#update ትግራይ ክልል⬆️
በአገራችን የትግራይ ክልል በ750 ሚሊዮን ይሮ ካፒታል የተጀመረውን የቱርክ ኢንዱስትሪ ዞን ግንባታ ሂደት ለማፋጠን በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ።
የኢንዱስትሪ ዞኑን ለመገንባት ስምምነት የፈጸመው የቱርክ ኩባንያ (Turkish Industry Holding) ሊቀመንበር መህመት ኮስኩን በቱርክ አንካራ ክቡር የኢ.ፌ.ዲ.ሪ አምባሳደር ግርማ ተመስገን ጋር ተገናኝተው በተወያዩበት ወቅት እንደገለጹት ኩባንያቸው የግንባታ ሂደቱን ለመጀመር ዝግጅት ማጠናቀቁን ገልጸዋል።
ግንባታው በመጪው መጋቢት ወር ይጀመራል ያሉት ሊቀመንበሩ የኢንዱስትሪ ፓርኩ በሁለት አመታት ጊዜ ውስጥ ግንባታው ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ስራ እንደሚጀምር ገልጸዋል፡፡
ምንጭ፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia

አብዲ ኢሌ🔝 የቀድሞው የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ #አብዲ_ሞሀመድ_ዑመር (አብዲ ኢሌ) ከማረሚያ ቤት ሆነው ምን አሉ? ትላንት የጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዝዳንት ወ/ሮ #መአዛ_አሸናፊ አቶ አብዲ ሞሀመድ ዑመር ያሉበት፣ በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ማዕከል ተገኝተው አያያዞት እንዴት ነው? ሲሉ ጠይቀዋቸዋል፡፡ ሳትነግሩኝ መጣችሁ … አያያዜም በጣም ጥሩ ነው ህግ ያለበት
ነው ያለነው ብለዋል፡፡
ምንጭ፦ ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ነው ያለነው ብለዋል፡፡
ምንጭ፦ ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጄነራሉ ተይዘው አዲስ አበባ መጥተዋል‼️
በዛሬው እለት በቁጥጠር ስር የዋሉት የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር ሜጄር ጀነራል #ክንፈ_ዳኘው አዲስ አበባ ገብተዋል።
የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ #እንዳረጋገጠው ተጠርጣሪው በሁመራ በኩል ከሀገር ለመውጣት ሲሞክሩ በትግራይ ክልል ልዩ ሀይል ነው በቁጥጥር ስር የዋሉት።
ግለሰቡ በአሁኑ ወቅት አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ #ደርሰዋል።
በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ ሌሎች የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ሰራተኞች በቁጥጥር ስር ውለው ትናንት ፍርድ ቤት መቅረባቸው ይታወቃል።
በእነዚህ ተጠርጣሪዎች ላይም ፍርድ ቤቱ የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ መስጠቱም የሚታወቅ ነው።
ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቪድዮ-አዲስ አበባ⬆️
የቀድሞው የሜቴክ ዋና ዳይሬክተር ብርጋዴር ጀነራል #ክንፈ_ዳኛው በቁጥጥር ስር ውለው አዲስ አበባ ሲገቡ።
ምንጭ፦ fbc

ማረሚያ ገብተዋል‼️በቁጥጥር ስር የዋሉት ሜጀር ጀነራል #ክንፈ_ዳኘው አዲስ አበባ ገብተው ወደ ማረሚያ ቤት አቅንተዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አቶ #ጌታቸው_አሰፋ ተይዘዋል ተብሎ በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨው መረጃ ከእውነት የራቀ ነው። የቀድሞ የደህንነት ሀላፊ እስካሁኗ ሰዓት ድረስ በፖሊስ ቁጥጥር ስር አልዋሉም።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update 20ኛው የአፍሪካ ህብረት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰብ ነገ ይጀምራል። ምክር ቤቱ በመሪዎች ስብሰባ ወቅት ውሳኔ በሚተላለፍባቸው ረቂቅ አጀንዳዎች ላይ ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል። በስብሰባው ለመሳተፍ የበርካታ የአፍሪካ አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አዲስ አበባ ገብተዋል።
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Update አዲስ አበባ ከተለያዩ አካባቢዎች ታፍሰው የተወሰዱና በእስር ላይ ያሉ ወጣቶች ፍርድ ቤት አልቀረብንም ሲሉ ለጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዝዳንቷ #ቅሬታቸውን አሰሙ፡፡
ምንጭ፦ ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ፦ ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኤርትራ ማዕቀቡ ሊነሳላት ነው‼️
የመንግስታቱ ድርጅት የኤርትራን #ማዕቀብ በነገው ዕለት #ሊያነሳ ነው። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በኤርትራ ላይ ላለፉት 10 ዓመታት ጥሎት የነበረውን ማዕቀብ ለማንሳት ውሳኔዎች እንደሚያስተላልፍ ተገልጿል፡፡
ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር ያደረገችውን የሰላም ስምምነት እንዲሁም ከጅቡቲ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማሻሻል ያደረገችውን ጥረት ከግምት ውስጥ በማስገባት ነው ማዕቀቡን ለማንሳት የፀጥታው ምክር ቤት አባላት ተደራድረው የጨረሱት፡፡
ሮይተርስ የድርጅቱን ዲፕሎማቶች ጠቅሶ እንደዘገበው ማዕቀቡን ለማንሳት በእንድሊዝ የቀረበውን ረቂቅ 15 የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ አባላትያለልዩነት እንደሚቀበሉት ይጠበቃል፡፡
ኤርትራ የሶማሊያውን አልሸባብ ለሚባለው ቡድን እገዛ ታደርጋለች በሚል እንደአውሮፓዊያኑ አቆጣተር በ2009 አ.ም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ማዕቀቡን እንደጣለባት ይታወሳል፡፡
ምንጭ፦ ሮይተርስ

ኦነግ‼️
የኢትዮጵያ መንግስት እና የኦነግ አመራሮች ያደረጉትን #ስምምነት መሰረት በማድረግ ወደ ሃገር ገብተው ስልጠና ሲወስዱ የነበሩ 1 ሺ154
የኦነግ ጦር አባላት እንደ #የፍላጎታቸው ወደ ስራ ሊሰማሩ ነው።
የኦሮሚያ ፀጥታና አስተዳደር ቢሮ እንዳሳወቀው፤ ስልጠና ሲወስዱ ከነበሩት የኦነግ ጦር አባላት ውስጥ 700ዎቹ በራሳቸው ፍላጎት የኦሮሚያን ፖሊስ እንቀላቀላለን በማለታቸው ግንዛቤ እንዲያገኙ የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሌጅ እንዲገቡ ተድርገዋል።
የአጭር ጊዜ ስልጠና በመውሰድም የኦሮሚያን ፖሊስ የሚቀላቀሉ ይሆናል። የቀሩትም እንደየፍላጎታቸው በግል ስራ፣ በመንግስት ስራ እና የኦነግ ፖለቲካ አባል በመሆን ወደ ስራ ይገባሉ ተብሏል።
ምንጭ፦ አርትስ ቴሌቪዥን

እናት ነበረች ልጇን የገደለችው-ደሴ‼️
‹‹ፖሊስን #በማድከሜ እና ህዝቡን #በተሳሳተ መረጃ በማስቆጣቴም ተጸጽቻለሁ፡፡›› እናት
.
.
.
ባለፈው ሳምንት ደቡብ ወሎ ዞን ደሴ ከተማ ላይ አንድ ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት መፈጸሙን ተዘግቦ ነበር፡፡ ድርጊቱም አንዲት የ7 ዓመት ህጻን #ከተደፈረች በኋላ እንደተገደለች የሚገልጽ ነበር፡፡
በዕለቱም ተጠርጣሪዉ በፖሊስ መያዛቸውን እና ድርጊቱም ነዋሪዎችን ማስቆጣቱን ነበር የተዘገበው፡፡
አሁን ከፖሊስ ያገኘነው መረጃ ደግሞ ጥርጣሬው ወደ ሌላ አካል እንዳመራ ያስረዳል፡፡ ጉዳዩን ለማጣራትም የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት የደሴ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ደረጃ አሰፋን አነጋግሯል፦ ኮማንደሩም መረጃው ትክክል መሆኑን ነው ያረጋገጡት፡፡ ድርጊቱ የተፈጸመው ጥቅምት 24/2011 ዓ.ም ነበር፡፡ ቦታውም ደሴ ከተማ ነው፡፡ በዕለቱም ወላጅ እናት ‹‹ልጄ ጠፋችብኝ›› ብለው ለፖሊስ መረጃ ይሰጣሉ፡፡ ፖሊስም የምርመራ መጀመሪያውን እናት በሚሰጡት #ጥቆማ ላይ ያደርጋል፡፡የእናት ጥቆማ ደግሞ የቀድሞ የትዳር አጋራቸው ላይ ያርፋል፡፡ ምክንያታቸው ደግሞ ከዚህ በፊት በህጻኗ ላይ ይዝቱ ነበር የሚል ነው፡፡
ፖሊስም ጥቆማውን ተቀብሎ ምርመራውን ይቀጥላል፡፡ ከዚህ ላይ አሳዛኝ ድርጊት ተፈጽሞ ይገኛል፡፡ህጻኗ ተገድላ እና ተጥላ ነበር ፖሊስ ያገኛት፡፡ ፖሊስም ለምርመራ አስከሬኑን ወደ ደሴ እና ጥቁር አንበሳ ሪፈራል ሆስፒታል ይልካል፡፡
በዕለቱ ደግሞ ተጠርጣሪው በግምት ከምሽቱ 3፡00 አካባቢ በቁጥጥር ሰር ይውላል፡፡ ፖሊስም ምርመራውን ይቀጥላል፡፡ እየተገኙ የነበሩ ቁሳቁሶችና መረጃዎች ግን ፖሊስ ምርመራውን በእናት ላይም ማድረግ እንዳለበት ፍንጭ የሚሰጡ ነበሩ፡፡ በሂደትም ምርመራውን በእናት ላይ ይጀምራል፡፡ የፖሊስን ጥርጣሬ የሚያጎላ መረጃም ያገኛል፡፡አሁን የመጀመሪያው ጥርጣሬ ሚዛን ወደ ሌላ አቅጣጫ ይዞራል፤ እናት የሰጡት የእምነት ክህደት ቃል ሌላ ገጽታ ነበረውና፡፡
እናት ይነገራሉ ‹‹ልጄን #የገደልኳት እኔ ነኝ፤ ድርጊቱን የፈጸምኩት ግን ልጄን ለመቅጣት እንጂ ለመግደል አስቤ አልነበረም፤ እስካሁን ፖሊስን በማድከሜ እና ህዝቡን በተሳሳተ መረጃ በማስቆጣቴም ተጸጽቻለሁ›› ነበር ያሉት
ይላል የፖሊስ መረጃ፡፡
እናት በሰጡት ቃል እንደተመላከተው ለልጃቸው ልብስ ከገዙላት በኋላ ‹‹ለምን ጫማ አልተገዛልኝም?›› በሚል ጭቅጭቅ ይፈጠራል፡፡ መግባባትም አልቻሉም ነበር፡፡ በዚህም እናት በልጃቸው ላይ አካላዊ ቅጣት ይፈጽማሉ፤ በድንገትም ህጻኗ እስከወዲያኛው ታሸልባለች፡፡
በድረጊቱ የተደናገጡት እናት የልጃቸውን አስክሬን ከአካባቢው ሰውረው ነበር ለፖሊስ ጥቆማውን ያቀረቡት፡፡ እናት ቃላቸውን ለደሴ ከተማ አስተዳደር ፍርድ ቤትም ሰጥተዋል፡፡ ተጠርጣሪዋም ለጊዜው በደሴ ማረሚያ ቤት እንዲቆዩ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡
ፖሊስ ግን ለተጨማሪ ምርመራ 14 ቀናት ጠይቋል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ከሆስፒታሉ የአስክሬን ምርመራ ውጤቱን እስከሚያገኝ እና መጀመሪያ ተጠርጥረው በተያዙት ሁለተኛ ተከሳሽ ላይም ተጨማሪ ምርመራ ማድረግ ስለፈለገ ነው ብለዋል ኮማንደር ደረጀ አሰፋ፡፡ የፍርድ ቤቱ ውሳኔ ግን ወደ ፊት የሚገለጽ ይሆናል፡፡
ምንጭ፦ አብመድ (አስማማው በቀለ)

#Update አምነስቲ ኢንተርናሽናል #የሳን_ሱኪን ሽልማት መንጠቁ ተሰማ። የማይናማሯ መሪ አውንግ ሳንሱኪ በሮሂንጊያ ሙስሊሞች ላይ የዘር ጭፍጨፋ ሲፈፀም ዝምታን መምረጣቸው ነው በፈረንጆቹ 2009 የሞራል አምባሳደር ተብለው የተሰጣቸውን ሽልማት ያስነጠቃቸው፡፡
©Arts TV
@tsegabwolde @tikvahethiopia
©Arts TV
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update መቀለ⬇️
የመቀለ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ ኢንጅነር #አርአያ_ግርማይ ምክትል ከንቲባ አድርጎ ሸመ።
ተሿሚው ቀደም ሲል የከተማው አስተዳደር ከንቲባ የነበሩት ወደ ሌላ የስራ ኃላፊትን በመሄዳቸው እሳቸው ተክተው እንደሚሰሩ ተገልጿል፡፡
ምክር ቤቱ ትናንት ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ ኢንጂነር አርአያ ግርማይ የከንቲባ ስራና ኃላፊነት እንዲሰሩ በሙሉ ድምጽ መርጧቸዋል፡፡
ኢንጅነሩ ካላቸው የትምህርት ዝግጅት ሌላ ለረጅም ዓመታት የሱር ኮንስትራክሽን ኃለፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የፕሮጀክት አስኪያጅና የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆኖው አገልግለዋል፡፡
ኢንጅነር አርአያ ግርማይ በበኩላቸው “በእኔ ላይ እምነት የጣለው የከተማው ምክር ቤትና ህዝብ በሙሉ ልብ ሌትና ቀን ለማገልገል ዝግጁ ነኝ” ብለዋል፡፡
አንድ ሰው ብቻውን የከተማውን ልማት መቀየር እንደማይቻል ያመለከቱት ኢንጅነሩ በየደረጃው የሚገኝ የህብረተሰብ ክፍል የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የከተማው አስተዳደር ለዓመታት መፍትሄ ሳያገኝ የቆየውን የመብራትና ውሃ ችግር ለመፍታት በትኩረት እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡
በመቀሌ ዩኒቨርስቲ የሲቪል ኢንጅነሪንግ ተማሪ ሃይለየሱስ ግርማይ በሰጠው አስተያየት ተሿሚውን በቅርበት እንደሚያውቃቸው ገልጾ ” በአመራር፣ በሙያ ብቃት ያላቸው በመሆኑ መሾማቸው ለከተማው እድገት መፋጠን ትልቅ ሚና ይኖራቸዋል” ብለዋል፡፡
የከተማው ነዋሪ አቶ ፍትዊ ባህታ በበኩላቸው ኢንጅነር አርአያ ግርማይ መመረጥ በከተማው ምላሽ ያላገኙ የመልካም አስተዳደርና የልማት ጥያቄዎች ምላሽ ያገኛሉ ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል፡፡
ምንጭ፦ ኢዜአ