TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#update ቦሌ ቡልቡላ⬆️

በአዲስ አበባ ከተማ በቦሌ ቡልቡላ አካባቢ የሚገኝ የመድሃኒያለም ቤተክርስቲያን ንብረት የሆኑ ሰባት ሱቆች ዛሬ በእሳት አደጋ ውድመት ደረሰባቸው።

የወደሙት ሁሉም ሱቆች የቤተክርስቲያኗ እንደሆኑም ኢዜአ በቦታው ተገኝቶ አረጋግጧል። የእሳት ቃጠሎ አደጋ የደረሰባቸው ሱቆችም ሁለት ግሮሰሪዎች፣ አንድ ዳቦ ቤት፣ ሁለት መዝሙር ቤት፣ አንድ የህንጻ መሳሪያ መሸጫ፣ አንድ የዘይት መሸጫ፣ የባልትና መሸጫና የምስለ ስእል መሸጫ ሱቆች ናቸው።

በሰው ላይና በንብረት ላይ ለደረሰ ጉዳት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮምሽንና የአዲስ አበባ እሳትና ድንገተኛ አደጋ መከላከልና መቆጣጠር ባለስልጣን በስፍራው በመገኘት የማጣራት ስራ እየሰሩ ነው።

በአሁኑ ሰዓትም እሳቱን በአካባቢው ማህበረሰብና በባለስልጣኑ የእሳት አደጋ ሰራተኞች ትብብር መቆጣጠር ተችሏል።

©ኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት

በቦታው የነበረች የቻናላች ቤተሰብ የ2 ህፃናት ህይወት እንዳለፈ እና ለእናታቸው ገንዘብ ሲሰባሰብ እንደነበር እንደነገረችን ይታወሳል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጎንደር⬆️

የጎንደር ከተማ ወጣቶች የአፄ ምኒሊክንና የእቴጌ ጣይቱን ልደት በጎንደር ከተማ በደማቅ ሁኔታ አክብረዋል፡፡

ምንጭ፡-ፋሲል ከነማ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ባህር ዳር⬆️

ዛሬ ባህርዳር ጃካራንዳ ሆቴል የአፄ ምኒሊክ 174ኛ የልደት በዓል ተከብሯል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በቦሌ ቡልቡላው የእሳት አደጋ ሁለት የ1 አመት ከ4 ወር መንታ ልጆች መሞታቸውን ከቅርብ ቤተሰቦች ሰምቻለሁ።

ለእናታቸው እንዲሁም ለመላው ቤተሰቦች መፅናናትን እንመኛለን!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አዲስ አበባ⬆️

የአፄ ምንሊክ እና እቴጌ ጣይቱ ልደት በአዲስአበባ ባህል እና ቱሪዝም እና ሰውኛ ፕሮዳክሽን ትብብር በእንጦጦ ቤተ መንግስት ተከብሯል። የአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ዋና ኃላፊ በረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬ አማካኝነት የአዲስ አበባ ከንቲባ የሆኑን ኢንጂነት #ታከለ_ኡማ የመልካም ልደት መልዕክታቸውን በማስተላለፍ፤ እስከ
አሁን የተዘነጋውን ታሪክ ለመዘከር እና ታሪካዊ ቅርሶችን በልዩ ሁኔታ ለመጠበቅና ለማልማት ቃል ገብተዋል።

©YSHT
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ዘመናዊነት የሕግ የበላይነት ማክበር ነው፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከድሬዳዋ⬇️

"ፀጋ የምስራቁ የኢትዮጵያ ክፍል ከኢንተርኔት አገልግሎት ውጭ እንዲሆን ከተደረገ ሳምንታት ተቆጥረዋል። የሚመለከተው አካል ኢተርኔት ስለተቋረጠበት ምክንያት እና መቼ አገልግሎት እንደሚጀምር በግልፅ ማሳውቅ ይኖርበታል። ስራ መስራት አልቻልንም"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
From Mekele University⬇️

The Tigray Institute of Policy Studies (TIPS) and Mekelle University with the full support of the Government of the National State of Tigray are organizing a high-level forum titled Meles Zenawi's Legacy and Ethiopia's Renaissance Path on the occasion of the sixth commemoration of Meles' departure. The forum is expected to be a venue for deep reflection on the works of Meles and the current state of affairs in Ethiopia.

Leaders, policymakers, scholars, representatives of different organizations, and others are expected to take part in the forum. This is therefore to cordially invite everyone to participate. The forum is scheduled to take place in Mekelle on 13/12/2010 E.C. (Sunday). 

Kindeya Gebrehiwot (PhD, Prof in Forestry), President 

Mekelle University, P.O.Box - 231, Mekelle, Tigray, Ethiopia
Office Tel - +251-344-409228 
Office Fax - +251-344-401090/ +251-344-409304 
Preferred email: [email protected] 
Website: www.mu.edu.et 
Twitter: @DrKindeya

@tsegabwolde @tikvahethiopia