TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
ጅግጅጋ🔝 በትላንትናው ዕለት የጥምቀት በዓል #በጅግጅጋ ከተማ በሰላም ተከብሯል!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
አዲስ አበባ!

በአዲስ አበባ ከተማ #በጃንሜዳ በዓሉ ሲከበር ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ የክልል አስተዳደሮች "እኛን #ሊለያዩን እና ሰው መሆናችንን ሊያሳጡን አልተፈጠሩም" ሲሉ ተናግረዋል። ሰው በሰውነቱ ሊከበር እንደሚገባ ለጥምቀት በዓል ታዳሚያን አስረድተዋል። የጥምቀት በዓል በክርስትና ዕምነት ተከታዮች ዘንድ አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች ሲከበር ውሏል። 

ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
''ለልማት የፈራ #ይመለስ መልካምነት ለራስ ነው !''

በደ/ብ/ብ/ህ/ክልል የሰገን አካባቢ ህዝቦች ልዩ ዞን ደራሼ ወረዳ #ጊዶሌ_ከተማ የሚገኘው ማቹ የወጣቶች የበጎ አድራጎትና ልማት ማህበር የጥምቀት በአልን ምክንያት በማድረግ ዛሬ ለአረጋውያን ምሳ አብልቷል። ከአመታት በፊት በልማት ስራዎች ብቻ ለመሳተፍ ታስቦ የተመሠረተው ማህበሩ አገልግሎቱን በማስፋት ወደ በጎ አድራጎት ስራም ገብቶ አረጋውያንን እየደገፈ መሆኑን የማህበሩ ሰብሳቢና መስራች አባል ወጣት አለምነህ አለማየሁ ተናግሯል።

via epa
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አክቲቪስት ጃዋር መሃመድ...
አክቲቪስት #ጃዋር_መሀመድ በሰሞኑ የሀረር ጉዞ ከህዝብ ጋር ባደረገው ውይይት ከተናገረው በጥቂቱ የተተረጎመ…

(በዘሪሁን ገመቹ)

"ቄሮ ነኝ..ከዚህ በፊት ታግዬ ነበረ... ታስሬ ነበር ስለዚህ አሁን ደሞዜ ሊከፈለኝ ይገባል ብሎ #ዘረፋ ውስጥ የሚገባ..ስልጣን ይገባኛል ብሎ የሚያስፈራራ እሱ ቄሮ ሳይሆን ወያኔ ነው። መኖሪያውም ከሜቴክ ባለስልጣን ጋር ቃሊቲ ነው መሆን ያለበት። ለህዝባችን ነፃነት እንጂ #ለግል ኑሮአችን አልታገልንም። የታገልነውም #መስዋዕትነት የከፈልነውም #ህዝባችን ለምኖን ወይም አስገድዶን ሳይሆን በራሳችን ፍላጎት ነው። ስለሆነም ከ ህዝብ የተለየ ነገር ማግኘት አለብን ብላችሁ የመጠየቅ መብት የላችሁም። ወላጆችም ልጆቻችሁ ለከፈሉት መስዋዕትነት ከማመስገንና ተገቢውን ክብር ከመስጠት ባለፈ ከህግ ውጭ እንዲሆኑ #ፊት_አትስጧቸው...ካለበለዚያ #አሸባሪ ነው የሚሆኑባችሁ። ቄሮ ማንኛውንም መኪና ኮንትሮባንድ የጫነ ነው ብሎ ሲጠረጥር ለፓሊስ እና ለህግ አካላት #መጠቆም እንጂ #የመፈተሽ_ስልጣን_የለውም። እንደዛ ማድረግ በቄሮ ስም ለሚነግዱ #ዘራፊዎች ሁኔታዎችን እያመቻቸሁላቸው ስለሆነ አካሄዱ መስተካከል አለበት። ለሚቀጥሉት ሁለት ዓመት መንግስታችን አንድ ነው ። አሁን ስልጣን ላይ ያለው። አዲስ አበባ ተመዝግቦ መጥቶ ፅ/ቤት የሚከፍት ማንኛውንም ፓርቲ ተቀበሉት፣ቢሮውን እንዲከፍት አግዙት፣ ኑሯችሁን እንዴት ለማሻሻል እንዳሠበ ቁጭ ብላችሁ ስሙ..ከዛ ቀኑ ሲደርስ የተሻለውን #ትመርጣላችሁ..ካዛ ውጭ ግን ዛሬ አዲስ:አበባ ተቀምጦ #ፓለቲካ_እያወራ እዚህ መሳሪያ #እንድትታኮሱ የሚጠይቃችሁ ካለ እሱ #ጠላታችሁ ስለሆነ ከተማችሁ ሳይገባ በሩቁ ተከላከሉት። የነፃነትን #መጠጥ በልኩ ጠጥቶ #መደሰት አግባብ ነው…ተገኘ ተብሎ ከመጠን በላይ በመጠጣት መስከር ግን ጥፋት ነው። ሪፎርሙ #ከከሸፈ በፊት ወደነበርንበት አንመለስም...እንደሱማሌ እና ዪጎዝላቪያ #በመፈረካከስ ተጫርሰን #እናልቃለን።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
animation.gif
358.6 KB
ምርመራው ተጠናቋል‼️

ፖሊስ በቀድሞ የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ መሐመድ (አብዲ ኢሌ)፣ ራሕማ መሐመድና ፈርሃን ጣሂር ላይ ሲያደርግ የቆየውን ምርመራ #አጠናቅቆ መዝገቡን ለጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ማስተላለፉን ለፍርድ ቤት አስታውቋል፡፡ መዝገቡን እንደተቀበለ ለፍርድ ቤቱ ያስታወቀው ዓቃቤ ሕግ ክስ ለመመሥረት የ15 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ቢጠይቅም፣ የተጠርጣሪዎቹ ጠበቆች ተቃውሞ አሰምተዋል፡፡ ፍርድ ቤቱም የ13 ቀናት የክስ መመሥረቻ ጊዜ ፈቅዶ ለጥር 24 ቀን 2011 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

via reporter
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የስደተኞች ጉዳይ...‼️

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጥር 9፣ 2011 ዓ. ም. ማለዳ ባደረገው አስራ ዘጠነኛ #መደበኛ ስብሰባ፤ #የስደተኞች_ጉዳይ ረቂቅ አዋጅን በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል።

አዋጁ በተለያየ ምክንያት ወደ ኢትዮጵያ ለሚመጡ ስደተኞች ልዩ ልዩ መብቶችን በማጎናፀፍ፤ ኢትዮጵያ ለምታስተናግዳቸው ስደተኞች የምታደርገውን እንክባካቤ ያስቀጥላል ተብሏል። አዋጁ በሦስት ተቃውሞና በአንድ ተዓቅቦ ፀድቋል።

በአዋጁ መሠረት ዕውቅና ያገኙ ስደተኞች ከመንቀሳቀስ መብት በተጨማሪ ትምህርትና ሥራ የማግኘት መብት ይኖራቸዋል።

ኢትዮጵያ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች የሚገኙባት ስትሆን፤ ይህም በርካታ ስደተኞችን ከተቀበሉ የአፍሪካ አገራት ከቀዳሚዎቹ ተርታ ያስመደባታል።

"በኢትዮጵያዊያን ሥራ ፈላጊዎች ላይ ተጨማሪ ፈተና ይደቅናል። ስደተኞችን የሚያስተናዱ የክልል መንግሥታት አልተማከሩበትም" የሚሉ ነቀፌታዎችን አዋጁ ላይ የሰነዘሩ የሕዝብ እንደራሴዎች ነበሩ።

አዋጁን የተመለከተ ማብራሪያ ሲሰጡ የነበሩት የሕግ፣ የፍትሕ እና ዲሞክራሲ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ፎዚያ አሚን፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሁሉም ኢትዮጵያዊያን ወኪል በመሆኑ፤ በጉዳዩ ላይ መወያየቱ የሕዝቦችን ድምፅ እንዳስተናገደ እንደሚቆጠር ተናግረዋል። በተጨማሪም በረቂቅ አዋጁ ላይ ሕዝባዊ ምክክሮች መደረጋቸውን አስረድተዋል።

በአዋጁ መሠረት፤ ስደተኞች ለውጭ አገር ዜጎች የተፈቀዱ የሥራ መስኮች ላይ የመሰማራት ዕድል የሚኖራቸው ሲሆን፤ ይህም የኢትዮጵያዊያንን ዕድል የሚነጥቅ ሳይሆን ክፍተትን የሚሞላ ይሆናል ተብሏል።

ከማርቀቅ እስከ ማስፀደቅ ከሁለት ዓመታት በላይ ጊዜ ወስዷል የተባለው አዋጅ፤ በዓለም አቀፍ ትብብር በሚቀረፁ ላይ ሰባ መቶ የሚሆነውን ድርሻ ኢትዮጵያዊያን እንዲይዙት ተደርጎ፤ የቀረውን ብቃት ባላቸው ስደተኞች እንዲያዝ የሚያስችል ይሆናል።

ለስደተኞች ክፍት ይሆናሉ ተብለው ከሚጠበቁት እና ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፍ አጋሮቿ ጋር በጋራ ከምትከውናቸው ፕሮጀክቶች መካከል የኢንዱስትሪ ፓርኮች እና የመስኖ ልማቶች ይገኙበታል።

ምንጭ፦ BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ክፍት የስራ ቦታ ማስታወቂያ!

የስራዉ አይነት፡ የኘሮሞሽን እና ሽያጭ ሠራተኛ

ተፈላጊ ችሎታ: ከዚህ በፊት የሽያጭ ስራ ልምድ ያለዉ እና ጥሩ ከሰዉ የመግባባት ችሎታ የለዉ

ፆታ፡ ወንድ

የስራ ቦታ፡ አዲስ አበባ

የስራ ሰዓት፡ ግማሽ ቀን

ደመወዝ፡ 2000 ብር እና ኮሚሽን

ለምዝገባ በ0920241178 ይደውሉ
Tulip advert & computing
ማስታወቂያ፦ ጥር 12/2011 ለአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ቅድመ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ከልዑካን ቡድናችው ጋር የአውሮፓ ጉብኝታቸውን ዛሬ ጀመሩ:: በዳቮስ በሚካሄደው የአለም የኢኮኖሚ ጉባኤ መድረክ ላይ ንግግር ከማድረግ ጎን ለጎን በአውሮፓ ጉብኝታቸውም ከተለያዩ የአለም አቀፍ የልማት አጋሮች ጋር ይወያያሉ::

#PMO
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሳዛኝ ዜና‼️

በሜድትራኒያን ባህር ላይ ስድተኞችን አሳፍረው ሲጓዙ የነበሩ ሁለት ጀልባዎች ላይ በደረሰ አደጋ 170 ያህል ስደተኞች ህይወት ማለፉን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ኤጀንሲ አስታውቋል።

የጣሊያን ባህር ሀይል ባወጣው ሪፖርት ከሊቢያ ባህር ዳርቻ ስተደኞችን በመጫን የተነሱት ጀልባዎቹ የመስጠም አደጋ ነው ያጋጠማቸው ብሏል።

የስፔን እና የሞሮኮ ባለስልጣናት ደግሞ በምእራብ ሜድራኒያ ባህር ላይ የጠፉትን ጀልባዎች እያፈላለጉ ነው ተብሏል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ኤጀንሲ በጀልባዎቹ ላይ በደረሰው አደጋ ትክክለኛ የሟቾቸን ቁጥር አላሳወቀም ተብሏል።

ሆኖም ግን ከስፍራው የወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት የመጀመሪያው ጀልባ 53 ሰዎችን አሳፍሮ የተነሳ መሆኑ የተነገረ ሲሆን፥ ከዚህ ጀልባ ላይም 1 ሰው በህይወት መትፈሩን እና በሞሮኮ ህክምና እየተከታተለ መሆኑ ተነግሯል።

ሁለተኛው ጀልባም 120 ሰዎችን በማሳፈር በትናትናው እለት ከሊቢያ መነሳቱን እና ጀልባው ላይ ተሳፍረው ከነበሩት ውስጥ 3 ሰዎች ብቻ በህይወት መገኘታቸው ተገልጿል።

በአሁኑ ወቅትም ጀልባዎቹ እና ከጀልባዎቹ ላይ በህይወት የተረፉ ስደተኞችን ካሉ በሚል የማፈላለግ ስራ የተካሄደ ቢሆንም፤ ስኬታማ አይደለም ተብሏል።

በአውሮፓውያኑ 2018 ብቻ ከ2 ሺህ 200 በላይ ሰዎች በህገ ወጥ መንገድ ወደ አውሮፓ ለመግባት ሲሉ በሜድትራኒያን ባህር ላይ ህይወታቸውን ማጣታቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ።

ምንጭ፦ www.bbc.com
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጊዶሌ🔝

ከጥር 11-13/2011 ዓ.ም በደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል የሰገን አካባቢ ህዝቦች ዞን ዲራሼ ወረዳ ጊዶሌ ከተማ ሲካሄድ የቆየው ታላቅ የፊላና የባህል ፌስቲቫል ዛሬ ይጠናቀቃል። በማጠቃለያው የውይይት መድረክ የተዘጋጀ ሲሆን የተለያዩ ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ነው። የፊላ ትርዒት በጎዳናዎች ላይ የሚካሄድ ሲሆን ከወረዳዋ አራቱ ብሄረሰቦች ይሳተፉበታል። ፊላ የዲራሼ ህዝብ መገለጫ ሲሆን በድምፅ፣ በአንድ አይነት ምትና እንቅስቃሴ የሚከወን ባህላዊ ስርዐት ነው።

via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአገሪቱ የሚታዩትን #ግጭቶች ለማስቆም ወጣቱ በውይይት የሚያምንና በምክንያት ላይ የተመሰረተ ሥራ ሊያከናውን እንደሚገባ ተገለፀ፡፡በሃይማኖት በዓላት ላይ የሚታየውን አንድነትም ግጭቶችን ለመፍታት መጠቀም እንደሚገባም ተመልክቷል፡፡ በወልድያ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር አቶ ሻለሙ ስዩም፣ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናሩት፤ በአገሪቱ የሚታየውን ግጭት ለማስቆም ወጣቱ የተለያዩ የአገሪቱ ጉዳዮችን በመተንተን ለግጭት ሊያደርስ የቻለውን ነገር በምክንያት ላይ ተመስርቶ በመለየት ችግሮችንም በውይይት መፍታት አለበት ብለዋል።

ምንጭ፦ አዲስ ዘመን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ 4ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ ከጥር 19 ቀን ጀምሮ #በሀዋሣ ከተማ ይካሄዳል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia