TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
ALERT‼️በጎንደር ዩኒቨርሲቲ እየሆነ ያለውን ጉዳይ የሚመለከተው አካል #ትኩረት እንዲሰጠው።

@tsegabwolde @tikvahethiopua
ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ‼️

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወይዘሪት #ብርቱካን_ሚደቅሳን የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ አድርጎ ሾመ። ምክር ቤቱ በዛሬው እለት ባካሄደው 7ኛ መደበኛ ስብሰባው ነው የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እጩ ሰብሳቢ ለመምረጥ የቀረበ የውሳኔ ሃሳብን መርምሮ ያፀደቀው።ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድም ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳን ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እጩ ሰብሳቢነት አቅርበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ እጩ ባቀረቡበት ወቅትም፥ የሀገሪቱን የምርጫ ሂደት ለማሻሻል የተገባውን ቃል ለማጠናክር እና ለ2012 ዓ.ም ምርጫ ዝግጅት ገለልተኛ የምርጫ ቦርድን ለማጠናከር ያለውን የፓለቲካ ቁርጠኝነት ምስክር ነው ብለዋል። በዚህም ምክር ቤቱ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እጩ ሰብሳቢነት የቀረቡትን ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ላይ አስተያየት ከሰጠ በኋላ የቦርዱ ሰብሳቢ አድርጓል።

ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ከብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳነትን በራሳቸው ፈቃድ የለቀቁትን ወይዘሮ ሳሚያ ዘካርያን የሚተኩ ይሆናል።

ምንጭ: FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ🔝

ዛሬ ጥዋት በጎንደር ዩኒቨርሲቲ(ማራኪ ካምፓስ) ተማሪዎች ሰልፍ አድርገው የነበር ሲሆን ሰልፉ ግቢውን ውጥረት ውስጥ ከቶት መጠነኛ አለመረጋጋት ተፈጥሮ ነበር። ተማሪዎች #ድንጋይ ሲወራወሩም እንደነበር የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ገልፀዋል። አሁን ላይ ዩኒቨርሲቲው የተአጋጋ ሲሆን ተማሪው ሰላማዊ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል። ተማሪዎች የካፌ አገልግሎት እየተጠቀሙ ናቸው።
.
.
TIKVAH-ETH ለሁሉም እንዲህ ይላል፦

ሰላም ዋጋዋ ትልቅ ነው!! አስተውሉ!! አስተውሉ!! ምንም ነገር ከሰላም አይበልጥም። በኃላ ደም እንባ ብናለቅስ ሰላምን መልሰን አናገኝም!!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#የግጭት ትርፉ፦

🔹ለቅሶ
🔹ስቃይ
🔹መከራ
🔹ረሀብ
🔹ስደት
🔹ሞት
🔹የሚወዱትን ማጣት
🔹ችጋር
🔹በሽታ
🔹እልቂት

ማስተዋል የሚችል ያስተውል!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጎነደር ዩኒቨርሲቲ🔝

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ የተፈጠረውን ችግር #ለመፍታት የሀይማኖት አባቶች ተማሪዎችን አነጋግረዋል። የፀጥታ አስከባሪዎችም በግቢ ውስጥ በመዘዋወር ተማሪውን ለማረጋጋት እና ግቢውን ሙሉ ወደሙሉ ወደቀደመው እንቅስቃሴ ለመመለስ እየሰሩ ነው።

©Nathy
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከሞት የተነሳው ኢትዮጵያዊ🔝

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን ሲቡ ስሬ ወረዳ አንድ ግለሰብ ህይወቱ ካለፈ በኋላ መነሳቱ ተገለፀ። ሟች አቶ #ሂርጳ_ነገሮ ለረጅም ጊዜ በፅኑ ህመም ሲሰቃይ ቆይቶ ባለፈው ማክሰኞ ማለትም ህዳር 11 ቀን 2011 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:30 ገደማ ህመሙ ፀንቶበት ህይወቱ ያልፋል። በአካባቢው ባህል መሰረትም ሳይገነዝ ለ1 ሰዓት አከባቢ ከቆየ በኋላ አስከሬኑ ተገንዞ ወደ ተዘጋጀለት ሳጥን ይገባል። የቀብር ስነ ስርዓቱን ለመፈፀምም ቤተሰቦቹ ሩቅ ላሉ ወዳጅ ዘመዶቻቸው መልዕክት ይልካሉ።

በመቀጠልም ወዳጅ ዘመዶቹ ቦታው እስኪደርሱ ቤተሰቦቹ የተለያዩ የሀዘን ስነ ስርዓቶችን እያከናወኑ ቆይታ አድርገዋል። ሥርዓቱ እየተከናወነ አስከሬኑ ሳጥን ውስጥ ገብቶ በግምት ከ5 ሰዓት በላይ ከቆየ በኃላ ግን አንድ አስደንጋጭ ነገር ተፈጠረ።ግብዓተ መሬቱ ሊፈፀም ስዓታት የቀሩት ሟች ከአስከሬን ሳጥኑ ወስጥ ድምፅ ማሰማት መጀመሩ ተነግሯል፡፡

ምንጭ: ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት
@tsegabwolde @tikvahethiopia