TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
ከሀዋሳ⬆️

"ከመነሃሪያ ዩኒቨርስቲ የሚወስደው መንገድ ላይ ወደ አረብ ሰፈር የሚወስድ የሚያቋርጠው የሚሰራው አስፋልት ላይ እየተሰራ ያለ መንገድ ቤት ፈርሶ #ባለፈውም ቦይ ተቆፍሮ ዝናብ በመዝነቡ ቤቶች መፍረሳቸው አይዘነጋም። አንተም በቻናልህ አስተላልፈህ ነበር አሁንም ይህው እጣ ገጥሞታል ማታ ዝናብ ዘንቦ መሬቱ ሲጠቀጠቅ አልተሞላም እና ማታ በዘነበው ዝናብ አሁን የሆነ ቤት እና የማብራት ሽቦ ተበጥሶ መንገድ ላይ ወድቋል ማብራትም በሰፈሩ ጠፍቷል
#የሚመለከተው አካል ማብራት ሃይል እና ሌሎችም የሚመለከታቸው አካላት በአፋጣኝ መንገዱ ላይ የተበጠሰውን የኤሌክትሪክ ገመድ እንዲያነሱ ሰፈሩ በተለምዶ አዲሱ ሰፈር ሃዋሳ ሚሊኒየም ጤና ጣቢያ ወይም ከበለጡ ትምህርት ቤት 200 ሜትር"

©CNaT
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኢሶህዴፓ⬇️

የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /ኢሶህዴፓ/ የክልሉን ወቅታዊ ሁኔታ እና የፓርቲውን አሰራር ገምግሞ ሶስት የስራ አስፈጻሚና አምስት የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ማገዱን የድርጅቱ ሊቀመንበር አሕመድ ሽዴ አስታውቀዋል።

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update Bole Bulbula⬇️

"Hi tsegab this is Hanan from Bole Bulbula. There was a big fire explosion around Bole Bulbula Medhanialem shops. The cause of the fire isn't known but twins died from the fire. It's such a sad day today 😔 ppl are collecting money for the victim's mother who has lost her kids and her items in her shop."

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ምስራቅ_አፍሪካ ጎረቤቶቻችን ሰላም እየሆኑ ነው። ተቀራርበው የማያውቁም ዛሬ እየተቀራረቡ ነው። እርስ በእርስ መገዳደሉም ቀርቶ ለልማት ለመስራት እየተማከሩ ነው። ዙሪያችን ሰላም ነው። የዚህ ሁሉ ውጤት ባለቤት እናታችን #ኢትዮጵያ ናት!

የቤታችንን ሰላም እንጠብቅ፤ ሳንከፋፈል አንድ እንሁን እመኑኝ አይደለም ለአፍሪካ ለአለም እተርፋለን!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኦፌኮ⬇️

መንግስት በየአካባቢው እየተስተዋሉ ያሉ ችግሮችን ህብረተሰቡን በማሳተፈና  ህግን መሰረት በማድረግ  ሊፈታው እንደሚገባ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ  ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና ገለፁ።

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ወቅታዊ የሀገሪቱን ሁኔታ በተመለከተ አባላቶቹና ደጋፊዎቹ  የተሳተፉበት ሲምፖዚየም በአዲስ አበባ አካሂዷል።

ሊቀመንበሩ ዶክተር መረራ ጉዲና ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፁት፥ ወጣቶች ትውልድ በሀገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች እየተስተዋሉ ባሉ ችግሮችና  የሀገር አንድነትን ሊያፈርሱ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ ተሳታፊ መሆን የለባቸውም።

ዶክተር መረራ የሀገር አንድነትን የበለጠ ለማጠናከር፥ በአፋጣኝ ብሄራዊ መግባባትን ሊፈጥር የሚችል መድረክ እንዲመቻች አሰስበዋል።

እንዲሁም አሁን በሀገሪቱ እየተስተዋለ ያለውን ለውጥም በፍጥነት ወደ ሁሉም አካባቢዎች ማዳረስ እንደሚገባ ነው ሊቀመንበሩ ዶክተር መረራ ጉዲና የተናገሩት።

#ወጣቱ ሁሌም ለለውጥ ተሰላፊ መሆኑን የገለፁት ሊቀመንበሩ፥ ነገ የተሻለ እንዲሆን የወጣቱ ሀላፊነት እንደሆነ ተናግረዋል።

ከዚህ ባለፈ ወጣቱ የአንድ ድርጅት አገልጋይ  ሳይሆን የህዝብ ውክልና በመያዝ ትግሉን በአንድነት መቀጠል አለበት ብለዋል።

©FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ወጣቶች በሀገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች እየተስተዋሉ ባሉ ችግሮችና የሀገር አንድነትን ሊያፈርሱ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ ተሳታፊ መሆን የለባቸውም።"

◾️◾️ዶ/ር መረራ ጉዲና◾️◾️
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር⬇️

ሀሳብን በአመጽ እና እኩይ በሆነ ምግባር መግለጽ እየታየ ያለውን ለውጥ ያደናቅፋ፡፡

በከተማችን ሀዋሳ በወርሀ ሰኔ ተከስቶ በነበረው ግጭት 3250 አባወራ እና እማወራ ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸው ይታወቃል፡፡

ይህን ተከትሎም የክልሉ መንግስት የከተማ አስተዳደሩ እና የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም የሀይማት አባቶች ባደረጉት ዘርፈ ብዙ ርብርብ
በከተማዋ ተፈናቅለው የሚገኙ የህብረተስብ ክፍሎችን መልሶ ወደ መኖሪያ መንደራቸው የመመለሱ ሂደት በሚፈለገው ልክ እየተከናወነ መቆየቱ ይታወቃል፡፡

በዚሁ መሰረት እስካሁን ተጨባጭ የሆነ ማስረጃ ያላቸው እና ሌሎች በተለያየ መንገድ በጊዜያዊ መቆያ ካምፖች ውሰጥ ተጠልለቀው የሚገኙ ዜጎች በሀገሪቱ የአደጋ መከላከል እና መልሶ የማቋቋም ደንብ (ኖርም) መሰረት ፍትሀዊ የሀብት ክፍፍል እንዲኖር ታሳቢ ተደርጎ እና ንብረት የተጎዳባቸው አንጻራዊ የሆነ የገንዘብ ድጋፍ እንዲያገኙ ታሳቢ ተደርጎ እስካሁን ድረስ እንደ ከተማ ከ3000 በላይ የሚደርሱ አባ እና እማወራዎችን ወደ መኖሪያ መንደራቸው መመለስ ተችሏል፡፡

ይህ ሆኖ ሳለ ግን የክልሉ መንግስት ከከተማ አስተዳደሩ እና ከህብረተሰቡ የተውጣጣ ግብረ ሀይል ድጋፍ ሊያገኙ ይገባቸዋል በሚል ካቀረበው መረጃ ውጭ ሌሎች ተፈናቃይ ነን ባዮች ከ10/12/2010 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በሚገኙ በመንግስት ተቋማት ላይ የንብረት ውድመት አስከትለዋል፡፡

በእነዚህ የጥፋት ሀይሎች በክፍለ ከተማው የኦሞ ማይክሮ ፋይናስ ተቋም፣ የሲዳማ ማይክሮ ፋይናስት ተቋም፣ የክፍለ ከተማው የአስተዳደር ጽ/ቤት፣ የንግድ ኢንዱስትሪ ጽ/ቤት በርና መስኮቶች የወደሙ ሲሆን በተመሳሳይ መልኩም መጠኑ ከፍተኛ የሆነ ጉዳትን እና ውድመትን በአዲስ ከተማ ሁለተኛ እና መሰናዶ ትምህርት ቤት ማስከተላቸው ይገኝበታል፡፡

ለአብነት ያክልም በአዲስ ከተማ ሁለተኛ እና መሰናዶ ትምህርት ቤት የመማር ማስተማሩን ሂደት ሙሉ ለሙሉ የሚያስተጓጉሉ የኮምፒዩተር፣ የፕላዝማ ቴሌቪዥን ሰበራ፣ የቤተ መጽሀፍት እና ቤተ ሙከራ ዘረፋ እና ውድመት እንዲሁም የመማሪያ ክፍሎች እና አስተዳደር ህንጻዎች በርና መስኮት ሰበራ ከሚጠቀሱት መካከል ይገኙበታል፡፡

ሌላው በእለቱ ከተመዘገበው የዝርፊያ ተግባር መካከል በአዲስ ከተማ ሁለተኛ እና መሰናዶ ትምህርት ቤት ተጠልው ለሚገኙ እና በአጣሪ ግብረ ሀይሉ መረጃ መሰረት ድጋፍ ሊያገኙ ይገባቸዋል ለተባሉ ዜጎች የቀረቡ ዘይት፣ ስኳር እና ሌሎች የፍጆታ እቃዎች ላይ ዝርፊያ ተከስቷል፡፡

ድርጊቱን አስመልክቶ የከተማው አስተዳደር ከክልሉ የጸጥታ ሀይል ጋር በመቀናጀት እስካሁን ድረስ በወንጀል ድርጊቱ የተጠረጠሩ 137 ግለሰቦችን #በቁጥጥር ስር ማዋል የተቻለ ሲሆን ምርመራም እየተካሄደባቸው ይገኛል፡፡ሌሎችም ከዝርፊያ እና ወንጀሉ ጋር ግንኙነት አላቸው የሚባሉ ግለሰቦችን የማጣራቱ ተግባር በሂደት ላይ ይገኛል፡፡

የፍቅር የሰላም እና የአንድነት ከተማ የሆነቸው ሀዋሳ እኩይ አላማ ባላቸው እና የከተማዋን ስኬት በማይፈልጉ ጥቂት ጸረ ለውጥ እሳቤ ባላቸው ግለሰቦች እና ሀይሎች የማይደናቀፍ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ እየገለጸ ተመሳሳይ አቋምን በማራመድ የህዝብን እና የሀገርን ንብረት እና ሀብት ለማውደም አቋም ያላቸው ግለሰቦችን የከተማ አስተዳደሩ ሰላም ወዳድ ከሆነው የከተማዋ ሕዝብ ጋር በመሆን ተጠያቂ ሊሆኑ የሚችሉበትን አግባብ በተጨባጭ ማስረጃ ላይ በመርኮዝ ለሕግ የበላይነት መከበር ከወትሮው በተለየ ሁኔታ የሚሰራ መሆኑን ያስታውቃል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኦነግ ---- ኦህዴድ⬇️

ሀገሪቱን ወደ ትክክለኛ ዲሞክራሲ ለማሸጋገር በሚደረገው ጥረት የሚታዩትን ህገ-ወጥነትና #የስርአት_አልበኝነት ተግባራት ለመከላከል እንዲሁም ለህግ የበላይነት መከበር እንደሚሰሩ ኦህዴድ እና ኦነግ አስታወቁ።

የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ ፅህፈት ቤት የገጠርና ፖለቲካ ዘርፍ አደረጃጀት ሀላፊ አቶ አዲሱ አረጋ እና የኦነግ ቃል አቀባይ አቶ ቶሌራ አደባ በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

በዚህ ወቅት በኦነግ ስም የሚደረጉ ህገ ወጥ ድርጊቶች እና የክልሉን የፖለቲካ ሽግግር ለማደናቀፍ የሚደረግ እንቅስቃሴ የህግ የበላይነትን ማስከበር በሚችልበት መንገድ ወደ ትክክለኛ አካሄድ አንዲመለሱ እንሰራለን ብለዋል።

©OBN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አንድነታችንን የሚያጠናክሩ፥ ኢትዮጵያዊ አብሮነታችንን የሚያጎለብቱ እንጂ ወንድማማች በሆነው ህዝብ መካከል ጥርጣሬንና #ጥላቻን ብሎም ጠብን የሚዘሩ ፅሁፎችም ሆኑ ንግግሮችን አጥብቄ #እቃወማለሁ!

#ETHIOPIA
ሁለተኛው ቀን⬆️ዛሬ በሁለተኛው ቀናችን ከላይ ያለውን ፁሁፍ ሁላችንም በፌስቡክ ገፃችን ላይ በመለጠፍ ሀላፊነታችንን እንድንወጣ ስል ዝቅ ብዬ እየለምናችኋለሁ።

100 ሺ ሆነን በፌስቡክ የሚሰራጩ የጥላቻ መልዕክቶችን እንዋጋለን!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በጥቂቱ⬆️በተወሰኑ ደቂቃዎች ፌስቡክን እየተቆጣጠር ነው እንገኛለን። እንግፋበት ሁሉም ጓደኞቻችን ሼር እንዲያደርጉት እንቀስቅስ! በፍቅር ማሸነፍ እንችላለን!

ቤተሰባችን በመላው ዓለም ተፅኖ መፍጠር ይችላል!
@tsegabwolde @tikvahethiopia