TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.9K photos
1.52K videos
215 files
4.17K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#update አትሌት #ፈይሳ_ሌሊሳ ነገ ጥዋት 2:00 ወደ እናት ሀገሩ ይገባል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አቶ #ጌታቸው_ኣሰፋ የትግራይ ክልል ር/መስተዳደር የጸጥታ እና የደህንነት #አማካሪ ሆነው ተሹመዋል።

ምንጭ፦ Getu Temesegen
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አትሌት #ፈይሳ_ሌሊሳ ከ30 ደቂቃ በኋላ ኢትዮጵያ- አዲስ አበባ ይገባል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሐረር⬆️ሐረር ከተማ ላለፉት ስድስት ወራት #ውሃ ተጠምታለች፣ በቆሻሻም ታፍናለች - የዚህ ምክንያቱ በአጎራባች አካባቢዎች ያሉ ወጣቶች በ5 ቀን ውስጥ 10 ሚሊየን ብር እንዲከፈላቸው በመጠየቅ የውሃ መስመሩን በመስበራቸውና ቆሻሻም አናስደፋም በማለታቸው ነው። እስካሁን ድረስ ከምሰራቅ ኦሮሚያ የሥራ ሃላፊዎች፣ አባገዳዎች፣ የሐይማኖት አባቶች እና ቄሮዎች ጋር ምክክር ቢደረግም መፍትሄ አልተገኘም። ወጣቶቹ ከውሃ ማጣሪያ ጣቢያ ሰራተኛው ቁልፉን #ነጥቀው ወስደዋል፣ ሞተሮቹን አጥፍተዋል፣ የውሃ መስመሩንም ሰብረው ውሃው በከንቱ እየፈሰሰ ነው፡፡

ምንጭ፦ ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በሰለም ገብቷል⬆️አትሌት #ፈይሳ_ሌሊሳ ወደ ኢትዮጵያ በሰላም ገብቷል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አትሌት #ፈይሳ_ሌሊሳ አዲስ አበባ ገብቷል!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ⬆️አትሌት #ፈይሳ_ሌሊሳ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ ከፍተ ኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ አትሌቶች እና ታዋቂ ሰዎች አቀባበል አድርገውለታል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሳዛኝ ዜና‼️አንጋፋው የኦሮሚኛ መሰንቆ ተጫዋች ጋሽ ለገሰ አብዲ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጅንካ⬇️

የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን በ60 ሚሊየን ብር ወጪ በጅንካ ከተማ ያስገነባው የከረጢት ፋብሪካ የምርት ስራው #ቆሟል

5 የኦሞ ኩራዝ ስኳር ፕሮጀክቶች በደቡብ ኦሞ ዞን መገንባታቸውን ተከትሎ በጂንካ ከተማ በ18 ነጥብ 2 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው የከረጢት ፋብሪካው "ኮርፖሬት ኒው ቢዝነስ ዴቨሎፕመንት” በተሰኘ ተቋም ግንባታው ተጠናቆ የሙከራ ምርት ማምረት ችሎ ነበር።

ሆኖም ፋብሪካውን የሚያስተዳድረው የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን አምርቶ መሸጥ ለሚችል 3ኛ ወገን ሳያስተላልፍ በመቆየቱና ለሙከራ የቀረበው ግብዓትም በማለቁ አሁን ፋብሪካው ምርት ማቆሙን fbc በስፍራው ባደረገው ቅኝት #አረጋግጧል

የጅንካ ከረጢት ፋብሪካ በሙከራ ወቅት ከ400 ሺህ በላይ ከረጢት ያመረተ ሲሆን፥ ፍብሪካው ለሚመለከተው አካል አለመተላለፉን ተከትሎ የገበያ ትስስር ሊፈጠርለት አልቻለም።

ከዚህ ባሻገርም ፋብሪካው በራሱ በብረታ ብረት እና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የውስጥ ስምምነት መሰረት 130 ሰራተኞችን ቀጥሮ እንዲንቀሳቀስ ሲያደርግ ቢቆይም፤ በተጠቀሱት ምክንያቶች ስራ እንዲያቆም ሲደረግ 89 ሰራተኞች ከስራ እንዲሰናበቱ መደረጉ እና በበረሃ አበል ክፍያ ላይ ችግሮች መኖራቸው ቅሬታ እንዲፈጠር አድርጓል።

የጅንካ ከረጢት ፋብሪካ ዋና ስራ አስኪያጅ ሺህ አለቃ ቀረብህ ህብስቱ እንደተናገሩት፤ ፋብሪካውን ተረክቦ ምርት እያመረተ መሸጥ ለሚችል አካል ለማስተላለፍ እና የሙከራ ምርቶቹንም ለመሸጥ የጨረታ ማስታወቂያ ወጥቶ ክትትል እየተደረገ ነው።

የፋብሪካው የሰው ሃይል አስተዳደር አና ልማት ሃላፊው ሺህ አለቃ ማጆር ተሰማ በበኩላቸው ከስራ ገበታቸው የተሰናበቱ ሰራተኞች ፍብሪካው እስኪተላለፍ ድረስም ቢሆን እንዲመለሱ እና የክፍያ ቅሬታቸውም ውይይት እንዲደረግበት መወሰኑን ገልፀዋል።

የጅንካ ከረጢት ፋብሪካ በሙሉ አቅሙ መስራት ሲጀምር በአመት 30 ሚሊየን ከረጢት የማምረት አቅም ያለው ሲሆን በሙከራ ወቅት በቀን ከ1 መቶ ሺህ በላይ ከረጢት የማምረት ብቃት እንዳለው ተረጋግጧል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ከ300 ሚሊዮን ብር በላይ አሴት (ካፒታል) ያስመዘገቡ ባለሀብቶች በደብረ ማርቆስ ኢንዱስትሪ ፓርክ #ሊሰማሩ ነው፡፡ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን #ደብረ_ማርቆስ ቅርንጫፍ ጽ.ቤት ለ12 ባለሀብቶች ቦታ፣ ካርታና የቦታ ፕላን ማዘጋጀቱን አስታውቋል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
ኢንጂነር አይሻ ከVOA ጋር ያደረጉት ቆይታ‼️
ኢንጂነር አይሻ⬆️ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #አብይ_አሕመድ ባዋቀሩት አዲስ የካቢኔ አባላት ውስጥ #የመከላከያ_ሚኒስቴር ሚኒስትር የሆኑት ኢንጂነር አይሻ መሐመድ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ አንደኛና ሁለተኛ የሚባል ዜጋ የለም "ኢትዮጵያ ለሁሉም #እኩል የሆነች አገር ናት" ብለዋል። ይህ ደግሞ ለፖለቲካ ፍጆታ ብቻ መዋል እንደሌለበት ገልፀው፤ "ፖለቲከኛም፣ ጤነኛም ሆነ በሽተኛ መሆን የሚቻለው #አገር ስትኖር ነው" ብለዋል።

በየትኛውም ደረጃ ያለ ማንኛውም የመንግሥት አመራር ላይ ያለ ሰው ገለልተኛ መሆን እንዳለበት የተናገሩት ወ/ሮ አይሻ፤ "ይህን ደግሞ በሚያንፀባርቁት ሐሳብም በድርጊትም ማሳየት ይገባቸዋል።"ብለዋል።

ምንጭ፦ VOA አማርኛው አገልግሎት(ፂዮን ግርማ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia