TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#አንድነታችንን የሚያጠናክሩ፥ ኢትዮጵያዊ አብሮነታችንን የሚያጎለብቱ እንጂ ወንድማማች በሆነው ህዝብ መካከል ጥርጣሬንና #ጥላቻን ብሎም ጠብን የሚዘሩ ፅሁፎችም ሆኑ ንግግሮችን አጥብቄ #እቃወማለሁ!

#ETHIOPIA
ሁለተኛው ቀን⬆️ዛሬ በሁለተኛው ቀናችን ከላይ ያለውን ፁሁፍ ሁላችንም በፌስቡክ ገፃችን ላይ በመለጠፍ ሀላፊነታችንን እንድንወጣ ስል ዝቅ ብዬ እየለምናችኋለሁ።

100 ሺ ሆነን በፌስቡክ የሚሰራጩ የጥላቻ መልዕክቶችን እንዋጋለን!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በጥቂቱ⬆️በተወሰኑ ደቂቃዎች ፌስቡክን እየተቆጣጠር ነው እንገኛለን። እንግፋበት ሁሉም ጓደኞቻችን ሼር እንዲያደርጉት እንቀስቅስ! በፍቅር ማሸነፍ እንችላለን!

ቤተሰባችን በመላው ዓለም ተፅኖ መፍጠር ይችላል!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አንድነታችንን የሚያጠናክሩ፥ ኢትዮጵያዊ አብሮነታችንን የሚያጎለብቱ እንጂ ወንድማማች በሆነው ህዝብ መካከል ጥርጣሬንና #ጥላቻን ብሎም ጠብን የሚዘሩ ፅሁፎችም ሆኑ ንግግሮችን አጥብቄ #እቃወማለሁ!

#ETHIOPIA #ሼር
ልትከበሩ የሚገባችሁ ሰላም ወዳድና ሀገር ወዳድ ድንቅ ኢትዮጵያዊያን ናችሁ። ፈጠሪ ረጅም እድሜና ጤና ይስጣችሁ። እናት ሀገራችን ሰላሟ በዝቶ ፍቅሯ ጠንክሮ ማየት የሁላችንም ምኞት ነው።

የሁላችሁንም የተለጠፉ መልዕክቶች እኔው እየገባሁ እያየሁ ስለሆን ወደኔ መላክም አይጠበቅባችሁም።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ለሙዚቃ_አድማጮች⬆️የጃሉድ አወል ሁለተኛ አልበም የፊታችን ረቡዕ ነሀሴ 16 2010 ዓ.ም በገበያ ላይ ይውላል። #ኦርጂናሉን ብቻ መግዛት እንዳይረሳ።

©በፍቃዱ አባይ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ባህር ዳር⬇️

ጠ/ሚ ዶክተር አብይ አህመድ ዛሬ ባህር ዳር ከተማ መግባታቸው ተሰምቷል። ከሳምንታት በፊት ከዚህ ዓለም በሞት በተለዩት የብአዴን አመራር አቶ ተስፋየ ጌታቸው መኖሪያ ቤት በመሄድም ቤተሰቦቻቸውን አፅናንተዋል።

©AM
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ልዩ_ዜና ታንዛንያ⬇️

በታንዛንያ ደቡባዊ ክፍል የምቤዬ ግዛት ፖሊስ የአንድ ሰፈር ሰዎችን በሙሉ #በቁጥጥር ስር አውሏል።

ፖሊስ ሰዎቹን በቁጥጥር ስር ያዋላቸው ለአካባቢው የውሃ አገልግሎት ለመስጠት የተዘረጋውን የቧንቧ መስመር ከጥቅም ውጪ አድርገውታል በማለት ነው።

የእስር ትእዛዙን ያስተላለፉት የግዛቲቱ ፖሊስ ዋና ኃላፊ በበኩላቸው የሃገር ሃብት የፈሰሰበትን የውሃ መስመር በማበላሸታቸው ምክንያት በቁጥጥር እንደዋሉ ገልፀዋል።

በአካባቢው ነዋሪዎች ጉዳት የደረሰበት የውሃ አገልግሎት መስጫ በብዙ ሺ ዶላሮች ወጪ የተሰራ ሲሆን፤ እስካሁን የአካባቢው ተመራጭን ጨምሮ ብዙ የአካባቢው ነዋሪዎችን በቁጥጥር ስር ውለዋል።

የአካባቢው ነዋሪዎች ግን ሁላችንም በጉዳዩ ስላልተሳተፍን የምርመራው ሂደት ንጹህ ሰዎችን እንዳያካትት እንሰጋለን እያሉ ነው።

ፖሊስ በበኩሉ ሁሉም የአካባቢው ነዋሪዎች ለህዝብ አገልግሎት የሚሰጡ መገልገያዎችን የመጠበቅ ግዴታ አለባቸው ብሏል።

የአካባቢው ነዋሪዎች ግን ይህንን ማድረግ ስላልቻሉ ለዚህ ውሳኔ እንደደረሰ ገልጿል።

©BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia