FBC (Fana Broadcasting Corporate)
206K subscribers
69.1K photos
1.33K videos
23 files
58.2K links
This is FBC's official Telegram channel.

For more updates please visit www.fanabc.com
加入频道
ብልጽግና የዕድልና ጥረት ድምር ውጤት ነው - ም/ጠ/ሚ ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ብልጽግና የዕድልና ጥረት ድምር ውጤት ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ሃሳብ፥ በትጋት የሚሠራና ዕድሎችን ሁሉ የሚጠቅም ጀግና ትውልድ ይፈልጋል ብለዋል።

ኢትዮጵያ ብልጽግናን እውን የሚያደርግ ይሄንን ጀግና ትውልድ እየገነባች ነው ሲሉም ገልጸዋል።
አየር ኃይሉ የውጊያ ዝግጁነት የሚያረጋግጡ በርካታ ስራዎች መሰራቱን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአየር ኃይሉን የውጊያ ዝግጁነት የሚያረጋግጡ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን የኢፌዲሪ አየር ኃይል ምክትል አዛዥ ለአየር ሎጀስቲክስ ብርጋዲየር ጄኔራል ነገራ ሌሊሳ ገለፁ፡፡ የአየር ኃይል ሎጀስቲክስ ተቋሙ የታጠቃቸውን የአቪየሽን፣ የአየር መከላከልና የምድር ድጋፍ ሰጭ ትጥቆችን ከመጠገን ጀምሮ የአየር ኃይልን የውጊያ ዝግጁነት በማረጋገጥ ለተቋሙ አሁናዊ የለውጥ ጉዞ ከፍተኛ አስተዋፅኦ…

https://www.fanabc.com/archives/281025
የጂቡቲው ፒፕልስ ሪለይ ፎር ፕሮግረስ ( አር ፒ ፒ ) ፓርቲ ዋና ጸሀፊ ኢያስ ሙሳ ዳዋለህ ለመ አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2017 (ኤፍኤም ሲ) ጸሀፊው ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ ጉባዔ ከጥር 23 እስከ 25 ቀን 2017 ዓ/ም ድረስ “ከቃል እስከ ባሕል” በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

በጉባዔው ከ15 ሀገራት የተውጣጡ የጎረቤት ሀገራት እህት ፓርቲዎች እና የብሪክስ አባል ሀገራት እህት ፓርቲዎች 43 ከፍተኛ አመራሮች እንደሚታደሙ ይጠበቃል፡፡
የናይጄሪያው ኦል ፕሮግረሲቭ ኮንግረንስ (ኤ ፒ ሲ) ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር አል ሀጂ አሊ ቡካር ዳሎሪ አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2017 (ኤፍኤም ሲ) ምክትል ሊቀመንበሩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ ጉባዔ ከጥር 23 እስከ 25 ቀን 2017 ዓ/ም ድረስ “ከቃል እስከ ባሕል” በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

በጉባዔው ከ15 ሀገራት የተውጣጡ የጎረቤት ሀገራት እህት ፓርቲዎች እና የብሪክስ አባል ሀገራት እህት ፓርቲዎች 43 ከፍተኛ አመራሮች እንደሚታደሙ ይጠበቃል፡፡
Live stream finished (1 hour)
ማስታወቂያ
የዚምባቡዌው አፍሪካን ናሽናል ዩኒዬን - ፓትሮይቲክ (ዛኑ ፒኤፍ) ፓርቲ የብሔራዊ ውጭ ግንኙነት ጸሃፊ አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2017 (ኤፍኤም ሲ) ጸሃፊው ሲምባራሼ ሙቤንጌግዊ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡

የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ ለጸሃፊው አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ ጉባዔ ከጥር 23 እስከ 25 ቀን 2017 ዓ/ም ድረስ “ከቃል እስከ ባሕል” በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

በጉባዔው ከ15 ሀገራት የተውጣጡ የጎረቤት ሀገራት እህት ፓርቲዎች እና የብሪክስ አባል ሀገራት እህት ፓርቲዎች 43 ከፍተኛ አመራሮች እንደሚታደሙ ይጠበቃል፡፡
የታንዛኒያው ቻማ ቻ ማፒንዱዚ (ሲ ሲ ኤም) ፓርቲ ዋና ፀሃፊ ኢማኑኤል ኔቼንቤ (ዶ/ር) አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2017 (ኤፍኤም ሲ) ዋና ፀሃፊው ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) እና በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ዳይሬክተር ጄነራል አምባሳደር ሽብሩ ማሞ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ ጉባዔ ከጥር 23 እስከ 25 ቀን 2017 ዓ/ም ድረስ “ከቃል እስከ ባሕል” በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

በጉባዔው ከ15 ሀገራት የተውጣጡ የጎረቤት ሀገራት እህት ፓርቲዎች እና የብሪክስ አባል ሀገራት እህት ፓርቲዎች 43 ከፍተኛ አመራሮች እንደሚታደሙ ይጠበቃል፡፡
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የጂቡቲው ፒፕልስ ሪለይ ፎር ፕሮግረስ (አር ፒ ፒ) ፓርቲ ዋና ጸሀፊ ኢያስ ሙሳ ዳዋለህ ለመ በብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ሲገቡ የተደረገላቸው አቀባበል
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የናይጄሪያው ኦል ፕሮግረሲቭ ኮንግረንስ (ኤ ፒ ሲ) ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር አል ሀጂ አሊ ቡካር ዳሎሪ አዲስ አበባ ሲገቡ የተደረገላቸው አቀባበል
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዋሽንግተን ዲሲ በተከሰተው የአውሮፕላን አደጋ የተሰማውን ሀዘን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዋሽንግተን ዲሲ የተከሰተው የአውሮፕላንና ሄሊኮፕተር መጋጨት አደጋ የሰዎችን ህይዎት በመንጠቁ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጿል፡፡

እንደ አሜሪካ አቪዬሽን አስተዳደር መረጃ÷ አውሮፕላኑ 60 መንገደኞችን እና አራት የበረራ ሰራተኞችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ ሲሆን ፥ ሄሊኮፕተሩ ደግሞ ሦስት ወታደሮችን ... https://www.fanabc.com/archives/281051
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የታንዛኒያው ቻማ ቻ ማፒንዱዚ (ሲ ሲ ኤም) ፓርቲ ዋና ፀሃፊ ኢማኑኤል ኔቼንቤ (ዶ/ር)አዲስ አበባ ሲገቡ የተደረገላቸው አቀባበል
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የዚምባቡዌው አፍሪካን ናሽናል ዩኒዬን - ፓትሪዮቲክ (ዛኑ ፒኤፍ) ፓርቲ የብሔራዊ ውጭ ግንኙነት ጸሃፊ ሲምባራሼ ሙቤንጌግዊ አዲስ አበባ ሲገቡ የተደረገላቸው አቀባበል
የቱርኬሚስታን ዲሞክራቲክ ፓርቲ መሪ አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2017 (ኤፍኤም ሲ) የቱርኬሚስታን ዲሞክራቲክ ፓርቲ መሪ አታ ሰርዳሮቭ እና የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የመካከለኛዉ ምስራቅ እና አፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ያዝጉሊ ማምዶቭ በብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ያዝጉሊ ማምዶቮ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ ጉባዔ ከጥር 23 እስከ 25 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ “ከቃል እስከ ባሕል” በሚል መሪ ሃሳብ ይካሄዳል።

በጉባዔው ከ15 ሀገራት የተውጣጡ የጎረቤት ሀገራት እህት ፓርቲዎች እና የብሪክስ አባል ሀገራት እህት ፓርቲዎች 43 ከፍተኛ አመራሮች እንደሚታደሙ ይጠበቃል፡፡

ዛሬ ማምሻውን የጅቡቲ፣ ናይጄሪያ፣ ዚምባቡዌ እና ታንዛኒያ ገዢ ፓርቲዎች ተወካዮች በጉባኤው ለመሳተፍ አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወቃል።
የኩባው ኮሚኒስት ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሜቴ አባል አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2017 (ኤፍኤም ሲ) የኩባው ኮሚኒስት ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሜቴ አባል ዩዲ ሜርሴዲስ ኸርናንዴዝ በብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ዩዲ ሜርሴዲስ ኸርናንዴዝ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የሴቶችና እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ ጉባዔ ከጥር 23 እስከ 25 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

በጉባዔው ከ15 ሀገራት የተውጣጡ የጎረቤት ሀገራት እህት ፓርቲዎች እና የብሪክስ አባል ሀገራት እህት ፓርቲዎች 43 ከፍተኛ አመራሮች እንደሚታደሙ ይጠበቃል፡፡

ዛሬ ማምሻውን የጅቡቲ፣ ናይጄሪያ፣ ዚምባቡዌ፣ ታንዛኒያ እና ቱርኬሚኒስታን ገዢ ፓርቲዎች ተወካዮች በጉባኤው ለመሳተፍ አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወቃል።
የካዛኪስታን አማናት ፓርቲ አባል አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የካዛኪስታኑ አማናት ፓርቲ እና የሀገሪቱ ፓርላማ የታችኛው ምክር ቤት አባል ሳማት ኑር ታተዛ በብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ሳማት ኑር ታተዛ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የሰላም ሚኒስትር መሀመድ እድሪስ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ ጉባዔ ከጥር 23 እስከ 25 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

በጉባዔው ከ15 ሀገራት የተውጣጡ የጎረቤት ሀገራት እህት ፓርቲዎች እና የብሪክስ አባል ሀገራት እህት ፓርቲዎች 43 ከፍተኛ አመራሮች እንደሚታደሙ ይጠበቃል፡፡

ዛሬ ማምሻውን የጅቡቲ፣ ናይጄሪያ፣ ዚምባቡዌ፣ ታንዛኒያ፣ ቱርኬሚኒስታን እና የኩባ ገዢ ፓርቲዎች ተወካዮች በጉባኤው ለመሳተፍ አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወቃል።
የዩናይትድ ራሺያ ፓርቲ ላዕላይ ምክር ቤት አባል አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ጥር 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የብሪክስ አባል ሀገር እህት ፓርቲ የሩሲያው ዩናይትድ ላዕላይ ምክር ቤት ቢሮ አባል፣ የሩሲያ ፌዴሬሽን ሴናተር እና የሴኔቱ ውጭ ጉዳዮች ምክትል ኃላፊ አንድሬይ ክሊሞቭ በብልጽግና ፓርቲ መደበኛ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።

አንድሬይ ክሊሞቭ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የመንግስት ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ ቤልጅጌ (ዶ/ር) አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ ጉባዔ ከዛሬ ጥር 23 እስከ 25 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ 'ከቃል እስከ ባህል' በሚል መሪ ሀሳብ ይካሄዳል።

ትናንት ማምሻውን የጅቡቲ፣ ናይጄሪያ፣ ዚምባቡዌ፣ ታንዛኒያ፣ ኩባ፣ ቱርኬሚኒስታን እና ካዛኪስታን ገዢ ፓርቲዎች ተወካዮች በጉባኤው ለመሳተፍ አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወቃል።
የደቡብ አፍሪካው ኤ ኤን ሲ ፓርቲ የብሔራዊ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ጥር 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የብሪክስ አባል ሀገር እህት ፓርቲ የደቡብ አፍሪካው አፍሪካ ናሽናል ኮንግረንስ (ኤ ኤን ሲ) የብሔራዊ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ኖጦሉ ኪይቬት አዲስ አበባ ገቡ።

ኖጦሉ ኪይቬት ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትሩ ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ ጉባዔ ከዛሬ ጥር 23 እስከ 25 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

በጉባዔው ከ15 ሀገራት የተውጣጡ የጎረቤት ሀገራት እህት ፓርቲዎች እና የብሪክስ አባል ሀገራት እህት ፓርቲዎች 43 ከፍተኛ አመራሮች እንደሚታደሙ ይጠበቃል፡፡

ከትላንት ምሽት ጀምሮ የጅቡቲ፣ ናይጄሪያ፣ ዚምባቡዌ ታንዛኒያ የኩባ ካዛክስታን የቱርኬሚስታን ገዢ ፓርቲዎች ተወካዮች በጉባኤው ለመሳተፍ አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወቃል።