TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#update አዲስ አበባ ዙሪያ ያሉ ከተሞች ወደቀደመው #ሰላማዊ እንቅስቃሴያቸው ተመልሰዋል። ከሰሞኑን በተለያዩ ከተሞች ችግር ፈጥረዋል ተብሎ የታሰቡ ግለሰቦች ፖሊስ እየለቀመ እንደሆነ ለመስማት ተችሏል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
የድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት ዲቪዥን ኃላፊ ዋና ሳጅን ባንታለም!
#update⬆️የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ኅብረተሰቡ በማኅበራዊ ድረ ገፅ በሚለቀቁ ስጋት ፈጣሪ ሐሳቦች ተነሳስቶ #ግጭት ውስጥ እንዳይገባ አሳሰበ። በከተማዋ ግጭት ለመፍጠር የሚፈልግ አካል ካለም ፖሊስ #የማይታገስ መሆኑን አውቆ ከጥፋት ድርጊት እንዲታቀብ አሳስቧል። የድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን ሕዝብ ግንኝነት ዲቪዥን ኃላፊ ዋና ሳጅን ባንታለምን ከVOA ጋር ያደረጉት ቆይታ ከላይ ባለው የድምፅ ፋይል ማድመጥ ትችላላችሁ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
145,737🙏ቻናላችን በመላው ሀገሪቱ ተፅዕኖ መፍጠር እንዲችል እያደረጋችሁት ላለው ትልቅ ስራ ከልብ አመሰግናለሁ!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከጅማ⬇️

"ዛሬ የODP ስብሰባው እንደተጠናቀቀ ማምሻውን ዶክተር አብይ የከተማዋን ወጣት ያነጋግራሉ ተብሎ ይጠበቃል።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኦዴፓ⬇️

የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) 9ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ ባለ ዘጠኝ ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት #ተጠናቀቀ

ከትናንት በስቲያ ጀምሮ በጅማ ሲካሄድ የቆየው ይህ ድርጅታዊ ጉባኤ በቆይታው የፓርቲውን ስያሜ ጨምሮ የአርማ እና የመዝሙር ለውጥ አድርጓል።

በተጨማሪም የፓርቲውን ሊቀመንበር እና ምክትል ሊቀመንበር እንደዚሁም የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ፣ የማእከላዊ ኮሚቴ እና የኢህአዴግ ምክር ቤት አባላት ምርጫን አካሂዷል።

በጉባኤው ማጠናቀቂያ ላይ የፓርቲው ሊቀመንበር በመሆን በድጋሚ የተመረጡት ዶክተር አብይ አህመድ የተለያዩ ውሳኔዎች የተላለፉበት
ይህ ድርጅታዊ ጉባኤ ታሪካዊ ነበር ብለዋል።

በተለይም አዳዲስ አመራሮች ወደ ፊት የመጡበት፣ የስያሜ፣ የአርማ እና መዝሙር ለውጥ የተካሄደበት መሆኑ ታሪካዊ ያደርገዋል ነው ያሉት።

ሊቀመንበሩ የኦሮሞ ዴሞራሲያዊ ፓርቲ ህዝቡን ለማገልገል ከዛሬ ጀምሮ #በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ቃል ይግባልም ብለዋል።

በአዲስ መንፈስና ሀሳብ ለማገልገል የተነሳው ፓርቲው በፍቅርና በአንድነት ለማገልገልም ተግቶ እንደሚሰራም አስታውቀዋል።

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Addis Abeba⬆️Happening right now at mosaic Hotel. #icogLabs @iCogSolveit
ከቴዲ አፍሮ⬆️
#update የቴዲ አፍሮ ኮንሰርት⬇️

"በቅድሚያ የከበረ ሰላምታችንን እያቀረብን ሰሞኑን በአዲስ አበባ እና በዙሪያዋ በተከሰቱ አንዳንድ ግጭቶች ምክንያት ህይወታቸው ላለፈና የተለያየ ጉዳት ለደረሰባቸው እንዲሁም በተፈጠረው ሁኔታ ከመኖሪያ ቀያቸው ለተፈናቀሉ ወገኖቻችን የተሰማንን ጥልቅ #ሃዘን እየገለፅን ከዚህም ጉዳይ ጋር በተያያዘ በንፁሀን ዜጎቻችን ላይ የደረሰውን ጉዳት ምክንያት በማድረግ እና እንዲሁም የአዲስ አበባ ከተማ የፀጥታ ሁኔታ ወደ አስተማማኝ መረጋጋት እስኪመለስ ድረስ ጉዳዩ ከሚመለከተው የከተማው አስተዳደር ጋር በመወያየት #ዝግጅቱ ከመስከረም 30 ቀን 2011 ዓ/ም በኋላ አቅምና ሁኔታዎች በፈቀዱ መጠን አስፈላጊው ጥረት ተደርጎ እንደሚካሄድ እና የሚካሄድበትን ትክክለኛ ቀን አስቀድመን እንደምናሳውቅ ስንገልፅ የመግቢያ ትኬቱን ቀደም ብላችሁ ለገዛችሁና ጥሪ ለተደረገላችሁ እንግዶች እንዲሁም ዝግጅታችንን ለመታደም ከተለያዪ የሃገራችን ክፍሎችና ከባህር ማዶ ጭምር ለመጣችሁ ክቡራን ወገኖቻችን ከአቅም በላይ በሆነ ወቅታዊና ሀገራዊ ጉዳይ ምክንያት በተፈጠረው ተደጋጋሚ ሁኔታ ለገጠማችሁ #መጉላላት በዚህ አጋጣሚ ከፍ ያለ #ይቅርታ ለማቅረብ እንወዳለን።"

አዘጋጅ ኮሚቴው

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ማስታወቂያ📌ኢትዮ ላይፍ ሪል ስቴት(Ethio Life Real Estate)
>የግንባታ ቦታ - ቦሌ(ወሎ ሰፈር)-Bole,Wollo sefer
>0920725945 & 0910931987
>ለቢሮ, ለሱቅ, ለሬስቶራንት, ለሾው ሩም እና የመኖሪያ አፓርታማዎች G+16
>የግንባታ ደረጃ - 15ኛ ፎቅ
>ስራ ተቋራጭ- ባማኮን ኮንስትራክሽን
____ከ8 ካሬ እስከ 180ካሬ አለ_______
በ 510,000ብር ብቻ ቦሌ ላይ የሱቅ ባለቤት ይሁኑ!
አፓርታማ-
ባለ 2 መኝታ-128, 133, 144ካሬ
ባለ 3 መኝታ-166, 186, 187ካሬ
****ቅድመ ክፍያ 30% ብቻ*****
ከቀርጫ ጉጂ ዞን⬆️
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኦዴፓ/ኢህአዴግ ስራ አስፍፃሚ ኮሚቴ አባልት ከላይ የምትመለከቷቸው ናቸው።

@tsegawolde @tikvahethiopia
ከጅማ⬆️

"ዶክተር ነገሪ ሌንጮ ዶ/ር አብይ በስራ መብዛት ምክንያት እንደማይመጣ አሳውቀውን ሌላ ጊዜ ይመለሳል ብለው ተበትነናል። ያበሳጫል!"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ቡራዩ⬇️

በቡራዩ ከተማና አካባቢዋ በደረሰው የሰው ህይወት መጥፋት የአካል ጉዳት፣ #ዘረፋና ንብረት እንዲወድም ከመስከረም 1 ቀን 2011 ጀምሮ በመቀስቀስ እና #ገንዘብ በማከፋፈል ግጭቱ እንዲነሳ በማድረግ የተጠረጠሩ ስድስት ግለሰቦችን የፌደራል ፖሊስ ፍረድ ቤት አቀረበ።

በፌደራልና በኦሮሚያ ፖሊስ ለሁለት ተከፋፍሎ የሚከናወነው ምርመራ የቀጠለ ሲሆን፥ ትናንት ከሰዓት በኋላ በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምደብ ችሎት 1ኛ ተረኛ ወንጀል ችሎት ስድስቱ ተጠርጣሪዎች ቀርበዋል።

መርማሪ ፖሊስ ለተጨማሪ ምርመራ የ14 ቀን ጊዜ ጠይቆባቸዋል።

#ተጠርጣሪዎቹ ሳምሶን ጥላሁን፣ ዓለሙ ዋቅቶላ፣ ቡልቻ ታደሰ፣ ሀሺም አህሚድ፣ ሽፈራው ኢራና እና ኢሉ ዳንኤል ሲሆኑ፥ ነዋሪነታቸው በቡራዩ፣ ገፈርሳና ከታ አካባቢ ነው።

መርማሪ ፖሊስ ግለሰቦቹ #የተጠረጠሩበት በቡራዩና አካባቢዋ በደረሰው የሰው ህይወት መጥፋት፣ ንብረት መውደም እና ዘረፋ የተጠረጠሩ ናቸው በማለት መነሻ መረጃ እንዳገኘባቸው አስረድቷል።

ተጠርጣሪዎቹ በበኩላቸው ድርጊቱን አልፈፀምንም ሲሉ አስረድተዋል።

ክርክራቸውን ያዳመጠው ፍርድ ቤቱ ፖሊስ ተጨማሪ ምርመራውን በ14 ቀናት ውስጥ አጠናቆ እንዲቀረብ በማዘዝ ለመስከረም 24 ቀን 2011 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

በተመሳሳይ በኦሮሚያ ፖሊስ ምርመራ እየተደረገባቸው ካሉ ግለሰቦች መካከል 45 ተጠርጣሪዎቹ ትናንት ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን፥ ቀሪዎቹ ዛሬ ይቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

©FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia