TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.5K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#updateሀዋሳ⬆️የኢህአዴግ 11ኛው ድርጅታዊ ጉባኤ የመክፈቻ ስነስርዓት እንደቀጠለ ይገኛል።

ፎቶ፦ አቶ ፍፁም አረጋ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ማስታወሻ‼️ጨፌ ኦሮሚያ በዚህ ሳምንት መጨረሻ #አስቸኳይ ስብሰባውን ያደርጋል። አስቸኳይ ስብሰባው ከመስከረም 25፣ 2011 ጀምሮ #በአዳማ ከተማ በጨፌ አደራሽ ነው የሚደረገው ለዚህም የጨፌ #አባላት በሙሉ መስከረም 24 2011 ዓ.ም #በአዳማ ጨፌ ኦሮሚያ አደራሽ እድትገኙ የጨፌ ኦሮሚያ ጽ/ ቤት ጥሪውን ያቀርባል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ⬆️

ኢንጂነር #ክፍሌ_ሆሮ የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ስራ አስኪያጅ ሆነው ተሾሙ። የቀድሞው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ስራ አስኪያጅ ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት የኢንጂነር ስመኘው በቀለ ሞትን ተከትሎ የግድቡን ግንባታ ኢንጂነር ኤፍሬም ወ/ኪዳን ላለፉት ሁለት ወራት በጊዚያዊነት ሲመሩት ቆይተዋል፡፡

በመሆኑም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር አብርሃም በላይ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት ለግድቡ ግንባታ ስራ አስኪያጅ እና ሁለት ምክትል ሥራ አስኪያጆች ኃላፊነት ሰጥተዋል፡፡

በዚሁ መሰረት ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ ከዛሬ ጀምሮ የታቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ስራ አስኪያጅ ሆነው ሲሾሙ፣ ኢንጂነር ኤፍሬም ወልደኪዳን እና አቶ ፍቃዱ ከበደ ደግሞ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ሆነው እንዲሰሩ መመደባቸውን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የውጭ
ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ለኢቢሲ የላከው መግለጫ ያስረዳል፡፡

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ኢትዮጵያ የግፍ ግፍ ሰርተው እንጦሮጦስ ያወረዷት መሪዎችም ነበሯት:: አንድ አድርገው ከነበሩባት ችግር ያወጧት መሪዎችም ነበሯት፡፡
ቁም ነገሩ አሁን ይህችን ታሪካዊ ሀገር ታሪካዊነቷን እንመልሳለን? ወይስ #ማፈሪያ እደርጋታለን? ወይስ የዓለም ተምሳሌት እናደርጋታለን? የሚለው ሲሆን ምርጫውም በእጃችን ነው፡፡ ሁላችንም በቀና ልቦና ከሰራን ሀገራችንን ወደ ቀደመ ገናናነቷ እንመልሳታለን፡፡"

▪️▪️ጠ/ሚ ዶክተር አብይ አህመድ▪️▪️
@tsegabwolde @tikvahethiopia
BiT⬆️ከላይ የምትመለከቱት ቅጣትን የሚመለከት ማስታወቂያ ዩኒቨርሲቲው ያወጣው እንዳልሆነ ልታውቁት ይገባል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በታማኝ በየነ የሚመራው ግሎባል አልያንስ ከቤኒሻንጉል #ለተፈናቀሉት 70 ሺህ ወገኖቻችን መርጃ #የጎፈንድሚ ከፍቷል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
AAU⬆️የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የነባር ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ከላይ የምትመለከቱት ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
#update DV 2020⬆️

የ2012 ዲቪ ሎተሪ ከዛሬ፤ #ረቡዕ መስከረም 23/2011 ዓ.ም. ጀምሮ ክፍት እንደሚሆን አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኢምባሲ አስታውቋል። በሎተሪው ለመሣተፍ የሚፈልጉ አመልካቾች #ለመመዝገብ ምንም ዓይነት ክፍያ ለማንም መክፈል እንደሌለባቸው አሳስቧል።

ማሳሰቢያ፦ በVOA ዘገባ በምትሰሙት ድምፅ ያለውን የቀን ስህተት ወደ ዛሬ ትቀይሩት ዘንድ በአክብሮት ጠይቃለሁ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አስቸኳይ መረጃ‼️

(ሼር ይደረግ)

ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ተፈናቅለው በምዕራብ ወለጋ ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ ለሚገኙ ከ70 ሺህ የማያንሱ ዜጎቻችንን አስቸኳይ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል።

ከብሔራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ጋር ባደረግነው ውይይት መሰረት ለኦሮሚያ አደጋ መከላከልና ዝግጁነት ቢሮ በአፋጣኝ ሰብዓዊ እርዳታዎች ለማድረስ ተስማምተናል።

በዚህም መሰረት በአዲስ አበባና በአካባቢው የምትኖሩ ለሰብዓዊ እርዳታ ገር ልብ ያላችሁ ጽኑ ኢትዮጵያዊያን የተለመደው ርብርባችሁ ይጠበቃል።

#የማይበላሹ_ምግቦች

መኮረኒ
ሩዝ
ፉርኖ ዱቄት
ዘይት
ሴሪፋም /ፋፋ/
ብስኩት /ጋቤጣ/

#የንጽህና_ቁሳቁሶች

ሳሙና
ኦሞ
ሳኒታይዘር
የሴቶች ንጽህና መጠበቂያ /ሞዴስ/

#አልባሳት

ብርድ ልብስ
ነጠላ ጫማ

የተለያዩ አልባሳት (ያገለገሉም ቢሆን)
እነዚህን ቁሳቁሶች ብቻ ለግዜው የፊታችን ሰኞ እና ማክሰኞ እኛ በምናዘጋጀው ግዜያዊ መረከቢያ ቦታ ታደርሱልን ዘንድ በታላቅ ትህትና እንጠይቃለን።

ቦታው #የሀገር_ፍቅር_ቴአትር ቅጥር ግቢ (ሰኞና ማክሰኞ መስከረም 28 እና 29 ብቻ) ጫካ ያደሩ ህፃናትና እናቶች አረጋውያንና ደካሞች ከምንም በላይ "የኢትዮጵያዊያን ያለህ!" እያሉ ነው።

#ሰብዓዊነት_ይቅደም !!
(ከአንድ ግዜ በላይ ሼር በማድረግ ማህበራዊ ኃላፊነትዎን ይወጡ)

ከያሬድ ሹመቴ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update DV 2020⬇️

የ2020 የዲቭ ሎተሪ መሙያ ጊዜ በዛሬው ዕለት እንደሚጀመር የአሜሪካ ኢምባሲ አስታውቋል።

ዛሬ ኦክቶበር 3, 2018 በምስራቅ አፍሪካ
ሰዓት አቆጣጠር #ከምሽቱ 7 ሰዓት ጀምሮ ዲቭው የሚሞላበት ድረገጽ ክፍት እንደሚሆን የገለጸው ኢምባሲው እስከ ኖቬምበር 6 ምሽቱ 8 ሰዓት ድረስ ይቆያል ብሏል።

አንድ ሰው አንድ ፎርም ብቻ እንዲሞላ ያሳሰበው ኢምባሲው; በፎርሙ ላይ አመልካቹ ለሚያቀርበው መረጃ ለእውነተኛነቱ ሃላፊነቱን ራሱ አመልካቹ እንደሚወስድ ገልጿል።

በነጻ በሚሞላው በዚህ የዲቭ ፎርም እድሜያቸው ከ21 ዓመት በታች የሆኑ የቤተሰብ አባላት አብረው በአንድ ፎርም መሞላት እንደሚገባቸው አሳስቧል።

በቤተሰብ አባል ውስጥ ዕድሜው ከ21 ዓመት በታች ሆኖ ሎተሪውን መሞከር ባይፈልግም እንኳ ስሙ በአመልካቹ ፎርም ላይ መካተት እንደሚኖርበትም ኢምባሲው ጠቁሞ በኢሚኤል ዲቭ ደረሳችሁ የሚል መል ዕክት ከሚልኩ አሳሳቾች እንዲጠበቁም መክሯል።

ምንጭ፦ ዘሀበሻ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
U.S. Embassy Addis Ababa⬇️

The online registration for the 2020 DV lottery will open for entries beginning 7PM East Africa Time on October 3, 2018. The ONLY way to apply is through www.dvlottery.state.gov. Instructions can be found at
https://bit.ly/2AonaLF

Key things to know:

- Entry in the DV Lottery is FREE

- Only one entry is allowed per person

- You are responsible for ensuring the information on your application is correct

- You must include all family members under the age of 21 even if they do not intend to immigrate

- Remember that selection is random and no one can help you "win" - beware of fraud.

The entry period will close entries at 8pm East Africa Time on November 6, 2018.

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አሳዛኝ_ዜና⬇️

በሶማሊያ የፑንትላንድ የንግድ ከተማ በሆነችው ቦሳሶ ውስጥ ሦስት #ኢትዮጵያዊያን #በአይሲስ ታጣቂዎች #ሲገደሉ ቢያንስ አንድ መቁሰሉ ተዘገበ።

ስለጥቃቱ በቀዳሚነት የወጡ ዘገባዎች እንዳመለከቱት ታጣቂዎቹ በርካታ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ይኖሩበታል በሚባለው ሳንቶስ ተብሎ በሚጣራው የከተማዋ ክፍል ውስጥ ባገኟቸው አራት ኢትዮጵያዊያን ላይ #ተኩስ ከፍተው ነው ጥቃቱን የፈፀሙት።

አንድ ስማቸውን ያልጠቀሱ የአካባቢው ባለስልጣን ኢትዮጵያዊያኑ በተፈፀመባቸው ጥቃት መገደላቸውንና መቁሰላቸውን ለቢቢሲ ሲያረጋግጡ፤ አፍቃሬ አይኤስ የሆነ ቡድንም በትዊተር ገጹ ላይ ስለጥቃቱ አስፍሯል።

ኢትዮጵያን ጨምሮ ከተለያዩ ሃገራት የኤደን ባህረ ሰላጤን በትናንሽ ጀልባዎች በማቋረጥ ወደ የመንና የመካከለኛው ምሥራቅ ሃገራት በህገ ወጥ መንገድ ለመሻገር የሚፈልጉ ስደተኞች #የቦሳሶን የባህር በር ይጠቀማሉ።

በአካባቢውም በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች እንደሚገኙ ተገልጿል።

እነዚህ በጥቃቱ የሞቱትና የቆሰሉት ኢትዮጵያዊያንም በህገ ወጥ አዘዋዋሪዎች አማካይነት ባህሩን ተሻግረው በጦርነት ወደ የምትታመሰው #የመን ለመጓዝ በቦታው የነበሩ ስደተኞች እንደሆኑ ይታመናል።

አይሲስ ከቅርብ ወራት ወዲህ በጉልህ የሚታዩ በርካታ ጥቃቶችን በሶማሊያ ውስጥ እየፈፀመ ሲሆን በተለይ ደግሞ በፑንት ላንድ ግዛት ውስጥ የአይኤስ ቡደን ከሌሎች አካባቢዎች በበለጠ ሰፊ እንቅስቃሴ ያደርጋል ተብሎ ይታመናል።

ፑንትላንድ በሰሜን ሶማሊያ የምትገኝ ከፊል ራስ ገዝ የሆነች ግዛት ናት።

ምንጭ፦ BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አስቸኳይ መረጃ‼️

ከቤኒሻንጉል ጉሙዝና ከምስራቅ ወለጋ ዞን አጎራባች ወረዳዎች #የተፈናቀሉ ዜጎችን #በገንዘብ ለመርዳት የምትፈልጉ፦

በኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ
937719

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000259030138

በኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ
1000072131111

#ሼር

ምንጭ፦ ኦሮሚያ ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#updateሀዋሳ 11ኛውን የኢህአዴግ ድርጅታዊ ጉባዔን የሚመሩ አራት #የፕሬዚዲየም አባላት ተመርጠዋል።

የፕሬዚዲየም አባላት ሆነው የተመረጡት የአራቱ እህት ድርጅቶች ሊቃነመናብርት ናቸው። በዚህም መሰረት፦

1. የኦዴፓ ሊቀመንበር ዶክተር አብይ አህመድ

2. የአዴፓ ሊቀመንበር አቶ ደመቀ መኮንን

3. የደኢህዴን ሊቀመንበር ወይዘሮ መፈርያት ካሚል

4. የህወሃት ሊቀመንበር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ናቸው።

በጉባዔው የኢህአዴግ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሄር የጉባኤውን ዝግጅት ሪፖርትን ያቀረቡ ሲሆን በሪፖርቱም ውይይት እየተካሄደበት ይገኛል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከጊምቢ⬆️

"ከቤኒሻንጉል የተፈናቀሉ ዜጎቻችን #በጊምቢ ከተማ #በቄሮ እና በአካባቢዉ ነዋሪዎች እርዳታ እየተደረገላቸው ነው።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከነቀምት⬆️

"የBethel Academy ት/ቤት ባለቤት የሆኑት አቶ ተስፋዬ ወዳጆ ከቤኒሻንጉል ለተፈናቀሉት ዜጎቻችን 500 ብርድ ልብስ እና 50 ፍራሽ የNeqemt ከተማ ከንቲባ ለሆኑት ለአቶ Alamiro Andarge አስረክበዋል። አስተማሪ፣ መካሪ፣ ጉአደኛ እና አባታችን ነህ! ሁሌም እንኮራብሀለን!!Nahilem ነኝ (class of 2014) ከነቀምት"
 
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ⬆️የ2011 ዓ.ም. የነባር ተማሪዎች የምዝገባ ቀን ከላይ በማስታወቂያው የተገለፀው ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia