የኢትዮጵያ ፕሬዘዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ‼️
በአዲስ አበባ ከተማ በ1943 ዓ.ም. የተወለዱትና በሊሴ ገብረ ማርያም ትምህርት ቤት ትምህርታቸውን የተከታተሉት አዲሷ ፕሬዚዳንት፣ ከፍተኛ ትምህርታቸውን በፈረንሣይ አገር ሞንትፔልየ ዩኒቨርሲቲ ተከታትለዋል፡፡
በፈረንሣይም የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር በመሆን ሲያገለግሉ፣ በተለያዩ የአፍሪካ አገሮች ኢጋድን ጨምሮ የኢትዮጵያ #አምባሳደር ሆነው አገልግለዋል፡፡
እ.ኤ.አ. በ2011 በቀድሞው የተመድ ዋና ጸሐፊ ባን ኪ ሙን በምክትል ዋና ጸሐፊነት ደረጃ የመንግሥታቱ ድርጅት የናይሮቢ ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ተደርገው መሾማቸው ሲታወስ፣ ኢትዮጵያን በመወከል በተለያዩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች አገልግለዋል፡፡
ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ የሁለት ወንዶች እናት መሆናቸውን ከገጸ ታሪካቸው ለማወቅ ተችላል፡፡
@tsegabwolde @tikvahethiopia

#update ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ⬆️
የጋምቤላ ህዝቦች ክልላዊ መንግስትን በመምራት ላይ ሚገኘው የጋምቤላ ህዝቦች አንድነት ዲሞክራሲዊ ንቅናቄ የማዕከላዊ ኮሚቴ ከአንድ ሳምንት በፊት በአዲስ አበባ የጀመረው #ግምገማ ቀጥሎ እየተካሄደ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍጹም አረጋ
ገልጸዋል፡፡
በግምገማው ላይ የተገኙት ክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የክልሉ ህዝብ ልማት የተጠማ በመሆኑ አዲሱ አመራር ጊዜውን በግል አጀንዳዎችና #ሽኩቻ ከማጥፋ ይልቅ ራሱን ከጎሰኝነትና ከጥላቻ በማጽዳት የክልሉን አመራር በማጠናከር የህዝቡን ችግር ሊፈታ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
ክልሉ በርካታ ሙያተኞች በየዩኒቨርሲቲው፣ በፌዴራል፣ በክልሉም ሆነ በዳያስፖራ የሚገኙ በመሆኑ እነዚህን በማፈላለግ በየደረጃው ክልሉን ለማጠናከር #ቅድሚያ ሰጥቶ ሊንቀሳቀስ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
ከኃላፊነት የተነሱት አመራሮችም በድርጊታቸው ተጸጽተው ይቅርታ መጠየቃቸው እና ህዝቡን ለመካስ በተመደቡበት የስራ መስክ ለመሰማራት መወሰናቸው መልካም መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
የፓርቲው ሊቀመንበር እና የክልሉ መንግስት ፕሬዚዳንት የሆኑነት አቶ ጋትሉዋክ ቱት እና ምክትላቸው አቶ ሰናይ አኩዎር ኃላፊነታቸው #መልቀቃቸውና ፓርቲው አቶ ኦሙድ ኡጁሉን የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ አኙአያ ጃከን ደግሞ ምክትል ሊቀመንበር አድርጎ ትናንት #መምረጡ ይታወቃል፡፡
ምንጭ፦ የጠ/ሚ ፅ/ቤት

#update ነጭ ሳር ብሄራዊ ፓርክ⬇️
በደቡብ ክልል ጋሞ ጎፋ ዞን ባለው የነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክ ማንነታቸው ያልታወቀ #ታጣቂዎች ትላንት ባደረሱት ጥቃት አራት ሰዎች #መገደላቸውን የዞን የጸጥታ እና አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ አቶ ለማ ቦሎ ለDW አስታወቁ።
አራቱ ግለሰቦች የተገደሉት በጥይት ተደብድበው ነው ተብሏል። ሟቾቹ እንጨት ለቅመው እና ሳር አጭደው የሚተዳደሩ እንደነበሩ የገለጹት ኃላፊው ከዚያ በተጨማሪ የደረሰ ጉዳት መኖር አለመኖሩ በእርግጠኝነት መናገር እንደሚቸገሩ ተናግረዋል። #ግድያውን የፈጸሙት ታጣቂዎች ማንነት በግልጽ እንደማይታወቅ ነገር ግን ከዚህ ቀደም በአካባቢው እንደሚንቀሳቀሱ ዞኑ መረጃ እንደነበረው ኃላፊው አስረድተዋል። አስራ ስድስት አባላት ያለበት አንድ የተደራጀ ቡድን እና አምስት አባላት ያሉት ሌላ የታጠቀ ቡድን በፓርኩ ውስጥ እንደሚዘዋወሩ መረጃው አለን ብለዋል። ከጉጂ አቅጣጫ የመጡ ናቸው የሚባሉትን እነዚህን ታጣቂዎች ለመያዝ የጸጥታ ኃይሎች ወደ ስፍራው ሲያመሩ እንደሚሰወሩም ገልጸዋል።
ምንጭ፦ DW አማርኛው አገልግሎት

#update የሀገር ስጋት⬇️
ሕገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር በአገር ደረጃ #ስጋት ሆኗል ተባለ፡፡ ከተለያዩ አገራት በድንበር በኩል የሚገባውን ሕገ-ወጥ የጦር መሳሪያ አስመልክቶ ጠንከር ያለ ሕጋዊ አሰራር ሊኖር እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ተናግሯል፡፡
በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የኢንዶክትሪኔሽንና ሕዝብ ግንኙነት ምክትል ዳይሬክተር የሆኑት ኮማንደር ፋሲካ ፋንታ በከተማዋ በስፋት እየተስተዋለ ያለውን ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር ለመግታት ጠንካራ የቁጥጥር ህግ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
412 ሽጉጦችን፣ ከ12 ሺ በላይ የሽጉጥ ጥይቶችንና ከ9 ሺ በላይ የክላሽ ጥይቶችን በህገወጥ መንገድ ሲያዘዋውሩ የተገኙ 5 ተጠርጣሪዎችን ፍ/ቤት በዋስ መልቀቁ ጥብቅ የሆነ አሰራር ላለመኖሩ ማሳያ መሆኑን ኮማንደር ፋሲካ ተናግረዋል፡፡
ከህገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር በተጨማሪ በጦር መሳሪያ የታገዘ ዘረፋና ቤት ሰብሮ ስርቆት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአዲስ አበባ እየተበራከተ መጥቷል ብለዋል፡፡
እነዚህን የወንጀል ድርጊቶች ለመከላከል የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በጥናት የተደገፈ የክትትልና የምርመራ ቡድን ማዋቀሩን ኮማንደር ፋሲካ ተናግረዋል፡፡
ኮሚሽኑ ህብረተሰቡን ከፍተኛ ጉዳት ላይ የሚጥሉና የአገርን ኢኮኖሚ የሚጎዱ የወንጀል ድርጊቶች ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ መሆኑን ተነግሯል፡፡
ነዋሪውም የከተማውን ፀጥታ አስተማማኝ ለማድረግ ለፀጥታ አካላት #ድጋፉን አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ተብሏል፡፡
ምንጭ፦ ሸገር 102.1

ልዩ የበርገር 🍔 ሽያጭ ፕሮግራም
ቦሌ ኤድና ሞል በሚገኘው ቺክን ሀት በርገር! እርስዎ የሚገዙት አንድ በርገር ለሀያት ጤንነት አስተዋፅዖ አለው!
ቅዳሜ ከቀኑ 6፡00 ጀምሮ እስከ 12፡00 ድረስ በሚቆየውና ዝነኛ አርቲስቶች በሚያስተናግዱበት በዚህ ፕሮግራም ላይ እንሣተፍ ዘንድ ሁላችንም ተጋብዘናል
(ሼር ) ማድረግ የሰከንዶች ስራ ቢሆንም ለሀያት ግን የመዳኗ ሰበብ ሊሆን ይችላልና ሼር ይድርጉ!

#update የደብረማርቆስ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ #ጉዳት በመድረሱ ደብረ ማርቆስ ፣ፍኖተ ሰላምና ብቸና ከትናንት ጀምሮ ኃይል ተቋርጧል፡፡
ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአዲስ አበባ ከተማ በሶስት ቡድን #ተደራጅተው ከባድ ወንጀሎችን ሲፈጽሙ የነበሩ 17 #ተጠርጣሪዎች ከነመሳርያቸው በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በመግለጫ አሳውቋል፡፡
ምንጭ፦ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮኒሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ፦ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮኒሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሳዛኝ ዜና‼️
ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለዶክትሬት ማጠናቀቂያ ጥናታቸው ወደ ምዕራብ ጎጃም ዞን ጎንጅ ቆለላ ወረዳ ወደ አዲስ አለም ከተማ ተጉዘው የነበሩ ግለሰቦች ላይ በተፈፀመ ጥቃት ሁለቱ #ሲገደሉ አንዱ መቁሰሉን የዞኑ የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ።
አጥኒዎቹ በከተማው ባለው አንድ ትምሕርት ቤት ውስጥ ለምርምር የሚሆን የሽንትና የዐይነ ምድር ናሙና እየሰበሰቡ ባሉበት ወቅት፤ “ሦስት ተማሪዎች ሞቱ” የሚል ወሬ በመሰራጨቱ ተቆጥተው በመጡ የአካባቢው ወጣቶች በደረሰባቸው #ከፍተኛ ጥቃት ሕይወታቸው ማለፉን የምዕራብ ጎጃም ዞን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ #አንማው_ዳኛቸው ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።
በተጨማሪም ለቤተ ክርስቲያን ህንፃ ግንባታ ግልጋሎት የሚውል ሲሚንቶ በራሳቸው መኪና ጭነው ወደ አካባቢው ተጉዘው የነበሩ ጥንዶች ንብረትም መቃጠሉ ታውቋል። በዚህ ድርጊት #ተሳትፈዋል በሚል የተጠረጠሩም 30 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን
ተናግርዋል።
በተፈፀመው ድርጊት የአካባቢው ማኅበረሰብም ሆነ መንግሥት ማዘኑን አቶ አንማው ገልፀው በድርጊቱ ተሳትፈዋል የተባሉትን #ማሰር መቀጠሉን ጠቁመዋል።
ምንጭ፦ የአሜሪካ ድምፅ ራድዮ