TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
From Bishoftu⬆️

"#Irrecha2011, Everything went fine Medical staffs from all Addis Ababa Hospitals, different Oromia region Hospitals and Oromia physician Association were volunteered and we were #succeeded Thanks to God, Thanks to all who participated!🙏"

Photo: Iddo(TIKVAH-ETH)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
From Bishoftu⬇️

"Tsegisho am from Bishoftu the program was so beautiful. And completed #peacefully the crowd is now going back to thier home singing loudly."

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን⬇️

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን #ወደነበረበት የሚመልስ ረቂቅ ዕቅድ ተዘጋጀ። ለመጀመርያ ጊዜ በአዲስ አበባ የፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ይቋቋማል

በግንቦት 1997 ዓ.ም. ከተካሄደው #ምርጫ በኋላ በተፈጠረው ቀውስ ወደ #ፌዴራል መንግሥት የተዘዋወረውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን፣ ወደ ከተማው አስተዳደር መመለስ የሚያስችል ረቂቅ ዕቅድ ተዘጋጀ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አደረጃጀትና መዋቅር ጥናት ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ባካሄደው ጥናት፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የራሱ የሆነ አዲስ የፀጥታ አስተዳደር ቢሮ እንዲመሠርት ምክረ ሐሳብ አቅርቧል፡፡

የፕሮጀክት ጽሕፈት ቤቱ ባከናወነው ጥናት ላይ የመጀመርያ ዙር ውይይት ረቡዕ መስከረም 16 ቀን 2011 ዓ.ም. ተካሂዷል፡፡

በውይይቱ ወቅት በቀረበው ጥናታዊ ጽሑፍ፣ ‹‹የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፀጥታ አስተዳደር ቢሮ›› የተሰኘ አዲስ የካቢኔ አባል የሚሆን ተቋም እንዲመሠረት ሐሳብ ቀርቧል፡፡

ይህ አዲስ ተቋም ላለፉት 14 ዓመታትአስተዳደር በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ሥር ሆኖ የቆየውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በድጋሚ ወደ ከተማው በመመለስ፣ የከተማውን ደንብ ማስከበር አገልግሎትና በክፍለ ከተማና በወረዳ የሚቋቋሙትን የፀጥታ አስተዳደር ጽሕፈት ቤቶችን አቅፎ ይይዛል፡፡

#የአዲስ አበባ ከተማ የፀጥታና ቢሮ ተጠሪነቱ በቀጥታ ለከተማ #አስተዳደሩ ከንቲባ ይሆናል ተብሏል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አደረጃጀትና መዋቅር ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሰይፈ ፍቃዱ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የተዘጋጀው ጥናት ለካቢኔ ቀርቦ ይሁንታ ካገኘ ለአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ቀርቦ ሲፀድቅ ተግባራዊ ይሆናል፡፡

በቀረበው ረቂቅ ጥናት ላይ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 49 ንዑስ አንቀጽ 2 እና በቻርተሩ 95 አንቀጽ 10 መሠረት፣ አዲስ አበባ ከተማ ራሱን የማስተዳደር #መብት አለው፡፡

‹‹የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ራሱን በራሱ የማስተዳደር ሙሉ ሥልጣን ይኖረዋል፣ ዝርዝሩ በሕግ ይወሰናል፤›› ሲል ሕገ መንግሥቱ በአንቀጽ 49 ንዑስ አንቀጽ 2 ላይ ደንግጓል፡፡

ረቂቅ ጥናቱን ያቀረቡት የፕሮጀክት ጽሕፈት ቤቱ ከፍተኛ አማካሪ አቶ ቤተ ማርያም መኮንን እንዳሉት፣ አዲስ አበባ ከተማ እስካሁን የራሱ የፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የለውም፡፡

‹‹ራሱን የቻለ የፀጥታ መዋቅር ባለመኖሩ የከተማውን ነባራዊ ሁኔታ መሠረት ባደረገ መንገድ ባለመደራጀቱ፣ የፀጥታ ተቋማቱ በተለያየ መዋቅር እንዲመሩ ሆኗል፤›› በማለት የገለጹት አቶ ቤተ ማርያም፣ ‹‹አዲስ የፀጥታ አስተዳደር መዋቅር ተግባራዊ ሲሆን ይህ ችግር ይፈታል፤›› ብለዋል፡፡

በአዲሱ መዋቅር መሠረት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን፣ የክፍለ ከተማና የወረዳ የፀጥታ አስተዳደር ጽሕፈት ቤቶች፣ በማዕከል፣ በክፍለ ከተማና በወረዳ ያሉ የደንብ ማስከበር ጽሕፈት ቤቶች በቢሮው ሥር ይተዳደራሉ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት ዓመታት የፍትሕ፣ የፀጥታ፣ የሰላም፣ የመልካም አስተዳደርና የሰብዓዊ መብት ጥያቄዎች መነሳታቸውን ያስታወሱት ደግሞ፣ የከተማው ፍትሕ ቢሮ ኃላፊ አማካሪ አቶ ኤፍሬም ግዛው ናቸው፡፡

ከነዋሪዎች የሚነሱትን እነዚህን ችግሮች ለመፍታት፣ የከተማውን ሰላምና ፀጥታ አስተማማኝ ለማድረግ አዲሱ መዋቅር ወሳኝ ድርሻ እንዳለው አቶ ኤፍሬም ተናግረዋል፡፡

ይህ ጥናት እንዲካሄድ መመርያ የሰጠው የከተማ አስተዳደር ካቢኔ በመሆኑ፣ በሒደት ላይ ያሉ ሥራዎች ሲጠናቀቁ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሏል፡፡

ምንጭ፦ ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
154,176TIKVAH-ETHIOPIA ለቤታችን መጠናከር እና ብዙ ቦታ መድረስ በሀገሪቱ ውስጥ ከጫፍ ጫፍ ያላችሁ እና በውጭ ያላችሁ ውድ ኢትዮጵያዊያን እየሰራችሁት ላለው ድንቅ ስራ ምስጋና እና ክብር ይገባችኋል።

🙏እናተን የማመሰግንበት ቃላት ያጥረኛል! ምክንያቱም ምን ያህል ለኢትዮጵያ #ሰላም እና #እድገት እንደቆማችሁ በየደቂቃው የምትሰሩት ስራ ምስክር ነው።

ጉዞው ይቀጥላል...
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከብሄራዊ ትያትር⬆️

"የክቡር ዶ/ር አርቲስት #ጥላሁን_ገሰሰ 78ኛ ዓመት #የልደት ቀን መታሰቢያ ዝግጅት ዛሬ #በኢትዮጵያ_ብሔራዊ ቲያትር በደመቀ ስነ ስርዓት እየተከበረ ይገኛል።"

ምንጭ፦ ሱራፌል
@tsegabwolde @tikvahethiopia
“ገፍተው ገፍተው #ወደማንፈልግበት ሁኔታ ሊከቱን የሚፈልጉ ሰዎች(አካላት) አሉ፤ #የመቻቻል ጥቅሙ ለራስ ሲባል እንጂ ለመለያየት አንድ ቀን በቂ ነው፡፡ ግለሰቦች በየመድረኩና በየመገናኛ ብዙኃን ሕዝብ #እንዲለያይ ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ በመሆኑ፣ እኛ #ኢትዮጵያውያን ቆም ብለን ይኼ #ፖለቲካ እያደገ ነው? ወይስ ወደኋላ እየሄደ? የሚለውን ጥያቄ ማንሳት አለብን። ከ30 ዓመታት በኋላ ወደ 1960ዎቹ ልንመለስ ነው? ወይስ እያደግን ነው? የሚለው ላይ በጥሞና መወያየትና መነጋገር ያስፈልጋል፡፡ ሁሉም #ካልተቻቻለ ሁሉንም ልትጠቅም የምትችል አንዲት ኢትዮጵያ መፍጠር እንደማይቻል አውቀን አንድነትን የሚጎዱ ነገሮች ሁሉም ሊያወግዟቸው ይገባል፡፡ ከምንም በላይ #ሕዝቡ ማውገዝ ያለበት የብሔር ብሔረሰቦችን አጀንዳ እያነሱ አንደኛው ወገን በሌላኛው ወገን ላይ የሚያሳያቸውን #ጥላቻዎች ነው።”

ክቡር ዶ/ር #ለማ_መገርሳ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና📌ብአዴን ስያሜውን ቀየረ፡፡
የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) በሚል ቀይሯል፡፡ #የአርማ ማሻሻያም አድርጓል፡፡ በአርማው የቀረበውን ማሻሻያ አካቶ አዲስ የሚመረጠው ማዕከላዊ ኮሚቴ እንዲያጸድቀው ውክልና ተሰጥቶታል፡፡ የፓርቲው የልሳናት ስያሜ የሚሻሻል ሲሆን አዲስ የሚመረጠው ማዕከላዊ ኮሚቴ #እንዲያጸድቀው ውክልና ተሰጥቶታል፡፡ በመተዳደሪያ ደንቡ ላይም የተወሰኑ #አንቀጾች ላይ ማሻሻያ ተደርጓል።

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጊፋታ2011 ከወላይታ ሶዶ⬆️

"HT ነኝ ፀግሽ ወላይታ ሶዶ ላይ የጊፋታ የወላይታ ዘመን መለወጫ በዓል በሙዚቃ ድግስ እንዲህ እየተከበረ ነው።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለነቀምት ነዋሪዎች‼️

ከቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል #የተፈናቀሉ ወገኖቻችን በ03፣ 04 እና 07 ቀበሌ፤ በነቀምት የመምህራን ኮሌጅ፣ ዳንዲ ቦሩ ኮሌጅ እንዲሁም በነቀምት ከተማ አስተዳደር ግቢ ውስጥ ይገኛሉ። እነኚህ ወገኖቻችን ምግብ እና መኝታ ያስፈልጋቸዋል። የነቀምት ነዋሪዎች እና #ቄሮዎች በቻላችሁት አቅም ድጋፍ እንድታደርጉላቸው ጥሪያችንን እናቀርባለን።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከዲላ ዩኒቨርሲቲ⬆️በመስከረም 3 የገባን የዲላ ዩኒቨርሲቲ የጤና ተማሪዎች እየተሰቃየን ነው። የምግብ ጥራቱ እጅግ በጣም ወርዷል። ይባስ ብሎ "ዜርፎር" እንኳን እያገኘን አይደለም። በአሁን ሰዓት እራሱ ማን እንደበላው ሳናውቅ ምግብ #አልቋል ተብለን ውጭ ቆመናል የሚመለከተው የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ችግራችንን ይፍታልን ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አዴፓ ወይም የቀድሞ ብአዴን በአሁን ሰዓት ከፓርቲው የሚሰናበቱ አባላትን በመለየት ላይ ይገኛል።

#Loading🔄
@tsegabwolde @tikvahethiopia