TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#update አርበኞች ግንቦት 7⬆️

አርበኞች ግንቦት 7 ዛሬ ነሀሴ 27/12/10 ዓ.ም ጠዋት #ሑመራ ሲገባ #ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል፡፡የአርበኞች ግንቦት 7 ታጣቂዎች ወታደራዊ ካምፑን በመዝጋት ወደ ኢትዮጵያ መግባት የጀመሩት ትናንት ነው፡፡

📌በአሁን ሰዓት ታጣቂዎቹ ወደ ጎንደር እየተጓዙ እንደሆነ ለመስማት ተችሏል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠ/ሚ ዶክተር አብይ⬆️

ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር #ዐብይ_አህመድ ከExim ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ #ሁ_ሻኦሊን ጋር በትብብር በሚሰሩበት እና በልማት ላይ ግንኛነታቸውን የበለጠ ማጠናከር በሚቻልበት ዙሪያ መወያየታቸውን እና የኢትዮጵያ ብድርን መልሶ ማደራጀት ላይ መስማማታቸን ከጠቅላይ ሚንስትር ጽህፈት ቤት ሀላፊው አቶ #ፍፁም_አረጋ ገልፀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Voice 10.3gpp
6.5 MB
ሀረር!
#update ሀረር⬆️

ዛሬ በሀረር የሚገኙ የጉራጌ ተወላጆች በሀገሪቱ ያለውን አዲሱን አመራር እንዲሁም በሀገሪቱ ውስጥ እየታየ ያለውን የለውጥ እንቅስቃሴ የሚደግፍ ስብሰባ አድርገዋል።

©ኤልያስ ከሀረር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ከ7 ዐመት በኋላ የእነ ጋዜጠኛ #እስክንድር_ነጋ "ኢትዮጲስ" መፅሄት ወደ ህዝብ መድረስ ሊጀምር ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዋልታ Live! ለአርቲስት እና አክቲቪስት ታማኝ በየነ በሚሊኒየም አዳራሽ የሚደረገውን የቅበላ ዝግጅት በዋልታ ቴሌቪዥን በቀጠታ ይተላለፋል።

📌ሰዓት 10:00
📌ሚሊኒየም አዳራሽ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
FANA Live! የአመቱ በጎ ሰው ሽልማት ፋና ቴሌቪዥን ላይ በቀጥታ በመተላለፍ ላይ ይገኛል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ⬆️ጎንደር ከተማ ለአርበኞች ግንቦት 7 ታጣቂዎች አቀባበል በመደረግ ላይ ይገኛል።

©ናትናኤል ከጎንደር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን⬇️

የኬንያ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ማህበር የኢትዮጵያ አየር ክልል ደህንነትን በተመለከተ ያወጣው መግለጫ በፍጹም እውነት #እንዳልሆነ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽ ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ የአየር ተቆጣጣሪ ሰራተኞች የስራ አድማ በመምታታቸው በኢትዮጵያ አየር ክልል ውስጥ #ምንም ዓይነት የደህንነት ስጋት ባለመፈጠሩ ማህበሩ ያወጣው መግለጫ መሰረተ ቢስ በመሆኑ ባለስልጣኑ በምንም መልኩ እንደማይቀበለው ገልጿል፡፡

ሰራተኞቹ አድማ ቢመቱም አሁንም በበቂ ሁኔታ ስለጠና በወሰዱ፤ በሙያው ዘርፍ ከፍተኛ እውቀት ባከበቱ እና ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቁ ሰራተኞች ስራቸውን እያከናወኑ በመሆኑ ምንም ዓይነት ስጋት አይፈርም ብሏል፡፡

በመሆኑም የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን የኢትዮጵያ አየር ክልል የተጠበቀ መሆኑን ለአየር መንገዶች፤ ለሃገራት ሲቭ አቪዬሽ ባለስልጣናት፤ ለዓለም አቀፍና ቀጠናዊ አካላትም እንደሚያረጋግጥ ገልጿል፡፡

📌የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ክቡር ዶክተር ለማ መገርሳ የ2010 ዓ.ም #የበጎ ሰው ሽልማት #ልዩ ተሸላሚ ሆነ!

@tsegabwolde @tikvahethiopia