TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#update ጠ/ሚ ዶክተር አብይ⬆️

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የዚህን ዓመት የመከላከያ እዝ ኮሌጅ ተመራቂዎች እንኳን ደስ ያላችሁ ብለዋል፡፡ በሥነሥርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር "ሕግና ሥርዓት የማህበረሰባችን መሰረት እና ያስተሳሰረን ነውና መንግሥት እየጨመረ የመጣውን ሥርዓት አልበኝነት #አይታገስም" ብለዋል።

©የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ፍፁም አረጋ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ማስታወሻ📌ዛሬ ነሐሴ 12 የአፄ ምኒልክ፣ የእቴጌ ጣይቱና የፊት አውራሪ ገበየሁ የልደት በዓል ነው።

#አፄ_ምኒልክ በህይወት ዘመናቸው የሰሯቸው ድንቅ ተግባራት በደማቅ ብእር እና ብራና የተከተቡ ናቸው።

1835 ዓ.ም. ---ወፍጮ
1882 ዓ.ም. ---ስልክ
1886 ዓ.ም. ---ፖስታ
1886 ዓ.ም. ---ባህር ዛፍ
1886 ዓ.ም. ---ገንዘብ
1886 ዓ.ም. ---የውሃ ቧንቧ
1887 ዓ.ም. ---ጫማ
1887 ዓ.ም. ---ድር
1887 ዓ.ም. ---የሙዚቃ ት/ቤት
1887 ዓ.ም. ---የፅህፈት መኪና
1889 ዓ.ም. ---ኤሌክትሪክ
1889 ዓ.ም. ---ዘመናዊ ህክምና
1889 ዓ.ም. ---ሲኒማ
1889 ዓ.ም. ---የሙዚቃ ሸክላ
1889 ዓ.ም. ---ቀይ መስቀል
1890 ዓ.ም. ---ሆስፒታል
1893 ዓ.ም. ---ባቡር
1893 ዓ.ም. ---ብስክሌት
1896 ዓ.ም. ---መንገድ
1897 ዓ.ም.---ፍል ውሃ
1898 ዓ.ም. ---ባንክ
1898 ዓ.ም. ---ሆቴል
1898 ዓ.ም. ---ማተሚያ
1898 ዓ.ም. ---ላስቲክ
1899 ዓ.ም. ---አራዊት ጥበቃ
1899 ዓ.ም. ---የጥይት ፋብሪካ
1900 ዓ.ም. ---ጋዜጣ
1900 ዓ.ም. ---አውቶሞቢል
1900 ዓ.ም. ---የሚኒስትሮች ሹመት
1901 ዓ.ም. ---ፖሊስ ሰራዊት
1904 ዓ.ም. ---የመድነኒት መሸጫ ሱቅ

አጼ ምኒልክ በመሪነት ጊዜያቸው ለሰሯቸው መልካም ስራዎች ሊመሰገኑ ይገባል። በመሪነታቸው ጊዜ የተሰሩትን ስህተቶች እኛ የአሁኑ ተውልዶች ተምረንበት፤ ወደፊት ጉዟችንን እንቀጥላለን

@tsegabwolde @tikvhethiopia
#update ኢቦላ⬇️

በዲሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ ኮንጎ የእርስበርስ #ግጭት ኢቦላ የበለጠ እንዲስፋፋ እያደረገ ነው፡፡

ግጭቱ እርዳታ ለማድረስም ችግር ፈጥሯል፡፡ የጤና ዘርፉ ኃላፊዎች እንደተናገሩት እስካሁን በበሽታው የተያዙ 78 ሰዎች ተመዝግበዋል፤44 ሰዎች ሞተዋል፡፡ በሰሜናዊ ኬቩ ክልል ደግሞ 1500 የሚጠጉ ሰዎች ለቫይረሱ ተጋልጠዋል፡፡

በክልሉ ያለው ሁከት ግን ለመድረስም ሆነ ስርጭቱን ለመግታት ፈተና ደቅኗል፡፡ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክትር ዶር. ቴድሮስ አድሃኖም ክልሉን ‹‹መድረስ የማንችልበት አካባቢ›› በሚል ጠርተውታል፡፡

ኢቦላ በአውሮፓውያኑ 1976 ነበር እንደ በሽታ የታወቀው፡፡ ትውኪያ፣ ተቅማጥ እንዲሁም በውስጥ እና ውጭ የአካል ክፍል ደም መፍሰስ ከምልክቶቹ ውስጥ ይጠቀሳሉ፡፡

©አልጀዚራ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ፌደራል ፖሊስ⬆️

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የሰው ሀይሉን ለማጠናከር ለ16ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን ከ5ሺህ በላይ ምልምል ፖሊሶችን በዛሬው እለት አስመርቋል፡፡ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሞሽነር ጀነራል ይደህጎ ስዩም ለተመራቂዎች መመረቃቸውን በማብሰር ወደተመደቡበት የስራ ቦታ ሲሄዱ ሀገራቸው የጣለችባቸውን አደራ በብቃት እንዲወጡ እና #የህግ_የበላይነት እንዲሰፍን ጠንክረው እንዲሰሩ ከአደራ ጭምር የስራ መመሪያ ሰጥተዋል፡፡

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የመደበኛና ልዩ ልዩ ሙያ ስልጠና ዳይሬክተር ኮማንደር ተስፋዬ ወንድሙ እነደገለጹት ምልምል ፖሊሶች ከመላ ሀገሪቱ የሚገኙ ወጣቶች መሀከል መስፈርቱን በማሟላት የተመለመሉ መሆናቸውን በማስታወስ ለተከታታይ 8 ወራት በፖለስ ሙያ የተለያዩ ስልጠናዎችን በብቃት የተወጡ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

የስልጠና ሀላፊው እነደገለጹት የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ሀላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶቸች በተገኙበት በጦላይ ማሰልጠኛ መዕከል ስነስረአቱ ተከናወናል ብለዋል፡፡ ፖሊስ መኮነኑ አየይዘውም ከተመረቂዎች መሀከል 822 ምልምል የሴት ፖሊሶች መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ምንጭ፦ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ⬇️

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በሃገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች የሚስተዋለው #የመንጋ_ፍትህ እና አላስፈላጊ ሁከት ተቀባይነት የሌለው እና የህግ የበላይነትን አደጋ ውስጥ የሚጥል መሆኑን ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት በ11ኛው እነ 12ኛው ዙር የሰለጠኑ የመከላከያ መኮንኖችን ባስመረቁበት ወቅት ባደረጉት ንግግር ነው።

በወቅቱ ባደረጉት ንግግር ድርጊቱ የህግ የበላይነትን የሚነድ በመሆኑ በአስቸካይ ሊቆም እንደሚገባው ገልጸዋል።

ህብረተሰቡ በተለይም ወጣቱ የተሳሳተ መረጃን መሰረት በማድረግ ለህግ ቅድሚያ ሳይሰጥ የሚፈጽማቸው ድርጊቶች እየተገነባች ያለችን ሃገር ከማፍረስ ውጭ ዋጋ እንደሌለውም ጠቅሰዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ የህግ የበላይነት ለአንድ ሀገር ማህበረሰብ መጠበቅ መሠረት መሆኑንም በዚህ ወቅት ተናግረዋል።

ከዚህ አንጻርም መንግስት አሁን ላይ እየተስተዋለ ያለውን ከህግ በላይ የመሆን ዝንባሌ እንደማይታገስም አንስተዋል።

#እንደመር ስንል ባለፍንበት መንገድ ያጣነውን ለመመለስ እንጅ ሃገሪቱን ውጤት #ለከፋ_ቀውስ ለመዳረግ አይደለምም” ብለዋል በንግግራቸው።

መንግስትም እነዚህን ክስተቶች ለመቆጣጠር የመከላከል እና #ህግ የማስከበር ስራዎችን ይሰራልም ነው ያሉት።

©FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጎንደር⬇️

ዛሬ ጎንደር ላይ በጅግጂጋ ለደረሰው ግጭት አና ለሞቱት ሰዎች ሀዘን በሚል በተዘጋጀው ዝግጅት ላይ ሙስሊም አባቶች መልእክት አስተላልፈዋል። ከመልእክቱ በኋላ በሙስሊም አባቶች ፀሎት ተደርጓል።

በሌላ በኩል⬇️

ሰሞኑን በሀገረ ስብከቱ እና በየ lአብያተክርስቲያኑ የተሰበሰበው ገንዘብ ከ600,000 ብር በላይ መሆኑ ሪፖርት ተደርጓል። ሙስሊሞ ወገኖችም ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልፀዎል።

©Jupi
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና! የቀድሞ የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ጸሐፊ ኮፊ አናን በ80 ዓመታቸው #አረፉ፡፡ ኮፊ አናን ለሰብአዊ ስራቸው የኖቤል የሰላም ሽልማት ተሸላሚ ነበሩ፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጎንደር⬇️

"በጎንደር ከተማ ሲደረግ የነበረው ስርአተ ፀሎት በሰላም ተጠናቋል፡፡ በመዘመር እና መፈክር በማሰማት ወደየቤታችን እየሄድን ነው።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የበጎ አድራጎት ማህበራትና በፀረ ሽብር አዋጆች ላይ የማሻሻያ ሀሣብ ቀረበ፡፡ ሀሣቡ በቅርቡ በተቋቋመው የፍትህና ህግ ጉዳዮች አማካሪ ቦርድ አጥሪ ቡድኖች የቀረበ ሲሆን ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ ምሁራን፣ ባለሙያዎችና፣ ፖለቲከኞች ተወያያተውበታል፡፡ መንግሥት የዜጐች መብት ሳይሸራረፍ እንዲጠበቅ ለማድረግ እየሰራ ነው ያሉት ጠቅላይ አቃቢ ህጉ አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ በአንድ ተቋም በአንድ ወቅት ማህበረሰቡን ያረካ የፍትህ ስርዓትን ለመዘርጋት ከመጣር ይልቅ ቦርዱ ስርዓት ባለው መንገድ ለማከናወን እንደሚያስችል ገልፀዋል፡፡

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከጋምቤላ⬇️

"ጋምቤላ ከወሬ ውጪ እንጂ ሰው መደበኛ ስራውን እየሰራ ነው። የፀጥታ ሀይሎች በብዛት መግባታቸውም እየተነገረ ነው። በዛሬው እለትም በየቀበሌው በሰላም ዙርያ ስብሰባ እይተደረገ ነው። ነገር ግን ሰብስባው እንደድሮ ነው ማለት በግዳጅ ነው።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ሶማሌ ክልል⬇️

የሱማሌ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ሙሃመድ ራሽድ እና የኢሶዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል አቶ ከድር አብዲ ከስልጣን መልቀቃቸውን ተሰምቷል⬇️

"Two leading regional lawmakers resign from the ruling party of Ethiopia Somali region (ESPDP). Mohamed Rashid Isaq who has been Speaker of regional Parliament (L) and leader of the central committee Khadar Abdi Ismail (R) have resigned according to party sources in Addis Ababa."

©HARUN MARUF-VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ⬇️

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር በአዛዥነት እና ስታፍ ኮሌጅ ያሰለጠናቸውን ከፍተኛ መኮንኖችን ሲያስመርቅ ከተናገሩት ዋና ዋና ነጥቦች:-

• ነፃነትና ስርዓት አልበኝነት ባለመለየት #መረን የወጣ ሕግና ስርዓትን የማያከብር የመንጋ ፖለቲካ ኢትዮጵያ ውስጥ መቆም ይኖርበታል፡፡

• ሕጋዊ ስርዓትን እያደከምን በመንጋ የሚሰጥ ፍትሕ ተከትለን የፍትሕ ስርዓቱን በግል ስሜት መንዳት የለብንም፡፡

• ሕግ አልባና አመጽን የሚታገስ ስርዓት እንደ አገር መቆጠራችንን ከንቱ ስለሚያደርግ አገራዊ አንድነታችንን በሕግ አግባብ ማስጠበቅ የዘወትር ተልዕኮአችን ይሆናል፡፡

#ዘመናዊነት የሕግ የበላይነት ማክበር ነው፡፡

• እንደመር፣ በይቅርታ አንድ አገር እንገንባ ስንል ከመረን እንውጣ፣ ሕግ አናክብር በየከተማው ሽፍታ ይበራከት ማለት አለመሆኑን በአንክሮ ማስገንዘብ እፈልጋለሁ፡፡

• የይቅርታው ዓላማ በለፍንበት መንገድ ያጠናውን ለማግኘት እንጂ የገነባነውን አገር ለማፍረስ ስላልሆነ እያንዳንዱ ዜጋ ይህ ከአብራኩ የወጣውንና በአነስተኛ ደሞዝ ሕይወቱን እየገበረ የአገር አንድነትን የሚያስጠበቀውን ኃይል የመውደድ፣ የማክበር፣ የሞራል ድጋፍ
የመስጠት ኃላፊነት አለበት፡፡

• በጄኔራል ሰዓረ መኮንን ያየነውን የመከላከያ አንድነት እና የለውጥ ኃይል መሆኑን የማስቀጠል ፍላጎት በሁሉም ጄኔራል መኮንኖች እንዲደገም፣ በጡረታ የተገለሉ ጄኔራሎች ለወታደር ጡረታ ስለማይሰራ በየትኛውም ጊዜ ችግር ካጋጠመን እናት አገር ጥሪ ልታቀርብላችው ስለሚትችል ቀርባችሁ ሁኔታ እያያችሁ በመምከር፣ በማገዝ፣ በመደገፍ፣ ወገናዊነታችሁን ማረጋገጥ እንዲትችሉ፣ እንዳትበተኑ፣ አንድ ሆናችሁ አንዲት ኢትዮጵያን እንዲታጠናከሩ አደራ ማለት እፈልጋሉ፡፡

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ትምህርት ሚኒስቴር⬇️

ኢትዮጵያ ለ12 አመታት የምትሰራበት የትምህርት ፍኖተ ካርታ ረቂቅ ለህዝብ ውይይት ሊቀርብ ነው ተብሏል፡፡

የትምህርት ፍኖተ ካርታው ባለፉት ሁለት አመታት ጥናት ሲደረግበት መቆየቱን የትምህርት ሚኒስትሩ ዶ/ር #ጥላዬ_ጌቴ ተናግረዋል፡፡

በረቂቅ ፍኖተ ካርታው ላይ ለመወያየት በዘርፋ ላይ የተሰማሩ ከ1 ሺ 300 በላይ ባለ ድርሻዎች መጋበዛቸውንም ተሰምቷል፡፡

ውይይቱም ከነሐሴ 14-18 2010 ዓ/ም ይቆያል ተብሏል፡፡ የኢትዮጵያ ትምህርት ለ12 አመታት የሚመራበት ፍኖተ ካርታ ውይይት መክፈቻ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት እንደሚሆን ዶር ጥላዬ ጌቴ አሳውቀዋል።

©ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia