TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.5K photos
1.52K videos
215 files
4.13K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#update⬆️በቻይና #ቤጂንግ የሚገኙት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዶ/ር #ዐቢይ_አህመድ በቻይና ቤጂንግ የህዝቦች #ጀግኖች መታሰቢያ ሀውልት “Peoples Heroe’s Monument” /ታይናንሚን አደባባይ በመገኘትም የአበባ ጉንጉን አኑረዋል።

📌ነሃሴ 27 ቀን 201ዓ.ም
©Office of the Prime Minister
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ⬆️

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዶ/ር #ዐቢይ_አህመድ ከቻይና ህዝባዊ ኮንግረስ ሊቀመንበር ሊ ዛን ሹ ጋር ተወያዩ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከቻይና ህዝባዊ ኮንግረስ ሊቀመንበር ሊ ዛን ሹ ጋር ተገናኝተው ተወያተዋል።

ከዚህ ቀደም ትውውቅ እንደነበራቸው በውይይታቸው ያወሱት መሪዎቹ በአከባኢያዊና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ፣ በእዳ ቅነሳና ብድር ዙሪያ፣ የቻይናና ኢትዮጵያ የቀደመ ግንኙነት፣ የአፍሪካና የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች እና ሌሎች ጉዳዮች ላይም ተወያይተዋል። ሊቀመንበሩ አክለውም አዲሱ አመራር በሀገሪቱ እያመጣ ያለውን ለውጥ አድንቀው ይህን ለውጥ ወደፊትም የሚደግፉ መሆኑን ገልጸዋል።

©Office of the Prime Minister
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ⬆️

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ_አህመድ ከግብጹ ፕሬዝዳንት #አብዱልፈታህ_አልሲሲ ጋር ተወያይተዋል። በውይይታቸውም የአባይን ጉዳይ ጨምሮ በአህጉራቀፍና ሁለትዮሽ ግንኙነት ላይ ወጤታማ ውይይት እድርገዋል። በተጨማሪም የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት በንግድ፣ ቱሪዝምና ሌሎችም ዘርፎች ለማስፋትና ለማጠናከር የተነጋገሩ ሲሆን ውይይቱም በጥሩ መንፈስና መግባባት ተጠናቋል።

©Office of the Prime Minister
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update Mitsewa⬇️

"The Ethiopian ship mv #Mekelle will make acall at Mits'iwa port this Tuesday evening, #Ethiopian and #Eritrean government officials are expected to make a visit on her arrival."

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update 10ኛ ክፍል⬇️

በ2010 ዓ.ም የ10ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የፈተና ውጤት እስከ #አርብ ድረስ ይፋ እንደሚሆን የሀገር ዓቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ አስታውቋል።

የተማሪዎችን እርማት ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ መረጃውን በአጭር ጽሁፍ እና በድረ-ገጽ በጥራት ለማሰራጨት ከሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር እየተሰራ መሆኑን የአገር አቀፍ የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ አርአያ ገብረእግዚአብሔር ለኢቢሲ ተናግረዋል፡፡

ኤጀንሲው እስካሁን ውጤት በየትኛውም የውጤት ማሳወቂያ ዘዴ እንዳላወጣና ተማሪዎች በኤጀንሲው ስም በሚወጡ #የተሳሳቱ መረጃዎች እንዳይታለሉም አቶ አርአያ አሳስበዋል፡፡

ውጤቱን ይፋ ለማድረግ የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች መጠናቀቃቸውንና እስከ መጪው አርብ ድረስ ውጤቱ እንደተለመደው በኤጀንሲው ድረ-ገፅና በአጭር የፅሁፍ መልእክት ይፋ ይደረጋል፡፡

ተማሪዎች የለፉበት ውጤት እንዳይሳሳት በከፍተኛ ጥንቃቄ እየተሰራ መሆኑን የገለፁት ዳይሪክተሩ የ2010 ዓ.ም የ10ኛ ክፍል የፈተና ውጤትን ተማሪዎች #በትእግስት እንዲጠባበቁም ጠይቀዋል፡፡

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የሳይንስ እና ቴክኖ. ዩኒቨርሲቲ⬇️

አዳማና አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና ለ3ኛ ጊዜ ሊሰጥ ነው።

በ2011 #የአዳማና #የአዲስ አበባ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ ተማሪዎች ፈተና ለ3ኛ ጊዜ ‘#በቀጥታ’ በበይነ መረብ ሊሰጥ መሆኑ ተገልጿል።

በሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ስር የሚገኙት የአዳማና የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲዎች ለ2011 የትምህርት ዘመን የመሰናዶ ትምህርት ጨርሰው #ከፍተኛ ውጤት ያመጡትና ለፈተና ከቀረቡት 4 ሺህ 700 ተማሪዎች መካከል በፈተና በማወዳደር 3ሺህ ተማሪዎች ሊቀበል መሆኑ ተገልጿል፡፡

ፈተናው #ረቡዕ ነሃሴ 30፣ 2010 ከጠዋቱ 2፡00 ጀምሮ እስከ 11፡00 ድረስ በተለያዩ ክልሎች ባሉ 37 ዩኒቨርስቲዎች በቀጥታ በበይነ መረብ የሚሰጥ ሲሆን፥ የመግቢያ ውጤቱ ለታዳጊ ክልሎች፣ ለሴቶችና አካል ጉዳተኞች ዝቅ እንዲል ተደርጓል ተብሏል፡፡

ፈተናው ፊዚክስ፣ ባዮሎጂ፣ ኬሚስትሪ፣ ሂሳብና ኢንግሊዝኛ የትምህርት ዓይነቶቸን የሚያካትት ሲሆን፥ ዝቅተኛው የማለፊያ ውጤት ከ50 በላይ ሁኗል ተብሏል፡፡

ፈተናው በበይነ መረብ ከአንድ ማዕከል የሚተላለፍ ሲሆን፥ የወረቀት ብክነትንና የፈተና ስርቆትን ለማስቀረት ከፍተኛ እገዛ እንደሚያደረግ ነው የተገለጸው፡፡

ታላላቅ ድርጅቶች ብዛት ያለው የሰው ሀይል ለመቅጠር በፈተና ማወዳደር በሚፈልጉበት ጊዜ ይህንን ስርዓት በመጠቀም ፈትነው ለቃለመጠይቅ ብቻ የሚፈልጉትን ሰው በመጥራት መቅጠር እንዲችሉ ያደርጋል ተብሏል፡፡

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርም ይህንን የፈተና ስርዓት መጠቀም ለሚፈልግ ማንኛውንም አካል ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑንም አስታውቋል፡፡

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Wabi Shebelle Hotel, Tuesday at 5pm(11 local time), let's all contribute our part!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ስለ ጠፋሁ ይቅርታ! ሁሌም ህይወት መንገዷ ምቹ አይደለም። ተጨንቃችሁ ለደወላችሁኝ እና ለፃፋችሁልኝ ወድ የቤተሰባችን አባላት ከልብ ከልብ ከልብ አመሰግናለሁ! እኔ እጅግ በጣም ደህና ነኝ!

ፈጣሪ ያክብርልኝ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ⬆️አርቲስ እና አክቲቪስት #ታማኝ_በየነ በደብረ ታቦር ከተማ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።

©AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር #ዐቢይ_አህመድ ከዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር #ቴድሮስ_አድሃኖም ጋር በዓለም አቀፍ የጤና ሽፋንና በመሰረታዊ የጤና አገልግሎት ዙሪያ ተወያይተዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia