FBC (Fana Broadcasting Corporate)
206K subscribers
69.2K photos
1.34K videos
23 files
58.2K links
This is FBC's official Telegram channel.

For more updates please visit www.fanabc.com
加入频道
ፕሬዚዳንት ማክሮን በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሐውልት ሥር የአበባ ጉንጉን አስቀመጡ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሐውልት ሥር የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤም ለፕሬዚዳንት ማክሮን የእንኳን ደህና መጡ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ የዓድዋ ድል መታሰቢያን መጎብኘታቸውን እና... https://www.fanabc.com/archives/276221
አርሰናል ክሪስታል ፓላስን በማሸነፍ ነጥቡን ወደ 33 አሳደገ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ17ኛ ሣምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በሜዳው አርሰናልን ያስተናገደው ክሪስታል ፓላስ 5 ለ 1 በሆነ ውጤት ሽንፈት አስተናግዷል፡፡

የመድፈኞቹን ጎሎችን በ6ኛው እና 14ኛው ጄሱስ፣ በ38ኛው ሀቨርትዝ፣ በ60ኛው ማርቲኔሊ እንዲሁም በ84ኛው ደቂቃ ራይስ አስቆጥረዋል፡፡

ማሸነፋቸውን ተከትሎም ነጥባቸውን ወደ 33 በማሳደግ በደረጃ ሠንጠረዡ ሦስተኛ ላይ መቀመጥ ችለዋል፡፡

16 ነጥቦችን ይዞ 15ኛ ደረጃ ለሚገኘው ክሪስታል ፓላስ ደግሞ ሳር በ11ኛው ደቂቃ ብቸኛዋን ግብ ከመረብ አሳርፏል፡፡

በተመሳሳይ 12 ሠዓት ላይ በተደረጉ ጨዋታዎች ዌስትሃም ከብራይተን ጋር አንድ አቻ ሲለያዩ÷ ኢፕስዊች ታውን በኒውካስል ዩናይትድ 4 ለ 0 እንዲሁም ብሬንትፎርድ በኖቲንግሃም ፎረስት 2 ለ 0 ተሸንፈዋል፡፡

በሌላ በኩል 9 ከ30 ላይ በተደረገ ጨዋታ በሜዳው ማንቼስተር ሲቲን ያስተናገደው አስቶንቪላ 2 ለ 1 ረትቷል፡፡
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር በሁለትዮሽ፣ ቀጣናዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በኢትዮጵያና ፈረንሳይ መካከል የተደረገ የመግባቢያ ሥምምነት ፊርማ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባለፉት ስድስት ዓመታት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ ለጉብኝት የመጡትን የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮንን ተቀብለዋል።
ፕሬዝዳንቱ በ2011 ዓመተ ምህረት በነበራቸው ጉብኝት ለላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት የእድሳት ሥራ ድጋፍ እንደሚሰጡ አሳውቀው ነበር።
ጠቅላይ ሚኒስትር በቅርቡ በታደሰው ብሔራዊ ቤተመንግሥት ክቡር ፕሬዝዳንቱን የተቀበሉ ሲሆን ቤተመንግሥቱንም ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
በሁለትዮሽ ውይይታቸው ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ፈረንሳይ ለብዙ ዘመናት ተዘንግቶ ለቆየው የብሔራዊ ቤተመንግሥት እድሳት ላደረገችው የእድሳት ድጋፍ አመስግነዋል።
ፕሬዝዳንት ማክሮን በበኩላቸው አስደማሚውን የቤተመንግሥት እድሳት አድንቀው በአድዋ መታሰቢያ ግንባታ እንደታየው የኢትዮጵያን ታሪክ እና ባሕል ለማክበር የተደረገውን ጥረት ክብር ሰጥተዋል።
መሪዎቹ ሰፊ መጠነ ርዕይ ባላቸው የሁለትዮሽ እና ባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ ውይይት ያደረጉ ሲሆን በኢንቬስትመንት፣ ባሕል እና ትምህርት ትብብር ለማጠናከር ተስማምተዋል።
የኢትዮጵያን የባሕር በር ጥያቄ በተመለከተም ረጅም ዘመን ለቆየው መሻት ዘላቂ መፍትሔ ለማስገኘት ሁለቱ ወገኖች በጋራ ለመስራት ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልፀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን የነበራቸውን ውሎ የጋራ ፍላጎታቸውን የትብብር ቁልፍ ጉዳዮች የተመለከተ በሰጡት የጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ አጠናቀዋል።
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እና የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት የሰጡት የጋራ መግለጫ
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት በብሔራዊ ቤተ መንግስት ያደረጉት ጉብኝት
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ማስታወቂያ

ምርቃት አለው!
****
ከባህር ማዶ በዓለም አቀፍ የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶች በኩል፣
በኢትዮዳይሬክት ( #EthoDirect ) እና ካሽ ጎ ( #CashGo )
ወደ ባንክ/ሲቢኢ ብር ሂሳብዎ ገንዘብ ሲላክልዎ፤ ወይም
ከባንካችን ሲቀበሉ
ገንዘብዎን ከምርቃት ጋር ያገኛሉ፤
በጉርሻውም ተጨማሪ ደስታን ይሸምታሉ!
*******
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!
#cbe #moneytransfer #banking #ethiopia #forex #EthioDirect #CashGo #mto
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
"በተፈለገ ጊዜ የተራዳ እርሱ እውነተኛ ጓደኛ ነው። ለሁሉም እናመሰግናለን።" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ብሔራዊ ቡድኑ ከሱዳን አቻው ጋር የቻን ማጣሪያ ጨዋታውን ያደርጋል

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአፍሪካ ሀገራት ዋንጫ ውድድር (ቻን) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሱዳን አቻው ጋር ጨዋታውን ያደርጋል። የሁለቱ ቡድኖች የቻን የመጨረሻ ዙር ማጣሪያ የመጀመሪያ ጨዋታ ቀን 11 ሰዓት በሊቢያ ቤንጋዚ ቤኒና ማርትየርስ ስታዲየም ይደረጋል። ጨዋታውን ለማከናወን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አስቀድሞ ወደ ሊቢያ ያቀና ሲሆን ለሁለት ቀናት በቤንጋዚ ልምምድ ሲያደርግ…

https://www.fanabc.com/archives/276242
ከ2 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ ያስመዘገቡ ባለሀብቶች በጅማ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ስራ ሊጀምሩ ነዉ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ከ2 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ ያስመዘገቡ ባለሀብቶች በጅማ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን በቡና እና በሻይ ቅጠል ምርት ስራ ሊጀምሩ ነዉ። የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር) እና የጅማ ዞን ዋና አስተዳደር ቲጃኒ ናስር በጅማ ዞን ማና ወረዳ በክላስተር እየለሙ ያሉ የቡናና…

https://www.fanabc.com/archives/276246
ስኬቶችን ለማስጠበቅ ቀጣይነት ያለው ድጋፍ ከሚያደርጉልን ሀገራት አንዷ ፈረንሳይ ናት – ም/ጠ/ሚ ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ የተገኙ ስኬቶችን ለማስጠበቅ ቀጣይነት ያለው ድጋፍ ከሚያደርጉልን ወዳጅ ሀገራት አንዷ ፈረንሳይ ናት ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው፤ የኢትዮጵያና ፈረንሳይ ወዳጅነት በጠንካራ የልማት ትብብር ምዕተ ዓመታትን ተሻግሯል ብለዋል። በኢትዮጵያ የተገኘውን ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ስኬቶችን ለማስጠበቅ ቀጣይነት ያለው…

https://www.fanabc.com/archives/276255
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በታደሰው እና የቅርስ ሀብቱ ለእይታ በቀረበበት ብሔራዊ ቤተመንግሥት የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮንን ተቀብለዋል።
ዕለቱ በምስል:-