TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#Update በምዕራብ ጎንደር ዞን ገንደ ውሃ እና ሸዲ ከተሞች፣ የመንግስት ወታደሮች መንገድ በዘጉ ወጣቶች ላይ በከፈቱት #ተኩስ 5 ሰዎች የተገደሉ ሲሆን 3 ሰዎች ክፉኛ ተጎድተው ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል። ከሟቾቹ መካከል የ10 አመት ታዳጊ ይገኝበታል። ግጭቱ የተፈጠረው አካባቢውን ለቆ በመውጣት ላይ የሚገኘውን የሱር ኮንስትራክሽን ድርጅት ማሽነሪዎችን ለማጀብ የመጡ ወታደሮች ተኩስ ከፍተው ሰዎችን ከገደሉ በኅላ ነው።

ምንጭ፦ ኢትዮጵያ ላይቭ ሀፕዴት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"የትግራይ ህዝብ #ህጋዊ በሆነው የመከላከያ ሰራዊት እንቅስቃሴ #ሊረበሽ አይገባም"--ዶክተር #ደብረጽዮን_ገብረሚካኤል

.
.
የትግራይ ህዝብ ህጋዊ በሆነው የመከላከያ ሰራዊት ከቦታ ወደ ቦታ መንቀሳቀስ ሳይረበሽ #በልማቱ ላይ ሊያተኩር እንደሚገባ የክልሉ ምክትል ርዕሰ-መስተዳደር ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ገለጹ።

ምክትል ርዕሰ-መስተዳደሩ ዛሬ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንዳመለከቱት የመከላከያ ሰራዊት ከቦታ ወደ ቦታ መንቀሳቀስ ህጋዊና #ኃላፊነቱንም ለመወጣት የሚያስችል ነው።

በመሆኑም የክልሉ ህዝብ ይሄንን ተገንዝቦ ያለምንም መረበሽ የልማት ስራውን #በተረጋጋ መልኩ ማከናወን እንዳለበት አሳስበዋል።

ህዝቡ የሚያነሳው የህገ-መንግስት ይከበርልን ጥያቄ እራሱ ከማክበር የሚጀምር መሆኑንም ምክትል ርዕሰ-መስተዳደር በመግለጫቸው አመልክተዋል።

የክልሉን ሰላምና ጸጥታ የማስከበርን ጉዳይም ህዝቡ በፈጠረው አደረጃጀት አንድነቱን ማስቀጠል እንደሚኖርበትም ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያና የኤርትራ መንግስታት ባደረጉት የጋራ ስምምነት የሁመራ ኦምሃጀር መንገድ መከፈትም ለሁለቱ ህዝቦች ግንኙነት ጠቃሚ እንደሆነ ዶክተር ደብረጽዮን ተናግረዋል።

መንገዱ የሁለቱን ሃገራት የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ከማሳደግ ባለፈው ቀጣይ ህጋዊ መስመር ለማስያዝም ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው አመልክተዋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ግብፃዊው የሊቨርፑል ክለብ አጥቂ መሀመድ ሳላ የ2018 የአፍሪካ የአመቱ ምርጥ ተጫዋች ሽልማትን በተከታታይ ለሁለተኛ ጊዜ ማሸነፍ ችሏል፡፡ የ26 አመቱ መሀመድ ሳላ አብረውት በእጩነት የቀረቡትን የክለብ አጋሩ ሳይዶ ማኔ እና የአርሰናሉ አጥቂ ፒር ኡሚሬክ ኦባሚያንግን በመብለጥ ነው የሽልማቱ አሸነፊ መሆን ያቻለው፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
“ኦነግ በሬ እያረደ በተቀበለው ህዝብ ላይ ዘረፋና #ግድያ ፈጽሟል” ጄኔራል #ብርሃኑ_ጁላ

• ሠራዊቱ ከትግራይ እንዳይወጣ የሞከሩት ህዝቡና የክልሉ መንግሥት አይደሉም

• መከላከያን ከኃላፊነቱ ውጪ የክልሎችና የፖለቲካ ሥራን የማሠራት ፍላጎት አለ

• በሠራዊቱ ላይ ጥላቻ በመንዛት አገርን ለማፍረስ የሚሠሩ አሉ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዴፓ🔝የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ(አዴፓ) ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ እያካሄደ ነው፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ገንደውሃ🔝

ትናንት መከላከያ ሰራዊት በምዕራብ ጎንደር ዞን የፈጸመውን ግድያ #በመቃወም በመተማ ገንደውሃ የተቃውሞ ሰልፍ በመደረግ ላይ ይገኛል። ሰልፈኞቹ ሰራዊቱ አካባቢውን ለቆ እንዲወጣ ጠይቀዋል። ሰልፈኞቹ መከላከያ 'ሪፎርም' ሊደረግ የማይችል ተቋም ስለሆነ፣ የሰራዊቱ አባል የሆኑ የአማራ ብሔር ተወላጆች ከሰራዊቱ እራሳቸውን እንዲያገሉም ጠይቀዋል።

Via ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የአየርላንዱ ጠቅላይ ሚንስትር ሊዮ ቫራድከር ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ገቡ፡፡ ጠቅላይ ሚንስትሩ ቦሌ አለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ድኤታ ዶ/ር ማርቆስ ታከለ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡ጠቅላይ ሚስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የአየርላንዱን ጠቅላይ ሚንስትር ሊዮ ቫራድከር ዛሬ በፅፈት ቤታቸው እንደሚያናግሩ ይጠበቃል፡፡

ምንጭ፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
University College Run,Jan 13,2019 ~ Starting Point- Adams Pavilion - Laphto Mall (End Point)

More፦
0911449805
0912688755
#Update የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ዕጣ ለማውጣት መረጃውን/ዳታ/ የማስገባት ሥራ #በገለልተኛ አካል እየተሠራ መሆኑን የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡ የጽሕፈት ቤት የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሥራ ሂደት መሪ አቶ ጋሻው ተፈራ፣ ቀደም ሲል ዕጣ የማውጣቱ ሥራ በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ(ኢንሳ)ይሠራ እንደነበር አስታውሰው፣ አሁን ግን የግንባታው ባለቤት የሆነው የአዲስ አበባ ቤቶች አስተዳደር ኤጀንሲ ሥራውን ተረክቦ እየሠራ ይገኛል ብለዋል፡፡

Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከአማራ ክልል...

"በአዊ ዞን እንጂባራ ከተማ በተፈጠረ የሹፌሮች አድማ የመኪና እንቅስቃሴ ከጥዋት ጀምሮ ቆሟል ወደ አዲስ አበባ፣ ባህር ዳር፣ ቻግኒ የሚሄድ ህዝብ እየተጉላላ ይገኛል።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ብሮድካ ስት ባለስልጣን‼️

ፈቃድ ወስደው ወደ ስርጭት ያልገቡ 17 የማህበረሰብ ሬድዮ ጣቢያዎች በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ወደ ሥራ ካልገቡ ፍቃዳቸው እንደሚሰረዝ የብሮድካስት ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

የማይጨው ከተማና የደብረብርሀን ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ ሬድዮ ፍቃድ #መሰረዙንም ባለስልጣኑ አስታውቋል፡፡

አክሱም ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ ሬድዮ ጣቢያ ለማቋቋም የጠቅላላ ጉባኤ እና የቦርድ ምርጫ መድረክ ባለፈው ሳምንት አካሂዷል፡፡

በመድረኩ ላይ የተገኙት በባለስልጣኑ የመገናኛ ብዙሃን ምዝገባና ፈቃድ ዳይሬክተር አቶ ሙሉጌታ ሲሳይ እንዳሉት በሀገሪቱ ለ50 የማህበረሰብ ሬድዮ ጣቢያዎች ፈቃድ መሰጠቱን ተናግረዋል፡፡

ፍቃድ ከወሰዱት ውስጥ 31 የማህበረሰብ ሬድዮ ጣቢያዎች ወደ ስርጭት መግባታቸውን ጠቁመዋል፡፡

የማይጨው እና የደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ሬድዮ ፈቃድ ወስደው ከአምስት ዓመት በላይ ስርጭት ባለመጀመራቸው ፈቃደቸው መሰረዙን ገልጸዋል፡፡

ፈቃድ ወስደው እስካሁን ወደስርጭት ያልገቡ 17 የማህበረሰብ ሬዲዮ ጣቢያዎች በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ወደ ስርጭት መግባት እንዳለባቸውም አቶ ሙሉጌታ አመልክተዋል፡፡

የኢሮብ፣ ኩናማ፣ ከሚሴ፣ እንጅባራ፣ ሸካ፣ ስልጤና ሌሎችን ጨምሮ 17 የማህበረሰብ ሬድዮ ጣቢያዎች በዚህ ዓመት ስርጭት እንዲጀምሩ በመንግስት በኩል ክትትልና ድጋፍ እንደሚደረግም ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

ባለስልጣኑ በስልጠና፣ በአሰራርና በሙያ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን የገለጹት አቶ ሙሉጌታ፣ ጣቢያዎቹ በተባለው ጊዜ ውስጥ ወደስርጭት ካልገቡ የተሰጣቸው ፍቃድ እንደሚሰርዝም አስገንዝበዋል፡፡

የአክሱም ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ ሬድዮ ጣቢያ ለማቋቋም ከባለስልጣኑ ፈቃድ ለማገኘት የፈቃድ ጠያቂውን ማህበረሰብ ፊርማ ማሰባሰብ እንዳለበትም አመልክተዋል፡፡

”ጣቢያው ህጋዊ ተቋም መሆኑን የሚያረጋግጥና የሚተዳደርበት ህግና መመሪያ፣ የሰው ኃይል አደረጃጀት እንዲሁም፣ የማሰራጫ መሳሪያዎችን አስመልክቶ ዩኒቨርሲቲው በአግባቡ የተደራጀ መረጃ ማዘጋጀት አለበት” ብለዋል፡፡

የጣቢያው የቦርድ ሰብሳቢ ሆነው የተመረጡት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ጸሐየ አስመላሽ በሰጡት አስተያየት ጣቢያው ሥራውን ሲጀምር ለአካባቢው እና ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ ሆኖ እንደሚያገለግል ገልጸዋል። “በዋናነት የህብረተሰቡን ፍላጎትና ችግሮች መሰረት ያደረጉ ሥራዎች ይሰራል” ብለዋል።

የማህበረሰብ ሬድዮ ጣቢያው የካባቢውን ባህል፣ ቋንቋ እና እምነት ከማሳደግ ባለፈ በልማት፣ ዴሞክራሲ ግንባታና መልካም አስተዳደርን በማስፈን በኩል የድርሻውን እንደሚወጣም አመልክተዋል፡፡

በተለይ ዩኒቨርሲቲው የሚያከናውናቸው የምርምር እና የማህበረሰባዊ ተኮር ሥራዎችን ለማስፋት ጣቢያው ጠቀሜታ እንዳለው ነው የገለጹት።

የማህበረሰብ ሬድዮ ጣቢያው ከተለያዩ አካባቢዎች ልምድ በመቀመር በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደሥራ ለማስገባት እንደሚሰራም ዶክተር ጸሐዬ አመልክተዋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia