TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#Update የዓለም ኤድስ ቀን የፊታችን ቅዳሜ ህዳር 22 ቀን 2011 ዓ.ም በፌደራል ደረጃ በዱከም እንደሚከበር ተገልጿል። በዓሉ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ31ኛ ጊዜ የሚከበር ሲሆን፥ አሁን ላይ እየታየ ያለውን #መዘናጋት በመስበር በየደረጃው የሚገኘው አመራርና አጠቃላይ ማህበረሰብ ቃሉን እንዲያድስ የሚደረግበት ነው ተብሏል።

©fbc
@tsegabwolse @tikvahethiopia
አፍሪካ ሞዛይክ🔝

አፍሪካ ሞዛይክ ታላቅ የሆነ የፋሽን ድግስ ያዘጋጀ ሲሆን ታላላቅ እንግዶች በሚገኙበት እና በስራቸውም አይን የሚያፈዙ ዲዛይነሮች ስራቸውን በሚያቀርቡበት ቀን እንድትመጡ እንጋብዞታለን!

🔹ትኬቶች በዕለቱ ዕለት በር ላይ የሚሸጡ መሆኑን እንገልፃለን!

ለማንኛውም ጥያቄ፦ 0988 14 22 57

ቦታ፦ አፍሪካ ሞዛይክ ዲዛይን ሴንተር - ለገጣፎ

ቀን-ቅዳሜ ህዳር 22
ትኬት-150 ብር ብቻ
#update መንግሥት አዳዲስ አምባሳደሮችን እና ከፍተኛ ዲፕሎማቶችን ሊሾም ነው፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ መለስ ዐለም ለጋዜጠኞች እንደገለጹት አዲስ የሚሾሙት 59 አምባሳደሮች እና ዲፕሎማቶች ከምሁራንና ታዋቂ ሰዎች ይውጣጣሉ፡፡ መስፈርቱ ሙያ፣ ዕውቀትና ክህሎት ሲሆን በ59ኙ ኢምባሲዎችና 11ዱ ቆንስላዎች ይመደባሉ፡፡ አንጋፋ ዲፕሎማቶችም በጎረቤት ሀገራት ይመደባሉ፡፡ አዲሱ ምደባ መስሪያ ቤቱ እየተገበረው ያለው መዋቅራዊ ማሻሻያ አካል ሲሆን ማሻሻያው የሀገሪቱን ብሄራዊ ጥቅም ያስከብራል፤ ዜጎችም በተቋሙ እንዲኮሩበት ያስችላል፡፡

©wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምስራቅ ወለጋ‼️

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን እና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አዋሳኝ አካባቢ በተፈጠረ ግጭት የሰው #ህይወትና ንብረት ላይ #ጉዳት መድረሱን የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ዴሬሳ ተረፈ ለfbc አንደተናገሩት፥ በግጭቱ የኦሮሚያ ክልል ፖሊስን ጨምሮ የበርካታ የአካባቢው ነዋሪዎች ህይወት አልፏል።

እንዲሁም ለጊዜው ግምቱ ያልታወቀ በርካታ ንብረት መውደሙንም ነው አቶ ዴሬሳ የተናገሩት።

ችግሩ ያጋጠመውም ባሳለፍነው ማክሰኞ ህዳር 18 2011 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን ሊሙ ወረዳ አርቁምቤ በሚባል አካባቢ መሆኑንም ነው የቢሮው ምክትል ኃላፊ ያስታወቁት።

በግጭቱም በአካባቢው ነዋሪዎች እና በኦሮሚያ ፖሊስ አባላት ላይ አሰቃቂ ወንጀል ተፈጽሟል ያሉት አቶ ዴሬሳ፥ በግጭቱ ህይወታቸው ያለፈ እና የተጎዱ ሰዎች ቁጥር በቅርቡ ይፋ ይደረጋልም ብለዋል።

በግጭቱ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች አስክሬን በትናንትናው እለት ነቀምቴ ከተማ ሲገባ ህዝቡ ሰልፍ በመውጣት #ስሜታዊ በመሆኑ የአንድ ሰው #ህይወት ማለፉንም ተናግረዋል።

ምክትል ኃላፊው አቶ ዴሬሳ ተረፈ፥ በምእራብ ኦሮሚያ አዋሳኝ አካባቢዎች ላይ እየተፈጠሩ ያሉ ግጭቶች ዋነኛ ምክንያት የክልሉን እና የሀገሪቱን ሰላም የማይፈልጉ እንዲሁም አሁን በሀገሪቱ እየመጣ ያለውን ለውጥ ለማደናቀፍ የሚሯሯጡ አካላት ናቸው ብለዋል።

የእነዚህ አካላት እቅድም እንደ ኦሮሚያ ክልል እና እንደ ሀገር እየመጣ ያለውን ለውጥ ማደናቀፍ በመሆኑ፤ ህዝቡ ከስሜታዊነት በመውጣት መንግስት ችግሩን በዘላቂነት ለመቅረፍ የሚወስደውን እርምጃ እንዲደግፍ ጥሪ አቅርበዋል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮሮፖሬሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ትኩረት ለቴፒ‼️ትኩረት ለቴፒ‼️ትኩረት ለቴፒ‼️ትኩረት ለቴፒ‼️ትኩረት ለቴፒ‼️ትኩረት ለቴፒ‼️
#Update በመቶ ሚሊየን ብር በባህርዳርና በጎንደር የኣዳሪ ትምህርት ቤቶች ሊገነቡ ነው። ትምህርት ቤቶቹ የሚገነቡት በአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ፣ በክልሉ የዩኒቨርስቲዎች ፎረም ፣ወንፈል በተሰኘ ግብረሰናይ ድርጅትና በአልማ ትብብር ነው።

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከወርቃ ከተማ🔝

"በምህራብ አርሲ ዞን ከዶዶላ ወደ ነንሰቦ ወረዳ ወርቃ ከተማ በሚወሰደው መንገድ ላይ ህዝቡ በመንገድ መበላሸት ምክንያት ጫካ ውስጥ እሰከ ሁለት ቀን ብርድ ላይ እየተንገላታ ነው። በተጨማሪም መኪኖች ጭቃ እያንሸራትታቸው በጣም ከባድ አደጋዎች እየተፈጠሩ ነው። ህዝቡ በሰላም ወቶ በሰላም መግባት ኣልቻለም የሚመለከተው ኣካል ችገራችንን ተመልክቶ መፍቴ እንዲሰጠን እንጠይቃለን!"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኦዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ‼️

የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ በዜጎች ላይ ጉዳት ያደረሱ አካላትን #ለሕግ እንደሚያቀርብ ገለጸ።

ፓርቲው በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት ካደረገ በኋላ ባወጣው መግለጫ ከመረራና እልህ አስጨራሽ ትግል በኋላ የተገኘውን ለውጥ #ለመቀልበስ ስልጣንን ያለአግባብ ተጠቅመው ዘረፋ ሲያካሄዱ የነበሩና አሁን ጥቅሙ የቀረባቸው አካላት በተለያዩ ቦታዎች እሳትን በማቀጣጠልና የሰው ልጆች ላይ መፈፀም የሌለበት ወንጀል እንዲፈጸም፣ ዜጎች እንዲፈናቀሉና የክልላችን ሰላም እንዲናጋ እየሰሩ መሆናቸውን ገልጿል፡፡

የእነዚህ አካላት ሴራ እነሱን በመቅበር የሚጠናቀቅ ይሆናል እንጂ ኦሮሚያን የግጭት ሜዳ ማድረግ አይሳካላቸውም ብሏል ፓርቲው በመግለጫው፡፡

እነዚህ አካላት የተጀመረው የህግ የባላይነትን የማስከበር ስራ እንዲስተጓጎል ሌተ ቀን እየተፍጨረጨሩ ይገኛሉ፡፡

የኦሮሞን የህዝብ ከሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች ጋር እንዲሁም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችን እርስ በእርስ በማጋጨት የጥፋት እጃቸውን እንደዘረጉ መግለጫው ያትታል፡፡

እንደ ፓርቲው መግለጫ፣ እነዚህ አካላት በቅርቡ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልልና የሱማሌ ወሰን አካባቢ የሚኖሩ የኦሮሞ ተወላጆች ላይ #የግድያ_እርምጃ ወስደዋል፣ ሰላማዊ ዜጎችንም አፈናቅለዋል፣ የተቀናጀ ጦርነት በመክፈትም በኦሮሚያ ፖሊስ ላይ ጉዳት አድርሰዋል ይላል መግለጫው፡፡

በዚህ በሰላማዊ ዜጎችና በኦሮሚያ ፖሊስ ላይ ለደረሰው አሰቃቂ ወንጀል ጥልቅ ሀዘን እንደተሰማው የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ በመግለጫው ገልጿል፡፡

ድርጊቱ በሌቦች፣ ዘራፊዎችና በሰው ልጆች ላይ የሰብአዊ መብት ጥሰት የፈጸሙ አካላት ላይ መውሰድ ከጀመርነው ሕጋዊ እርምጃ ወደ ኋላ እንደማይመልስ ተገልጿል፡፡

በህዝባችን ላይ ይህንን ጉዳት ያደረሱ አካላት የገቡበት ጉድጓድ ገብተን ለሕግ እናቀርባቸዋለን፤ እንዲሁም እነዚህ አካላት ያላቸውን ኃይል በድጋሚ በማይጠገን መልኩ ሰብረን እንቀብረዋለን ብሏል የፓርቲ መዕከላዊ ኮሚቴ በመግለጫው፡፡
ማንኛውም የሰበአዊ ጥሰት የፈፀሙ አካላት በሕግ የሚጠየቁ መሆኑን የማዕከላዊ ኮሚቴው መግለጫ ያስረዳል፡፡

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ህዳር 30 የሚዘጉ መንገዶች‼️

በአዲስ አበባ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ለመከላከል ከትራፊክ ፍሰት ነፃ የሆነ ቀን ለማክበር #ሚዘጉት_መንገዶች ይፋ ሆኑ።

ለትራፊክ ዝግ የሚሆኑ ሁለት መንገዶች የተለዩ ሲሆን አንደኛው ከጊዮርጊስ አደባባይ- በቸርችል ጎዳና-ኢትዮ ኩባ ወዳጅነት ፓርክ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ከጊዮርጊስ አደባባይ-በ6ኪሎ-በ5ኪሎ አድርጎ መድረሻውን ጊዮርጊስ አደባባይ ያደርጋል፡፡

የአዲስ አበባ አስተዳደር ጤና ቢሮ ከአዲስ አበባ ስፖርትና ወጣቶች ፌዴሬሽን ጋር በመሆን በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ የጤና ቢሮ ምክትል ሃላፊ ዶክተር ሳሙኤል ዘ/መንፈስ ቅዱስ ፤የስኳር፣ የደም ግፊት እና የጡት ካንሰር #ነጻ የምርመራ አገልግሎትም ይሰጣል ብለዋል፡፡

በእለቱ የህብረተሰቡን የጤና ግንዛቤ ለማሳደግ የተለያዩ የጤና መልእክቶች ይተላለፋሉ፡፡

በአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የስፖርት ውድድርና ተሳትፎ ባለሙያ አቶ እንግዳወርቅ ዳንኤል በበኩላቸው በእለቱ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን የሚመሩ የአካል ብቃት ባለሙያዎችም እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡

የፊታችን ህዳር 30 በሚካሄደው ከትራፊክ ፍሰት ነጻ ቀን የመንግስት የስራ ሃላፊዎችና ዲፕሎማቶች የሚሳተፉበት ሲሆን፤ በዕለቱ ከ3ሺ እስከ 5ሺ ሰዎች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

🔹ፕሮግራሙ ከጠዋቱ 1 ሰዓት እስከ 6 ሰዓት የሚካሄድ መሆኑም ታውቋል፡፡

ምንጭ፦ አርትስ ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የአፍሪካ ዋነኛ መግቢያ በርነትን ሚና ከዱባይ አየር መንገድ ተረከበ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት አየር መንገዶች ጋር ድርሻ ወስዶ መስራቱ ደግሞ የተጓዦችን ቁጥር 40 በመቶ አሳድጎታል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ሕይወት #አጭር ናት። ሀብትና ንብረት ይዘን አንቀበርም። ባዶ ኪሳችንን ነው የመጣነው ባዶ ኪሳችንን ነው የምንሞትው። ስትቀበሪ ሳንቲም ሬሳ ሳጥንሽ ውስጥ የሚያጭቅልሽ አይኖርም። ባዶ ገላን ይዘን ነው የመጣነው ባዶ ገላችንን እንለመሳለን።" አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ

@tsegabwolde @tikvahethiopia