነግ ዛሬ እንደገና አምቦ ላይ #ዕርቅ ፈጽመዋል፡፡ የኦሮሞ አባ ገዳዎች በመሩት ባህላዊ የዕርቅ ስነ ሥርዓት ላይ ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት #ሚልኪያስ_ሚደቅሳ (ዶ/ር)፣ ከኦነግ ደሞ ሊቀመንበሩ #ዳውድ_ኢብሳ ተገኝተዋል፡፡

እንደ ባህሉ ኮርማ ታርዶ በተከናወነው ስነ ሥርዓት ሁለቱ ወገኖች ያለፈውን ሁሉ ከኋላቸው ትተው ድጋሚ ደም በመካከላቸው እንዳይፈስ በዕርቅ መንፈስ በጋራ ለመሰራት ተስማምተዋል፡፡ ዝርዝር የስምምነት ነጥቦችም ይፋ ይደረጋሉ ተብሏል፡፡

ዛሬ ረፋዱ ላይ ግን የኦዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ ዋና ጸሃፊ አለሙ ስሜ ኦነግ የሠራዊቱንና ትጥቁን ጉዳይ ለአባ ገዳዎች ትቻለሁ ማለቱ ለሰላም ቁርጠኛ አለመሆኑን ያሳያል ሲሉ ለሸገር ተናግረው ነበር፡፡

via wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አፋር🕊ሱማሌ!!

ሰሞኑን በአፋርና ሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች ተፈጥሮ የነበረውን #ግጭት ለመፍታት የሁለቱ ክልሎች የሃይማኖት መሪዎችና የሀገር ሽማግሌዎች #ተስማሙ

በቅርቡ በሁለቱ ክልሎች የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ የሁለቱ ክልሎች የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሰላም ሚኒስቴር ዴኤታና ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበት የውይይት መድረክ ተካሂዷል።

በውይይቱም የተፈጠረውን ግጭት  ለመፍታት የሁለቱ ክልሎች የሃይማኖት መሪዎችና የሃገር ሽማግሌዎች መስማማታቸው ነው የተገለፀው።

ከዚህ ባሻገርም የተፈጠረውን ግጭት  መንስኤ ለማጣራትና ግጭቱ ዳግም እንዳይከሰት ለማድረግ ከሁለቱ ክልሎች  የተውጣጣ የጋራ ኮቴ ተቋቁሟል።

በውይይቱ ላይ ንግግር ያደረጉት ኡስታዝ አቡበክር ሁለቱ ህዝቦች በሃይማኖት በባህል እና በጋብቻ ተሳስረው የኖሩ በመሆናቸው በመካከላቸው መሰል ግጭት መፈጠሩ አግባብ አለመሆኑን ተናግረዋል።

ስለሆነም የሁለቱ ክልሎች የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች በቀጣይ ምንም ዓይነት ግጭት እንዳይከሰትና ሰላምና ለማውረድ መስማማታቸውን ገልፀዋል።

ስለሆነም የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ከስምምነት ባሻገር ወደ ህብረተሰቡ ወርደው ለጋራ  ሰላም መስራት እንደሚገባቸው አሳስበዋል።

የሰላም ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ #ዘይኑ_ጀማል በበኩላቸው መንግስት በአካባቢው ግጭት ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን አስታውቀዋል።

በዚህ መሰረትም ከሁለቱ ክልሎች ርዕሰ መስተዳድሮች እና የፀጥታ አካላት ጋር ውይይት በማድረግ የጋራ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ የግጭቱን መንስኤ ለማጣራት እና ዳግም እናዳይከሰት ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል።

ከዚህ ባለፈም መንግስት በአካባቢው ሰላምን ለማስፈን ለሚሰራው ስራ የሃይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎች ድርሻ ከፍተኛ መሆኑን  ጠቁመዋል።

ምንጭ፦ fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰላም🕊በአፋርና ሶማሌ #አዋሳኝ አካባቢዎች የተፈጠረውን ግጭት #ለማስቆም ስምምነት ላይ ተደርሷል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፋሲል ከነማ‼️

የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች አሳፍሮ ከባህርዳር ወደ ጎንደር በማምራት ላይ ያለ አውቶብስ #ተገልብጦ በሰው ህይወት እና አካል ላይ ጉዳት መድረሱ ተነግሯል።

የፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ ደጋፊዎቹ ትናንት በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 12ኛ ሳምንት በባህርዳር ከተማ እና ፋሲል ከነማ መካከል ከተደረገው ጨዋታ በኃላ ወደ ጎንደር እየተመለሱ ጣራ ገዳም በሚባል አካባቢ ሲደርሱ ነው የመኪና አደጋው ያጋጠማቸው።

በአደጋውም የሁለት ደጋፊዎች ህይወት ሲያልፍ ለጊዜው ቁጥራቸው ያልታወቀ ደጋፊዎች ላይም የተለያየ መጠን ያለው የአካል ጉዳት መድረሱ ተገልጿል።

በተሽከርካሪ አደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ደጋፊዎች በጎንደር ሆስፒታል እና በአዲስ ዘመን ሆስፒታል ህክምና እየተከታተሉ መሆኑን የፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ አስታውቋል።

የፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ በደጋፊዎቹ ህይወት ማለፍ እና በደረሰው ጉዳት የተሰማውን መሪር ሀዘን ገልጿል።

“ለክለባቸው ሲሉ ህይዎታቸውን ያጡ ለክለባቸው ታምነው የህይወት መስዋዕትነት የከፈሉ ደጋፊዎች ታሪካቸው በመላው የፋሲል ከነማና የስፖርት ቤተሰብ ስማቸው በወርቅ መዝገብ ተፅፎ እስከወዲያኛው ሲዘከር ይኖራል” ሲልም ክለቡ አስታውቋል።

Via FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቅዱስ ጊዮርጊስ🔝የቅዱስ ጊዮርጊስ #ደጋፊዎች እና #ተጫዋቾች በፋሲል ከነማ ሁለት ደጋፊዎች ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገልፀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዱራሜ🔝ዛሬ ዱራሜ ላይ በከፋ ዞን ለሞቱ የከንባታ ተወላጆች የሃዘን መግለጫ እና ሻማ የማብራት ፕሮግራም ተካሂዷል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዴፓ!!

የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) #አዲሱን አርማውን በዛሬው እለት ይፋ አደረገ።

አዴፓ ባሳለፍነው መስከረም ወር ባካሄደው 12ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ ላይ ነበር የአርማ #ለውጥ እንዲደረግ ውሳኔ ያሳለፈው።

ፓርቲው በድርጅታዊ ጉባዔው አዲሱ አርማ  መደቡ ከላይ አረንጓዴ መሃል ላይ ጎህ ሲቀድ የሚኖር ቀለም (ቢጫ) ሆኖ ከግርጌ ቀይ እንዲሆን መወሰኑ ይታወሳል።

እንዲሁም መሃሉ ላይ የስንዴ ዘለላ እና የኢንዱስትሪ ምልክት በግራ እና በቀኝ እንዲሆን የአባይ ወንዝ እና መጽሃፍም በአርማው መሃል ላይ እንዲካተት በውኖ ነበር።

በዚህም መሰረት የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) አዲሱ አርማውን በዛሬው እለት በፌስ ቡክ ገፁ ይፋ አድርጓል።

ምንጭ፦ ፋና
@tsegabwolde @tikvahethiopia