#update ቃሊቲ⬆️
"ሰላም እንዴት አደርክ? ዛሬ አንድ አሳዛኝ ነገር ልነግርህ ነው ዛሬ ጠዋት በቃሊቲ ምግብ (ቸሬአልያ) ሰራተኞች ዛሬ የጠዋት ፈረቃ የነበሩት ሰራተኞች ወደ ስራ እየገቡ አቃቂ መሿለኪያ ሲደርሱ መኪናው መውጣት ባለመቻሉ እዛው በቆመበት መኪናው በውሃ ተሞልቶ የቻለ እንደምንም ወጥቶ ፎርቶ መጋላ ላይ ቆሟል መውጣት ያልቻሉ አሁንም እዛው መኪና ውስጥ በውሃ እንደተዋጡ ነው ከሌሊቱ 11፡45 ጀምሮ እዛው ቆሟል አሁን ክሬን መጥቶ እላይ ያሉትን ሰዎች እያወጣኀ ነው። ተሙ"
©ፎቶ፦ J
@tsegabwolde @tikvahethiopia

#update ገላን⬆️
በገላን አዲሱ ማረሚያ ቤት አካባቢ ያለው የዛሬ ጥዋት ገፅታ በፎቶው የምትመለከቱትን ይመስላል።
©ፎቶ፦ ሙሌ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በገላን አዲሱ ማረሚያ ቤት አካባቢ ያለው የዛሬ ጥዋት ገፅታ በፎቶው የምትመለከቱትን ይመስላል።
©ፎቶ፦ ሙሌ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ትምህርት ሚኒስቴር⬇️
የትምህርት ፎኖተ ካርታው የመወያያ ረቂቅ ሠነድ እንጂ ፖሊሲ ሆኖ አልጸደቀም አለ ትምህርት ሚኒስቴር፡፡
ትምህርት ሚኒስቴር የትምህርትና ሥልጠና ፍኖተ-ካርታ ረቂቅ የጥናት ሠነድ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ እያወያየ ነው፡፡
ከቅድመ መደበኛ እስከ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ያሉትን ችግሮች በመፈተሽ መፍትሄ ሰጭ ሀሳቦችን ማቅረብ ነው የውይይቱ ዓላማ፡፡
ሚኒስትሩ ዶክተር #ጥላዬ_ጌቴ ለአ.ብ.መ.ድ እንደተናገሩት ውሳኔ ላይ እንደተደረሰ ተደርጎ በማህበራዊ ድረ ገጾች የተሰራጨው መረጃ የተሳሳተ ነው፡፡ እንደ ሚኒስትሩ መረጃ በተጠናው ረቂቅ ሠነድ ላይ እየተመከረ እንጂ ድምዳሜ ላይ ተደርሶ ይፋ የተደረገ መረጃ የለም፡፡
ረቂቁ የትምህርትና ሥልጠና ፍትሃዊ ተደራሽነትን ፣ አግባብነትና ጥራትን እንዲያረጋግጥ ታስቦ ነው እየተመከረበት ያለው፡፡
©አ.ብ.መ.ድ

ከአርሲ ዞን⬆️
"ይህ የምታየው በአርሲ ዞን ከኢቴያ ከተማ-ሁሩታ-አርሲ ሮቤ የሚወስድ መንገድ ነው፡፡ መንገዱ በERA ባለቤትነት ለቻይና ኮንትራክተሮች በ1.9 ቢልየን ብር ከተሰጠ ሁለት አመት አልፎታል፡፡ ኮንትራክተሩ በአሁን ሰዓት ምንም ተለዎጭ መንገድ ሳይስራ ከኢተያ ሁሩታ ያለውን መንገድ ቁፍሮ እና ሙሌት እየሰራ ነው፡፡ ምንም አይነት ተለዎጭ መንገድ ባለመኖሩ ህብረተሰቡ በከፍተኛ ችግር ውስጥ ይገኛል፡፡ በአካባቢው በአሁኑ ሰዓት በከፍተኛ ደረጃ የ ሽንኩርት ምርት የሚደርሰበት ጊዜ በ መሆኑ በ ገበሬው እና ነጋዴው ላይ ከፍተኛ ኪሳራ እየደረሰ ነው፡፡ ከላይ የምታየው በመንገድ ምክንያት ማለፍ ያልቻሉ መኪኖችን ነው፡፡"

#update የ“አርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ” ሊቀመንበር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ፤ 100 ያህል አመራሮችና አባላትን ይዘው #ከጳጉሜ 3 ቀን ጀምሮ (በሦስት ምድብ) ወደ ሃገር ቤት እንደሚገቡ ታውቋል። ንቅናቄው በሃገር ውስጥ በአዲስ አደረጃጀትና ቅርፅ እንደሚዋቀር ተሰምቷል፡፡
©ጋዜጠኛ ጌጡ ተመስገን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
©ጋዜጠኛ ጌጡ ተመስገን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የቼራሊያ ሰራተኞች⬇️
በአቃቂ ክፍለ ከተማ አቃቂ መሿለኪያ ድልድይ በደራሽ ጎፍ መሙላቱን ተከትሎ የቼራሊያ የሰራተኞች ሰርቪስ በደራሽ ጎርፍ ተውጦ ነበር።
የአዲስ አበባ እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ባለስልጣን የኮሙኒዩኒኬሽን ጉዳዮች የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ስለሽ ተስፋዬ የሰራተኞች ሰርቪስ ሰራተኖቹን እንደጫነ በውሃ የተሸፈመነ ሲሆን፥ የባለስልጣኑ ጠላቂ የነፍስ አድን ባለሙያዎች በሰው #ህይወት ላይ ጉዳት ሳይደርስ የጠለቁትን ሰዎች #ማውጣታቸውን አስታውቀዋል። እንዲሁም በደራሽ ጎርፉ ተውጦ የነበረው ሰርቪስ #እንደወጣ ባለሙያው ለFBC ተናግረዋል።