እቅበተ ተዋሕዶ
96 subscribers
113 photos
49 links
ይህ ኦርቶዶክሳዊ የእቅበተ እምነት ተዋስኦዎች የሚቀርቡበት ገጽ ነው።
加入频道
✝️የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከስልጤ ዞን የሃይማኖት ፎረም አባልነት መልቀቋን አሳወቀች።✝️
+++
በስልጤ ዞን ቅበት ከተማ ላይ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምዕመናንን ላይ በደረሰው የቤት ለቤት ውድመት፣ዘረፋ እና ፍረጃ የተነሳ የስልጤ ዞን የሃይማኖት ፎረም ላሳዬው የአንድ አካል ወገንተኛ አቋም ምክንያት
የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ከእዚህ ተቋም ጋር ያላትን ግኑኝነት እና የአብሮነት ተግባር ሙሉ በሙሉ እንዳቆመች በሀዲያ ስልጤ ሀገረ ስብከት በኩል ባወጣችው መግለጫ አስታውቃለች።
በእዚህ ውሳኔ መሰረት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስልጤ ዞን ከሚገኙ ማንኛውም ዓይነት የዕምነት ተቋም ጋር በምንም ዓይነት ርዕስ ላይ የትብብር የጋራ የተግባር እንቅስቃሴዎች ላይ የማትሳተፍ ሲሆን መንግስታዊ የኅብረት ተግባር ላይ የተዐቅቦ ምላሽ ይኖራታል።
እንዲህ ገፊዎቻችንን እና የገፊዎቻችንን ተላላኪ ተቋማትን ከእራስ ላይ #ማንሳት በቶሎ የመስፈንጠር አንድ ትልቅ ርምጃ ነው።
✝️ጽኑ ጸሎተኛው ፣ብፁዕ አቡነ ሰላማ ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ!!✝️
+++
ጸሎታቸው ግዳጅ ፈጻሚው፣ደጉ፣ሩህሩሁና ታጋሹ አረጋዊው አባት ብፁዕ አቡነ ሰላማ ዛሬ መስከረም 18 ቀን 2016 ዓ.ም ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።
ብፁዕ አባታችን ባደረባቸው ሕመም ምክንያት በአዲስ አበባ ሃሌሉያ ሆስፒታል በሕክምና ላይ እንዳሉ ነው፣ ከዚህ ዓለም ድካም ያረፉት የብፁዕነታቸውን ሽኝት መርሐ ግብር በተመለከተ በቋሚ ሲኖዶስ እንደተወሰነ ዝርዝሩን የምናሳውቅ ይሆናል።
የብፁዕነታቸው በረከት ይደርብን!
✍️ኦርቶዶክሳዊ ዕቅበተ እምነት ምንድን ነው?✍️
+++ክፍል - 1
ዕቅበት የቃሉ መነሻ “Apologia” የሚል የግሪክ ቃል ሲሆን ትርጉሙም ቃላዊ መከላከያ/መልስ ማለት ነው፡፡ በሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት “Apologia” የሚለውን የግሪክ ቃል ብዙ ቦታዎች ላይ ተጠቅሶ እናገኘዋለን፡፡ #በአማርኛው መጽሐፍ ቅዱስ “መልስ፣ ክርክር፣ መመከቻ፣ ወዘተ” ተብሎ ተተርጉሟል፡፡ በተለመደው የቃሉ አጠቃቀም መጠበቅ የሚል ትርጉም አለው። ስለዚህ ዕቅበተ እምነት ማለት በእምነት ላይ ለሚነሡ ጥያቄዎች መልስ በመስጠት እምነትን መጠበቅ ማለት ነው፡፡
በአጠቃላይ #ዕቅበተ እምነት ስንል፡-
ምእመናን በዕውቀት ላይ የተመሠረተ እምነት እንዲኖራቸው ማድረግ፣
የኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ሃይማኖትን እውነትነት የሌሎችን “እምነቶች” ሐሰተኝነትና አመክንዮ-አልባነት በማስረጃ በማስደገፍ ማስረዳት፣ ያላመኑትን አሳምኖ ወደ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ሃይማኖት እንዲመጡ ማድረግ ማለት ነው። መናፍቃን ምእመናንን እንዳይነጥቁ ብቻ ሳይሆን እነርሱም የድኅነት ተካፋዮች እንዲሆኑ መመለስን የሚመለከት ነው፡፡
ብዙ ሰው መዳን ከሚገኝበት እውነተኛ የሕይወት መንገድ በዕውቀትም ይሁን በየዋሕነት ይወጣልና፡፡
በየዋህነት የሚወጣውን ሰው ሃይማኖትን በምድራዊና በሰው ሠራሽ አሳብ ላይ እንዳይገነባ ማድረግ፣ በዓላማ የሚወጣውን ደግሞ እምነት በሥጋዊ ዕውቀትና ጥበብ ተመሥርቶ የሚሻሻል አስተሳሰብ አለመሆኑን ማስረዳት
በትክክለኛው መሠረት ላይ የቆመውን ሰው በዕውቀት ላይ ተመሥርቶ እንዲያምን ማድረግም ዕቅበተ እምነት ነው፡፡
#እምነት የሚጠበቀው ከምንድን ነው ?
1. ከሥጋዊ ፍላጎት/አስተሳሰብ፣
2. ከሥርዓት አልበኝነት አካሔድ፣
3. ከዓለም ፍልስፍና፣
4. ከዓለማዊ ርእዮተ ዓለም (Secularism)
5. ከመናፍቃን እና ከአሕዛብ ቅሰጣ፣
6. ከኢአማንያንና ከከሐዲያን “ትምህርት”
የዕቅበተ እምነት አገልግሎት #አስፈላጊነት
የዕቅበተ እምነት ሥራ ከየትኛውም ጊዜ በበለጠ በዚህ ዘመን እጅግ አስፋለጊ ነው። ጥቂቶችን ለመጠቀስ ያክል ዕቅበተ እምነት ስለእነዚህና ሌሎች ምክንያቶች አስፈላጊ ነው።
1. #መጽሐፍ ቅዱስ ስለሚያዝና ሓላፊነትን ለመወጣት
“በእናንተ ስላለ ተስፋ ምክንያትን ለሚጠይቋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር የተዘጋጃችሁ ሁኑ፤ ነገር ግን በየዋሕነትና በፍርሃት ይሁን” (፩ኛ ጴጥ. ፫፡፲፭)።
2. #ስለ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ እምነታችን የበለጠ ለማወቅና ለማስረዳት (የሚያስተምር ብዙ ይማራልና)
3. #ከዘመን አመጣሽ የማንነት ወረራዎች ለመጠበቅ (ግብረ ገብነት የሚታወቅ መለኪያ የለውም የሚሉ ወጣቶች መበርከት)
4. #ሰዎችን ከክሕደት ለመጠበቅ (የመዳኛ አማራጭ መንገድ ያለ ለሚመስላቸው)
5. #በቤተ ክርስቲያን እና በአስተምህሮዋ ላይ ታቅደው የሚደረጉ ትችቶችን በብቃት ለመከላከልና መብቶቿን ለማስከበር
6. #በዘመናዊ ትምህርት ቤቶች ውስጥ በሚሰጡ ትምህርቶች ምክንያት በወጣቶች ላይ የሚፈጠሩትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሰዎችን ወደ ድኅነት መንገድ ለመምራት እጅጉን አስፈላጊ ነው።
የዕቅበተ እምነት አገልግሎት ለመፈጸም የሚያስፈልጉ ዝግጅቶችና ጥንቃቄዎችን በክፍል 2 እንመለስበታለን።
#share በማድረግ ለብዙዎች እንዲደርስ ይተባበሩ።
የ2016 ዓ.ም #ጥቅምት ሲኖዶስ ጉባኤ አጀንዳዎች።
ስልባዊ ተመስጦ ምስለ ባራኬ ግብረ ሰዶም!
ከእናቷ በላይ የሆነች የፓለቲካ ልጅ !!
የጥምቀት ቄስ ብቻ
(ከማዕበል ፈጠነ)
የጥንት ሊቃውንት ከሴት ርቀው ንጽሕናቸውን ጠብቀው ከዓለም ተደብቀው የሚኖሩ ነበሩ። ቅጽል ስማቸው ሳይቀር  የጋን መብራቶች ነበር። የጋን መብራት ለጋኑ የብርሃን ወጋገን ይለግሳል። በጋኑ ውስጥ ነጸብራቅ ይፈጥራል። ከጋኑ ውጪ ብርሃን የለውም። የጋን መብራት የሆኑ ሊቃውንት ሊቅነታቸው በጉባኤ ላይ ነው። የአብነት መምህራን እንደመሆናቸው በጉባኤው ዙፋን ሲሰየሙ የምሥጢር ወላፈን ይረጫሉ። በምሥጢር ሠረገላ ይመሰጣሉ። መንፈሳዊ ጥበብ ያዘንባሉ።
ዳሩ ግን ከአደባባይ ፈጽመው የራቁ ናቸው። ፎቶ መነሣት ዕርማቸው ነው። በአጭር ቃል #ባሕታውያን ነበሩ።
ዝናቸው የሚታወቀው በቅኔአቸው ምሥጢር ነው። ለጥምቀት የተቀኙት ቅኔ ከጽንፍ እሰከ ጽንፍ ይደርሳል። በየቅኔ ቤቱ ዕፁብ ድንቅ ሲባል ይሰማል። መልካቸው ግን ኅቡዕ ነበር።
እኔ ለአብነትነት ያኽል ተፍጻሜተ ሊቃውንት ሊቀ ሊቃውንት ያሬድ ሺፈራውን እጠቅሳለሁ። እናንተም የጋን መብራቶችን እየፈለጋችሁ ጨምሩበት።

#የዛሬ መምህራንስ?
የዘመኔ መምህራን ግን የጋን መብራቶች ሳይሆን  የፌስ ቡክ መብራቶች ናቸው።  ከልደት ዋዜማ ጀምሮ  ተናዳፊ ዐይን ባላቸው ቆነጃጅት ታጅበው ወደአደባባይ ይወጣሉ።
እንደ ሟቹ ሙሐመድ ጋዳፊ በሴት ጋርዶች ተከበው ወደ ባሕረ ጥምቀቱ ይወርዳሉ። ለጊዜው  ባርኔጣቸውን አውልቀው ሻሻቸውን ያጠልቃሉ። ረቂቅ ትምህርታቸው ሳይሆን ዲስኩራቸው በየቲክቶኩ ይመላለሳል።
  ከጥምቀት መልስ ሱፋቸውን  ያጠልቃሉ። ሻሽቸውን ያወልቃሉ። ባርኔጣቸው ወደራሳቸው ይመለሳል። ሥልጣኔ ማለት ይኸው ነው። የጥምቀት ቄስ ከመሆን ይሰውረን!!
✍️ዓመቱን ጠብቀው ክህደታቸውን ደግመውታል✍️
ድጋሜ መላእከ ሞትን እየጠሩት ነው።
+++
ከሐዲዎቹ የኦሮሚያ ተወካይ ነን ባይ ሕገወጦች በፕራይምና ኦቢኤስ ሚዲያዎች ቀርበው #መግለጫ ተሰጥተዋል። ጋዜጣዊ መግለጫውን በንባብ ያቀረቡት ገብረ ማርያም ነጋሳ በቋንቋችን ለመማር እና በነጻነት ለማምለክ ለዘመናት መከልከላችን ይታወሳል ብለው #የእናት ጡት ነካሽነታቸውን ቀጥለውበታል።
እንደሚታወቀው የቤተ ክርስትያኗን ዶግማና #ቀኖና በጣሰ መንገድ የዛሬ ዓመት ጥር 14 ቀን 2015 ዓ. ምሕረት ሕገ ወጥ ሲመተ ጳጳስ ማካሄዱንና የብሔር ብሔረሰቦችን ሲኖዶስ ብሎ መፈንቅለ ሲኖዶስ ማወጁን የምናስታውሰው ነው።
"መንግስትም የህዝቡን ሰላምና ደህንነት የመጠበቅ ኃላፊነት ስለነበረበት ነገሩ በእርቅ እንዲያልቅ ለማድረግ ወስኖ እኛም ተቀብለናል፤ ይሁንና መንግስትን በመሸንገል ሐምሌ 2015 ጥያቄያችን ተዳፍኖ አልፏል" ብሏል የከሐዲው ስብስብ።
#ለትግራይ ተፈቅዷል የአማራም ህዝብም ሲኖዶስ አለው ስለምን ኦሮሞ ህዝብ በራሱ ቋንቋ ማምለክ ይከለከላል ሲል ዓይን ያወጣ ክህደቱን ደግሞታል። ለ5 ኪሎ ሲኖዶስ መላም የኦሮሞ ህዝብ እንዳይገዛ ጥሪ እናስተላልፋለን ብሏል የከሐዲዎች ስብስብ።
የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ምንም ዓይነት #ቀለም ያለው ባንዲራም ሆነ ምልክት ስለሌላት በኦሮምያ ምድር ላይ የማንንም የፖለቲካ ፖርቲ ባንዲራ በቤተክርስትያን ሽፋን እንዳይውለበለብ፣ እንዳይሰቀል የሚል አዋጅ አስተላልፏል።
በመጨረሻም፣ የኦሮሚያ ቤተ ክህነት የወለደው የዘውግ ስብስብ መንግስት ጥያቄው የሕዝብ መሆኑን አውቆ #ከሕገ ወጥ ሲኖዶሱ ጎን ይቆም ዘንድ ክህደታዊ ተማጽኖ ለአለቆቹ አቅርቧል።
***
ይህ እንደሚመጣ እናውቅ ነበር። የተሰጠው መፍትሔ ስር ነቀል አልነበረምና።
ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል መጽሐፋቸውን ይዘው እንዳይወጡ ተከልክለዋል። *** ትናንት ማታ በ19/05/2016 ዓ.ም ወደ አሜሪካ ለሕክምና ለመሄድ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ በአየር መንገዱ ያሉ የደኅንነት አካላት ከቤተክህነት በደብዳቤ ተፈቅዶላቸው የያዙትን 837 መጽሐፍ ቀምተው ወስደውታል። ችግሩ ምንድን ነው ብለው ሲጠይቁም የታዘዝነው ከላይ ነው የሚል መልስ ተሰጥቷቸዋል። ይህ የሚያሳየው የቤተክህነቱን ሰዎች ማንገላታትና፣ ንብረቶቻቸውን መቀማትና ደብዳቤዎቻቸውን ማጣጣል እንደ መቀጣጫ እየወሰዱት መሆኑን  ነው።

ይህ ባለፈው ሳምንት በብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የተደረገው ቅሚያ ነው ትናንትም በብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል የተደገመው ።
#ቤተ ክርስቲያንን መድፈር ዋጋ ያስከፍላል!"
ሀገር ሲጠፋ #ጃርት ያበቅላል ያለው ማን ነበር ? የሆነ አካልን ከሥርዓቱ ገለል አድርጎ ፣የራስን ዘውግ ለመተካት የተካሄደው የድንቁርና ጥግ የት እንደሚያደርስ አንዱ ማሳያ ይህ ነው ።
በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ኦርቶዶክስ ተኮር በሆኑ ጥቃቶች ባሳለፍነው ጳጉሜ 1 ቀን 2016 ዓ.ም 5 ኦርቶዶክሳውያን ተገደሉ።

በሮቤ ወረዳ ቤተ ክህነት ጄና ገዳምሳ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለምና ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን 5 ምእመናን ተገድለው ሁለቱ ደግሞ እስካሁን የደረሱበት እንዳልታወቀ የአካባቢው ምእመናን ለማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

ይህ ኦርቶዶክሳዊ ተኮር ጥቃት ከ 8 ወራት በላይ በአስከፊ ሁኔታ መቀጠሉ እና ምእመናን እየታገቱ ከ600 ሺህ ብር በላይ እንደሚጠየቁ ከቦታው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ።

በአሁኑ ሠዓት ኦርቶዶክሳውያን ቤት ንብረታቸው እየተቃጠለና ቀያቸውን ጥለው እየተሰደዱ እንደሚገኙም ተጠቁሟል።

ይህንን ጥቃት ለማስቆም ሰሞኑን የሀገር መከላከያ ሠራዊት ወደ ቦታው መግባቱን የጠቀሱት አስተያየት ሰጭዎች ዘላቂ መፍትሔ ለማምጣት ጥረት እየተደረገ ባለመሆኑ የምእመናን ስጋት አሁንም እንደቀጠለ ነው ብለዋል፡፡

Mahibere kidusan tv